Saturday, March 29, 2014

ቀዳማይ ወያኔ፤ ዓድዋ እና የካቲት 11 በወያኔ ትግሬዎች እይታ ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)



ቀዳማይ ወያኔ፤ ዓድዋ እና የካቲት 11 በወያኔ ትግሬዎች እይታ 

 ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያ ሰማይ አዘጋጅ)


ከላይ በግራ በኩል የሚታየው ፎቶግራፍ፤ የቀዳማይ ወያኔ መሪ ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ለዳግማይ ወያነ መሪ ለመለስ ዜናዊ በቀዳማይ ወያኔ የተገለገሉበት የጦር ሜዳ መነፅር ሲያስረክቡት ነው።
Insanity

ከላይ በግራ በኩል የሚታየው ፎቶግራፍ፤ የቀዳማይ ወያኔ መሪ ብላታ ሃይለማርያም ረዳ ለዳግማይ ወያነ መሪ ለመለስ ዜናዊ በቀዳማይ ወያኔ የተገለገሉበት የጦር ሜዳ መነፅር ሲያስረክቡት ነው።

ብዙዎቹ በዚህ ጽሑፍ የቀረቡ መረጃዎች እና ትንታኔዎች በሂደት ላይ ካለ ከሚቀጥለው አዲስ መጽሐፌ የተገኙ ምንጮች ናቸው።እኛ በታሪክ አጋጣሚ ተገኝተን ጸረ ወያኔ አቋም ይዘን የምንተነትን ጸሐፊዎች የተቻለንንን ያህል የወያኔ ቅጥፈቶች እያጠናን ስናቀርብ ማንበብ ሰልችቶአቸው ግማሽ ገጽ አንብበው ወደ ቀላል ዜና እና ትንታኔ የሚሮጡ ብዙ እንደሆኑ አገምታለሁ።እንዲህ ዓይነት ልምድ ጥልቅ እውቀት እንዳይኖረን ያግደናል።እንድያ ከሆነ የሚሞግቱንን ጠላቶች በማስረጃ ለመመከት ደካሞች እንሆናለን።መረጃ ሲያጥረን ሕዝቡ የጠላት ‘ፕሮፓጋንዳ’ ተማሪ ይሆናል።። ስለዚህም ብርቱ ድካም፤ምርምር ጌዜ እና መስዋእት የተደረገባቸው ጽሑፎች ማንበብ ድርሻችሁ እንደሆነም አትዘንጉ።

ባለፈው በክፍል ፩  የወያኔ  ትግሬዎች በጉንደት፤በጉራዕ፤በዶጋሊ ፤….ርነቶች የሚዋሹት ውሽት ሲመረመር” በሚል ለብዙ አመታት ሲነግሩን የነበረውን  “የወቅቱ ጦርነቶች” የገጠሙት ትግሬዎች ብቻ ነበሩ፤ እያሉ የሌሎች ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ዋጋ በማሳጣት ሲዋሹን የነበረው ጀብደኛ ትምክሕት በጐንደር፤በጐጃም፤በወሎ  እና በሸዋ ጦር ተዋጊዎች ጭምር እየታገዙ ጦርነቱን ገጥመው ድል የተቀዳጁ አንደነበር አንጂ ትግሬ ብቻውን እንዳልተዋጋ እና ድሉም የብቻችን ነው የሚለው የወያኔ የታሪክ ቅሚያ እንደበፊቱ በቸልተኛነት መታለፍ እንደሌለበት ከሃቅ የራቀ ውሸታቸውን በወቅቱ የተጻፉ መረጃዎች በማስረጃ አጋልጫለሁ። ክፍል ፪ “የዓፋሮች እና አፄ ዮሐንስ ፍትግያ” የሚለው ጽፌ አዘጋጅቼው ልለጥፈው ነበር፤ እሱን ወደ ክፍል ሦስት በማቆየት ይህ ክፍል ሁለት ብለን በመሰየም እናንብበው። 

ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግባቴ በፊት ባለፈው ሰሞን አንድ የወያኔ ደጋፊ በአንድ የድሮ መጽሔት ታትሞ ከነበረው ጽሑፌ የሚከተለው አንብቦ ነበር።

“ዓድዋ አኽሱም ሽረ ጹሩያት ተጋሩ
ራያ እንደርታ ተምቤን ጎረቤት አምሓሩ”
ማለትም
“ዓድዋ አኽሱም እና ሽሬ የጠሩ ትግሬዎች
ራያ እንደርታ ተምቤን ያማራ ጎረቤቶች

ይህ ዘረኛ ግጥም ወያኔዎች በረሃ እያሉ በእረኞች በኩል እንዲዘፈን ካሰራጩት ዘፈን አንዱ ነው። የወያኔው ደጋፊ ይህንን ግጥም ካነበበ በሗላ፤ ሰሞኑን በኢመይል የስድብ ውርጅብኝ እና ንዴት የተቀላቀለበት ደብዳቤ በመላክ “ወያነ ትግራይ አንኳን በገዛ የራሱ ሕዝብ በቀዳማይ ወያኔ ዋና አንቀሳቃሾች በነበሩት በተምቤን፤በእንደርታ እና በራያ ሕዝብ ቀርቶ፤ በሌሎችም ቢሆን ዘረኝነት እንደሌለው እያወቅክ፤ ሆን ብለህ ከጽንፈኞቹ ጋር በመወገን ለጽንፈኛ ፖለቲካህ አንዲመችህ የፈጠርከው ፈጠራ እንጂ ወያኔ በነዚህ ሕዝቦች ምንም የዘረኝነት አባዜ አላሳየም።” በማለት ያቀረብኩት መጣጥፍ በውሸት የተመረኮዘ እንደነበር ተከራክሮኛል። እኔም ይህ አስተሳሰብ በብዙ የዋህ ደጋፊዎቹ ላይ ስለሚኖር፤ሁሉም አንዲያውቀው መረጃው ከዚህ መጣጠፍ ባቀርበው ለሚጠራጠሩ ሁሉ ጠቃሚ ይሆናል ብየ ስላሰብኩ ጽሑፌን በዚህ በመግቢያ ልጀምር እና ወደ ዋናው ርዕሴ ልግባ።

ወያኔ በእንደርታ ታጋዮች ላይ በአውራጃዊነት የተመሰረተ የማግለል ፖሊሲ ይከተል እንደነበር ከድርጅቱ የስለላ እና የሓለዋ ወያኔ (እስር ቤት) ዋና ሓላፊ ከነበረው ከአክሱማዊው ከብስራት አማረ አንደበት የተነገረን መረጃ እነሆ እንዲህ ይላል።  

1969-..በድርጅቱ ተነሳስቶ የነበረው ቀውስ/ትርምስ (ሕንፍሽፍሽ) እያሉ የሚጠሩት የደቡብ ትግራይ ልጆች ገብሩን መሃል አድርገው ከሌሎች የዓድዋ እና የአክሱም ተወላጆች በማነጻጸር የሃላፊነት ቦታ (የደቡብ ሰው) ማለትም የእንደርታ ሰው በመሆኑ አልተሰጠውም። መለስ ዜናዊ(ዓድዋ) አታኽልቲ ቀጸላ፣ ሸዊት ዳኘው (አክሱም) በመሆናቸው የማአከላዊ ኮሚቴ ውክልና ተሰጥቷቸዋል። ገብሩ አስራት ግንአስተዳደር እና በመሳሰሉት ከእነሱ የተሻለ እንጂ ያነሰ አይደለም ብለው የመከራከርያ ነጥባቸው አድረገው እንደወሰዱት ይታወቃል፣፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ገብሩ በአሉታም በአዎንታም ያለው ነገር እንደሌለ ቢታወቅም ያኔ የተሓህት መሪዎች በገብሩ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው ግልፅ ነው፣፣…” ብስራት አማረ ( በትግሉ ወቅት የህወሓት የስለላው ክፍል እና የህወሓት እስር ቤቶች ጉዳይ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረ )። ከዚያ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር” (ካናዳ ውስጥ ከሚታተም  በሐዋርያ ጋዜጣ የቀረበ)
1981/82 . አቤራ ላይ በተደረገው የማሌሊት/ህወሓት ጉባኤ ገብሩ አስራት ለማሌሊት/መለስ ለስላሳ ለም መሬት ሆኖለት መለስ ዜናዊ ያለውን ሁሉ በታማኝነት ለማረጋገጥ በፖሊሲያቸ/ባመለካከተቻው ለየት ያለ አቋምና ጥንካሬ ያላቸው ጓዶቹን {አንዳንዱም በእንደርታ ተወላጆች ላይ ሳይቀር ማለቱ ነው ለምሳሌ እንደ እነ መስፍን አማረ ላይ}፣፣(ኮሎኔል) መስፍን አማረ 1969 /70 ገብሩ አስራት ለአመራር ብቁ ነው አድልዎ መፈጸም የለባችሁም ብሎ ስለ ገብሩ የቆመ ከድርጅቱ መሪዎች ጋር የተከራከረ የእንደርታ ተወላጅ፣- የሗላ ሗላ ገብሩ ከመለስ ዜናዊ ጋር ሆኖ ስሙን በማጥፋት በመወንጀል መስፍን አማረን አመራር እንዳይወጣ እንቅፋት በመሆን ቀደም ብሎ በአራጃዊነት አድልዎ የተጠቃው ገብሩ አስራት በአድርባይነት ለመለስ ካደረ በሗላ (ለዓድዋዎች እና አክሱሞች.. አድሮ) ስልጣኑን ለማቆየት ችሏል”   ብስራት አማረ ከዚያ ያደረሰ መንገድ ሲመረመር በአህጽሮት የተጨመረ የኔ። (የወያኔ ገበና ማሕደር ገጽ 149-151 ደራሲ ጌታቸው ረዳ። ምንጭ ሃዋርያ ጋዜጣ -አዘጋጅ ሙሉቀን ሙጨ- ካናዳ)። በነገራችን ላይ ኮሎኔል መስፍን አማረ ዛሬ ብርጋዴር ጀኔራል ማዕርግ ያለ የስረርዓቱ የውጭ እና የውስጥ ልዩ የደህንነት ጉዳይ ዋና የበላይ ተቆጣጣሪ ነው።
በድርጅቱ ዋና ዋና ሰዎች አንደበት የተነገረን በደም ጥራት ቀለም የተቀባው ፋሺስታዊው የወያኔ የጥላቻ ብትር ለራሱ ሕዝብ እንኳ እንዳልማረው ነው። በነገራችን ላይ ብስራት አማረ ወያኔ ዘረኛ ነው ይበለን እንጂ እራሱም ባለፈው ቅዳሜ (ማረቸሀ 15/2014 በፈረንጆች አቆጣጠር) “ገዛ ተጋሩ” በመባል የሚታወቀው በተዋጣላቸው ጸረ አማራ ዘረኞች የሚመራ ፓል ቶክ የጎጃም ሕዝብ “ዝቅተኛ፤ኢድየት፤ እና ሪታርድ ነው!” በማለት የጎጃም ሕዝብን የዘለፈቺው ሕድያት ትግራይ የተባለቺው የራያ እና አዘቦ “ጨርጨር፤መዀኒ” ልጅ /የፓልቶኩ ዋና ባለቤት ልብ ይለዋል።) በእንግዳነት ተጠርቶ “አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ሲደርስ ወደ አገር አንዳይገባ በመከልከሉ” ምክንያት ይመስለኛል፤ በጉዳዩ ማብራርያ እንዲሰጥ በተጠየቀበት ወቅት ያገዱትን የወያኔ ከፍተኛ ሹሞች “ዲቃላዎች” በማለት ሲዘልፋቸው ተደምጧል። አንግዲህ የትግል አጋሮቹ ወደ አገር አንዳይገባ ስላገዱት “ዲቃላዎች” ብሎ ሲዘልፋቸው፤ የወያኔ ዘረኛ በሽታ ሁሉንም አንዳጠቃቸው ማሳያ መረጃ ነው። በጎሳ ፖለቲካ መደራጀት ‘የማሰብ ሚዛንህ የሚያዛባ’ የጥላቻ ፖለቲካ ነው፤ወያኔ በደም ጥራት የሚጓዝ ፋሺስት ነው፤የምላችሁም ለዚህ ነው። አሁን ወደ ዋናው ርዕስ ልውሰዳችሁ።

በዛሬ ትችቶቼ ሚከተሉት ርዕሶችን እንመለከታለን።

1)     ዓድዋ እና የካቲት 11
2)    አንድ ሃይማኖት፤ አንድ አገር፤ አንድ ቋንቋ፤ የቀዳማይ ወያነ ፍልስፍና?
3)    ዮሐንስ ትግሬዎች አንደሚቀባቧቸው ሳይሆኑ፤ በጥፋትም ከምኒልክ አይለዩም
4)    በቀዳማይ ዋያኔ ያልተሳተፈ የትግሬ ተወላጅ ከማሕበረሰብ አንዲገለል የታወጀው አዋጅ

በቅርቡ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በጋለ ስሜት የዓድዋን በዓል ሲያከበሩት ወያኔዎች ብቻ አንጀታቸው አርሮ ሳያከብሩትና ብዙ ሳይናገሩበት ውሃ ውስጥ እንደገባች አይጥ ድማጻቸው እንዳጠፉ ታዝባችሗል። ለምን አንጀታቸው አረረ? የሚለው ጥያቄ መመለስ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ከንጉሥ ሃይለስላሴ ይልቅ ጣሊያኖች ትግራይን ቢያስተዳድሯት ምርጫቸው እና ምኞታቸው እንደነበር “የማነ ገብረመስቀል” የተባለ የወያኔ ደራሲ “ቀዳማይ ወያነ” በሚለው የትግርኛ መጽሐፉ ነግሮናል። የተገላቢጦሽ ሆኖ የትግራይ ሕዝብ በጣሊያን ከመንበርከክ ያዳኑትን አፄ ምኒልክን በጠላትነት በመፈረጅ፤ አፄው በአዋጅ ጠርተው፤ ያስተባበሩት እና የመሩት የዓድዋ ጦርነት “የድል ብስራት” በዓል ከማክበር ይልቅ ‘ባንዳው ወያኔ’ ኢትዮጵየን ለማፈራረስ እና ‘የባሕር ወደቦቿን’ ለጠላቶቿ አሳልፎ ለመስጠት ከጠላቶቿ ጋር በማበር የካቲት 11/1967 ዓ.ም ደደቢት ወደተባለው በረሃ የወጣበትን “የታላቁ ሴራ” የካቲት 11 ቀን  በመላ ዓለም የሚገኙትን የወያኔ ጀሌ ትግሬዎች በማሰባሰብ በደመቀ አክብሮ ውሏል።

 ደረግን ለመጣል በሚል ሽፋን የአማራን ሕዝብ መንፈስ እና ሕልውና ለማጥፋት በየካቲት 11/1967 ዓ.ም የተመሰረተበትን ይህ “የባንዳዎች ታላቁ ሴራ” ብለን የሰየምነው በዓላቸው በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ፤ በትግሉ ግዜ የረዷቸው አገሮች እና በተለይም የሱዳን መንግሥት አምባሳደር ሆኖ አዲስ አበባ ተቀማጭነቱ ያደረገ የወያኔን ድረርጅታዊ መልዕክቶችን ከሱዳን እየተቀበለ አዲስ አበባ ለነበሩ ዋና ዋና የወያኔ ህቡእ አባሎች (አንደ እነ ዶክተር መንገሻ የመሳሰሉትን) በመገናኘት ሲያስተላልፍ የነበረው እና በሗላም ወያኔ ደርግን ድል ነስቶ አዲስ አበባ ሲገባ ባንዳዎቹ መለስ ዜናዊ እና ሥዩም መስፍንን ከካርቱም አዲስ አበባ ድረስ በስሲና አይሮፕላን እያበረረ ወደ አዲስ አበባ ያደረሳቸው ሱዳናዊው አምባሳደር ‘ጀኔራል ደ/ር አልፋቲሕ’ እንዲሁም የሱዳኑ መሪ ‘ዑመር አል በሽር’ በተገኙበት አክብረውታል። በነገራችን ላይ ዶክተር መንገሻ የወያኔ አባል አልነበረም፤ ዶ/ር መንገሻ ትግሬ በመሆኑ ብቻ “ደርግ”  እስር ቤት አስገብቶ በመግረፍ ገድሎታል። በማለት በራዲዮናቸው እና በመጽሐፍቶቻቸው ደርግን በውሸት ወንጅለውታል። አሁን ድግሞ ዶ/ር መንገሻ ደምበኛ የወያኔ አባል እንደነበር እና መልእክቶች ሲተላለፉም ከወያኔ ወደ አልፋትሕ፤ ከዚያ ወደ ዶር መንገሻ ይተላለፉ እንደነበረ አልፋትሕ በአንደበቱ በዓሉ ቀን ለተሰበሰበው ሕዝብ ተናግሯል።

አምባሳደር፤ እንዲሁም የጸጥታ እና ደህንነት ሹም የነበረው አልፋትሕ በወያኔ በዓል ላይ ተገኝቶ “የወያኔ አባል መኖሩ እና ‘ጥብቅ ምስጢሮች ሲተላለፉ’ በእርሱ በኩል ወደ አዲስ አበባ ይተላለፍ አንደነበር በአንደበቱ የተናገረው አስደንጋጭ ታሪካዊ ምስክርነቱ በስሕተት “በዩቱብ ስዕለ ድምፅ” ላይ ከተለጠፈ በሗላ፤ በማግስቱ ባስቸኳይ አንዲነሳ እና “ሬስትሪክትድ” አንዲሆን አድርገውታል። ዩ ቱብ ስትፈትሹ የምታገኙት የአህያቸው የ “ብፃይ ደሳላይ (ሃይለማርያም ደሳለኝ) (ብፃይ ደሳለይ የማታውቁ ካላችሁ፤አስገደ ገብረስላሴ በ45.00 ብር ገዝቶ ለወያኔ ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ የሰጠው ‘ብፃይ ደሳለይ’ ሲባል የነበረ የወያኔ ‘ሲናር አህያ’ ነው። ደሳለይ ከብፃይነት የማዕረግ ሹመት አልፎ ወያኔ ለጭነት ሲገለገልባቸው ለነበሩ በርከት ላሉ ትግራይ ውስጥ  የነበሩ የወያኔ አህዮች ሁሉ አለቃቸው የነበረ አህያ ነው። የደሳለይ ታሪክ ብዙ ነው። ጠላት በቅርብ ርቀት ወደ እነሱ እየተጠጋ ከሆነ ጆሮው ‘ኩር’ አድርጎ በማቆም ያስጠነቅቃቸዋል፤ይባላል። ሌላም ሌላም… ) ማለት “የሃይለማርያም ደሰላይ” ንግግር፤ “የስዩም መስፍን” እና “የአልበሽር” ብቻ  ነው የተለጠፈው። አንዱ ወዳጄ ደውሎ “አልፋትሕን” አድምጬው አንደሆን ጠይቆኝ ፤እኔም አንዳደምጥቁት ስነግረው፤ እሱም ለምን የአልፋትሕ ብቻ ከዩቱብ እንዳነሱት ሲጠይቀኝ፤ ወያኔዎች ያልጠበቁት ምስጢር በአልፋትሕ ድንገት ይፋ በመሆኑ፤ ሱዳኖች በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሳይወሰኑ “እራሳቸውም ታጋዮች ሆነው ድርጅታዊ ስራ በመስራት” የኢትዮጵያን ደህንነት አንዴት አንደተፈታተኑት ምስጢሩ በታሪክ አንዳይመዘገብ ስለሰጉ” ይሆናል። ስለው፤ እሱም “አይመስለኝም። ሲል ለምክንያቱ እንዲህ ይላል። አልፋትሕ የተጠቀመበት ቋንቋ ጥሩ አንግሊዚኛ ስለነበረ፤ አስተርጓሚ ሆኖ ወደ ትግርኛ ሲተረጉም የነበረው የወያኔው ታጋይ ደ/ር ተወልደ ዓጋመ ሲተረጉም መላቅጡ አበላሽቶት ባሳፋሪ የቋንቋ አተረጓጎም ችሎታ ይተረጉመው  ስለነበር፤ ለተወልደ ክብር ሲሉ ነው “ያገዱት” ብሎ ነግሮኛል። እውነትም ትርጉሙ ካንድ በዱክትርና መዓረግ ያለ ምሁር የሚደመጥ የትርጉም ችሎታ አልነበረም። ስለሆነም ቪዲዮው ማግኘት አትችሉም። አግደውታል።

 የሱዳን ስትራቴጂ ፍላጐት ምን እንደሆነ የምናውቀው ቢሆንም አገራዊ በዓል ሳይሆን አንድ የፖለቲካ ድርጅት ባዘጋጀው በዓል  ለማክበር መንግሥትን የሚያክል የወከለ የአንድ አገር ፕረዚዳንት ሲገኝ ፈረንጆች “ስትረንጅ” የሚሉት ድምዳሜ አድርሶናል። ይህ የሱዳኖች ግንኙነት ከወያኔዎች ያገኙትን የመሬት እና የሰክዩሪቲ ጥቅማጥቅም ተንተርሰው እንደሆነ የሚያጠያይቅ አይደለም።  ወያኔዎች አገርን እና ሕዝብን ለሥልጣናቸው ሲሉ ሸጠውታልና የወያኔ ትግሬዎችን እንጂ ሱዳናዊያኖችን መውቀስ አይቻልም።  የአልፋትሕ አስገራሚ ንግግር የዩቱብ አድራሻው ከዚህ በታች ያለው አድራሻ ነበር፡ በማግስቱ እንዲነሳ ተደርጓል።
ሆኖም ወያኔዎች ከማገዳቸው በፊት በሌሎች ኢትዮጵያዊያን በኩል ተቀድቶ ስለነበር፤ በዩቱብ ወጥቷል። ይህንን የአልፋታሕ ንግግር ሙሉውን ለማድመጥ ይህንን አድራሻ ይጠቀሙ፡ Sudan official reveals TPLF screts   http://youtu.be/yfeBMv885pk


የዓድዋ በዓል ለምን አላከበሩትም ወይንም ለምን ተገቢውን ድምቀት ነፍገው ወደ የካቲት ወደ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት የምስረታ ቀን በዓል ቀልባቸው ተጠመደ? ብዙ ምክንያቶች አሉ። ወየኔዎች ዓድዋን የሚመለከቱት ‘የአማራዎች፤የምኒልክ ክብር የሚያሞግስ ነው የሚል ስሜት ስላላቸው ባያስገርመንም፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው በየመጽሐፍቶቻቸው ገልጸውልናል። “ምኒልክ ይዟት የዘመተ “አረንጓዴ፤ ቢጫ እና ቀይ” ሰንደቅ አላማ ከጣሊያኖቹ “አረንጓዴ ነጭ እና ቀይ” ባንዴራ በትግራይ ሕዝብ ዓይን የሚታዩት እኩል  ናቸው። የሰንደቃላማዎቹ ልዩነት በቀለም ሲለያዩ፤ ሁለቱ ቅኝ ገዢዎቻችን እንዲሁ ያኛው ነጭ ያኛው ጥቁር (አበሻ) ቆዳ ስላላቸው ብቻ እንጂ፤ ሁለቱም (ገዢዎቻችንም ሆኑ ሰንደቃላማዎቻቸው) ለትግራይ ሕዝብ ምናችን አይደሉም። ባዕድ እና ኮሎኒያሊስቶች ናቸው።” በማለት የወያኔ ጋዜጠኞች፤ደራሲዎች በመጽሐፍ መልክ እየጻፉ ወጣቱን እያስተማሩት እንደሆነ ገልጫለሁ። ያውም “ጣሊያን ቢቆይልን ይሻለን ነበር በማለት የትግራይ ሕዝብ ተናግሯል” እያሉ በድፍረት ጽፈዋል። (‘ቀዳማይ ወያነ’ የሚለው የትግርኛ መጽሐፍ በየማነ ገብረመስቀል የተጻፈውን እና በገብረኪዳን የተጻፉትን….የመሳሰሉትን አንብቡ)።

የማነ ገብረመስቀል የተባለው ወያኔ አንዲህ ይላል። ትግርኛ ለማታነብቡ ወገኖቼ ትንሽ ቀንጨብ አድርጌ ከዚያ የየማነ ገብረመስቀል  ጉደኛ መጽሐፍ ልጥቀስ። እንዲህ ይላል።

“የጣሊያን ወራሪ አምስ አመት በቆየበት ዘመን፤ ለራሱ ጥቅም ሲል ጀምሮዋቸው የነበሩ የልማት ተቋማት፦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤የጤና ተቋማት፤መንገድ/ጥርጊያ፤ዘመናዊ አስተዳደር፤የግብር አከፋፋል እና ዘመናዊ ሸቀጣ ሸቀጥ ዕቃዎች በማቅረብ በኩል ከሃይለስላሴ መንግሥት ሲነጻጸር የጣሊያኑ ሥርዓት ለትግራይ ሕዝብ የተሻለ አስተዳዳር እና ልማታዊ ነበረ ማለት ይቻላል። የሃይለስላሴ ስርዓት ከስደት ዓለም ከተመለሰ በሗላ፤ ጣሊያን ጀምሯቸው የነበሩት ማሕበራዊ ዕድገቶች ትግራይ ውስጥ ተቋረጡ። እነኚያ ጣሊያን ያቋቋማቸው የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶች ወና ሆነው ፈራርሰው የአህያ እና የበቅሎ ማሰሪያ ቦታ ሆነው ቀሩ። ይህ ሊሆን የቻለው፤የሻዋ ገዢ መደቦች ‘በጀት የለንም’ በሚል ሽፋን የትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት የተፈጸመ እርምጃ ነበር። ይህም ሴራ በትግራይ ሕዝብ  መጥፎ ስሜት ፈጥሮ ነበር። (ኮ/ል ቃለ ክርስቶስ አባይ (1997) የ1953 ዓ.ም የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ከ1908-1966 ዓ.ም የኢትዮጵያ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ሂደት ገፅ 71) (ቀዳመይ ወያነ ገጽ 68-69 የማነ ገብረመስቀል)

“የንጉሱ ከስደት መመለስ በሗላ የትግራይ ሕዝብ እንደተመኘው ሳይሆን የተካው ባዕዳዊና ወራሪ የሆነ አገር በቀል ወራሪ ነበር ጣሊያንን የተካው። በነጭ ጣሊያን ወራሪ ወታደሮች ሲወረር የነበረው የትግራይ ሕዝብ በአገር በቀል በሃይለስላሴ ጥቁር ወራሪ ወታደሮች ተወረረ፤ተጨቆነ፤ተጨፈጨፈ። ጣሊያን ለራሱ ሲል ልማት እና ማሕበራዊ አግልግሎት አስፋፍቷል። የክፍለሃገሩ ተወላጆች በሆኑ መሳፍንቶች አንዲያስተዳድሩት አድርጓል።  ሃይማኖታቸው እንዲያስፋፋ በቋንቋቸው እንዲጽፉ እና እንዲዳኙ ፈቅዶላቸው ነበር። ሃይለስላሴ ሲመጣ ግን የነበሩትን መብቶች እና ልማቶች ተነጥቀው ወደ ፍጹም አሃዳዊ ስርዓት መተካቱ ሕዝቡ አልወደደውም፤፡ጣሊያን ለትግራይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የአካባቢ አስተዳደር መብቶች በቋንቋቸው፤በሃይማኖታቸው እንዲኰሩ እና እንዲያድጉ ሲፈቅድ፤ሃይለስላሴ ግን እነኚህ በጣሊያን የተፈቀዱ መብቶች ነጥቋቸዋል።”  ((ቀዳመይ ወያነ ገጽ 69-70 የማነ ገብረመስቀል 2005 ዓ.ም)

ጣለያን ከተባረረ በሗላ፤ ነፃነት መጣ የተባለው ነፃነት ሳይሆን ነጭ ወራሪ ወጥቶ እሱን (በቆዳ ቀለም የትግራይን ሕዝብ) በሚመስሉ ጥቁር ወራሪዎች መተካቱ ነው። በሌላ አነጋጋር፤ልዩነቱ አረንጋዴ፤ነጭ፤ቀይ ቀለም ያለባት የፋሺስቶች የነጮቹ ጣሊያን ወራሪ ባንዴራ ከተሰቀለችበት ወርዳ፤ አረንጓዴ ቢጫ፤ቀይ ባንዴራ እማሃልዋ ዘውድ የደፋ የይሁዳ አንበሳ ምልክት በአረፈባት ባንዴራ መተካቷ ብቻ ነው። እሷም ብትሆን የሸዋ ገዢ መደቦችን የምትወክል እንጂ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ወይንም የትግራይን ሕዝብን የምትወክል ባንዴራ አይደለችም።” ((ቀዳመይ ወያነ ገጽ 70-71 የማነ ገብረመስቀል 2005 ዓ.ም)

ስለዚህም የማነ ገብረመስቀልም ሆነ መሰል ወያኔዎች የነገሩን፤ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ በምንም መልኩ የትግራይ ሕዝብ ሰንደቃላማ አይደለችም ብለውናል። ሰለሆነም ነው የቻይናው ቅድ የሆነው ኮሚኒስታዊ የድርጅታቸው ባንዴራ በማሰራት ያንተ ሰንደቃላማ ሰርተንልሃል፤ ይህ ነው ባንዴራህ ብለው በልብሳቸው እና በየበዓላቸው እንዲሁም በየመኪናቸው እና መኖርያ ቤታቸው እንዲሁም በየቤተክርስትያን፤ መስጊዳቸው፤ በትምህርት እና መንግስታዊ ተቋማታቸው የድርጅት ባንዴራ የሕዝብ ባንዴራ በማለት እያውለበለቡት የምናያቸው። ለዚህም ነበር መለስ ዜናዊ “ጨርቅ” በማለት ሰንደቃላማችን ያንኳሰሰበት ዋናው በስተጀርባው የገፋፋው የመነሻ ምክንያትም ይኼው “ሰንደቃላማችን አይደለችም” የሚለው ስሜት ነው።

የወያኔ ካድሬዎች ስለ ዓድዋ ድል ያላቸው መጥፎ እይታ ከዚህ ሰንደቃላማ እና ምኒልክ ጋር የተያያዘ ጥላቻ ነው። ማስረጃ አንዳንዱን ልጠቅስላችሁ እሻለሁ። ለምሳሌ በትምክሕት በጎሰኛነት በመነሳሳት የትግራይ ነገሥታት ደካማ ሰነድ በመሸሸግ የሸዋ/አማራ ነገሥታትን ደካማ ሰነድ እያጐላ በአገር ሸያጭነት ሲከሳቸው ፤ የትግራይን ነገሥታት እና መሳፍንትን ግን በአገር ወዳድነት በማሽቀርቀር በከንቱ መወጠር የሚታወቀው ሽማግሌው የወያኔው ታጋይ መምህር ገብረኪዳን ደስታ፤ ስለ ዓድዋ ጦርነት የተናገረው ቃል በቃሉ እጠቅሳለሁ። እንዲህ ይላል፦

“በዓድዋ ጦርነት አረ የምኒልክ ሰራዊትም አያስፈልግም ነበረ! የትግራይ ትግርኚ ሕዝብ (ትግሬ እና ኤርትራ ሕዝብ) ብቻውን ይችለው ነበር፡ ብቻውን ጣሊያንን! የምኒልክ ሠራዊትም አስፈላጊ አልነበረም! እጅ እና እግሩን አስረው፤ መንቀሳቀስ የለብህም ስላሉት ነው። የትግራይ ሕዝብ እኮ ጣሊያንን ለመምታት የምኒልክ እርዳታ እኮ ምንም አያስፈልገውም። ይኸ ሕዝብ እኮ ለዝንተ አለም እራሱ የራሱን አካባቢ ጠብቆ የቆየ ህዝብ እኮ ነው።” ምንጭ Exclusive Interview With Memhir Gebrekidan Desta - Part 2  http://youtu.be/Qm3WZL1doLo

በቃለ መጠይቁ ብቻ ሳይሆን በየትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንተ እስከ ዛሬ በገጽ 179 መጽሐፉ እንዲህ ብሏል፦

“የትግራይ ሕዘብ ብቻውን የተፋለመባቸው የጦር ሜዳዎች ብዙ ናቸው። አብነት ካስፈለገም ጉዳጉዲ፤የጉራዕ፤የስሐጢ፤ የኮፊት፤የዶጋሊ፤የመተማን እና የኰዓቲት ዓውደ ውግያዎች ብቻ መጥቀሱ ይበቃል። (የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንተ እስከ ዛሬ በገጽ 179)

ይህ አባባል፤ ከንቱ መወጣጠር ካልሆነ በስተቀር፤ በወቅቱ የትግራይ ሕዝብ ሲያሰማው ከነበረው “የረዳት ያለህ” ጩኸቱ ጋር አበሮ አይሄድም። “ሓጺርያ ኣድግስ ወትሩ ዒሉ” (አጭር አህያ ሁሌም ውርንጭላ)፤ካንገቱ በላይ አሻግሮ ማየት ያቃተው በመሳፍንቶች ባሕሪያዊ ትዕቢት የሚመራው ገብረኪዳን ደስታ፤ የጣሊያንም ሆኑ ሌሎች ወራሪዎች በትግራይ መሬትም ሆነ በኤርትራ (አምደጽዮን በ13ኛው ክ/ዘመን ከቱርክ ጋር ያደረገው ውግያ አስታውሱ፤ከዚያም በሌሎቹ በ16ኛው ከ/ዘመን) ሌላ ቀርቶ መተማ የተደረገው ጦርነት እንኳ ጎንደሮችንም አልተካፈሉም ብሏቸዋል። አንደምናውቀው በዓድዋም ሆነ በሌሎቹ አውደ ውግያዎች የትግራይ ሕዝብ ብቻውን የገጠመበት የውግያ ታሪክ አልነበረም። በተለይ ትግራይ በጣሊያን ወራሪዎች (ዓድዋ እና ከዚያም በሗላ በሰለኽለኻ፤ሽሬ..እንደባጉና..በማይጨው ወዘተ….ከጐጃም እና ከጐንደር ከሸዋ መጥተው የመሩት ውግያም ወያኔዎች አልተካፈሉም ብለው በዘፋኛቸው በኪዳነማርያም ረዳ ግጥምና ዘፈን ከድተውታል።ትዝታ ሃዲስ አለማዮህ መጽሐፍን አንብቡ) በሗላም በ1998ዓ.ም በባድሜ ከሻዕቢያ ጋር ያደረገው ጦርነት) የተደረጉ ጦርነቶች የትግራይ ሰው ብቻውን ገጥሞ ያሸነፈበት ታሪክ የለም። በተለይ ዶጋሊ ጉራዕ የመሳሰሉ ውጊያዎች የትግሬዎች ብቻ የተሳተፉበት አይደለም። (ገጽ 289 እስከ 299፣“የኢትዮጵያ ታሪክ ከመጀመሪያው  እስ አሁኑ ዘመ፣ጸሐ ፊዎች፦ አንድርዜይ ባርትኒስኪ እና ዮዓና ም ቴል- ኒየችኮ” ተርጓሚ፦ ዓለማ የሁ አበበ 2003) ለዚህም መረጃ የሚሆናችሁ ባለፈው መጣጥፌ http://www.ethiolion.com/Pdf/02262014yeweyanie_tegrewoch.pdf በኢትዮላዮን እና በሌሎቹ ድረገጾች ያቀረብኩትን ሙግት ይመልከቱ።

ወያኔዎች ሆኑ ኤርትራኖች፤ በተለይ ወያኔዎች በትግርኛ መጽሐፍቶቻቸው እየነገሩን ያለው፤ “ተጋሩ ናብ ዘለውዎ አይትዝመት ተጋሩ ከይሐዝካ አይትዝመት ተባሂሉ እስካዕሎሚ ይዝረብ” (ትግሬ ወደ አለበት አካባቢ አትዝመት፤ ወደ ዘመቻ ስታቅድ ትግሬን  ሳትይዝ ወደ ዘመቻ አትሂድ) እየተባለ እስካሁን ድረስ በታሪክ ይነገራል። በማለት ከሚገባ በላይ ሰዎች ከሰውነታቸው ባሕሪ በማስወጣት፤ ወያኔዎች “ይካአሎ” (ሁሉም ነገር የሚቻለው) የሚሉት፤ ፈረንጆች “ኦምኒፖተንት/ኦልማይቲ/ሱፕረም/ኤብል ቱ ዱ ኤኒቲንግ” ሁሉም ነገር ማድረግ የሚቻለው፤የማይሸነፍ፤የሌሎች ዕርዳታ የማይጠይቅ፤ልዩ ፍጡር አድርገው በመሳል፤ ከፍተኛ ትምክሕት በሕሊናቸው እየተገነባ በመምጣቱ፤ በልዕለ ሃያልነት ባሕሪ ተወጥረው የታያሉ።

ሌሎች ወገኖቻችን በትግሬዎች የድረሱልን ጥያቄ እኛን ትግሬዎችን ለመርዳት ወደ ክፍለሃገሩ መጥተው ከጠላት ጋር ገጥመው ድል ላስገኙልን ወገኖቻንን ፤ አንድ ጊዜ “ትምክሕተኞች” ሲሏቸው ሌላ ጊዜ ደግሞ ‘ድሉ “የትግሬዎች” አንጂ ለእርዳታ መጥተናል የሚሉን የሸዋ መሪዎችና ትምክሕተኞች አይደለም ይላሉ። የሸዋ መሪዎች በተለይ ምኒልክ “ወራሪ፤ጥሬ ገንዘብ እና ሃብት ፍለጋ የመጣ፤“የሁለቱ ትግሬዎች” (የትግራይ ትግርኚ) ጉልበትና አንድነት ለሁለት ከፍለው ለማዳከም የመጡ ወራሪዎች ናቸው” እያሉ ወንጅለዋቸዋል። ወላጅ እናቴ ለእንደ እነ ገብረኪዳን የመሳሰሉ ከሃዲዎች የምትለው አባባል ነበራት፦ “ጹቡቕ ዝገበረ ጹቡቕ ተዝፍደ ብዕራይ እኳ ዱቋ ንሰተየ” (በጎ ሰሪ የእጁ ቢያገኝ ኖሮ በሬ ዱቃ/ (ያልተበረዘ ጉሽ ጣላ) በተገባው) ትል ነበር።ቤተሰቦቻቸው በትነው የትግራይን ቤተሰብ ከጠላት ለማዳን ሲሉ እና የኢትዮጵያን ክብር ላለማስደፈር ወንድ ሴት ሳይሉ በረሃ ድካም፤ርሃብ ሳይበግራቸው በእግራቸው ከየአቅጣጫው ጎርፈው በምኒልክ መሪነት ወደ ትግራይ የገሰገሱትን ኢትዮጵያዊያን ተዋጊዎችን በወራሪነት ሲወነጅሉ፤ ‘የተገኘው ዓድዋ ድልም’ የትግሬዎች ፤የአሉላ ውጤት እንጂ ሌላው እሚንት ነው እያሉ በጣም በሚገርም አስደንጋጭ ፍክቲሼስ/ልብ ወለድ ትረካ ሲተርኩ ማንበብ ልቦና ላለው እጅግ ያሳምማል።

ይህ የትግሬዎች የአሉላ የአዋጊ ብቃትንት እንጂ የምኒልክ ወይንም የምኒልክተዋጊ አዛዦችና የሸዌዎች ድል አልነበረም የሚሉት የጎሰኞች ስካር ሳይሆን በታሪክ ጻሐፈዎችስ ምን ይላሉ? አሉላ ብቁ ተዋጊ እና አዋጊ ነበሩ? አዎ። ግን አሉላ ብቻቸውን ወይንም የትግሬ ተዋጊ ብቻውን ነበር  ዓድዋ  ላይ ጣሊያንን ድል ያደረገው? ብቻቸው አይደሉም። ምክንያቱም ብቻቸውን ጣሊያንን ድል ማድረግ የሚቻላቸው ቢሆን ኖሮ ራስ መንገሻ ከአከለ ጉዛይ አካባቢ እና ለአጋሜ በጣሊያን ተገፍተው መቀሌን ለቀው ማይጨው ድረስ መሽገው በመራቅ ለአፄ ምኒልክ ተሎ ድረሱልን ብለው ለምን  ዕርዳታ ጠየቁ? አሉላ የሚል መጽሐፍ የፃፈ ወያኔዎች አስሬ ለመረጃ የሚጠቅሱት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሃጋይ ኤርሊክም  ስለ አሉላ ሱታፌን የደረሰበት ምርመራ ነግሮናል። መረጃየም ይሄው። አርሊክ ሃጋይ “አሉላ” በሚል የእንግሊዝኛ መጽፉ ውስጥ አንዲህ ይላል።

Alula’s roll in the battle itself is not known. He had only a small force and probably played a limited part in actual fighting” (Erlic 193)

ይህ ሆኖም እኔ በይድረስ ለጎጠኛው መምህር መጽሐፌ ላይ የጠቀስኩት “ሽንፈቱም ሆነ ድሉ የጋራ ነበር” በገጽ 90 ይመልከቱ። ትግሬዎቹ አካባቢያቸው ስለሆነ በጦርነቱ ቅየሳ እና በስለላ ረድፍ አሉላ አባ ነጋ ለድሉ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው የሚገልጹ አንደ እነ ግሪን ፊልድ የመሳሰሉ አንግሊዞች አሉ (በነገራችን ላይ ግሪን ፊልድ ጸረ ኢትዮጵያ ነው)። ስለላን በማቀናበር እና በውግያው የስልት ቅየሳ የአሉላ እጅ ቢኖሮውም ‘ በአውደ ውግያው ሱታፌ” ግን  ሃጋይ ኤረሊክ የአሉላ ሱታፌ እስከዚህም አንደሆነ እና ብዙም ተዋጊ ጦር አንዳልነበራቸው ነው የነገረን። ያም ሆኖ ይህ ድሉም ሽንፈቱም የጋራ አንደሆነ ነው የምደመድመው። ወያኔዎች ግን ድሉ የትግሬ ብቻ እንደሆነ ነው የሚዘላብዱት። ይባስ ብሎ ደግሞ ጌታ እየሱስ አርብ እለት በአይሁደች ሲሰቀል አንደታየው ሁሉ፤ አፄ ዮሐንስ በሌሉበት ጊዜ የጣሊያን ወራሪ ወደ ትግሬ ዘልቆ በመግባቱ፤ ፀሐይ ጨልማ፤ ጨረቃ ደም ሆና ከዋክብት ከስለው እና ረግፈው በሚታዩበት በትግራይ ሕዝብ ሕሊና ወቅት ከዚህ “ፀሊም ጉበአ” (የጥቁር ሕዝብ መአት) አድኑን በተባለበት ተማጽኖ እነ ገብረኪዳን ደስታ እውነታውን በመሸሸግ “በዓድዋ ጦርነት አረ የምኒልክ ሰራዊትም አያስፈልግም ነበረ! የትግራይ ትግርኚ ሕዝብ (ትግሬ እና ኤርትራ ሕዝብ) ብቻውን ይችለው ነበር፡ ብቻውን ጣሊያንን! አዎ ብቻወን! የምኒልክ ሠራዊትም አስፈላጊ አልነበረም!” ሲል ለጀሮ በጣም አንግዳ ከመሆን አልፎ፤ “ሕልሚ ለይቲስ ተስፋ ድኻ” (የድሃ ተስፋ ሕልም ነው) የሚሉት ወላጆቻችን ትግሬዎች ለእንደ እነ ገብረኪዳን ይመስለኛል። ገብረኪዳን በሕልሙ የጣሊያንን ወራሪ ትግሬ ብቻ የተዋጋው መስሎት በሕልሙ ሲቃዥ የታየውን ነው እውን እየመሰለው በግሃዱ አለም ሳያፍርር እየነገረን ያለው። ለዚህም ነው ገብረኪዳን ደስታ የሃጋይ ኤርልክን ምስክርነት በመመርኰዝ

“ሃጋይ ኤርሊክ አንደገለጸው ከ1875-1896 ዓ.ም ድረስ ከተለያዩ ወረራዎች ጋር የተደረጉ 9 ውጊያዎች፤በዘጠነኛው ዓውደ ውጊያ ማለትም በዓድዋው ጦርነት ብቻ ነው የተሳተፉት።”  በማለት ዓድዋ ላይ የተሳተፉትን አርበኞች “ትምክሕተኞች” በማለት የትግራይ ሕዘብ እና የትምክሕተኞች ሴራ መጽሐፉ በገጽ 148 የዘለፋቸው።

ሀቁን እንነጋገር ከተባለ “ውለታ ቢሱ” ገብረኪዳን አንዴ በባንዳነት አንዴ በትምክሕተኛነት ከላይ በሰጠሁት አውዲዮ ቪዲዪ ትግርኛ ላይ ሲከሳቸው ያደመጥነው ስለ ራስ መኮንን በዘመኑ የነበሩ ጻሐፊዎች የተዘገቡ ዘገባዎች ላስነብባችሁ
 Femaous Abyssinian Name King Menlik Appointed Gen. Ras Makonnen to Attend King Edward's Coronoation
ይላል ባጭሩ ቀንጭቤ ያቀረብኩላችሁ; የ1902 ኒውዮርክ ታይምስ ያተመው ጽሑፍ። አነ ራስ መኰንን ደማቸው ያፈሰሱበትን ጦርነት ይትግሬዎች ድል አንጂ “ትምክሕተኞች አይደለም” እያሉ ላገራቸው የተዋደቁ ጀግኖችን ሲያንኳስሱ መስማት አጅግ ያሳዝናል።
ግራም ነፈሰ ቀኝ በመጨረሻ በጦርነቱ ወቅት ብቻኛ ጋዜጠኛ የነበረውዋይልደ/Wylde ስለ ራስ አሉላ እና ምኒልክ ግንኙነት አክሱም ባሰሩት አዲሱ መኖርያ ቤታቸው ውስጥ ድረስ በመሄድ ያነጋገራቸውን እና ራስ የነገሩትን አንዲህ ይላል።

መጀመሪያ ኤርሊክ ሃጋይን ልጥቀስ 
Ras Alula was nominated over a substantial area in the Tigre province, all the territories between Mai Weri and Merebe, with Adua as his capital. Menlik, however, in his shrewed strategy of installing outsiders over the various provinces, in which he differed from Yohannes, gave Alula the most important part of northern Ethiopia, atleast, from the Historical point of vie. Thus, paradoxically, but quite significant ly for the feudal structure of Tigre, it was the Shoan emepror who installed one of the province’s great worrieors, though not a member of the provinicial elite, as the local governor there. Alula was of cource, now Menlik’s grateful supporter.(Erlik Hagay page Alula 94)

On June 1896 in his new house at Aksum, he told Wyle  how he had turned to Menlik “as the only man who could restore order…. I have thrown all my influence on his side in order to unite Abyssinia once more” 80 (A.Wylde, “An unoficial mission to Abyssinai, “the manchester Guardian, 14.5.97) ሲል ጽፋል። እውነት እንነጋገር ከተባለ ምንሊክ እንጂ ራስ መንገሻ ዮሃንስ ዙፋኑን ቢወርሱት ኖሮ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ መጠበቅ አይቻላቸውም ነበር።

(2) አንድ ሃይማኖት አንድ አገር አንድ ቋንቋ የቀዳማይ ወያነ ፍልስፍና?

ወያኔዎች የሸዋ ነገሥታት/አማራ ነገሥታት እያሉ ከይኩኖ አምላክ ጀምሮ “አንድ አገር፤ አንድ ሃይማኖት፤አንድ ቋንቋ” እያሉ አትዮጵያን በአሃዱ ሥርአት ሲገዟት ነበር በማለት ሲወነጅሉ ሰምታችሗል። ኦነጎችም ወያኔዎችም ሁሉም በዚያው በማያዛልቅ ተረት፤ተረት ሙግታቸው ብዙ ብለዋል። ሃቁ ግን ኦሮሞዎችም ሆኑ ትግሬዎች ስልጣን ስይዙ የተከተሉት ዓላማ ከዚህ የተለየ አልነበረም። ምናልባትም እጅግ የባሰ የጭካኔ እና የግፍ ፍትሕ የተሰራበት በዘመናቸው ነው።

አንድ ሃይማኖት፤አንድ ቋንቋ” እያሉ አትዮጵያን በአሃዱ ሥርአት ሲገዟት ነበር በማለት ይኩኖ አምላክን፤ ምኒልክን፤ሃይለስላሴን እና ደርግን በመወንጀል በግምባር ቀደም የሚታወቀው ገብረኪዳን ደስታ እና ዶ/ር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ናቸው። ውንጀላቸው በአማራ መንግሥትነት የሚወነጅሏቸው ከላይ የተጠቀሱ ነገሥታት አንጂ ዮሃንስን አይመለከትም። ሆኖም ወያኔዎች ሆን ብለው ታሪክ ለመደበቅ የሚያደርጉት አሳሳች ዘመቻቸው በዮሃንስ/በትግሬዎች ስርዓት ላይ ሲደርሱ ግን ዘመነ ዲሞክራሲ በማስመሰል ይቀባቡታል። ለምሳሌ ገብረኪዳን ደስታ አንዲህ ይላል “አንድ ሃይማኖት፤አንድ አገር፤አንድ መንግስት፤አንድ ቋንቋ፤አንድ ባንዴራ የሚሉ ከይኩኖ አምላክ ጀምረው የሚፈክሩ ሰርዓቶች የኛ ታረክ ነው ብለን አንቀልም”

ወያኔዎች የማይክዱት እና እራሳቸውም አንደ ትልቅ ጀብዱ አድርገው የሚጽፉበት የእንደርታ እና የራያ ዓዘቦ እንቅስቃሴን ስንመለክት፤ በቀዳማይ ወያኔ ዘመን (1936) ‘ጊዜአዊ መንግሥት በማለት” ያወጁትን የጊዜያዊ መንግሥት መተዳደሪያቸውን ስንመረምር የምንከተለው ሃይማኖት (የቀዳማይ ወያኔ ጊዜአዊ መንግስት) ሃይማኖታችን (የአፄ ዮሐንስ)፤ጠባቂያችን (እየሱስ ክርስቶስ) ፤ መሪያችን (ሃይለማርያም ረዳ)፤ባንዴራችን (የኢትዮጵያ) ነበር ያሉት። አንዲህ ይላል። በትግርኛ፤

“…ስምዑ፤ስምዑ!
አዋጅ ሃይለማርያም አዋጅ ገረብ እዩ
ገዛኢና እየሱስ ክርስቶስ፤
ሓላዊና ሃይለማርያም፤
ዳኝነትና ናይ ዓሰርተ ክልተ ገረብ፤
ባንዴራና ባንዴራ ኢትዮጵያ፤
ሃይማኖትና ናይ ሃፀይ ዮውሃንስ
ህዝቢ ትግራይ ወያነ ተኸተል፤
ገረብ መንግሥቲ ተቐበል።”

(አዋጅ ስማ! አዋጅ ስማ! ይህ አዋጅ የሃይለማርያም እና የገረብ አዋጅ ነው። (ገረብ ማለት ጅረት/የአካባቢ ወንዝ ማለት ነው) (ከ12 የውሃ ፈለግ/ወንዞች ከሚዋሰነው ሕዝብ የተውጣጣ የጊዜያዊ መንግሥት ተወካዮች ማለት ነው።)፤ገዢያችን እየሱስ ክርስቶስ፤ ጠባቂያችን ሃይለማርያም፤ ዳኝነታችንም ከ12 ገረብ ተወጣጥተው የወሰኑት የፍትሕ ዳጅነት ይሆናል። ባንዴራችን የኢትዮጵያ ባንዴራ ነው። ሃይማኖታችንም የአፄ ዮሐንስ ነው። የትግራይ ሕዘብ ሆይ! ወያኔን ተከተል። የትግራይ ሕዝብ ብቸኛ የሆነው የገረብን መንግሥት ተከተል!) በማለት ‘በአንድ እየሱስ፤ አንድ ሕዝብ፤ አንድ ድርጅት፤ አንድ ሃይማኖት፤ አንድ መሪ፤ አንድ ሃይማኖት” የሚከተል “የገረብ መንግሥት” ተከተል ሲል አወጇል። 

አፄ ዮሃንስም አንድ ሃይሞኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ፕሮተስታንት ወይንም እስላም የተባለ ወደ ኦርቶዶክስ ካልተጠመቀ ከትግራይ ግዛቴ ለቃችሁ ወደ ሌላ አገር ሂዱ ብለው አውጀዋል። መረጃየን ላቅርብ፡

“Internal Rivalries and Foreiggn Threats (1869-1879) Edited by  Sven Rubenson page 6 ስንመለከት  አሰገኸይ የተባሉ የቤተክሕነት ምሁር የሆኑ ትግሬ ሰው  “የአንቶይን ዲ አባዲ” የተባለ አውሮጳዊ ወዳጅ/አስተርጓሚ/ዜና ነጋሪ/አገር አስተዋዋቂ የነበሩ በAssegehen to Antoine d’ Abadie, 12,Feb, 1869 በሚል ርዕስ ለ ዲ አባዲ የጻፉትን ደብዳቤ አንዲህ ይላል።

“ትብጻሕ ሃበ አቶ አንደጦንዮስ ዘአባዲያ ሙሑረ ጥበባት…….” እያሉ ሰፋ ያለ በግዕዝ ሰላምታቸውን ካቀረቡ በሗላ፤ ወደ አማርኛ በመግባት፤
“ታሪክ ዘደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ የትግሬ ንጉሥ አንዲህ ነው፡ አባ ተክለ አልፋ የሚባሉ መነኩሴ ዘደብረ በርበሬ ነበሩ፡ ቅባት ናቸው፡ ያባ በዝብዝ የንስሐ አባት ወደ ተዋህዶ ሃይማኖት ግቡ ብሎ ተማጠናቸው። አባ ተክለ አልፋም፤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ ትርጓሜው እንዴት ነው፡ ብለው ጠየቁት። አላውቅም አለ። ደጃዝማች ካሳም ደንቆሮ ነህ፡ብለው .. የነብስ አባታቸውን ገረፉት።

፪ኛ ታሪክ፤
ደጃዝማች ካሳ አባ በዝብዝ በትግሬ ያለ ቅባት ሁሉ ወደ ሃይማኖቱ ይግባ። እምቢ የሚል ሁሉ በምገዛው አገር  አይኑር አሉ። በትግሬ ያሉ ቅባቶች ሁሉ ወደ አባ በዝብዝ ሃይማኖት ገቡ፡ አባ ተክለ አልፋ ግን ገዝተው ወደ ታላቅ ገደል ወጡ፡ ያባ በዝብዝ አጎት ደጃዝማች አርአያ ከብዙ ጦር ጋር ተከተለው፡ከገደል አወረዱዋቸው፤በነፍጥም አንደመቱዋቸው፤ፈርተው ከገደል ወረዱ፡ ግዝታቸውንም ፈቱ፡ ወደ ሌላ አገርም አባ ተክለ አልፋ ተሰደዱ።”  (ምንጭ ከላይ የጠቀስኩት መጽሐፍ ገጽ 6)

እንግሊዝኛ ትርጉሙም
Dejazmach Kasa Abba Bezbize said,
“All the Qibat who live in Tigray must accept my faith. Let no one who refuses live in the land which I rule.” All the Qibat who lived in Tigray embraced the faith of Abba Bezbiz. Abba Tekle Alfa, however, excommunicated (them) ascended a cliff. Dejazmach Araya, the uncle of Abba Bezbiz, persued (him) with a large army and brought him down the clif.He camedown from the mountain because he was afraid that they would kill him with a rifle (-shot). He withdrew his excommunication. And Abba Tedla Alfa sought refuge in another region.”  ( Internal Rivalries and Foreiggn Threats (1869-1879) Edited by  Sven Rubenson page 6)

ሃይማኖትን በሚመለከት እንግዲህ አጼ ዮሐንስ ማለት እኚህ ነበሩ። የሃይማኖት እኩልነት አክባሪ ነበሩ፤ እያሉ እነ ገብረኪዳን ደስታ በውሸት ታሪክን ባልነበረ መልኩ ሲያጣምሙ እና አዲሱን ትውልድ በውሸት ሲያወናብዱት የትግራይ ምሁራን ደግሞ ተቀብለው ያንን ውሸት በመድገም “አበጀህ” “እንዲህ ያለ ታሪክ ጻሐፊ” ትግራይ ወልዳ አታውቅም፤ እያሉ አብረው ከገብረኪዳን ጋር ያብዳሉ። “አንድ አገር፤አንድ ቋንቋ፤አንድ ሃይማኖት” እያሉ ከይኩኖ አምላክ ጀምረው እስከ ምኒልክ እስከ ሃይለስላሴ ድረስ ያሉ አማራ ነገሥታት ጸረ ትግሬ በመሄድ፤ኢትዮጵያን በአሃዳዊ ስርዓት ገዝተዋታል፤ እያሉ ወያኔዎች እና እነ ገብረኪዳን አማራ የሚሏቸውን ነገሥታት ሚዛን ባልጠበቀ ዘለፋ እና ውንጀላ ሲወነጅሏቸው፤የራሳቸው የትግራይ መሳፍንት እና ነገሥታት ግን ከላይ በማስረጃ አንዳቀረብኩላችሁ ታሪካቸውን እየሸሸጉ በየሚዲያቸው ሲያብዱ ሌላውን ሲወነጅሉ እያዳመጧችሗቸው ነው። እነሆ አሁን የትግራይ መሳፍንቶች እና ነገሥታት ሥርዓት እውነታው በመረጃ ይዛችሁታል። እነቀጥል።

(3ኛ) ዮሐንስ ትግሬዎች አንደሚቀባቧቸው ሳይሆኑ፤ በጥፋትም ከምኒልክ አይለዩም
ትግሬ ውስጥ ረሃብ አልነበረም፡ ረሃብ አይታወቅም፤ ረሃብ የመጣው በሸዌው በምኒልክ ነበር ትግራይ የወደመው (ለዚህም ዘመን ሸዌ ይባል ነበር)፤ ያለቀው የተራበው እና የተፈጀው፤ በማለት ምኒልክ እና ሃይለስላሴን በረሃብ ሲከሱ እነ ገብረኪዳን (ገጽ 144 የትግራይ ሕዝብ አና የትምክሐተኞች ሴራ)፤ እና “ጋላህቲ ሰጊ” ሙሉጌታ ደባልቀው እና  መሰሎቻቸው ሲናገሩ/ሲጽፉ አድመጠናል/አንብበናል። በዘመነ ደጃዝማች በዝብዝ ካሳ (18ኛው ክ/ዘመን) የነበሩ ከላይ የጠቀስኳቸው አሰገኸኝ ለዲ አባዲ በሌላ ቀን በጻፉት ደብዳቤ ላይ ግን የወያኔ ጸሐፍት ውሸት በመጻረር እንዲህ ሲሉ በእጅ ጽሑፍ የተውልንን ማሕደር ይነገሩናል።
(ሁ) “ትግሬ ርሃብ ገብቶ በ፩ብር ፪ ቁና ሲሸመት ከረመ። በዓድዋ አንድ ጎበዝ የሰው ሥጋ ሲበላ ተገኘ፡ አባ በዝብዝ የተባሉት ደጃዝማች ካሳ ሰቀሉት።” ሲሉ ርሃብ ትግራይ ውስጥ በምንልክ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በዮሐንስ ጊዜም ገብቶ እንደነበር ነው። በዮሐንስ ዘመን ብቻ ሳይሆን ድሮም በ15ኛው ክፍለ ዘመንም ‘ግራይ አህመድ’ ክርስትያኑን እያረደ ትግራይን እና ኤርትራ ደጋማ ቦታዎችን በተቆጣጠረበት ወቅት ትግራይ ውስጥ የቆየበት ጊዜ አጭር አንደነበር እና ትግራይን ለቆ ባስቾኳይ ሊለቅ የተገደደበትም ምክንያት ርሃብ በመከሰቱ ነበር። የትግራይ ሕዝብ በርሃብ ቸነፈር በማለቁ ምክንያት የሚላስ የሚቀመስ ባለመኖሩ ወታደሮቹም የሚበሉት ስላጡ  ይዟቸው የመጡት ፈረሶቹ እና በቅሎዎቹ በሙሉ የሚበላ ግጦሽ አጥተው በሙሉ ስለሞቱበት፤ ሰራዊቱን ተሎ በማንቀሳቀስ፤ እሱም ሆኑ አሽከሮቹ  በግር ጉዞ ጓዙን በትከሻው እየተሸከመ ወደ ወልቃይት አካባቢ ወደ ለሙ ቦታ ደረሰ። በማለት Arab Faqih) የተባለው  የመናዊ ዓረብ  ጋዜጠኛ  ፉቱሕ አልሓበሻ” (Futuh Al- Habasa – the Conquest of Abyssinia {16th Century} በዓይኑ  የተመለከተውንወቅቱ ታሪክ ዘጋቢ  ነግሮናል (የዓረብ ፋቂሕ ዘገባ ለማንበብ “ በሃይማኖት እና በፖለቲካ  የማሻኮር ባሕሪ- ጌታቸው ረዳ ” ብላችሁ ጽሑፌን ጉጉል በማድረግ ማንበብ ትችላላችሁ።  ስለዚህም በአፄ ምኒሊክ የቀረበው ክስ ሚዛን ይኑረው፤ የምለውም ለዚህ ነው።
(ለ) ምኒልክ እና ሃይለስላሴ “ሥዩመ እግዚአብሐር” (በእግዚአብሔር የተሾምን ነን) እያሉ ሲፈክሩ፤ ዮሐንስ ግን አንዲህ አይሉም ነበር፡ የሚለው የእነ ገብረኪዳን ውሸት በዮሐንስ ደብዳቤ ግን ተጻራሪውን አንመለከታለን።  ምኒልክ ከጣሊያን ጋር እተመሳጠረ እና እየተለማመጠ ኤርትራን ለጣሊያን ሰጠ፤ወደባችንን አስነጠቀን የሚሉትንም ክስ በጨረፍታ እንመልከት።  
ዮሐንስ የዓሰብ ወደብ ዓፋሮቹ ወንድማማቾቹ እነ ሱልጣን ኢብራሂም አሕመድ ለጣሊያናዊው ለእነ ጁሴፔ ሳፔቶ ሲሸጡለት እና ኮንትራት ሲዋዋሉ  ኖቨምብር 15/1869 ዝም ብለው ይመለከቱዋቸው ነበር። በወቅቱ እሳቸው እንጂ ምኒልክ በአከባቢው ስልጣን አልበራቸውም። ያውም በእዛው በኖቨመብር ወር 17 ቀን (ከሁለት ቀን በሗላ) ራስ ወልደሚካልን በሚመለከት፤ “በሙሲንጀር’ ላይ የመግደል ሙከራ በመደረጉ ጉዳይ ለማጣራት ወንጀለኛውን ለመያዝ  ወደ ሙሲንጀር ወዳጃቸው ደብዳቤ ጽፈውለት ነበር። ወዳጃቸው ናፔርም በዛው ዓመት ነበር ሰተት ብሎ ፈቅደውለት፤ተባብረውት፤ በሕንጣሎ ገጠራዊት ከተማ ላይ፤ ድንኳን ዘርግተው፤  አብልተው አጠጥተው ሰላይ እና መንገደኛ አስይዘው ወደ መቅደላ ያሻገሩት። ለውለታቸውም ከናፕየር ያገኙትን መሳሪያ እና የመሳሪያ ሰልጣኞች ተጠቅመው ጉልበት በማግኘት የመላ ኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ለመሆን በቁ። ወራሪው እንግሊዛዊው ጀኔራል ናፔርም በዛው ወር በኦጎስት/ነሓሴ ውስጥ ነው በዛው አመት የመጣው። ከዚያ በሗላም ዮሐንስ ለግራኒቬል በጻፉት ደብዳቤ (በመይ 18/ 1873) አንዲህ ሲሉ የባሕር ወደብ ለማግኘት ተለማምጠዋል።
“ተጽሐፈ በሐገረ ጐንደር።በ ፰ ቀን  ግንቦት። በ ፲ ወ  ፰ ወ ፭ ዓመተ፤ምሕረት።
መልእክት ዘሥዩመ እግዚአብየር፤ዮሐንስ ንጉሠ፤ነገሥት ዘኢትዮጵያ ወኩሉ አድያሚሃ።
ይድረስ ከኤርል ግራንድ ቢል። እጅጉን አንዴት ነዎ። እኔም ሰራዊቴም ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ \.............ካሉ እና ሰፊ ወግ ከጻፉ በሗላ  አንዲህ ሲሊ አንድ የባሕር በር ወደብ አንዲፈቅድላቸው ልመና አቅርበዋል፦

“…… አሀንም፤ ከባሕር ዳር አገር አንድ በር አሰጡኝ። ወደ እላንተ ደብዳቤ እና መልአክተኛ፤ ንግድ የሚገኝበት፤የሚመላለስበት። አንፊላና ዙላን የጥንት አገሮቼ ናቸው፡ እና በር ግን ካላገኘሁኝ፡ ካላንተ ከነገሥታቱ ጋር ከወንድሞቼ ፍቅር መንገድ አጥፍቼ ተዘግቼ መኖሬን ይወቁት።” (ማሕተም፦ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ንጉሠ ጽዮን ዘኢትዮጵያ፤ በማሕተሙ ላይም ከግዕዙ ጋር ዓረብኛ አለበት) (And now make them an outlet on the seacoast, throgh which I can exchange letters and messengers (and where) trading can take place. Anfila and Zula have been my district since early time.Know, then,  that if do not get a port , I shall remain  shut in, without a road (and) the friendship of my  brothers, you the kings. (seal: king of Kings Yohannes, king of Zion of Ethiopia) ምንጭ -ዜኑ ከማሁ። ምኒልክን ተላማማጭ እያሉ ማንኳሰስ ዮሐንስ ግን የማይለማመጡ ማለት ከዚህ ወዲያ መለማመጥ ማለት ምን ሌላ ትርጉም አለ?

(4ኛ) በዝባን ዓሰርተ ክልተ ገረብ ስም ሲባል ያልቆመ የትግሬ ተወላጅ ከማሕበረሰቡ አንዲገለል የታወጀው አዋጅ

ካሁን በፊት በብዙ የወያኔ የመገናኛ ዘገባዎች እና የወያኔ መጽሐፈት እና መጽሔቶች ላይ በስፋት ሲነበብ የነበረው ውሸት “ቅንጅት ደርግ ነው፡ ቅንጅት አማራ ነው፡ ስለሆነም ጸረ ትግሬ ድርጀት ነው። በትግሬ አቋሙ የተነሳም ከትግሬ ተወላጆች ጋር ቡና አንዳትጠጡ፤ሃዘን አንዳትላቀሱ፤ አንዳትደርሱ፤ጠበል፤ማሕበራዊ ስራ አንዳትገናኙ……በማለት ትግሬዎችን ከማሕበራዊ ግንኙነት አንዲገለል አዋጅ አውጥቷል። በማለት ቅንጅትን በውሸት ለመወንጀል ያልጣረው አልነበረም። የዚህ የውሸት ቀንደኛ ተዋናይ ደግሞ “ቴዎድሮስ ሐጎስ” እና “በረከት ስማኦን” እና የወያኔ የሕግ ምሁራን ነን ባዮች፤ በሬድዮ ድምፂ ወያኔ በተደጋጋሚ በመቅረብ ያልተባለውን ሲጐነጉኑ ባጅተዋል። የራዲዮ አድማቾችም ወደ ጣቢያው ስልክ እየደወሉ የቅንጅት መሮዎች አንኳን በ መአመክሮ መለቀቅ ቀርቶ አንዲያውም ‘መሰቀል’ አለባቸው እያሉ የዋህ ጀሌዎቻቸውም እውነት መስሏቸው ነገር ሳያጣሩ የቅንጅትን መግለጫ ሳያነብቡ ‘ቅንጅት ጸረ ትግሬ ነው” እያሉ ይጮኹና ይወነጅሉት አንደነበር የቅርብ ጉዜ ትዝታችን ነው። በመጀመሪያ የቅንጅት መግለጫ ምን አንደሚል አንመልከት እና ቅንጅት ከቀዳማይ ወያኔ የተለየ ምን አዋጅ/መግለጫ አውጥቶ ለውግዞት እንደደረሰ አንመልከት እና ጽሑፈን ልደምድም።
የቅንጅት መግለጫ
 ምርጫ ከመደረጉ በፊት በግንቦት ወር 1997 ዓ.ም (June 8, 2005) ወደ 3 ሚሊዮን የሚገመት የአዲስ አበባ ኗሪ ሕዝብ ቅንጅት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በአብዮት አደባባይ መገኘቱ ይታወሳል። 
ያን ያህል አስገራሚ ትርኢት ከታየ ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወያኔ 99.6% ድምጽ አግኝቻለሁ በማለት በዘራፊ ባሕሪው ምክንያት ምርጫው ካጭበረበረ በሗላ፤ ‘ቅንጅት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ’ የተባለው የወያኔ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅት ምርጫው መጭበርበሩን ጥቅምት 1997 ዓ.ም  (October 29, 2005) ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚከተለው አገር አቀፍ የሆነ ሰላመዊ ሕዝባዊ ልግምት/ተቃውሞ እንዲያደረግ ማስተላለፉ ይታወሳል።
ትከክለኛ የመግለጫው ቅጂ ለማግኘት በኢንተርኔትም ሆነ የድርጅቱ አባሎች የነበሩ እና አንዳንድ ኢትየጵያዊያን ጠይቄ ማግኘት ስላልቻልኩ፤ ሕዝቡ ተቃውሞውን በሚከተሉት ሁኔታዎች አንዲገልጽ ጥሪ አድረጎ የነበረውን ከግርድፍ ትውስታዬ በግሌ የማስታውሰው ያስተላለፈው መግለጫ ጥቂቶቹ አቀርባለሁ።
እቤት በመቀመጥ (ወደ ስራ አለመሄድ/የቁጭ አድማ) ተቃውሞውን መግለጽ። 5 ቀን የሚቆይ የእቤት መቀመጥ አድማው የሚጀምረው ለእስላሞች ክብር እና ወንድማዊ ደስታ ለመካፈል ሲባል ሮሞዳን የተባለው እስላሞችን በዓል ካለፈ በሗላ ነበር።  
በኢሕአዴግ ባለቤትነት የሚካሄዱ የንግድ ተቋማት አንደ አምባሰል፤ጉና፤ዲንሾ፤ዎንዶ፤ዳሸን ቢራ ፋቭሪካ እና ሜጋ የመሳሰሉት ሕዝቡ ግብይት እንዳያደርግ።  ከንግድ ድርጅቶቹ አልፎ በቁጥጥሩ ስር የሚገኙ የዜና ማሰራጫ ራዲዮኖች (ድምፂ ወያነ ትግራይ፤ ፋና፤ኢ ቲ ቪ ፤ FM 97.1  FM 96.3 የመሳሰሉ) እና እንዲሁም በጋዜጦቹ ላይ የንግድ ማስታወቂያ አለማድረግ፤ ስርዓቱ የሚያስተላልፋቸው ዜናዎች እና ቅስቀሳዎች እንዳያነብ እና እንዳያዳምጥ። በምትኩ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮን እና ዶቸቬለ አንዲሁም ትንሳ ራዲዮ የመሳሰሉት ከውጭ የሚሰራጩ  የዜና አውታሮች ችን ማድመጥ።
ስርዓቱ የሃይል እርምጃ በወሰደ ቁጥር፤ በኢሕአዴግ አባላት እና እንዲሁም የተጭበረበረውን ምርጫ በግድ ተቀበሉ እያሉ ሰላማዊ የፖለቲካ ተቃወሚ አባሎችን እና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉልበት በማሳየት፤ በመደብደብ፤ በማሳሰር፤በመግደል፤ በመሰለል፤በማስፈራራት ሕግን በመጣስ መብት የሚረግጡ የስርዓቱ ደጋፊዎች ሁሉ ሕብረተሰቡ እንዲያገላቸው።
ቅንጅት ይህንን መግለጫ ሲያወጣ ማንኛውም የቅንጅት አባልም ሆነ ደጋፊ ከላይ ከተጠቀሱ ምክንያቶች ውጭ “ሃይማኖትን እና ጎሳን” መሰረት ያደረገ ማሕበራዊ ማግለል አንዳይደረግ በጥብቅ አሳስቧል። (ግርድፍ ይዘት ጌታቸው ረዳ።)
የቀዳማይ ወያኔ መግለጫ
ድሮ በሃይለስለሴ ዘመን አንድ ሞገደኛም ሆነ አንድ ሰው ወደ ሕግ ለማቅረብ አንሂድ ስትለው “በሃይለስላሴ በሕግ አምላክ” ሲባል ነበር። የመሳፍንቶች እና የነገሥታት ዘሮች የሚበዙበት እና የሚወለዱበት አካባቢ አንደርታ አውራጃ በቀዳማይ ወያኔ ለንጉሥ ሃይለስላሴ አንገዛም በማለት “12 ገረብ” (አስራ ሁለት ጅረት) በሚል ስም ጊዜያዊ የአማጽያን መንግሥት ሕዝባዊ ባይቶ/አሰምብሊ) መስርቶ በነበረበት ወቅት ደግሞ “ዝባን ገረብ” (በገረብ ሕግ አምላክ) በማለት አንድ ሰው አንድትቆም ተማጽኖህ ካልቆምክ፤ ወይንም በገረብ ሕግ ዳጅነት ላለመዳኘት አምቢ ካለ የገረብ ሕግ ረግጦ አንደሄደ ተቆጥሮ የሚከተሉት በሕግ የጸደቀ የገረብ አዋጅ ይፈረድበታል።
(1ኛ)-የገረብ ሕግ ያላከበረ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ በሆነበት ወቅት አግዚአብሔር ይማርህ ተብሎ በማንኛውም ጐብኚ እንዳይጎበኝ፤
(2ኛ)- በሃዘን ጊዜ ጥናቱን ይስጥህ ተብሎ አንዳይጠየቅ
(3ኛ)-ከሕዝብ እና ማሕበራዊ ግንኙነት እንዲገለል። የሚሉ ነበሩ።
በዚህ ድንጋጌ እና በቅንጅት ድንጋጌ ምን ልዩነት ታያላችሁ? ምንም። ታዲያ አንዴት ሲኾን ነው ፤ በኢሕአዴግ ንግድ እና የዜና አውታሮች እንዲሁም በአባላቱ እና ደጋፊዎቹ ወይንም ነብሰገዳዮች እና ሰላዮች ላይ ማሕበራዊ ማግለል እና ማዕቀብ ያስተላለፈው ‘በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ ተስምቶ የማይታወቅ እርምጃ’  በማለት ቅንጅትን በመወንጀል የቅንጅትን ውሳኔ ዘረኛ እና ጸረ ትግሬ ነው ሊሉ የቻሉበት ምክንያታቸው ምንድ ነው? መልሱ እና የሕሊና ፍርድ ለናንተ እየተውኩ እዚህ ስሰናበት፤ ክፍል 3 ይቀጥላል። አመሰግናለሁ’ጌታቸው ረዳ ኢትየጵያን ሰማይ)። getachre@aol.com         (Ethiopian Semay)