Monday, November 3, 2014

በተቃዋሚዎች እየታፈነ ያለው የአማራው ድምፅ በትግላችን ይደመጣል! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)



በተቃዋሚዎች እየታፈነ ያለው የአማራው ድምፅ በትግላችን ይደመጣል!
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

ቅንጅት መጣ ቅንጀት ሄደ፤ አንድነት መጣ አንድነት በወጣት ተመራ፤ መድረክ መጣ መድረክ ካንድነት ተነታረከ፤እስላሙ ለድምጻችን ይሰማ ኡ ኡ ! አለ፤ ታማኝ መሐመድ አበሻውን ፤ *አሰላም አሊኩም ወረሑመትላሂ ወበረካቶ፤ አላህ ወ አክበር! አላህ ወ አክበር!* አለ፤ ሰማያዊ መጣ ለአምቦ ተገንጣይ ኦሮሞ ተማሪዎች ኡኡ አለ….፤ ሚዲያዎች የአመቱ የእምዬ ቁርጥ ልጅ እገሌ ነው…እገሌ ነው… ወድድር ንትርክ ተጋባ …. ወዘተ.. ወዘተ..ወዘተ… በዚህ የማያልቀው የወዘተ ዜና የተረሳ ክፍል አለ። አማራ የተባለ በካራ እየተቆራረጠ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ የሚያስንቅ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ የተሰወረበት፤ውጣ እየተባለ፤ የሚባረር የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበት እንደ እምየ የቁርጥ ልጅ በሕሊና ጸሎት ያልታሰበ፤ በጣም የዋህ ገበሬ ማሕበረሰብ! *ወይለይ* አለ ትግሬ በግልጽ እንወያይ እንጂ!

 የአማራ አርሶ አደር ገበሬ ሰቆቃ so what! እየታባለ በስላቅ ታይቷል። በሺዎቹ እንዳውም በሚሊዮን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል ስንል በጣም ቀለል አድርገው የሚያዩት ዕድገታቸው ያላገባደዱ የሰው እንሰሳዎች አሉ።በታቃዋሚውም በወያኔ ደጋፊዎችም ውስጥ።

ተቃዋሚው በደምብ አደርጐ ይህንን ወንጀል እየተፈጸመ አንዳለ ያውቃል። ግን ሁለቱንም ዓይኑን ገልጦ ትኩረት ሊያደርግ አልፈለገም። የትግል መፈክሩ አድርጐትም አያውቅም። ለምን? የሚል ጥያቄ ለምታቀርቡልኝ ወገኖች ካላችሁ፤ የኔ መልስ በአሲምባ የፓል-ቶክ ክፍል ተጠይቄ የሰጠሁት ሰፊ መልስ ለማድመጥ ይህንን ተጫኑ እና አድምጡ።  Getachew Reda   http://youtu.be/pXtJPLbbL48

መልሱ በሚገባ ተንትኘዋለሁ። እያንዳንዱ ተቃዋሚ ከወያኔ ባልተናነሰ በማወቅም ባለማወቅም የአማራውም ሆነ የአገሪቱ ሕልውና መጋዝ ይዞ የመገዝገዙ ዘመቻ ድርሻውን እንዴት እየተወጣ አንዳለ እዛው ትገነዘባላችሁ።

በፖለቲካ ተቃዋሚ ክፍሎች መዳፍ ቁጥጥር ስር  የወደቀው ‘ነፃ ሚዲያ”፤ ብላችሁ ጥሩኝ የሚለው ነፃ ሚዲያ ተብዬው፤ በተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች መዳፍ ሰር መውደቁ እና አብሮ ከተቃዋሚ ፖላቲካ ድርጅቶች ጋር ጭቃ ውስጥ ገብቶ እራሱን በማጨቅየት ትዕይንቱም ሆነ ትግሉን እያበላሸው አንደነበር አሁንም እየቀጠለበት አንዳለ ብዙ መረጃ መስጠት ይቻላል። በጐብኚዎች ብዛት ቀዳሚ ነው ስለሚባልለት የዘሃበሻ ድረገጽ አዘጋጅ በመተቸቴ የአንድ ታዋቂ የፖለቲካ ድርጅት (አንድነት /ዩዲጄ/) ስርጭት ማኒፌስቶ/መግለጫዎች እና ዜናዎች በየወቅቱ በየኢመይላችን የሚልክልን በስም ያልተጠቀሰ (ኢመይል ብቻ የምናውቀው) በውጭ አገር የዩዲጄ ከፍተኛ አማራር ኮሚቴ እና የሚዲያው ሰው ተብሎ የሚገመት በዘሃበሻ ሰም (ጥብቅና) የተላከልኝ ኢመይል አንደኖረ ብገልጽላችሁ በጣም ትገረማላችሁ።

ድረገፆቹ በማን ቦርድ አባልነት ወይንም በማን የፖለቲካ ቡድን የሚንቀሳቀሱ አባሎች መሆናቸው ይህ ከዚህ በታች የምገልጸው ክስተት አመላካች ነው። ኢመይሉ ሁላችሁም የምታውቁት ከአንድነት ፓርቲ ሚዲያ እያለ የሚልክልን Alyou Tebeje aatebeje@gmail.com የተባለው ነው። በመጨረሻ ማሕተሙ ላይ  Zehabesha.com Group ይላል። የሚዲያዎች እና የተቃዋሚዎች ትስስር ምን እና ምን አንደሆነ ማየት ትችላላችሁ።

እነሱ የሚደግፏቸው ቡድኖች መውቀስ መተቸት ሚዲያዎቻቸውን መተችት ከቶ በምንም መልኩ የማይታሰብ እና ከወያኔ የባሰ አማተር የሚዲያ ታይራንቶች መሆናቸውን አትዘንጉ። በዚህ ትስስራቸው ስለ አማራው መጮህ ቅድሚያ መስጠት ወይንም እነዚህ የዜና ማሰራጫዎች እነሱ የሚደግፏቸው ወይም ትስሰር ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሰሩዋቸውን አፍራሽ ስትራተጂ ሰርስሮ በመለየት ለሕዝብ ማሳወቅ ይችላሉ ወይ? ብለን ብንጠይቅ፤ መልሱ *የገዛ ድርጅታቸውን ለሕዝብ አሳልፈው መስጠት አይፈልጉም*። ለዚህ ነው ሚዲያዎች ሲነኩ ከዚህ መጣ የማይባል በፖለቲካ ድረጅት ልሳን አሰራጭነት የታወቀው  የኢመይል አድራሻ ብቅ ብሎ ስለሚተቸው ሚዲያ በመቆርቆር *እኛ ነን* ሲሉ ከሕዝቡ ተደብቀው ነፃ ሚዲያዎች ነን እያሉ ሲያጃጅሉን ከርመው እራሳቸው የማን ደጋፊ እና የፖለቲካ ሰዎች መሆናቸውንና ማንነታቸው ሲነግሩን የምናነባቸው።

እኔ በታላቅ አክብሮት የማያቸው ታዋቂው አንጋፋ ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ/ፀጋዬ ገብረመድህንም ሆነ ስንሻው ተገኘ መጽሔታቸው ጦቢያ ከመዘጋቷ በፊት ከፓርቲዎቹ በላይ (የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሩም አልመሰለኝም ምናልባት ከነበሩም መጽሔቱ ከፓርቲ በላይ የሕዝቡን ሰቆቃ በመዘገብ አነጋጋሪ ጉዳዮችን ለሕዝብ ያቀርብ ነበር እና የፓርቲዎቹም የጋዜጠኞቹም ስራ ደብሎ በመስራቱ ሊመሰገን ይገባዋል። የመላው አማራ ድርጅት እና የአርበኛው የዶ/ር ታዬ አስደናቂው ትግል ሳትረሱ ማለቴ ነው።) የሚደነቅ ስራ ሲሰራ መኖሩ የሚታወስ ነው። ታዲያ በወቅቱ ስንሻው ተገኘ በአንድ ጽሑፉ ላይ የሚከተለው ብሎ ነበር፡-

*ለምሳሌ አርባ ጉጉ… ወዘተ..ወዘተ የደረሰው ግፍ ስናስብ ኤምባሲዎቻቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች *ሕዝብ ለምን ያልቃል? የሚል አንድ ቃል አልተነፈሱም። ይል እና ለፀሓፊው እሮሮ መነሻ ዘርዘር አድርጐ ሲገልጽ አንዲህ ይላል፦

“አንድ ሺህ የሚሆኑ የመኢዐድ ደጋፊዎችና በከፍተኛው ፍርድ ቤት ለግል አቤቱታና ክስ የቀረቡ ባለጉዳዮች ታፍሰው ተላጭተውና ለወራት በእስር ቤት ሲንገላቱ ከሰብአዊነት ውጭ የተዳረገ ኢፍትሐዊ አርምጃ ነው ብሎ ባያወግዝ እንኳ የጠየቀ ኤምባሲ አልነበረም።”
ይላል ስንሻው ተገኘ።

እዚህ ላይ ለማስመር የምፈልገው፤ ጋዜጠኞችም ሆኑ የፓለቲካ መሪዎች አብዛኛው ወቅት ለምን አያወግዝም ብለን የምንተችበት ትኩረት በውጭ አገር ኤምባሲዎች እና አገሮች ላይ እንጂ ትችቱ ፡ሕዝቡም ሆነ የፖለቲካ መሪዎች ለምን ይህንን በአማራ ላይ የተፈጸመ ተከታታይ ግፍ አትኩሮት ሰጥተውት አልተነሱም፤ሰላማዊ ሰልፍ አልወጡም? ብሎ የጠየቀ ጋዜጠኛም ሆነ የፖቲካ መሪ አልሰማሁም። ተጠቂው ገበሬ ለምን አይነሳም ብለን ትችት ውስጥ ሳናስገባ ስለ ሊሂቁ ነው እየተናገርኩ ያለሁት።

ይባስ ብሎ ጦቢያ እና ጥቂት ታዋቂ ጋዜጦች ከተዘጉ በሗላ እና ከድርጅቶችም ታዋቂው መኢዐድ ከፈረሰ በሗላ፤ የሕዝቡ ሕይወት የወደቀው በውጭ አገር ተቃዋሚ ጋንጎች የሚቦወዙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶች እና ጋዜጠኞች እጅ ወድቆ እሮሮው ብሶ ተዳፈነ። ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች የየራሳቸው ልሳን በማተም ደካማ እና ቀዳሚው ሚና ሚጫወቱትን ጨዋታ ሳትረሱ!

አሁን ያለው ተቃዋሚው እና ሚዲያው ቢያንስ ለ22 አመት በምንም መልኩ በአማራው ሕብረተሰብ ሕይወት እየደረሰበት የነበረው መከራ ሊያነሳው ቀርቶ ጭራሽኑ እየተገፋም ያለ አልመሰለውም (ባጠቃላይ ከአንዳንድ እየነጠሩ እዚህም እዚያም ከሚዘግቧቸው ተባራሪ ዜናዎች እና በመድረካቸው አንድ ዘለላ ሐረግ እና የ5 ወይንም 10 ደቂቃ ፡ክሊፕ፡ ብልጭ ከሚያደርጉት አጠር ያለ ዘገባ አንደተጠበቀ ሆኖ ማለቴ ነው፤ለቱኒዚያዊው ቦአዚዙ ለግብጹ ታሕሪር ስኩዌር አብዮት የለገሱትን ያህል ጊዜ ባነሰ መልኩ ማለት! )።

ሰሞኑን ያስገረመኝ ዜና ፤ዘሐበሻ የተባለው ድረገጽ አማራ በተጠቃበት ሰሞን የዘገበው አንድ አስገራሚ ዜና ነበር። ይኼውም ዜና ስለ አንድ ጥጋብ ወጥሮት ቁርጥ በመብላት ውፍረት ያስቸገረው ስለ አንድ ከያኒ (አርቲስት ይሏቸዋል መሰለኝ የዘመኑ የዜና ማሰራጫዎች) የዘገበው ዜና ነበር።ምቾትና ቁንጣን ያስቸገረው ዘፋኝ (ዘፋኝ ሳይሆን አይቀርም ካልተሳሳትኩ) ንዲህ ይላል፡-

“ቁርጥ መብላት ካቆምኩኝ በሗላ ውፍረቴን ቀነስኩ።” ይላል። ወጣቱ በምቾት አይኑር ሳይሆን ነጥቡ- የወሲብ መጽሔት/ዜና አዘጋጆችም ሆኑ፤ቁርጥ ሥጋ በመብላት ቁንጣን የያዛቸው ሰዎችን እንደ ትልቅ ዜና አድርገው በመዘገብ የዜና ማሰራጫ ዘጋቢዎች መድረክ ከፍተው ዜናውን ሲያስተጋቡት በዚህ አማራ በታፈነበት ዘመን፤ ስለ አማራ መከራ ለሕዝብ በማስተጋባት ሕዝብ አንዲነሳ የሚጥሩ አገር ወዳድ ጸሐፊዎችን መድረክ በመንፈግ የሚታወቁ እነዚህ የፖለቲካ ተቃዋሚ ሚዲያዎች የሚዘግቡት እንዳጡ፤ምን ያህል በግዝገዛው ስራ አንደተደመጡ ማሳያ ጠቋሚ ነው።

ለእንዲህ ያለው ዜና ጀሮ ሰጥተው ገዢ ለማግኘት በመንደፋደፍ የሚጥሩት ደግሞ የአማራው ጥቃት ተከታታይ በሚፈጸምበት ወቅት ነው። ቁርጥ በመብላት በቁንጣን የተቸገሩ ቁንጣን የያዛቸውም ሆነ የአገር ውስጥ ምንጭ የሆነው ዘጋቢ ጋዜጠኞች የአማራ ነገዶች ከሆኑማ የባስኑ ያናድዳል!

በኢንተርሃሙዌዎቹ ዘመቻ በአማራው ሕዝብ እየተፈጸመ ያለው ዘር የማጥፋት ጥቃት እየተፈጸመ ያለው በቀን ብርሃን አገር እያየ ፊት ለፊት እየተፈጸመ መሆኑን ስመለከት፤ሚዲያውም ሆነ እራሱ አማራ የተባለው በምቾት እየተንደላቀቀ ያለው ከበርቴው/ሊሂቅ፡ አይቶ አንዳላየ ከከንፈር መምጠጥ ያለፈ ቁጭትና ስራ ሳይታይበት ዝም ብሎ እያየው ሲጓዝ ስመለከት ይህ የተባባሪነት ዝምታ አንድ ቦታ መቆም አንዳለበት እና በገሃድ መነገር አንዳለበት ወሰንኩ። 

ድምዳሜው ላይ የደረስኩትም፤አማራው በራሱ ድርጅት ቆሞ ራሱን መከላከል እንዳለበት አማራጭ የሌለው የትግል ስልት ነው፤ የሚል ነው።

ጣጣቸው ያላደረጉት የዜና ማሰራጫ እና በፖለቲካ መሪዎች እጅ ምሕረት/መዳፍ/ 
ውስጥ ገብቶ የታፈነውን ድምፁ ያስተጋቡልኛል ብሎ ከዛሬ ጀምሮ ላንድ አፍታ አንኳ መጠበቅ አንደሌለበት አንዲነገረው ያልተደፈረው ድፍረት በይፋ መናገር ከወሰንኩ ቆየት ያለ መሆኑን የምታውቁት ነው። ይህ በማስተጋባቴ ፤ ተቃዋሚም ሆነ አማራው ሊሂቁ ከፍል፤ ተንጫጫብኝ። ከመንጫጫት አልፈው እኔ በማቀርበው እውነታኛ እውነታው በምንም መልኩ ሊፍቁት ስላልቻሉ ስሜን በማጉደፍ በዩቱብ ፎቶየን ለጥፈው የጦጣ ግጥም የገጠሙብኝ የመንፈስ ድሃዎች አንዳሉ አድምጣቹሃል። አሁንም ተለጥፎ ይገኛል።

ያውም ድርጅቶች እና የዜና ማሰራጫ ማዕከሎች ውስብስብ ባለ ኔት/መረብ ተቆላልፈው አንደማፊያ እየተሰባሰቡ ተምረው አንዳልተማሩ ከሚያስቡ ከነ ዶክተር ዜሮዎች/0 ጋር ስብስባቸውን በማቀናጀት አንዲሁም ስያምራቸው ከታወቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በመዶለት ፡ሕዝቡ ጠላቱን አንዲወድ እና ለዳግም መጃጃል ሲያዘጋጁት እና ለነሱ ጥብቅና ቆመው ልክ ወያኔዎች ለኤርትራኖች ጥብቅና ይቆሙ አንደነበረው ዓይነት በየስብሰባው እና የዜና ማሰራጫዎቻቸው የጠላቶቻችን ፕሮፓጋንዳ በድጋፍ በማራገብ ስራ ተጠምደው የአማራው ጉዳይ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት በተወሰኑ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ መሪ ግለሰቦች እስራት ብቻ በማትኮር ፤ በሚሊዮን የሚቆጠር የአማራ ነብሳት ከምድረ-ገፅ ሲጠፋ አጀንዳቸው/ጣጣቸው አልነበረም እና የማይተካውን የአማራ ሕዝብ በሕይወት ለማቆየት ሐላፊነቱ በራሱ ትክሻ ወድቋል።

የአማራው  ገበሬ ሰቆቃ እያዳመጡ *ንዴት* ባበገናቸው ልጆቹ መሪነት እራሱን ተማምኖ ለዳግም ትንሳኤ የተነሱትን አርበኞች አንደየመስካችን የሞራል፤የፕሮፓጋንዳ እና የገንዘብ ድጋፋችንን መስጠት ይጠበቅብናል!

እዚህ ላይ አደራ የምላችሁ፤ ወያኔም ሆነ በሌሎች የግል ኢጎ/ደንቃራ ባህሪ/ ተጠምደው የተለያዩ 10 የአማራ ድርጅቶች አንዳይመሰረቱ እና ትግሉን እና አትኩሮቱ አንዳይኮላሽ ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው። እዚህ ላይ ደግሞ አባላቶቹም ሆኑ አመራሮቹ ስሜትን ከማያሸንፍ ውስጣዊ ንዴት መጽዳት እና ትኩረታቸው የአማራው አርሶ አደር ድሃ ሕብረተሰብ ከጥቃት ለማዳን እንዴት መቀናጀት አንዳለባቸው ብቻ ማትኮር ይኖርባቸዋል።

በእገሌ ሕዝብ ላይ እንዝመት እያሉ በንዴት ስሜት እየተገፉ ዓላማው ሃዲዱን አንዳይስት ቀዳሚ የስትራተጂ እና የታክቲክ ትኩተረታችሁ በምን ላይ ማትኮር አንዳለበት በጥንቃቄ መንደፍ አለባችሁ።

ጉዘው እና ጅማሮው አድካሚ ፤ተስፋ አስቆራጭ፤ እልህ ተፈታታኝና ገንዘብ እና ጉልበት ጠያቂ መሆኑን ሳይተለም የተፈታ እውነታ ቢሆንም፤ አሁን የተጀመረውን የመከላከል አነስተኛ የአማራው ህዋስ/ድርጅት ከፍ እያለ በማደግ ጉልበቱን በማሳደግ ሕዝቡን ማስነሳት የሚችል ጅማሮ አንደሚሆን አልጠራጠርም።

አትኩሮታችን አማራው አንዲያዳምጠን እና እሮሮው ወደ ተቃውሞ ለውጦ በራሱ ሚሊዮን ሕዝብ ደምፅ ተማምኖ የራሱን ድምፅ ማስተጋባት እና ዋስትናውን ማስጠበቅ የለበትም የሚሉ የስትራተጂ እና የታክቲክ ንድፍ ባልተገራ በኢትዮጵያዊነት ስሜት ብቻ/ እደግመዋለሁ *የአማራውን ሕዝብ በረሳ አገራዊ ስሜት ብቻ*፤ የተጃጃሉ አማራዎችን በየመድረካችሁ በመጥራት እንድትከራከሯቸው እና ሃሳባቸውን አንዲለውጡ ማድረግ ከምትቀይሱት ንድፍ አንዱ የስትራተጂው ዘመቻ መሆን አለበት። ባይቀላቀልዋችሁም ቢያንስ በያሉበት ሚዲያ እና ድርጅት ስለ አማራው አንዲጮሁ ማድረግ ትግሉን ያፋጥነዋል።

ምክንያቱም የፖለቲካ ድርጅቶች እና የዜና ማዕከሎች የተቆጣጠሩት እና የሚመሩትም ሆነ  የሚጠቀሙበት ቋንቋም አማራዎች እና አማርኛ በመሆኑ “በመጃጃሉ” እና  “በግዝገዛው ዘመቻ“ እየተሰማሩ ያሉትና ቁልፍ ሚና በመጫወት ያሉት ብዙዎቹ የአማራ ልጆች በመሆናቸው፤ ትግሉ ከባድ ያደርገዋል።

ትግሉ አንዳይደፈርስ እየተባለ በጥንቃቄ ስትጓዙ የነበራችሁ አሁን ለአማራ ሕዝብ ድምፅ የቆማችሁ አማራዎች ሁሉ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ፖለቲካው አንዳይደፈርስ የምትሉት የጨዋ/አስተዋይ ጥንቃቄ ስትከተሉ የነበራችሁ አርበኞች ምስጋና የሚገባችሁ ቢሆንም ፤ ማቆሚያችሁ አሁን ነው። 22 አመት በደፈረሰ ፖለቲካ ሲጓዝ የነበረው ፖለቲከኛ እና የዜና ማዕከል ሐላፊነታቸው ለጥቂት ጋዜጠኞች እና ለጥቂት ግለሰቦች መታሰር እና መፈታት ጥብቅና ቆመው ሌት ተቀን የሚዘግቡና ለሕዝቡ ማነሳሺያ ቀዳሚ የመነሻ ስትራተጂ ነው ብለው የጦማርያኖች እና ጋዜጠኞች እሮሮ አንዲያስተጋባ መቀስቀሱን ከተያያዙት እናንተ የአማራ ታጋዮች ደግሞ የአማራውን ደምፅ አንዲሰማ ቀዳሚ ጣጣችሁ አንጂ ጉዘው የጠፋበት ፖለቲካ አንዳይደፈርስ መጨነቁን አቁሙ!        
እንዲህ ስታደርጉ በሚሊዮን የሞቆጠረው አማራ ሕብረተሰብ አሰልፋችሁ ፖለቲካውን ማስተካከል ትችላላችሁ። የአማራው ሕዝብ በቁጥር ሚዛን ላይ ማስቀመጥ አለባችሁ። መጀመሪያ ስለ ሕልውናችሁ እንጂ ስለፖለቲካው የዲሞክራሲ ቁንጅና በማቆነጃጀት ስራ ተጠምዳችሁ በዲሞክራሲ የቁንጅና ውድድር መግባቱ ጊዜው አሁን አይደለም። ሕልውና ሳይኖር ስለምትለብሱት የዲሞክራሲ ፋሺን መጨነቅ ሞኝነትን መከተል ነው።
ጉዞአችሁ ፣አማራውን ከጥቃት ለመከላከል፤ ከዘር ማጥፋት ለማዳን ከሆነ፤ ስለ ዲሞክራሲ የምትጨነቁት ጣጣ ለምን አንደሆነ አይታየኝም።ሁለት ሚሊዮን አማራ ከምድረ ገጽ አጥፍተናል ብለው ሲነግሯችሁ ፤ስለ ዲሞክራሲ ከታገላችሁ ጠላት በሰጣችሁ የማጃጃያ  ስራ ተጠምዳችሁ ሳታውቁት በግዝገዛው ስራ ተጠምዳችሗል ማለት ነው። የአማራው ጭፍጨፋ በዲሞክራሲ እጦት ምክንያት የተነሳ መነሻ ሳይሆን፤ በወያኔ ትግራይ የሚመራው የኢንተርሃሙዌው ቡድን ለአማራ ሕብረተሰብ ያለውን ጥላቻ ለማሳየት የነደፈው ዘመቻ እንጂ በግብር የገለጸው አስነዋሪ ወንጀል አንጂ ከዲሞክራሲ መኖር እና መታጣት ጋር የሚያያዘው አንዳችም መሰረት የለውም። ጨዋታው አንዲረዳችሁ ያስፈልጋል። ጨዋታው የካዚኖ ዲሞክራሲ ጨዋታ ነው።

የካሲኖ ባለቤት አጫዋች እና አክሳሪው በራሱ ጨዋታ አንድትገባ አብለጨላጭ የብር መብራቶች እያሳየ ዓይንን በማሞኘት በጫዋታው ተጠምደህ ኪሳራ ውስጥ ገብተህ በአክሳሪ ጨዋታ ላይ አንድትጠመድ የማድረጉ ዘዴ እና ድርጅቶቹ የሚጃጃሉበት ጨዋታ አንድ ነው። ለዚህም ነው የሎተሪ እና የካሲኖ ቁማር ድረጅቶች “ፕለይ ሪስፖንሲብል” በማለት ማጃጃያ ጨዋታው ለነሱ አንደሚጠቅም የተቀየሰ አንደሆነ እንጂ ለብዙሃኑ ተጫዋች አክሳሪ መሆኑን አሳማኝ በሚመስል *ውብ ቃል* በተዘዋዋሪ ለሚገባው ሰው በማስታወቂያቸው ግልጽ የሚያደርጉት። ወያኔም እየነገረን ያለው “በተከለለው ሕግ ፕለይ ሪስፖንሲብል” ሲል ለራሱ አንዲያመቸው በከለለው አጥር ውስጥ ብቻ ጫዋታው መሆን አንዳለበት የሚነግረን ።

 የወያኔዎች ዲሞክራሲ የአጭበርባሪዎች ካዚኖ ቤት ነው። ሂትለርም በዛው ዲሞክራሲ ተጠቅሞ እራሱን የት አንዳስቀመጠ አስታውሱት!

ወቅቱ ለዲሞክራሲ የሚጮህለት አይደልም።አማራው በዛው የቁማር ጨዋታ መግባት የለበትም።ሁለት ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ የአማራ ሕይውት ሲጠፋ ፤ስለ ዲሞክራሲ መተንተን፤መጠየቅ እና ስለ ጥቂት ጋዜጠኞች እስራት ከምርጫ 97 ጀምሮ መጮህ ያሳየን ነግረ ቢኖር፦ አሳሪው ክፍል የአማራውን ደምፅ አንዲታፈን እና ቀልቡ በጋዜጠኞች መታሰር ብቻ አንዲያተኩር ወያኔ እና ተቃዋሚው የገቡት የፖለቲካ ጨዋታ/ንድፍ መሆኑን ይግባችሁ። አስገራሚ ትዕይንት ነው። ቆማሪው እና ቁማር ተጫዋቾቹ በዲሞክራሲ የእሽክልሌ ጨዋታ ገብተው የሚሊዮኖች የዘር የማጥፋት ዘመቻ እና ኡኡታ በየተራራው እና ጫካው እየተስተጋባ ባለበት ጊዜ ነው  ጩኸቱ እንዳይደመጥ ዲሞክራሲ በሚባል በቀልብ የማደናገሪያ (አተንሺን ዲስኮርስ ወይንም ይቨርስ አተንሺን ታክቲክ) ጨዋታ እያስገቡን ያሉት። ህፃን  በሐይል ስያለቅስ ከፊት ለፊቱ የሚስብ ነገር አሳይቶ ጩኸቱን ዝም ለማሰኘት አንደመሞከር የአማራውንም ኡኡታ አንዲታፍን እየተደረገ ያለው በዚህ ስልት ነው።


ለዚህም ይመስላል፤ አገር ውስጥ  ያለው ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ማውለብለብ አሳፍሮአቸው የተለያዩ ቀለሞችን በማንገብ እስላሞቹ የተጠቀሙበት የግራኝ አህመድ ቁርጥራጭ ጨርቆችን ቅጅ ይዞ አንደ መሃረም መሳይ አድርጎ በማውለብለብ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ተብየውም ሆነ አንድነት የተባለው የነሱን መንገድ ተከትለው ቁርጥራጭ ባለ ቀለም ጨርቆችን ባደባባይ በማውለብለብ ስለ ጋዜጠኞች መታሰር የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰልፍ አንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡት። (በነገራችን ላይ መኢአድ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማና የድሮ ሕጋዊ የአገሪቱ የቆዳ ስፋት የሚያሳይ ካርታ ይዞ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱ በዚህ ምስጋና ይገባዋል።)


በቅርቡ ስለ አማራው ግፍ የዘገበው ቪኦኤ እና  ኢሳት የተባለው የግንቦት 7 የዜና ማሰራጫ ስታወዳድሩት ነፃ ሚዲያ የተባለው ቪ ኦ ኤ አስደናቂ ዘገባ ሲዘግብ ኢሲት የተባለው ግን ስለ መዠንገር ፖሊሶች ሞት ብዛት ነበር የዘገበው (ኢትዮ ሚዲያ የተባለው እማ ጭራሽኑ አልዘገበውም። ይባስ ብሎ ለመገንጠል የራሱን ባንዴራ አሰርቶ ጋምቤላን ለማስገንጠል በኤርትራ ድጋፍ የሚንቀሰቃሰው ቡድን መግለጫና ባንዴራቸውን ነበር ለጥፎ ያስነበበን። ይህ የምነግራችሁ እወነት ነው። አዘጋጁም ይህንን አይክድም። ኤርሚያስ ለገሰ የተባለው ከፍተኛ የወያኔ ካድሬ/ሚኒስቲር የነበረው በስያትል ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ስለ ወጣት ጋዜጠኞች መታሰር ሲናገር ስለ አማራው ሞት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አልተናገረም። ካድሬው ወያኔ ከከዳበት ቀን ጅመሮ ያነሳው አንዲት ዘለላ ሐረግ አልሰማሁም፤ አላነበብኩም።አሁንም ኢትዮ ሚዲያ መደመጥ ያለበት ንግግር ብሎ ለጥፎለታል። ስለ አማራ ያለው ነገር አለ  የምትሉኝ ካላችሁ እታረማለሁ።ሚዲያው በርዕሱ የጠቀሰው ስለ *ጎሳዎች ግጭት* ብቻ እንጂ የኢንተርሃሙዌ የጥቃት ሰለባ የሆነው የሚሊዮኖች ጭፍጨፋና መፈናቀል ስለ አማራው ጉዳይ አይጠቅስም። )። ኢሳትን  ስራየ ብዬ በተከታታይ ስለማላዳምጠው ካልተሳሳትኩ ኦክቶበር 25 የዘገበው ዘገባ መሰለኝ ቪኦኤ ከዘገበው ዘገባ ምን ያህል የተራራቀ መሆኑን ማየት ትችላላችሁ።


ስለ አማራው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ሰላማዊ ሰልፍ እጠራለሁ ያለው መኢአድም ከዚያ ወዲያ ያስሰማው ደምጽ የለም። አማራዎች ነን የሚሉ (ብያንስ መሪው ፤ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ፤ አማራ ይመስለኛል፤ ካልተሳሳትኩ።ምክትሉ ስለሺ ፈይሳ ነገዱን አላወቅኩትም) ስለ ኦሮሞ ነጻነት ግንጠላ እንቆማለን ያሉት የአምቦ ኦሮሞ ተማሪዎች፤ ካልሆነ በስተቀር አማራን በሚመለከት ለአማራም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አገር አቀፍ ሰላማዊ ጥሪ እስካሁን ድረስ የለም (በባሕር ዳር ተጀመረ ከዚያ ጠፋ)።
በወጣቶች ካልተመራ ውጤት አያመጣም ሲሉ የሚጃጃሉት የአንድነት ፓርቲ ጅላጅሎችም በቅርቡ ስለተፈጸመው ስለ አማራው ሕዝብ ሰቆቃና ህፃን መታረድ  በመቃወም አገር አቀፍ ጥሪ ያደረገው የለም። ደርጅቱ ያደረገው *በወጣቶች* የሚመራው የአንድነት ፓርቲ የሰሞኑን የሕዝባዊ ጥሪ መግለጫውም አንዲህ ይነበባል፤

ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሥርዓቱ ያሰጉኛል የሚላቸውን ንፁሀን የፖለቲካ አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያንን በህገ ወጥ መንገድ ክስ መስርቶ ማሰሩ ሳያንስ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ በእስር ቤት እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ ፓርቲው ይህንን የበደል ዘመን ለማሳጠር እንዲቻል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን።” ይላል።

በአዲስ መንፈስ አንመራለን ተብሎ በወጣት የሚመራ ይህ አንድነት የተባለው ወጣት የሚመራው ድርጅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንዲነሳ እና *የበደል ዘመን* አንዲያጥር ያቀረበው ጥሪ ስለ ጦማሪያኖች/ጋዜጠኞች አንጂ ስለ አማራ መጨፍጨፍ መፈናቀል *የበደል ዘመን* ሆኖ አልታያቸውም። አሁንም ልድገመው!!! በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ እየተጨፈጨፈ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ ባለበት ወቅት ነው ድርጅቱ የጥቂት  ጦማሪያን በእስር መንገላታትን ለማሳጠር እንዲቻል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲነሳ ጥሪ እናቀርባለን*፡፡ ሲል ጥሪ እያቀረበ ያለው። 

የበደል ዘመን ለማሳጠር* መግለጫው እየነገረን ያለው ጥሪ *የግፉ ዘመን መገለጫው* የዘር ማጥፋት ዘመቻ ወንጀል* ሳይሆን የበደሉን ዘመን መገለጫ፡ ለምን ወያኔን ተቻችሁ ተብለው በታሰሩ ጋዜጠኞች ሆኖ ሕብን ማስነሳት ይቻላል ብሎ *አንድነት* የነደፈው ስትራተጂ ደካማ አስገራሚ ነው። እውን አሁን ከመንደሩ እየተፈናቀለ ባለበት
In 1993, Ethiopian calendar, hundreds of Amhara homes in wollega,oromia were burned to the ground. Thousands of Amharas were brutally massacred. Federal police and local militias rounded up and marched 15,000 Amharas north and dumped them over the Bure, Gojjam concentration camp, with the full knowledge of the lethal consequences such hostile area would surely have on these highlander settlers. Many Ethiopians, local and international human right organizations new that the TPLF-OPDO militias were terrorizing Amhara communities in wollega, deporting Amharas to mysterious heavily guarded area. There were even rumors that the conditions in this area were appalling. But few could imagine that the deported Amharas were being exterminated on mass. Eventually all of the 15,000 Amharas that were relocated vanished into thin air in the biological genocide of a malaria outbreak, of which the area had long been notorious for, at the Bure-Auschwitz concentration camp. In the final moments before their distraction, the last survivors of the Amhara people in Bure-Auschwitz appealed to the whole world for help. They were not heard. May this last voice from the abyss reach the ears of all humanity.


ወቅት ይህ አስፈሪ እና አስደንጋጭ የጭፍጨፋ ግፍ፤ የግፍ ዘመን መለኪያ መሆኑን ቀርቶ የጥቂት ጦማሪያን መታሰር እና መንገላታት የዘመኑ የግፍ መለኪያ አድርጎ ጥሪ ማድረጉ መነሻው ምንድ ነው ብለን ለመጠየቅ ተገድደናል። ወጣት የተባለውስ መሪያቸው ምን እያሰበ ነው?

ለሳምንታት ምግብ መብላት እየቀፈፈኝ ሲያንገሸግሸኝ የነበረው የአንድ አፍሪካዊ ህፃን ልጅ በቢላዋ ታርዶ የተጣለው ፎቶግራፍ ለማየት እዚህ ይጫኑ (see below the posted replacement photo happened in Ethiopia ኢትዮጵያ ውስጥም በአማራ ሕፃናት የተፈፀመወ የዘር ማጥፋት ወንጀል ደግሞ ከታች የተለጠፉት ፎቶግራፎችን ይመልከቱ እና ይህ የጭፍጨፋ ግፍ የዘመኑ የግፍ መለኪያ ሆኖ ለሕዝብአዊ ጥሪ ካልበቃ ሌላ ምን ሊኖር ይችላል? አንጀታችሁ የማይችል አንባቢዎች ስዕሉን ተሎ እለፉት።  የፖለቲካ መሪዎች ለሃያ ሁለት ዓመት የመታገያ አጀንዳ ሳይኖራቸው በየወሩ የሚከሰቱት ግፎች እየለቃቀሙ አንዱን
እየጣሉ አንዱን እየረሱ የሚታገሉለት መዳረሻ እና መነሻ አጥተውታል።

ሕዝቡን ማስነሳት የሚችል የግፍ ጥልቀት ለሕዝቡ ማስደመጥ፤ ማስነበብ፤ ማስነገር፤ማስተጋባት ማሳየት፤ የትኛው ግፍ ብዙሃኑን ሕብረተሰብ ማስነሳት እንደሚችል  ፍጹም ሊያውቁት አልቻሉም። አውቀውትም ከሆነም ሆን ብለው በግዝገዛው የማጃጃያ ስልት ካልገቡ በስተቀር፤ ጥቂት ጦማሪያን በመታሰራቸው ሕዝብን ማስነሳት ይቻላል የሚል ስትራተጂ/ቀዳሚ የመተገያ ትኩረት/ የማይሰራ ከመሆኑ አልፎ ተቃዋሚው መራራ የሆነ ጥሪ የሚያስተጋባበት ስትራተጂ/የማንቀሳቀሻ ግብ የላቸውም ብሎ ወያኔ አንዲሳለቅባቸው መንገድ መክፈት ነው።ለሃያ ሁለት አመት ያልሰራ የፖለቲካ ሰልት መቀየር አለበት!የምለውም ለዚህ ነው።    

የአማራውንም ግፍ በስትራተጂ አንጻር የጥሪ መነሻ ሲደረግ በመጀመሪያው ጥሪ በርካታ ባያንቀሰቅስም መላው ሕዝብ አንዲሰማው እና ለቀጣይ አንቅስቀሴዎች ሆ ብሎ በነቂስ አንዲነሳ ይረዳል (በተለይ የግፉ ሰለባ የሆነው አማራው ብዛቱ መገመት አያዳግትም)። ለምሰሌ ወያኔዎችና አሽከሮቻቸው በጉራ ፈርዳ በአመራ አርሶ አደሮች ያደረሱት ግፍ ተቃውመን ሰንጮህ በመስማታቸው ደጋፊዎቻቸው ሳይቀሩ በየፓልቶኩ  መነጋገርያ አድርገውት ከመሰንበታቸው ሌላ፤ እርስ በርሳቸው አጨቃጭቆአቸው አንደነበር እናስታውሳለን። ምክንያቱም እዛው ውስጥም አማራዎች በብዛት መኖራቸውን አትሳቱ። በግንቦት 7፤ በኢሳት፤በአዲስ ድምፅ ራዲዮ አዘጋጆች በኩል ልዩ አንክብካቤ ተደርጎለት የአንድ ሰሞን “እፍ እፍ ፍቅር” የዟቸው አብሮ ከነሱ ጋር በየከተማው በአንድ የምግብ የጋራ መሶብ ቀርበው እየተጎራረሱና እየተቀላለዱ ሽር ጉድ ሲሉለት የነበረው፤አባመላ፤ የተባለው የወያኔዎች አገልጋይ በዛው ወቅት ስለ አማራ እሮሮ ሲናገር ነበረውን አስታውሱ። ትንሽ ስጋ አንደመርፌ ትወጋ እንደማለት!


ውም በወቅቱ መለስ ዜናዊም ሆነ ተላላኪያቸው ሃይለማርያም ደሳለኝም ሳይቀር በፓርላማቸው ያንጫጫቸው እና ያስበረገጋቸው ጣጣ/አጀንዳ ይህ የአማራው ጉዳይ አንደነበር እናስታውሳለን። በግብር ባይፈጽመውም ሃይለማርያም ደሳለኝ ለፍጆታ ተብሎ ቢሆንም፤በወቅቱ  ምን አንዳለ አስታውሱ! ሁኔታው እንኳን ለፈጻሚው ለሰሚውም የወንጀሉ ከባድነት እና አስፈሪነት የሚያስከትለው ተጠየቃነት በጣም ከባድ ወንጀል በመሆኑ ስርዓቱ ይህንን አጀንዳ አሁንም ሆነ ለወደፊቱ በከባድነቱ ከጦማሪዎች መታሰር ይልቅ ይህ ዘር ማጥፋት ወንጅል ያስደንግጠዋልና በተቃዋሚዎች በኩል ሊነሳ አይፈልግም።


ተቃዋሚዎቹ ግን ይህንን ለሕዝብ ማስነሻ መጠቀሙን አልፈለጉትም። ምክንያቱም ለአማራው ከጮኹ “ጠባቦች አንዳይባሉ!” (ለዚህ ነው አማራ ነኝ ብየ ለመጠራት አልፈልግም እኔ አንድ እና አንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ……ነኝ……..ነኝ  እያሉ የሚሉን።) ስለ አማራ መቆም ጠባብነት ነው ብሎ የነገራቸው ማን አንደሆነ ባላውቅም ፡መቃብሩ ይጥበበው ከማለት ምን ማለት ይቻላል።

በዚህ አጋጣሚ ይህ ጽሑፍ አገር ውስጥ በፌስ ቡክ በኩል አንደምንም ሸልኮ ቢገባ፤ አገር ውስጥ ላሉ አማራ ሕብረተሰብ ወገኖቼ ለማስተላለፍ የምፈልገው አገር ውስጥ  ያለው ተቃዋሚም ሆነ የዜና ማሰራጫዎቻቸው ወይንም አንደ ጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ አባባል፤ “የኛን ነፃነት ራሳችን አስነጥቀን ሌሎች ሞግዚቶች (አሜሪካ፤እንግሊዝ ወዘተ..) አንዲያስነሱልን አለዚያ ከባሕር ማዶ የመሸጉት ተቃዋሚ ሃይሎች በአራቱ መአዝናት በመርከብ እና በአይሮፕላን ጭነው አንዲያመጡልን ምጽአትን አንጠብቃለን፤”  አንዳሉት የምትጠብቁትን ነገር አቁማችሁ፤በዘር ማጽዳት ዘመቻ እየተጨፈጨፈ ያለው አማራ እራሱን፤ ዘሩን እና አገሩን ለማዳን ሌሎቹን አንጋጦ ከመጠበቅ እራሱ በራሱ ተደራጅቶ እሮሮው በማስተጋባት በራሱ ሕልውና ቆሞ፤ ትግል ውስጥ ገብቶ ራሱን መከላከል አለበት! የራሱ መጽሔቶች እና ድረገጾችን እና ፓልቶኮችን በመመስረት ትግሉ አንዲጀምር ማድረግ ግዴታ ነው።

እዚሁ አሜሪካ ሚኔሶታ/ካሊፎርኒያ (?) ሲታተም የነበረው ሞረሽ የተባለው መጽሔትም አርአያነቱን አንደገና ማንሳት ነው። ሰለዚሁ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ።
በሚዲያው እና በተቃዋሚ ተብዬ ጥርስ በሌላቸው ውሾች አጥር ተከብበህ መከራዬን ያስተጋቡልኛል ማሉቱን አቁም ። ውጭ አገር ያላችሁ አማራውን ለመከላከል የቆማችሁ ታጋዮች የአማራ  ልጆችም፤ ከከርካሳው አማራ ከበርቴው ምሁር ጋር ያላችሁን የሻከረ ግንኙነት በክርክር አንዲከፈት አምድ አዘጋጅታችሁ አጋልጧቸው፤ በክርክር ጥመድዋቸው። ጭራሽኑ አማራ አይደለሁም! እኔ ኢትዮጵያ አንጂ! እያሉ አጉል ስሜታዊ የማንነት ትንተና ውስጥ በመግባት ስለ አማራ ጭፍጨፋ ቀዳሚ አጀንዳ አናደርገውም የሚሉ የአማራ ሕዝብ አንዳይነሳ በተዘዋዋሪ ለእንቅስቃሴው ደንቃራ ሆነው ጭፍጨፋው በዓለም አንዳይታወቅ የሚያኮላሹት ዩኒቨርሳሊስቶች/ዓለም አቀፋዊ አማራዎችም ለችግሩ ጋሬጣዎች ናቸውና አስቡበት።ከነዚያ ከበርቴ አማራዎች ይልቅ “ናይጄሪያዊቷ የዩቱብ ጋዜጠኛዋ አድዮላ የተባለቺው ሴት ስለ አማራው ጭፍጨፋ ለዓለም በመንገር ትሻላለች። ሁላችንም አማራዎች ነን ማለት አሳፍሯቸው፤ ሁላችንም አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ከሚሉት አማራዎች እሷ አማራ ነኝ ብላ ሰለ አማራ ያገባኛል ብላ በአፍሪካዊነቷ መቆርቆሯ እሷ ትሻላለች ማለቴ ነው።” 

(በነገራችን ላይ ኢሳቶች/ጉንበቴዎች በባዓላቸው ጥሪ አድርገው ጋብዘዋት አንደነበር ሰምቻለሁ። ምናልባትም ፡እኔም አንዳርጋቸው ነኝ፡ ስላለች ይመስለኛል። ብትልም መመስገን አለባት። ጉደኛው ይህ ጥንግንግ (ሶፊስትሪ/ ቡድን ካገር የመጣው ካድሬም ፖሊሱም፤ ጦሩም፤ዳኛውም፤ጋዜጠኛውም፤ተዋዛዋዡም፤ ቀልድ ነጋሪውም፤ አብራሪውም፤ ምን የቀረው አለ? ሁሉንም በስሩ አሰልፏቸዋል። የነሱ ቱለቱላ ነፊዎች ሆነው መቅረታቸው ግን አስገራሚ የሚያደርገው ይኼው ገጽታው ነው። የቡዱኑ ሁሉንም የማጥመድ ስልቱ ከማፊያዎች የረቀቀ ሰልተኛ አጥማጅ መሆኑን ግን ሳላደንቀው አላልፍም። ምናልባትም የሻዕቢያ ማፊያዊ የትግል ተሞክሮ ትረይኒንግ/ስልጣና እየሰራ ይመስላል። 
      
ከጅብ የማያስጥል የአህያ ባል የሆኑት የፖለቲካ ድርጅቶች ተማሪዎች የሆኑት ዋናውን ጠላት ትትን ወደ ተቃዋሚዎች ደካማ ጎን አናትኩር የሚሏችሁ “ለመበላት ዝግጁ የሆኑ የፖለቲካ ገንፎዎች” (ደጋፊዎቻቸው) የሚዘላብዱት ንትርካቸው ከቁም ነገር አታስገቡት። አሁንም ጥሪው እና አንገብጋቢው የትግል ስትራተጂ በአማራ ሕብረተሰብ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቀዳሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስትራተጂ አይደለም የሚሉ ፖለቲከኞች  እና ሚዲያዎቻቸውን ከትችት ነፃ መሆን የለባቸውም። እነሱንም እንደየ ግባራቸው  እናወግዛቸዋለን።

ስለሆነም የትግሉ ጥሪ/ስትራተጂ “በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ቀዳሚ አጀንዳ አድርጎ የማይንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት/ሃይማኖት” የአማራው ሰቆቃ ድምፅ አንዳይሰማ በማድረጉ ረገድ እንቅፋት የሚሆን ሁሉ እያወገዝን ፤ አማራ የተባለው ታላቅ ሕዝብ ከጭፍጨፋ ለማዳን ለታላቅ ክብር እና ለታላቅ ብሔራዊ ክብር ቆመናል የምትሉ ዜጎች በነዚህም ላይ ተቃውሞአችሁን አንድታስተጋቡ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ለ22 አመት የታፈነው የአማራው ጩኸት አንድ ቦታ ላይ መቆም አለበት። ከጭፍጨፋው ባሻገር፤ አማራው ከማንኛውም የኢትዮጵያ ነገድ ሆን ተብሎ በስርዓቱ ሰዎች በባሰ ሁኔታ ድሃ አንዲሆን ከመደረጉ በላይ በትራኮማ በሽተኛ አንዲጠቃ ዓይነስውር ሆኖ በምርኩዝ እየተጓዘ ያለ በርካታ የአማራ ገጠር ሕብረተሰብ መሆኑን እየታወቀ “ከዛሬ ጀምሮ እኛም አማራዎች ነን፤ ማለት ያሳፈራችሁ የመንፈስ ሽባ ተቃዋሚዎች” በላያችሁ ላይ ቀና ብላችሁ የምታዩት እየጮኸ ያለው በሰማዩ ወለል ተስሎ ያለው በብዛት እየፈሰሰ ያለው የእምባ ከረጢት የማን መሆኑን በትከክል አንድታዩት ጥሪዬን አቀርባለሁ።  

አመሰግናለሁ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)  getachre@aol.com   Editor Ethiopian Semay -  Novemebr 03, 20014