Sunday, July 15, 2012

ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር


Note from the Editor;----
It is obvious that TPLF's hate monger propaganda against EPRP which TPLF sees EPRP as NewTeNga and  Amhara/Neftenga party (though some of the founders and many of the leaders and members and fighters of the party "EPRP" are from Tigray!!) for the last 21 years misguided the thinking of many youngsters and even the young journalist those of the opposition journalists like that of Fitih GazeTa Mr.Temesgen Desaleng trusted TPLF's filthy propaganda.  Simply sad to read Mr.Temesgen the way TPLF and Derg referred EPRP! What was Temesgen's intention to use such filthy terminology he learned it from TPLF?  To Join the Joiner.....? If that is the case, well, EPRP as a Party or as individual is not allowed to  live in Ethiopia and write as Temesgen is allowed and licenced to be a commentator of any paper in Ethiopia to defend all sorts of true or false propaganda against EPRP. What makes you think EPRP is dead and no one will correct your young mind?  Well, here is Beljig Ali's response to you if you are ready to re correct yourself.

ቆንጆዋን ልጅ በተሰበረ መነጽር
በልጅግ ዓሊ

ተከታታይ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የሚያቀርባቸውን ጽሁፎች አነባለሁ። በብዙዎቹ ብስማማም በመሃል ጣልቃ በሚያስገባቸው አንዳንድ ትንታኔዎች ላይ አልስማማም። አለመስማማትም ሳይሆን መታረም አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።

ተመስገን <<የኔ ትውልድ>> የሚለውና <<ያ ትውልድ>> የሚለው ነገር አለው። ከብዙ ጽሁፎቹ እንደምንረዳው “የእሱ ትውልድ” ከቀይ ሽብር በኋላ የተፈጠረው ሲሆን፣ “ያ ትውልድ” የሚለው ደግሞ ከቀይ ሽብር በፊት ያለው ይመስላል። ብዙውን ትንታኔው የሚያተኩረው “ያ ትውልድ” ሞኝ፣ ለማይረባ ነገር መስዋትነት የከፈለ፣ ቅራኔዎችን በሚገባ ባለማያዙ የተጋደለ አስመስሎ ያቀርብና . . . የእሱ ትውልድ ግን “አርቆ አሳቢ ፣ በእንቶ ፈንቶ የማይጣላ፣ ቅራኔን በበሰለ ሁኔታ የሚመለከት” አድርጎ ለመሳል ይሞክራል። ይህ የእሱ ትንተና ከእሱ ጽሁፍነት አልፎ እውነት ቢሆን በጣም አስደሳች ነበር። እውነቱ ግን ሌላ ነው።

ተመስገን ትውልድ በአብዛኛው በእኔ ትንታኔ <<የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት>>ነው ። ይህ ደግሞ ካለ ምክንያት አይደለም። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ትግል የግል ጥቅም ከፖለቲካ መድረክ ላይ ማጋበስ የተጀመረውም ከቀይ ሽብር በኋላ ሆኖ እናገኘዋለን። ቀይ ሽብር በኅብረተስብ ውስጥ የፈጠረው ፍርሃት ዜጎች የፖለቲካ ጥያቄ ቢያነሱ ሊደርስባቸው የሚችለው አሰቃቂ ሥቃይ በእውን እንዲያዩት ስለተደረገ ሃገርን ከሚመለከት ማናቸውም ጉዳይ መራቅን የመርጠ ትውልድ ነው። ይህንንም አያይዞ ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው ተጀመረ። ከቀይ ሽብር በኋላ ለሃገር መሞት ማስከበሩ ቀርቶ፣ የድህንነት ሠራተኛ፣ የአየር በአየር ነጋዴ፣ “የሕዝባዊ ድርጅቶች” (የአኢወማ፣ አኢሴማ ፣ መኢሠማ . . .ወዘተ) መሪ ሆኖ መመረጥ ወይም መሳተፍ ጥቅም እንዳለው እየታወቀ መጣ።

በዚህም ምክንያት አብዮታዊ አስተዋፆ የሥራ፣የትምህርት(በሃገርም ይሁን በውጭ )፣ አልፎም ተርፎ ሕይወትን ለማሰንበት አስፈላጊ ሆነ። አብዮታዊ አስተዋፆ የማይጠየቅበት ቦታ ቢኖር ብሔራዊ ውትድርና ነበር። ለዚህም ነው በዘመኑ የነበሩ ወጣቶች ለጦላይ (ብሔራዊ ወታደር ማሰልጠኛ ጣብያ ) የድጋፍ ወረቀት አያስፈልግም ብለው የተሳለቁት። ለሃገር፣ ለሕዝብ፣ ለዴሞክራሲ መሞት የተዋረደውና ለግል ጥቅም መሮጥ በሰፊው የተጀመረው ያኔ ነው።

ይህ “የድጋፍ ወረቀት ሠራዊት” በደርግ አብዮቱ ውስጥ የሚያደርገው ተሳትፎ እየታየ የሚያገኘውን ጥቅም ከሃገር ፍቅር ይበልጥ ሲያሳድድ የነበረ ነው። አልፎ ተርፎ ንቅዘቱ በሠራዊቱ ውስጥ ሳይቀር በጉልህ ይታይ ነበር። ታላላቅ የጦር መኮንኖች በተራ አለብላቢ ካድሬዎች ይታዘዙ እንደነበር የሚረሳም አይደለም። ከዛም አልፎ የሃገሪቷን ጥቅም በገንዘብ የለወጡ ስንት ናቸው? ታሪክ ይፍረደው!

ከዚህ የግል ጥቅም ሩጫ ጋር ለሃገሩ የተስውትን ጅግኖች ማዋረድ በደርግ እንደ አብዮተኝነት ሲያስቆጥር በሌላ በኩል ደግሞ ለግል የሞራል ማካካሻ፣ በሃገር ላይ የሚደረገውን ክህደት ማሳመኛ ሆኖ ማገልገል የጀመረው ከቀይ ሽብር በኋላም ቢሆን እስከ አሁን በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ነው የዘንድሮ ፖለቲከኛ በአንድ ወገኑ ኢንቨስትር በሌላው የተቃዋሚ ድርጅት መሪ ሆኖ የምናገኘው። አስረጅ የምጠየቅ አይመስለኝም። <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ላይ ተነስቶ የዛን ትውልድ ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋፆ ማጣጣል የተጀመረው በደርግ ወቅት ቢሆንም አሁንም በሰፊው እንደቀጠለ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ በቂ ምክንያት አለው።

በዚህ ወቅት በአብዮታዊ ተሳትፎ ጥቅም ያጋባሱ ግለሰቦች ከቀይ ሽብር ማግስት ያ ቆራጥ ትውልድ ያለቀው አልቆ የተረፈው በእሥር ተንገላቶ፣ ሞራሉ በቀይ ሽብር ተጎድቶ፣ እንዳይሰራ፣ እንዳይማር ያጠቆርከው የአብዮት ሸማ እጠብ እየተባለ የድጋፍ ወረቀት ተክልክሎ በነበረበት ወቅት አብዮታዊነታቸውን በማሳየት

ጥቅም ያገኙ ግለሰቦች፣ በተሰጣቸው ሰፊ የትምህርት እድል በመጠቀም ዛሬ ምሁራን እየተባሉ ይገኛሉ። እነዚህ ግለሰቦችም ይህንን <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> የሚለውን መፈክራቸውን ለመሸጥ በሚያደርጉት ጥረት የዛን ትውልድ የዴሞክራሲ ትግል ወደ ታች በማውረድ የቃላት ጦርነት እንደነበር ሲያስረዱ ይታያሉ። ሌሎችም ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ይዘው ያስተጋቡ። ሃቁ ይህ አይደለም ሊላቸው የሚችለው ትውልድ

ግማሹም ከመቃብር በታች ነው። ሌላውም በሃገር ውስጥ ስደት የድጎማ መምህር ሆኖ ቀርቷል። የተረፈው ደግሞ ከድርጅት ድርጅት እየቀያየረ ያንን ትውልድ መስደብ የፖለቲካ አዋቂነት መጀመሪያ አድርጎ ሲመጻደቅ ይታያል።

 እውን ያ ትውልድ የተሰዋው በቃላት ልዩነት ነበር?
ተመስገን “‹‹ይቅርታ›› የኢህአዴግ ቃጭል? ወይስ…” በሚለው ጽሁፉ ውስጥ

“ የዚህ ትውልድ ፖለቲካ አንድምታ፣ ከያ ትውልድ የፖለቲካ አንድምታ እንደወረደ የተተገበረ ነው፡፡ በመጠፋፋት ሳጋ እና ማገር የቆመ ማለቴ ነው፡፡ ሀቅ ነው! ያ ትውልድ ከፍ ሲል በርዕዮት አለም ልዩነት እርስ በእርሱ ተጠፋፍቷል፡፡ ዝቅ ሲልም ‹‹በቃላት አጠቃቀም›› ተገዳድሏል፡፡ ለምሳሌ አንዱ

‹‹ወዛደር›› ሲል ሌላኛው ‹‹ላብአደር ነው የሚባለው›› ብሎ ጦርነት ሲያውጅበት አይተናል፡፡ ‹‹ኢህአፓ›› የተሰኘው ነውጠኛ ድርጅት ‹‹እናቸንፋለን!›› ሲል በመፈከሩ ብቻ፣ መኢሶን የተባለ ሌላ ነውጠኛ ‹‹አብዮተኛ እናሸንፋለን!› እንጂ እናቸንፋለንአይልም››

ሲል በፈጠረው የሆሄያት ልዩነት ወደጎዳና ላይ መገዳደል መሸጋገራቸው የትላንት ታሪክ ነው።” ዛሬ ተመስገን በ”ላ” በ “ቸ” ፊደሎች ተላለቁ ብሎ የሚሳለሰቅባቸው ወጣቶች የተሰውበትን ራዕይ በዘንድሮ የነጻ ገበያ ፖለቲካ አንጻር( የግል ጥቅም የለውምና) ለማይረባ ነገር የተደረገ መስዋዕትነት ተብሎ ሊታይ ይችላል። ውስጡ ለነበሩት ግን ምን ያህል ከግል ጥቅም በላይ የሃገር ፍቅር ጎልቶ ይታይ እንደነበር እውነትና ታሪክ ይመሰክራሉ።

 በኢሕአፓና በመኢሶን መካከል የነበረውን ልዩነት ወደ ቃላት አውርዶ፣ ጉዳዩን አልከስክሶ መተንተን የሚሰጠውን ጥቅም (ከሞራል ማካካሻ ባሻገር) ሊገባኝ ባይችልም፣ ከተራ የፖለቲካ ትንተና በላይ ሊሆን እንደማይችል እረዳዋለሁ። ይህን ትንተና ሄዶ ሄዶ ለሃገራቸው የተሻለ ሥርዓትን እናመጣለን ብለው <<ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዴሞክራሲ መብት ያለገድብ . . . >> ሌሎች መፈክሮችን አንግበው የተሰውቱን ወጣቶች በ“ቸ” ና በ”ሸ” ልዩነት ተላለቁ ብሎ መደምደም ተገቢ አይደለም።

 ዛሬ ከወያኔ ጋር መስራትና አለመስራት የሚለው ጥያቄ ጉልህ እንደሆነ ሁሉ ከደርግ ጋር መስራት አለመስራት የሚለውም በዚያ ወቅት ገሃድ ነበር። ዛሬ ሕዝባዊ መንግሥት የሕዝብ ጥያቄ እንደነበር ያኔም የወጣቱ መፈክር ነበር ፣ ያኔ የዴሞክራሲ አለገደብ ጥያቄ ያስገድል ያሳስር እንደ ነበር ዛሬም አያሸልምም። ያኔ ደርግን የሚቃወሙትን አናርኪስት ፣ ፀረ ሕዝብ ተብለው ይገደሉ እንደነበር ዛሬም አሸባሪ ፣ ፀረ ሰላም . . . እየተባሉ አይለቀቁም። እንዲህ ከሆነ ታዲያ የዛን ወቅት ትግል ለቃላት የዘንድሮውን ለዴሞክራሲ የሚደርገው ምኑ ነው? ምንአልባት ትግል ነውና የተሠሩ ስህተቶች ይኖራሉ። እንዚያን በትክክል ካልተተነተኑና ያንን ትውልድ ለመውቀስ ብቻ ሲባል <<ጽንፈኛ>> የሚል ቃል መጠቀም ቆንጆዋን ልጅ በተሰባበረ መነጽር ተመልክተው አስቀያሚ ነች ከማለት ተለይቶ አይታይም።

 ዛሬ ለሃገሩ ቆሞ የሚታገል እያነስ በመጣበትና የግል ጥቅም ጎልቶ የሚታይበትን ምክንያት አበጥሮ ማየት ያስፈልጋል ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሃገሩ ሟች ትውልድ ለማፍራት ከተፈለገ ቀደም ለሃገራቸው በንጽሁ ዓላማ የተስውትን ጀግኖች ታሪክ የጠጅ ቤት የአግዳሚ ወንበር ጨዋታ አለማድረግ አስፈላጊ ነው።

እኔ በማምንበት በጀግኖች ታሪክ ላይ ጀግንነት ይፈጠራል። ጀግኖችን አዋርዶ ፣ የሞቱበትን ግዙፍ ዓላማ አጣጥሎ በቃላት ልዩነት እንደሆነ አድርጎ መተንተን ነገም ለሃገር የምንሰዋበት ምክንያት ሊጣጣል እንሚችልና እንደ ዘንድሮ ደልቃቃ ፖለቲከኛ <<ሞኝ ያለቀው በቀይ ሽብር>> በሚል መፈክር ሥር ተሰባስቦ አነስተኛ የሆነውን መስዋትነት ለመክፈል አለመዘጋጀትን ያመጣል። ተመስገን ከላይ በጠቀስኩት ጽሁፉ እንደገለጸውም መታሰርን እንደ ታላቅ መስዋእትነት ተቆጥሮ በወያኔ የፊርማ ስነ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ በራስ ላይ የእንጥልጥል ፍርድ አስፈርዶ መፈታትንም ያስከትላል። ለሃገር፣ ለሕዝብ መሞት ከገለባ የቀለለ ለግል ጥቅም መቆም ደግሞ ከተራራ የገዘፈ ሲደረግ እንዲዚህ ነው።

 ውድ ታናሽ ወንድም ተመስገን . . . ለዓላማ መሞት ከባድ ነው። መሣሪያ ይዞ ሊገድል የቆመን ፋሽሽት ጊዜያዊ ሕዝባዊ መንግሥት ፣ የዲሞክራሲ መብቶች አለገደብ እያሉ መሞት "ቸ ቸ ቸ" ወይም "ላ ላ ላ" እያሉ መሞት አይደለም። የመጻፍ መብት ስትከለከል “አደፍርስ “ የሚባል የማባዣ መሣሪያ ሠርቶ

በድብቅ የሚያምኑበትን ጽፎ መበተንና ከዚያም ተይዞ መገደል “ቸ” ና የ”ላ” ትግል ውጤት አይመስለኝም። የተገፈፉትን ነጻነት በትግል የማግኘት የዴሞክራሲ ጥያቄ እንጂ!

በእነዚያ የዴሞክራሲ ጥያቄ አንግበው በተስዉ ጀግኖች ልቦና ውስጥ ምን እንደነበረ ከኢዲስ ዘመን ወይም ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተገኘም ንቃት አይተነትነውም። ያንን ለመገንዘብ በእነሱ ቦታ ራስን ማስቀመጥ ያስፈልጋል። ዛሬ በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ብዙ ቅጽል ስም ከመንግሥት ደጋፊዎች ይወጣላቸዋል። ይህንን ስም ማጥፈት የሚያምኑ ይኖራሉ። ከሁለት አስርተ ዓመታት በኋላ አንድ የደላው ጋዜጠኛ በአሁኑ ወቅት ያለው ትግል “ዓባይ ይገደብ አይገደብ ነበር” ብሎ ቢጽፍ የዘንድሮውን ሁኔታ ተነተነ ማለት አይቻልም። እነሽብሬም ፣እነ ተስፋዬም ፣ እነ አስፋ ማሩም፣ እነ ጋይምም በዚህ ምክንያት ተሰዉ ማለት አይደለም። ትግል ሙሉውን ሳይሆን በቅንጣቢ መተንተን የሚመጣው ስህተት ይህንን ይመስላል።

 ጽሁፌን ለማጠቃለል ያህል ታላቁ ደራሲ ዩሐንስ አድማሱ ከዚህ ዓለም የተለየው በእድገት በኅብረት መጀመሪያ ወቅት ላይ ነበር። ከዚህ ከሚባለው ክፍፍል በፊት በመሆኑ እድለኛ ነው። እዚህ ውስጥ በቃላት አጠቃቀምም ቢሆን እንኳን ለመዶል መሞከሩም አስፋላጊ አይደለም። ይህም ቢሆን ቁንጽል የሆነ ጽሁፍ ጠልቆ ታሪኩን ለማያውቅ ግለስብ ሌላ ትርጉም ይሰጣል። ዮሐንስ አድማሱን ለመጥቀስ ከተፈለገ ውብ የሆኑ ሥራዎችን ከዚህ ክፍፍል ውጭ ለብቻቸው አንስቶ መወያየትን በግሌ እመርጣለሁ።

ስለ ያ ትውልድ የሚያስብ ሁሉ በሰላም ይክረም !
በልጅግ ዓሊ Beljig.ali@gmail.com