Monday, July 14, 2014

‘የቀራንዮው እየሱስን’ ስም የተቸረው የአንዳርጋቸው ጽጌ ገበና ማሕደር፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ታጋዮች ጉዳይ!




 

ይህ ፎቶግራፍ በኢትዮጵያዊነት ስም በሴራ ተጨፍለቀው እነ አርበኞች ግምባር እነ ቤንሻንጉል ወዘተ…በጥምት ስም ለሻዕቪያ ተወርዋሪ ሃይል/ፈጥኖ ደራሽ ተብሎ ለሚጠራው “ለትህዴን” (ቲ ፒ ዲኦ ኤም) ተሰጥተው በስሩ እንዲንቀሳቀሱ የተደረገ ሻዕብያ ያዘጋጀው የጥምረት መሪዎች ምስል ነው።


ሻዕብያ ያዘጋጀው የጥምረቱ የ “ኢጥዴለ” መግለጫ ማንፌስቶ ነው
‘የቀራንዮው እየሱስን’ ስም የተቸረው የአንዳርጋቸው ጽጌ ገበና ማሕደር፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ታጋዮች ጉዳይ!


ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)
ከፍል  -2-


በአንድ ጠረጴዛዬ ላይ ቁጭ ብየ ሳስብ አማካሪዬ እና ተሟጋቼ የሆነው ሕሊናዬ አንዲህ አለኝ፦

“እኔ እና አንተ የምናርስበት የእርሻ ቦታ ታሪክ  ይባላል።በእርሻው ላይ ጊንጦች፤ እባቦች እና አመኬላዎች ይጋሩናል። ምርታችን “ፍትሕ ነው”። ፍትሕን አንዘራለን፤አንኮተኩታለን፤እናሳድጋለን። አጭደን ከምረን ፈጭተን የምንመገበውም ምግብ ከፍትሕ ሌላ ምግብ አናውቅም ። የሰዎች ልጆች ሁሉ የላቀ ምርት ነውና ፤እየተነደፍንም ሆነ ከሥር እየተወጋን  ፍትሕን ከመከላከል  የማንቦዝን በታሪክ እርሻ የምንገኝ የፍትሕ ሰብል አምራች ገበሬዎች ነን አለኝ” (ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)          


ይህ ሐተታ፤ ፍትሕን እየረገጡ፤ስለ ፍትሕ መጮሕ ልማድ ለሆነባቸው አንዳንድ የዲያስፖራ ጸሐፊዎች፤የሕግ ምሁራን፤ ተቃዋሚዎች እና ሚዲያዎቻቸው የዳሰሰ ሐተታ ነው። ባለፈው ሰሞን የሕዝባዊ ሃይል/ግንቦት 7 አባል የነበረው አንተነህ ጌትነት  ጋዜጤኞችን "ጠያቂዎች ብቻ መሆናችሁን አታስቡ ተጠያቂዎችም እንደሆናችሁ አትዘንጉ።" በማለት ለአንዳረጋቸው ጽጌ በመወገን ፤ኤርትራ ውስጥ  በሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች ላይ አንዳርጋቸው ጽጌ የፈጸመባቸው “ሰብአዊ ጥሰት” ለተቃዋሚ ሚዲያዎች ቢያሳውቁም፤ የአንዳርጋቸውን ገበና ላለማጋለጥ በወገንተኛነት ለግንቦት 7 ወግነው እሮሮአቸውን “አፍነው” ፤ ወተኞች በመሆን የተቃዋሚ ሚዲያዎች እና ጸሐፊዎቻቸው ላይ አባሪ ተባባሪነታቸውን በቅሬታ የገለጸበት በእኔ ብሎግ ላይ ከተለጠፈው ካለፈው የተወሰደ ሚዲያዎችን የወጠረ ጥቅስ ነበር። ዘሬም ሌላው የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባ የሆነው ወጣት ሽታው ሽፈራውን እና ኤርትራ ውስጥ ለ10 አመት መሽገው ወያኔነን ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት የሻዕብያ መሰሪ ገበና በአካል የሚያወቁ ሰዎች የሰጡንን መረጃ በጥልቀት አንቃኛለን።


የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ተከታዮች ‘አጭበርባሪ መሪዎቻቸውን’ ወደ ማንዴላ፤ወደ ጋንዲ እና ወደ ረቂቅ መንፈስነት በመለወጥ፤ የሰው ልጅ መብት ሲረግጡ፤አገር ሲሸጡና ሲክዱ ከሚገኙት “ጲላጦሶች” ጋር ሆነው ሲተሻሹ፤ዊስኪ ሲጫለጡ፤ ፖለቲካቸውን ሲያሻሽጡ ፤ሕዝብ ሲያተራምሱ፤በግድያ እና በሰይል (ቶርች) ዜጎችን ሲያቃዩ የነበሩትን፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሆኑትን የምናውቃቸው የኤርትራ እባቦችን “ወደ እርግብነት” ለውጠው ሊሸጡልን የከጀሉ፤ ፍትሕ ረጋጮችን ሁሉ ወደ ፖለቲካ ገበያ አውርደው “የቀራንዮው ክስቶስ” አስመስለው በተካኑበት የጽሑፍ ችሎታቸው ቀባብተው በማስዋብ  የፈዘዘው እና የደነነዘው ማሕበረሰብ አንደገና ለማጃጃል፤ የቀራንዮ ክርስቶሳቸውን አንድንገዛላቸው፤ አንዳርጋቸው ጽጌ የተባለ ፖለቲካዊ  ሸቀጣቸውን መሸጥ የጀመሩት አሁን አይደለም።

ወደ ሗላ ተጉዘን ብንኝ፦ በፍትሕ ረጋጭነት እና በብሔራዊ ወንጀሎች በመሳተፍ እና በመምራት መጠየቅ የሚገባቸው ለገበነኞቹ ለእነ ስዬ አበርሃ፤ ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ለእነ ቡልቻ ደመቅሳ፤ ለእነ ብርሀኑ ነጋ ፤ነጋሶ ጊዳዳ፤ ለሸኽ አብደል ከሪም (ጃራ)፤ለእነ ሌንጮ እና በያን አሶባ፤ከማል ገልቹ; እነ ጃዋር መሓመድን …. ወዘተ…ወዘተ… የቀራንዮውን እየሱስ፤የማንዴላ እና የጋንዲ የረቀቀ መንፈስነትን እና የፍትሕ አርበኞች የሚል ስም እየተቸራቸው የፖለቲካ ሸቀጣቸውን እንድንገዛቸው፤ ተሞክሯል።

የወያኔው ታምራት ላይኔም በአሜሪካኖች “የሃይማኖት ኔት ወርክ” በኩል እየታገዘ ተከታዮች አግኝቶ እንደ የቀራንየው እየስ እግሩ ላይ እየተደፉ የሚያለቅሱለት ተከታዮችን አይተናል። ታምራትም ከቀራኒዩው እየሱስ ጋር ኢትዮጵያ እስር ቤት ውስጥ ነጭ ልብስ ለብሶ በብርሃን ታጅቦ በሞስኮቱ ብቅ ብሎ እንዳገኘው እና እንዳየው፤ ለተከታዮች እያለቀሰ ሲያስለቅሳቸው አይተናል። ይህች ጉደኛ ዓለም ስንት ሸቀጥ በዱሩጇ አሽጋ ይዛለች።


የዲያስፖራውን ጭንቅላት በሃሰት ፖለቲካ እያጃጃሉ በየፓልቶኩ እና በድረገጾች ተሰግስገው ንባ እያፈሰሱ ስቅስቅ ብለው በማልቀስ አንዳርጋቸውን ወደ መለኰትነት እየለወጡት የሚገኙት የግንቦት 7 ጓዶች እና ጀሌዎች መለስ ብዬ ወደ ሗላ ስቃኛቸው፤ የወያኔ ጀሌዎች አምና ነሐሴ ውስጥ መሪያቸው መለስ ዜናዊ በድንገት ሲሰወርባቸው “ገዛ ተጋሩ” በሚባል የትግሬዎች ፓልቶክ የሰማሁት ልቅሶ፤ ምግብ አልበላም ባይነት፤ ዋይታ፤ ድንጋጤ እና ባዶነት ሳመዛዝነው፤ የግንቦት 7 ጀሌዎች ሊህቃን እና ሚዲያዎች፤ የገዛ ተጋሩ የመለስ ዜናዊ “ካልቶችን” ቦታ ተክተዋል።

በዚህ “የማይንድ ኰንትሮል ቢዝነስ” የማሻሻጥ ስለት ስንፈትሽ  ሊሂቃን የሚባሉ አብዛኞዎቹ የዲያስፖራ የተቃዋሚ ‘ኤሊቶች’ ግምባር ቀደም ተዋናዮች ሆነው ተገኝተዋል። የለመድናቸው ሸቋጮች፤ በፖለቲካው ብቻ ሳይወሰኑ በስፖርት ሴክተር ውስጥ ሳይቀር ተሰግስገው በታራ ዜግነት ሽፋን ፖለቲካ ሸቀጣቸው እና የገንዘብ ምንጫቸው ለማድረግ ሆን ብለው በረቀቀ ዘዴ የተንጠላጠሉባቸው ምልከቶች ተዛቤአለሁ።

የሓፈረት ትርጉም የማያወቁ አንዳንድ ምሁራን ተብየዎችም የንቀታቸው ብዛት “የኦሮሞ ነፃነት ግምባር” ብሎ ራሱን የሰየመ የሽብር ድርጅት “ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት አልከሰሰም፡ ከኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ አቅርቦ አያውቅም” ብለው ከኦነጐች እና ከነብርሃኑ ነጋ ጋር በየአለማቱ እየዞሩ እንደ እነ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው (ዶ/ር ዜሮ/0) የመሳሰሉ በአደባባይ ለሐሰት ጥብቅና ቆመው ሐሰትን ሲሸጡ እና ሲያሻሽጡ አንደነበር እና ዛሬም ከዛው ምግባራቸው የተቆጠቡ አይመስሉም ። ሐሰትን ለመከላከል አንዲያመቻቸው፤ “የፖቲካው ሸካራነት ለማስወገድ ሲሉ ነው አንዲያ ያሉት” የሚሉ የዋሃንም ገጥመውኛል። ኦነጎች “To fully exercise the rights of self - determination of the Oromo people” .  All Urban lands inside Oromia is part and parcel of the Oromia state that they will be controlled  by the Oromian government. The state of Oromia will have its own policy to these urban lands” የሚሉትን እስካሁን ደረስ የሚነበብ አንደ አዲስ የተጻፈው ይህ ፕሮግራማቸው ተዘርግቶ እያነበብነው “ደላሎቹ” ከነሱ በባሰ አሁንም “ወደ ኢትዮጵያዊነት መንገድ ተሞርደዋል” እያሉ  እየዋሹን ነው።

ህ ማኒፌስቶ “ኦነጐች ወደ ኢትዮጵያዊነት መጥተዋል” እያሉ እነ ብርሃኑ ነጋ ከሚዋሹን “የተሞረዱ ኦኖጎች” (የተሻሻሉ) ከሚባሉት ኦነጐች ያገኘሁት ፕሮግራም ነው።

እነሱ በግልጽ እየነገሩን እያሉ፤ኦኖጎች መገንጠልን ትተዋል የሚሉ በርከታ የተጃጃሉ አዋቂዎች እና አሻሻጮች ዛሬም አሉ። ኦነጐች ብልጠት እየተማሩ በመምጣታቸው፤ አብረዋቸው ከኢሳት ጋር ፤ከግንቦት7 ጋር ከጥምረት ፤ምናምን ምናምን ከሚባሉት፤  አሿሿጮች ጋር አብረው አሁንም በየእስቴቱ፤ በየገንዘብ ቅራማቱ አብረው “ኢትዮጵያዊያን” ተመስለው  ቄሶች እና ሼኮችን ጭምር ሁሉ ሳይቀሩ ይዘዋቸው ይዞራሉ።  ኦኖጐች “ነፍጥ” አንደማያዋጣቸው 40 አመት ስላዩት፤ አዲስ ስልት በመቀየስ “መርሲናሪ ሴልስ ሜን/ሴልስ ወመን/’ “አሻሻጮች” በማግኘታቸው ከማንም ጊዜ በበለጠ የተካኑ/better smarter /better intelligent ሆነዋል።  

ኦነግ የተባለው ከስልጣኔ እጅግ ፤እጅግ በጣም የራቀ ጀሌ የሚያስከትል ቡድን “አውስትራሊያ- ፐረዝ” ከተማ የሞረሹ አቶ ተክሌ የሻውን ሕይወት ላይ አደጋ ለመጣል በመዶለት “አሲድ” ወደ ፊታቸው ደፍተው አደጋ ለመጣል ዶልተው አንደነበር ተዘግቧል። ይህ ነው “ኦነግ ወደ ልቦናው ተመልሷል፤ በሰለጠነ ፖለቲካ እየተራመደ ነው” እያሉ ደላላዎቻቸው እኛኑን ለማጃጃል እየሞከሩ ያሉት

ሬ ደግሞ የሽምቅ ተዋጊ መሪነት እና የተጠራጣሪነት ስልት ስልጣና እና ልምድ ሳይላበስ፤ የኤርትራ ሰዎች ምንነት ሳያጠና፤ እነሱን አምኖ፤ ያለ ምንም ጥርጣሬ በእየ ዓረብ መዲናው እና በየ አውሮጳ እና አሜሪካ ከወዲያ ወዲህ ሲዘልል፤ ጠላት እጅ ውስጥ የገባው አንዳርጋቸው ጽጌ፤ በጠላት ሲያዝ  “ደጋፊዎቹ”  ወያኔን  ማውገዝ ሲገባቸው፤ ከላይ እንደጠቀስኩት ስብእናውን ወደ “ክርስቶስ ፤ ወደ ረቂቅ መንፈስነት፤ ከዚያም ወደ ማንዴላነት እና ወደ ጋንዲነት፤ እና የፍትሕ  ጠበቃ ” እያሉ  መቀባባቱን ስንመለከት፤ አንዳርጋቸው ኤርትራ ውስጥ እያለ “በአድርባይ ባሕሪው” ለሻዕቢያዎች አድሮ የገፋቸው ኢትዮጵያዊያን ማሕደር ስንፈትሽ፤ “አድማቂዎቹ አንደሚቀባቡት “የቀራንዮ ክርስቶስ፤ ረቂቅ መንፈስ” ሳይሆን፤ እሱን አምነው ኤርትራ ድረስ ሄደው በሰይል ላሰቃያቸው እና ለሻዕቢያ አስረክቦ ለሞት እና ለድብዳባ፤ አንዲሁም ለሻዕቢያ እርሻ አምራቾች እንዲሆኑ ለባርነት ላስረከባቸው ኢትዮጵያዊያን ሰለባዎቹ ግን “የሃሬና መጻጉእ” ነው። ፍትሕ እና አንዳርጋቸው አይገናኙም። ከቶውንም  አይጣጣሙም። 

ሕሊናን በመቦወዝ ስራ የተሰማሩ የግንቦት 7 “የማይንድ ኮንትሮል ፍሪክስ ግሩፕ” ደጋፊዎች፤ገጣሚዎች እና ጸሐፊዎች ማወቅ ያለባቸው፤ አንዳርጋቸው ጽጌ ይመራው ነበር የተባለው የግንቦት 7 ሽምቅ ተብዬው “ኤርትራ ውስጥ ኢትዮጵያዊ መንፈስም ሆነ ራእይ ያለው እንቅስቃሴ የለም።” ሲል የሕዝባዊ ሃይል የፋይናንስ እና  የአስተዳደር ክፍል ሓላፊ የነበረው በአንዳርጋቸው ጭካኔ እና ውሳኔ ለሻዕቢያ ደብዳቢዎች ተላልፎ “ሄልኰፕተር” ተብሎ በሚጠራው የሻዕቢያ ድብደባ /ቶርቸር/ በገመድ ቁልቁል ተዘቅዝቆ ታስሮ ሰውነቱ በሰይል የተዳከመው ከሞት አፋፍ ያመለጠው ወጣት “ሽታው ሺፈራው” ነግሮናል።

ወጣት ሽታው ሺፈራው በየ እንተርኔቱ የሚዘላብዱትን ፤ የግንቦት 7 ጉድ እና የአንዳርጋቸው ጽጌ ስብእና እና ምንነት፤ ኤርትራ በረሃ ሄደው በቅርብ በቅጡ፤ ያላዩት ጉዱን ያልተረዱ፤ ደጋፊዎች እና ያለቦታቸው የሚለቀለቁ ቃላቶችን እና ለቅላቂዎችን እጅግ ስላስገረሙት “የወረቀት ላይ ደፋሮች” ይላቸዋል።


አንዳርጋቸው ነበረበት በተባለው ሃረና መስልጠኛ ጣቢያ እና በረሃ የነበረው የሸምቅ ተዋጊው ሃይል ከፍተኛ ሃላፊነት የነበረው ሽታው “ኤርትራ ወስጥ” ስለሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ድርጅቶች ጉዳይ አንስቶ አንዲህ ይላል። 

“እነዚህን ሻቢያ አቡክቶ የጠፈጠፋቸውን ድርጅቶችንም ሆነ ለግል የእኩይ ተግባር ሲባል ሻቢያ የኛ ሆነውን አላማ ተሰማምቶ የገቡ ድርጅቶችን ተስፋ ማድረግ በራሱ ላም ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም ያክል ራስን ማዘጋጀትና መሸንገል ነው።” ይላል።

ተስፈኞቹ “የሚያከብሩት የቀራኒዮ  ክርስቶስ” ጭምር ድንገት ከሰማዬ ሰማያት ወርዶ ሽታው ሺፈራው የነገረንን፤ አውነታ ቢደግምላቸውም የሚያምኑ አይሆኑም። እስኪ ከሽታው በተለየ ሌላ የደርጅት መሪ “ከኤርትራኖች ጋር የቀረበ ግንኙነት መስርቶ የነበረ” ፤በትግሉ ለብዙ አመት እዛው ኤርትራ ለአስር አመት የቆየ፤ ልክ ሽታው እንደነገረን በሰፊው እና በጥልቀት ከነመረጃው የገለጸልንን “ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝን” እናዳምጥ። አንዲህ ይላል፦

“ይህ ሁሉ መረጃ በቪዲዮ የማሳያችሁ በኤርትራ ውስጥ ብዙ አመት በከንቱ ያሳለፍነው ኢትዮጵያ ወንድሞቻችን ከእኛው ትምህርት አንዲማሩ እና ተሳስተው ወደ እዛው አንዳይሄዱ ነው።”  ይላል ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ በዩቱብ ስለቀቀው መግለጫው ምክንያት ሲናገር።

ባጠናቀረው “የስእለ ደምፅ” መረጃው ላይ አንዲህ ይላል። “ኑ ወደ ኤርትራ እርዳታ እንሰጣችሗለን” ብሎ ሻዕቢያ የስልጠና የገንዘብ፤ የምግብ እና  የመረጃ እርዳታ ከሰጠን በሗላ “ተዋጊው ሃይል “በራሱ አስተዳዳር፤ በራሱ መሪነት፤ የድርጅት መግለጫ እና ፕሮግራም ሳይቀር ቀርጾ የሚሰጠን እሱ ነው። የኢትዮጵያዊነት ጥንካሬ ካየ ሆን ብሎ፤ አመራሩን በማናከስ ፤በመለዋወጥ በማጨቃጨቅ ስራ ጣልቃ ገብቶ ያምሰናል።

አርበኞች ግምብርን “አጋሮ” ውሰጥ ስንመሰርት ሁለት በሬ አርደን እንዳንካካድ “ደም” አፍስሰን ተማምለን ነው አርበኞች ግምባርን መሰረትነው። የረባ ስራ አንኳ ሳንሰራ፤ ለምሳሌ  ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ ለአምስት አመት ሙሉ በጭቅጭቅ ሻዕቢያ መሪ ሲቀይርልን አንዱ ካንዱ ሲያሳብቅ፤ እርስ በርስ ስንናከስ፤ በከንቱ ጊዜ አለፈ። ይህ ሁሉ ሲሆን በቅርብ የሚቈጣጠን የሻዕቢያው ትልቁ  ሰው ኮለኔል ፍጹም ይባላል። ከላይ ሆኖ የማናከስ ሴራ የሚመራው እሱ ነው።  የእኛ ጽ/ቤት እና የኮለኔሉ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ነው (በረሃ ውስጥ)።


ከዚያ ጠቅላላ ኤርትራ ውስጥ  ያሉትን ኢትዮጵያ የሚላቸውን ተዋጊዎችን ብቻ ሰብስቦ በኤርትራዊው ኰለኔል ፍጹም ቁጥጥር ሥር “ፕሮግራም ቀርጾ” እኛ ያላጸደቅነው ያልነደፍነው፤ ያለወቅነውን ፕሮግራም በመንደፍ  “ወህደት/ጥምረት” ብሎ ፤ ሁላችን ሰብስቦ “በትፕዲኤም”  በትግሬ ተዋጊው ሃይል ስር አንድንጠቃለል አድርጎ ፤ የወያኔ ተጋይ እና የስለላ ኦፊሰር የነበረው  ከኰለኔል ፍጹም ቢሮ ደርሶ ሲመለስ መንገድ ላይ አብሮት ሲጓዝ የነበረው ጥይት አርከፍክፎበት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሟቹ የ“ትፕዲኤም’ ፍስሃ ሃይለማርያም መሪያችን አደረጉት። በዚህ በጣም ተበሳጨን ፤ብዙ ንትርክ ተደረገ።

እዛው (ኢትዮጵያ) ውስጥ ያለምንም ዲሞክራሲ ወያኔ ከትግሬ መጥቶ እየገዛን ፤ አሁንደ ደግሞ እዚህ በረሃ ዲሞክራሲ ፍለጋ ስንመጣ ሌላ ትግሬ “ያለ ምርጫ እና ያለ የኛ እውቅና በጎ ፈቃድ አንዴት ይመራናል? እንዴትስ የኛ ድርጅት በትግራይ ቁጥጥር መሪነት አንዲውል አንፈቅዳለን!” በማለት ንትርክ ተፈጠረ ፤ በጣም ከፍተኛ ሁከት። …”።   ይላል ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ።

 ኮለኔል ፍፁም እና ኢሳያስ አፈወርቂን አንድንወዳቸው እና እንድናመሰግናቸው ሲሰብከን የነበረው አንዳርጋቸው ጽጌ፤- ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ የሻዕቢያ ምንነት በሚገባ ገልፆልናል።

ያውም ይላል፤- ፕሮፈሰር ሙሴ ተገኝ “ሻዕቢያ አርበኞች ግምባር የሚለውን መጠሪያችንን ቀይሮ ፤ አንዲሁም የሌሎችን ስም ቀይሮ በትግራይ ተዋጊዎች እና መሪዎች ስር አንደንመራ በማድረግ “ኢጥዴል” (EADC)
የኢትዮጵያዊያን ጥምረት ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ) በማለት ትህዴን አንዲመራው ተነገረን። በሻዕቢያ ትእዛዝ የአዋጁ እና መተዳደሪያ ረቂቅ አንዲሁም ያዋጁ ሰንደቃላማ እና የጥምረቱ ዲዛይን  ሻዕቢያ አዘጋጅቶ ተግባር ላይ አንዲውል ተደረገ።  ብዙ ጭቅጭቅ አስነሳ። 

ቡድኖችም የሚከተሉት ሲሆኑ ሁሉም በ “ኢጥዴል” የተጨፈለቁ። አነሱም (1)ትህዴን (TPDM) “ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት” ምናምን እያለ የወያኔዎች ቶን የሚመስል የሚዘላብድ ድርጅት ነው። ዛሬ አንደሚታወቀው (ዛሬ የሻዕቢያ ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ተብሎ በኤርትራኖች የሚነገርለት እና ‘የትህዴን’ ባንዴራም የኢትዮጵያ ሆኖ እመሃሉ ላይ የአክሱም ሃውልት ያለበት ነው። (2)ኢሕአግ (EEPPF) (3) ቤህነን (BPFM) (ቤንሻንጉል)  (4) ደኢሕፍግ SEPJEF (ደቡብ ሕዝቦች)ናቸው። ይላል።


ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ እየነገረን ያለው፤

የሻዕቢያ ዋና አላማ አራቱን ድርጅቶች አሰባስቦ፤ በአንድ ጨፍልቆ፤ ሻዕቢያ እያጠናከረልን ያለው ዘዴ/ሰትራተጂ የሚከተለው ነው ይላል። ‘ሌላው የሻዕቢያ ተላላኪ የሆነው በትግሬ ተዋጊ ሃይል ስር በትሀዴን ስር በመሆን በሂደት ተውጠን ‘አጀንዳ አስፈጻሚዎች” እንድንሆን፤ ሻዕቢያ ለወደፊቱ ሌላ ሁለተኛ የወያኔ ትግሬዎች አሻንጉሊት በማጠናከር ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር እንዲያመቸው የራሱን ስልት እና አጋር ቡድን ለማጐልበት የጠነጠነው ስተራተጂካዊ  ስልት ነው።’ ይላል። እውነቱ ነው ፕሮፌሰር ሙሴ።


አርበኞች ግምባር ከኤርትራ ለመውጣቱ ዋናው ምክንያት የሆነው ይላል ፕሮፌሰር ሙሴ “ቢረባም ባይረባም 10 አመት ሙሉ ራሳችንን ችለን የኖርነውን ኢትዮጵያዊያኖች፤ በትግሬዎች ድርጅት ገብትን ተውጠን “ትህዴን” አንዲመራን መደረጉ ነው”። “ይህ ያደረገው ደግሞ እኛ ሳናወቀው ማእከላዊ አመራሩ ሳይሰበሰብ “ማአዛው” የተባለው መስከረም አታላይን የተካው የሻዕቢያ አስፈጻሚ ሆኖ የነበረው የግማባራችን ሃላፊ ተብሎ ሻዕቢያ የሾመው ሰው፤ የሻዕቢያ “ሪሞርክዮ” (ተሳቢ/ተጐታች መኪና) ተብሎ ቅጽል ስም የተሰጠው ማአዛው ነው።” ይላል።   

ስለ ኦነጐችም አንዲህ ይላል። ኦኖጎችም ሆኑ ኦጋዴን ነፃ አውጪዎች አብረን ተሰባስበን ነን ያለነው።  እና የኛ መስርያቤት ከአስመራ ከከተማው ትንሽ ወጣ ብሎ ያለው ስፍራ ነው፤ እኛ እና ኦነጐች ያለነው መስርያቤት “አንድ ቦታ ነን” አንጫወታለን ፤እንገናኛለን። እነሱ የሚደረስባቸው በደል በጣም ብዙ ነው፤ ከእኔ ይልቅ እነሱ ራሳቸው ቢነግሯችሁ የተሻለለ ነው።”ይላል።


(ታስታውሱ እንደሆነ ከጥቂት ወራቶች በፊት ብርሃኑ ነጋ  በቃለመጠይቁ ላይ “አርበኞች ግምባርን” አንስቶ “አርበኞች ግምባር የተባለ ተዋጊ ኤርትራ ውስጥ የለም። ካሁን ወዲህ ስለ እነሱ “ኢሳት” ምንም ዜና አንዳያነሳ ያነገረዋል!” ማለቱን ትዝ ይላችሗል?)። ለምን ይመስላችሗል? ሻዕቢያ ልክ የድሮው አርበኞች ግምባር በ “ትጥዴ” ለመጨፍለቅ አንደሞከረው ሁሉ፤ ዛሬም ግንቦት 7 እንዲመራው ያንኑ ስልት በአንዳርጋቸው እና በብርሃኑ ነጋ ተሞክሮ “አምቢ” ስላሉት እንደሆነ ምንም አያጠራጥርም። “ኤርትራዊ/ዐዘቦታይ(?)” ነው እያሉ አንዳንድ ሰዎች የሚጠረጥሩትን  በሞላ አስገዶም የሚመራው የሻዕቢያው ተወርዋሪ ሃይል “የትህዴን”  ቡድን አመራር እና ሰራዊት ለመቆጣጠር አንዲያመቸው “ግንቦት 7” ግምባር ፈጥረናል እያለ የነሱን መዝሙር እና ሰልፍ ሲያሳይ በግንቦት 7 ቱለቱላ ሚዲያው በኢሳት እየደጋገመ ሲያሳየን የነበረው ልብ ይለዋል። ለዚህም ነበር ሞላን እየደጋገመ በቃለ መጠይቅ ኳኩሎ “ሊሸጥልን” የሞከረው።  

ፕሮፌሰር ይህነን አስመልክቶ ገለጻው ይቀጥላል።

"ኤርትራ ውስጥ ሄደን በኢትዮጵያዊነት የተደራጀን ሁሉ የድምበር ጠባቂ ነው ያደረገን። ለምሳሌ “ወያኔ እና ሻዕቢያ” ዘወትር የሚፈላለጉበት አደገኛ የድምበር ቀጣናዎች “አይተርፍ” “ኩርባ ዲዳ”፤ “አንቶረ” “ማይ ጠብ” ወዘተ…በሚባሉ ፤ አደገኛ የድምበር ቀጠናዎች እኛን ሳያማክር በስልጣኑ፤ በጉልበቱ፤ ሻዕቢያ ሆን ብሎ እኛን እዛው ‘ወታደራዊ ካምፕ/ ቤዝ/ጣቢያ” መስርተን ፤ አንድንሰፍር አድርጎናል። ምን ለማድረግ? ደምበሩን ለመጠበቅ እና የመጀመሪያ ጥይት ቀማሾች እና “አብሪዎች” ሆነን አንድንሰዋለት እና አንድንከላከልለት ሆን ብሎ እዛው በሳተላይትነት/በአብሪነት መድቦን ነበር። አስር አመት ሙሉ ደምበር ጠባቂ አድርጎ ሲጫወትብን ኖሯል።” ይላል፡፤ ኤርትራ መሄድ የሚታየው እውነታ ሲያስረዳን።


አርበኞች ግምባር ተበሳጭቶ ግማሹ ሸሽቶ  እየጠፋ ብትንትኑ ከወጣ በሗላ የኢፒፒኤፍ ሰራዊቱ ባዶ ቀረ ። እነ አቶ ዘወድ አለም እና ስለሺ ጥላሁን ፤ግሩም ዘገዬ ከለንደን አርበኞች ግምባር ለመጎብኘት በመጡበት ጊዜ፤ ባዶ ስለነበር፤ ሻዕቢያ አጭር “ማልያ” (ከናቲራ) የለበሱ ከቲፒዲኤም/ ከትግሬዎቹ/ ሰራዊት ተበድሮ አርበኞች ግምባር በማሰመሰል፤ አቀረበ። በተንኰል ሰንደቃላማ እየተውለበለበ፤ ቀረርቶው ሁሉ እንዲያሰሙ ተደረገ። ያኔ ትግሬዎቹ ወደ 5 ሺሕ ተዋጊዎች ነበሩዋቸው። እኛ ግን በዛው ሁሉ አመት ኖረን፤ ሁለት/ሦስት መቶ ግፋ ከዚያ በላይ መውጣት አልቻልንም። ሆን ብሎ የሚመጡትን ተዋጊዎቻችን ወደ ሻዕቢያ እርሻ እያላከ “አዳክሞ” በኤርትራ ጠባቂዎች  አክላሽንኮቭ እየተጠበቁ በቀን 30 ናቅፋ እየተከፈላቸው አንዳንዱም በነፃ የሰቲት እርሻ እያሳረሰ
አዳከማቸው።

የሆኖ ሆኖ ሻዕቢያ የሚፈልገው፤ እኛም ሆነ ትህዴን በብዛት አሰልጥኖ ወያኔ ድምበር ለመጣስ ሲሞክር መጀመሪያ የሚዋጋለት ሰራዊት ትህዴን እና እኛ ነን። እዛው ድምበር በራሱ ትዕዛዝ የሚመድበንም ደምብሩ አንድንጠብቅለት ነው። ምክንያቱም ሻዕቢያ ተዋጊ ሰራዊት የለውም፤ አጅግ ተዳከሟል፤ ወኔ ያለው፤የጠነከረ ተዋጊ የለውም። ስለዚህም እነሱን በትህዴን እየተካ ይገኛል”።  ይለናል ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ። "ስለዚህ ለኛ ሲል ያደረገው በጎ ነገር የለም። ሻዕቢያ እርግማን እና ውግዘት እንጂ ምስጋና የሚገባውም አይደለም"  ይላል ፕሮፌሰሩ።


ይህንን አስመለክቶ በተመሳሳይ በቅርቡ ከሕዝባዊ ሃይል ከሞት ያመለጠው የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባ ወጣት ሽታው ሺፈራውም አንዳርጋቸው ጽጌ አሜሪካ ድረስ መጥቶ “ስለ ሻዕቢያ ምጋና አንደሚገባው እና እስካሁን ድረስ ነጻነታችን የዘገየው በኤርትራ በኩል መሽገው ለአመታት የተቀመጡ ፈዛዛ ተዋጊ ሃይሎች ስንፍና እና ዳተኛነት አንጂ  ሻዕቢያ “ፋይፍ/5 ስታር” ኰከብ በሚባል ለነፃነት ኢትግላችን ለምናደርገው ምቾት እና ድጋፍ ውስጥ እያስተናገደን ስለሚገኝ  “ሻዕቢያን አንውደድ፤እናክብረው፤ ‘ሻዕቢያ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋና” ይገባዋል። በማለት አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ሻዕቢያ አዛኝነት እና በጐ ስራ ሰሪነት አንድናመሰግን ሲማጸነን፤ የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባ የሆነው ወጣት ሽታው ሺፈራው ግን በበኩሉ አንዲህ ይላል።


“በተለይ ደግሞ ትልቅ ፌዝ የሚሆነው ለዚህ የሻቢያ እኩይ ተግባር ምስጋናይ ገባዋል ሲባል ነው። ከፌዝም የሞኝ ፌዝ ማለት ይህ ነው። የገዛ መንግስታቸው ኤርትራኖች አንኳ ሳይቀር ያልወደዱት እኛ የምንወድበት ምን በወጣን? ሻዕቢያ ምንድ ነው የሰራልን?"  ይላል ወጣት ሽታው ሺፈራው።

ህዝባዊ ሃይሉ ከሌሎች ድርጅቶች በተለየ የሻቢያ ቸርነትን አግኝቶ የተመሰረተ እንዳልሆነ አንዳንድ ሃቆችን ማስቀመጥ ይቻላል። በተለይ ለአመታት በመዋጮ ተማሮ ቅሬታውን አምርሮ መግለጽ የጀመረውን በውጭ በስደት የሚኖረውን ዲያስፖራ የፖለቲካ ኪሳራ እና ተችሮት የተቋቋመ ለመሆኑ እና ከቸነፈሩ ለመዳን የተደረገ የተሎ ተሎ ይድረስ፤ የትግል ምስረታ እንደሆነ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው።

ስለዚህ የግል ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ካልሆነ በቀር የሻቢያ አቋም እየታወቀ ወደ ኤርትራ ለመሄድ የሚያስደፍር የሌሎች ድርጅቶች ተሞክሮም ሆነ የራስ ፖለቲካዊ ስብእና እንዳልነበረ በወቅቱ ውሳኔው ሲወስን በአንድ ሰው የበላይነት (በአንዳርጋቸው) የጸደቀውን በሌሎች ለይ ምሰል በተሰየሙት የስራ አስፈጻሚዎች ውድቅ የሆነውን ነገር ግን ተግባራዊ የሆነውን ውሳኔ ያስታውሷል።” ይላል ሽታው።

እንዲያውም “ህዝባዊ ሃይሉ ከተመሰረተ በኋላም ይታዩ የነበሩ ችግሮች የዚህ አይነት የድርድር ችግር ውጤት ለመሆናቸው ምንም አይነት ጥርጥር የለኝም።” ይላል ወጣት ሽታው ሺፈራው የሕዝባዊ ሃይሉሉ የአስተዳደር ክፍል ሃላፊ የነበረው።

ሽታው ስለ አንዳርጋቸው ምንነት ሰሞኑ የግንቦት 7 አድናቂ እና ደጋፊ ሚዲዎች የሆኑት. “ኢሳት፤ዘሓበሻ፤ ኢትዮሚዲያ….” አንደሚለቀልቁት ሳይሆን አንዳርጋቸውን በቅርብ ያወቀ እና አብሮ ባሕሪውን የተከታታለ ሽታው አንዲህ ሲል ይነግረናል።

በሻቢያ መርህ መሰረት መንቀሳቀስ ለይስሙላ የተዘጋጀው ድርጅታዊ ህገ ደንብ ተግባራዊ ያለመሆን፤አባላት በሻቢያ የጉልበት ስራ ላይ መጠመድ፤ለትግል ቆራጥ አላማ የነበራቸው አባላት በሆነ ባልሆነው ሰበብ እየተፈለገላቸው ብቻ መታሰር፤የተለመደ ክስተት ነው።….

…..በተለይ በአንዳርጋቸው በኩል ከፎቶ ግራፍ እና ከቪዲዮ ቀረጻ የዘለለ ስራ ለመስራት ያለመፈለግ፤ወደ አውሮፓ ለገንዘብ ስብሰባ ሲሄድ የሚለብሰውን ኮንጎ ጫማ ተሸክሞ ለመሄድ ጉጉት ያለበትን ያህል ሲመለስ ደግሞ ጠላት እንዳየች ጃርት የሸበተ ጸጉሩን እንጨፍርሮ ለሻቢያ ነው የማስረክባችሁ በሚል ስሜት ሁል ግዜም የሚገልጽ መሆኑ እና ሌሎችም ከሻቢያ ምድር ላይ የግድ ሊታጨዱ የሚገቡ ውጤቶች ሆነው ተገኝተዋል። በመሪዎች በኩል ያለውን ከወረቀትያልዘለለ የትግል ሞራል በማንሳት ትግሉ ከግለስቦች ጥቅም እና ከሻቢያ ፍጆታ የዘለለ ትርጉም የሌለው መሆኑን በተጨባጭ ስላየነው ድርጅቱ በፈጣን ኪሳራ ከመውደቅ አይድንም። ይህነን  ማስቀመጥም ይቻላል።”…

….ትንፋሽ ለትንፋሽ የመጠጋጋትን ያህል የሚጠይቅ ሆኖ ሳለ በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት እና በገንዘብ ፍለጋ ሽፋን እያመካኙ በየውጭ እና አረብ አገሮች ኮንጐ ጫማ ተጫምተው ለማሳያ አገሩ ሁሉ ሊዞሩ  መፈለጋቸው፤ አንዳንዶቹ  ያውም በትርፍ ጊዜ ትግልን አሜሪካ እና አውሮጳ ተቀምጠው ለመምራት ሲከጅሉ ማየት የዋህ ታጋዮችን ከንቱ ጽዋ እና መከራ አንዲቀበሉ ከማድረግ አይዘልም።”


ስለ ሕዝባዊ ሓይሉ ያለበት ሁኔታም አንዲህ ያብራራል።

“የሻቢያ አቋም እና የሰዎችን ድብቅ አጀንዳ በአሳዛኝ ሁኔታ በቅጡ መረዳት የቻለው የሃይሉ አባላት ያለበትን ሁኔታ መግለጽ ተገቢ ነው የሚል እምነት አለ። አንድም ሆነ ሁለት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያላስገባ ያለመኖሩ ቀዳዳውን ተጠቅሞ መውጣት የማይፈልግ አንድም አባል (ከአንዳርጋቸው ውጭ) ያለመኖሩ ነው።

ባለፈው ሁለት ወር አካባቢ እንኳን 16ሰዎች ጥበቃውን ሰብረው ማምለጥ መቻላቸው፤በዚህም አጠቃላይ የሰው ሃይሉ ወደ ግማሽ እንዲወርድ ማድረጉ ሌሎችም ቢሆኑ አንድም ሊያመልጡ ሲል ስላልተሳካላቸው እስርቤት የሚገኙ፤አለበለዚያም ሊያመጣ የሚችለው የፖለቲካ ኪሳራ ተፈርቶ በቁም እስር ላይ የሚገኙ መሆናቸው እና የመሳሰሉት በቦታው ተገኝተው የእነ አንዳርጋቸውን መሰሪነት ጠንቅቀው የተረዱ ውድ የኢትዮጵያ ጅግኖች እያስተናገዱ የሚገኟቸው ትይንቶች ናቸው።”
ይላል የአንዳርጋቸው ሰለባ ሽታው ሺፈራው።

ለማጠቃለል ያህል ዛሬ አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ የመውደቁን ድንገተኛ ክስተት ተከትሎ ምሁራን ተብየዎች እና ጀሌ ሚዲያዎቹ አንዲሁም ተቃዋሚ ጻሀፊዎች እና አንዳንድ የፖለቲካ እና የስቪክ ድርጅቶች አልፎም “አክቲቪስቶች” እያስተጋቡ ያሉትን አንዳርጋቸውን በማዋብ ዘመቻቸው  የሚጠቀሙባቸው አስገራሚ ቃላቶች ስመለከት እነዚህ ሁሉ “ፍትሕን የሚረግጥ አንቃወማለን” እያሉ ሲለፍፉ፦ ፍትሕን ረግጦ ሻዕቢያን ተማምኖ ኢትዮጵያዊያን ለሰይል (ቶርቸር) እና ለግድያ፤ አንዲሁም ለጉልበት ሥራ ለሻዕቢያ ጨካኝ ገራፊዎች መጫወቻ አድርጎ አሳልፎ፤ ሲሰጣቸው የነበሩትን የአንዳርጋቸው ጽጌ ሰለባዎች ያስሰሙት የድረሱልን ዋይታ እሮሮ፤እምባ እና አቤቱታ ጀሮ ዳባ ብለው፤ ስለ ፍትሕ ምንንት ሲጮሁ መስማት አጅግ ይዘገንናል።


ይህንን አስመልክቶ፤ ከግንቦት 7 እና የሻዕቢያ አፈናና ግድያ በመከራ አምልጠው ከወጡት የህዝባዊ ኃይል አመራሮች አባስ/ ማስረሻ (የስልጠና ከፍል ኃላፊ) አና ኮስሞስ (የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) ቴዎድሮስ ስዩም (ምኒሊክ) (የምልመላ ክፍል ላፊ) ሽታው (አስተዳደር እና ፈይናንስ ሃላፊ)፤ዳኒኤል፤አንተነህ፤ ወዘተ ወዘተ… የመሳሰሉ ታጋዮች አንዳረጋቸው ጽጌ ከሻዕቢያ ጋር በጠበቀ ሴራ እየተመሳጠረ፤ ጨካኝነት እና ጸረ ኢትዮጵያ እና ጸረ ሰብአዊነት ስብእናውን ያዩትን “በእኛ ይብቃ” በሚል
ፈው ያሰራ ትን መግለጫ፤ ሕሊና ላለን ሰዎች ያስደመመንን ሰነድ አስነብበውናል።


ሽታው ሽፈራው ለሦስት ወር ከዛፍ ጋር እየታሰረ ከጥዋት እሰከ ምሽት ለ 12 ሰዓታት አንድ ጊዜ ብቻ ውሃ እንዲጎነጭ እየተደረገ ሄሎኮፕተር/ወፌ ላላ እየተገረፈ ያሳለፈው መከራ በዝርዝር እንባ እየተናነቀው በቪዲዩ እና በድምጽ ገልልናል።

ይህንን የተመለከተ

 ለግንቦት 7 ሆነ ለሌሎች ተቃዋሚዎች ያለመተቸትን ከለላ ማን ሰጠ? የእነ “… ወይም ሞትፖለቲካ  (ያሬድ  ኃይለማሪያም) 

በሚል ትችት ከወደ አውሮጳ አካባቢ የሚኖር የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ወጣት ያሬድ ኃይለማሪያም በፌብርዋሪ 2014 አንዲህ በማለት ያሰመረበትን ልጥቀስ እና ትችቴን ልደምድም።

“ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው “…. ወይም ሞትአስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል። ደርግ ወይም ሞትየጀመረው የኼው የተወላገደ እና ጸረ-ዲሞክራቲክ የሆነው አስተሳሰብ ሳንወጣ ዛሬምወያኔ ወይም ሞትግንቦት 7 ወይም ሞትኦነግ ወይም ሞት ‘… ወይም ሞትበሚሉ ካድሬዎችና ስሜታዊ የድርጅት አምላኪዎች ተተክቶ እያደናበረን ይገኛል።  … ያለመታደል ሆኖ ከሃገር መሪዎች አንስቶ የፖለቲካ ተሿሚዎች፣ ካድሬዎችና ደጋፊዎች ለዚህ አይነቱ ኃላነፊት ብዙም ሳይጨነቁ ባደባባይ ያሻቸውን ይናገራሉ፣ የዘላብዳሉ፣ ይሳደባሉ፤ የሚጠይቃቸውም የለም። …

,…. ያጎለበትነው የፖለቲካ ባህል ቁጥራቸው ቀላል ለማይባሉ እጃቸው በንጹሃን ደም ለጨቀየ፣ በርሃብና በድህነት በሚሰቃየው ሕዝባችን ውድቀት ሞስነው ለጠበደሉ፣ በግል ህይወታቸውም ሆነ በሙያቸው ላልተሳካላቸው አዳዲስ እና ነባር ፖለቲከኞች መደበቂያ ጫካ ሆኗል። … 

ይልና ያሬድ 

" ከግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች እና መስራቾች የነበሩ ከኤርትራ ካንዳረጋቸው የሞት ገመድ ሸሽተው በየቦታው ተደብቀው ሕይወታቸው በስጋት አሁንም የሚኖሩ ዜጎቻቻን እሮሮ እና አቤቱታ አስመልክቶ በጻፈው ከላይ በተጠቀሰው ርዕስ ከአንባቢዎች ያገኘው አስተያየት በሦስት ከፍሎ አንዲህ ሲል ይገመግማቸዋል።

 “…  በዚህ ርዕስ እንድጽፍ ምክንያት የሆነኝ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይበእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ፤ የወያኔ ሳያንስ የነፃ አውጪዎቻችን (የግንቦት 7) የግፍ ተግባር እና የመገናኛ ብዙሃን ዝምታበሚል ርዕስ (ለጻፍኩት )ከአንባቢዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶች ናቸው። …..”ሦስት አይነት ነቀፌታ አዘል አስተያየቶች ጽሑፌን አትመው ባወጡ ድኅረ-ገጾችና በማኅበረሰብ የመወያያ መድረኮች ላይ ተነበዋል።  ”…..በሦስቱ ጎራ ላሉት አስተያየቶች ምላሽ ልስጥ።” ይል እና በሦሰት አይነት የተከፈሉ አስተያየት ሰጪዎች ከዘረዘረ በሗላ ባስገረመው በአንደኛ ክፍል የመደባቸው የሰዎች ነጸብራቅ የታዘባቸውን አንዲህ ይገልጻቸዋል፤-

 “የመጀመሪያው አስተያየት ባነሳሁት ፍሬ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሳይሆን ብስጭትና ንዴት በተቀላቀለበት ስሜት ዝልፊያናዋናው የአገር ጠላት ወያኔ እያለ እንዴት ግንቦት 7 ትተቻለ ግንቦት 7 የነቀፈ ሁሉወያኔነው፣ ተቃዋሚዎችን መተቸትትግሉንያዳክማል፣ ተቃዋሚዎች ከነሃጢያታቸው መደገፍ ብቻ ነው ያለባቸው፣ ገፋ ብሎም ወንጀልም ቢሰሩ እንኳን ሊጠየቁ አይገባም ወያኔን እስከታገሉልን ድረስ የሚሉ ሃሳቦች የታጨቁበት ነው። እውነት ለመናገር ከእንደነዚህ አይነት ግራ ከተጋቡ ሰዎች ጋር ለመወያየት ያስቸግራል። ስለፖለቲካም ያላቸው ግንዛቤ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል። ከዚህ በፊት በሌሎች ጽሑፎቼም እንዳልኩት እነኚህ ሰዎች ገሚሱ በቅን ልቦና ለውጥን ብቻ ከመናፈቅ፣ ገሚሱም አዕምሯቸው በቂምና በበቀል ስሜት ተወጥሮ ፖለቲካውን መሳሪያ ያደረጉ፣ ገሚሶቹም ስለ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል ያላቸው ግንዛቤ ውሱን ወይም የተዛባ በመሆኑ መፈክራቸው ሁሉግንቦት 7 ወይም ሞትኢሳት ወይም ሞት ወዘተ የሚል ነው። እነዚህ ሰዎች አዕምሮዋቸውን ከፈት አድርገው በፃነት እንዲያስቡ እና ከካድሬነትና ጭፍን ድጋፍ ወደ ሰላና በእውቀት ላይ ወደተመሰረተ የፖለቲካ ደጋፊነት እራሳቸውን እንዲያሳድጉ እመክራለሁ።”

ካለ በሗላ በሦስተኛ ደረጃ የመደባቸው አስተያየት ሰጪዎች (ሁለተኛ የመደባቸው ‘ወያኔ ነህ ብለውታል) ደግሞ እንዲህ ይገልጻቸዋል፡

“ሦስተኛው አስተያየት ኃላፊነት ከሚሰማቸውና የጉዳዩን ክብደት በቅጡ ከተረዱ ወገኖች የተሰነዘረ ነው። ይህውም ጉዳዩ የሰብአዊ መብትን የሚለለከት ስለሆነ በተበዳዮቹ ላይ ደረሱ ለተባሉት ጥቃቶች በቂ ማስረጃ አለህ ወይ? የሚል ነው። በመጀመሪያ እንኳን ለፍትሕ፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት እንታገላለን ያሉትን የፖለቲካ ኃይሎች ይቅርና አለም በሰብአዊ መብቶች እረጋጭነት ያወቀወን አንባገነናዊ የወያኔ ሥርዓት ለመተቸትም ሆነ ለመንቀፍ የሁል ጊዜ መነሻዬ ማስረጃዎች ናቸው። እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች መረጃና ማስረጃዎች ያላቸውን ልዩነትም ሆነ ጠቀሜታ ጠንቅቄ ስለማውቅ ያለመረጃም ሆን ያለ ማስረጃ ማንንም ባደባባይ ለመውቀስም ሆነ ለመተቸት አልደፍርም። በተነሳው ጉዳይ ላይም በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይም ማስረጃዎችን መዘርዘር ይቻላል።” ሲል የግንቦት 7 የአንዳርጋቸው ሰለባዎች ክስ በበቂ ማስረዳት እና መረጃ አንዳለው መልሶላቸዋል።


በመጨረሻ የሕዝባዊ ሃይል ተዋጊዎች የነበሩ የአንዳርጋቸው ሰለባዎች እሮሮአቸውን እና በግንቦት 7 አመራር ላይ እያሰስሙት ያሉትን ክስ አንዳይደመጥ ሆን ብለው በማገድ (አሳት፤ዘሐበሻ ኢትዮ ሚዲያ፤ቋጠሮ… የመሳሰሉ የግንቦት 7 ስብስቦች )የሚባሉ ሚዲያዎች  የኔንም ጽሑፎች እና ምርምሮች ጭምር እንዳይነበቡ ከወያኔ በባሰ መልኩ እያገዱኝ ያሉትን የተቃዋሚ ሚዲያዎችን ላንዳድዶቹ እትችቱን እና ምሬቱን እንዲህ ሲል  ያጠቃልላል፦


“የፍረጃ ፖለቲካውን ፈርታችሁ ወይም እናንተም ’… ወይም ሞትየፖለቲካ አዙሪት ውስጥ ገብታችሁ አቋም ለያዛችሁትም ሁሉ እግዚያብሄር ለእውነት የምትቆሙበትን ልቦና እና መንፈሳዊ ወኔ ይስጣቸሁ በሚል ልሰናበት።” በማለት አንዳርጋቸውን ወደ ማንዴላነት፤ጋንዲነት፤ ክርስቶስነት እና ረቂቅ መንፈስነት እየለወጡብን ያሉትን ሚዲያዎች እና ጸሐፊዎቻቸው  ስለተቸበት  በሰፊው ስለ ሰብአዊ መብት ጉዳይ ጥልቅ አውቀቱን እና መረጃወን ለመመልከት ለግንቦት 7 ሆነ ለሌሎች ተቃዋሚዎች ያለመተቸትን ከለላ ማን ሰጠ? የእነ “… ወይም ሞትፖለቲካ  (ያሬድ  ኃይለማሪያም)  በሚከተለው አድራሻ ጐብኝቶ የወጣቱን ስራዎች ማየት ይቻላል።(http://humanrightsinethiopia.wordpress.com/) 

ተቃዋሚው እና ሚዲየዎቻቸው ከነጻሐፊዎቻቸው ጭምር የፖለቲካ አጭበርባሪዎችን ፤በክርስቶስ ተክለ ሰውነት መለወጥ እና ቀባብቶ ለመሸጥ የሞሞከር ልምዳቸውን ካላቆሙ ፤እኛም የንጹሓን እሮሮ እና ጩኸት ክስ ማስተጋባት ቀዳሚ ትግላችን ከማድረግ አንቆጠብም።

ያሬድ ሃይለማርያም እንዳለው፤  ደርግ ወይም ሞትየጀመረው የኼው የተወላገደ እና ጸረ-ዲሞክራቲክ የሆነው አስተሳሰብ ሳንወጣ ዛሬምወያኔ ወይም ሞትግንቦት 7 ወይም ሞትኦነግ ወይም ሞት ‘… ወይም ሞትበሚሉ ካድሬዎችና ስሜታዊ የድርጅት አምላኪዎች ተተክቶ እያደናበረን የሚገኘው መቆም አለበት።  … ያለመታደል ሆኖ ከሃገር መሪዎች አንስቶ የፖለቲካ ተሿሚዎች፣ ካድሬዎችና ደጋፊዎች ለዚህ አይነቱ ኃላፊነት ብዙም ሳይጨነቁ ባደባባይ ያሻቸውን ይናገራሉ፣ ይዘላብዳሉ፣ ይሳደባሉ፤ የሚጠይቃቸውም የለም። …

,…. ያጎለበትነው የፖለቲካ ባህል ቁጥራቸው ቀላል ለማይባሉ እጃቸው በንጹሃን ደም ለጨቀየ፣ በርሃብና በድህነት በሚሰቃየው ሕዝባችን ውድቀት ሞስነው ለጠበደሉ፣ በግል ህይወታቸውም ሆነ በሙያቸው ላልተሳካላቸው አዳዲስ እና ነባር ፖለቲከኞች መደበቂያ ጫካ ሆኗል..." እና ምሁራን ተብየዎች እና ጀሌ ሚዲያዎ አንዲሁም ተቃዋሚ ጻሀፊዎች እና አንዳንድ የፖለቲካ እና የስቪክ ድርጅቶች አልፎም “አክቲቪስቶች” መንገዳቸውን ያስተካክሉ። እንላለን። አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) Google it “Ethiopian Semay”.  Email  getachre@aol.com