Monday, February 6, 2012

ጥቁር አሞራው ሙሴ

Tesfaye Gebreab the EPLF spy giving interview on Meniesey EPLF's Youth magazine in Asmara


to view this  page in a bigger font/ wider page use your keyboard and press Ctrl and + sign at the same time. to

ጥቁር አሞራው ሙሴ

ጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com




ያረጁ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች እያሉ የሚዛበቱ “የሳንድውች ጀነረሽን” አብዮተኞች  በዚህ ወር በኢሕአፓ ላይ ዘመቻው አጧጡፎዉታል። ከምርጫ 97 ወዲህ ወዲያውኑ ወደ ውጭ አገር በመምጣት  ለመጀመሪያ ጊዜ በኢሕአፓ ላይ ዘመቻ የከፈተው (ጹሑፉ ያዘጋጀሁለት እኔ ነኝ የሚሉ አንድ ጸሐፊ እራሳቸው ሰሞኑን  አስነብበውናል) “ስኩለር” ነው። ስኩለር በደራሲ በመስፍን ማሞ ተሰማ የጆርጅ ኦርዌል “የእንስሳት አብዮት”   መጽሐፍ ላይ የተጠቀሰው ገጸ ባሕሪይ ነው። እኔ “ስኩለር” የምለው የግንቦት 7ቱ ብርሃኑ ነጋን ነው።

ወዳጄ ደራሲ መስፍን እንደገለጸው “ስኩለር” ኦርዌል በእንስሳት አብዮት ውስጥ ከቀረፃቸው እጅግ ውስብስብ አመራማሪና አስገራሚ ገፀ ባህሪያት መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል። ከአመፁ መሪዎች አንዱ የሆነው ስኩለር “ድንጋይ ዳቦ ነው” ብሎ የማሳመን ችሎታ ነበረው። ብሩህ ኣእምሮ ያለው ፈጣን ተነጋሪና እጅግ ጮሌ ሲሆን የሌሎችን ሀሳብ (ለመልካም ግብ ሳይሆን ለማደናገሪያ ወይም እውነትን ለማድበስበሻ) የማስለወጥ ሀይሉ ከአነጋገር ስልቱ ጋር ተዳምሮ ወደር የማይገኝለት ‘አጭበርባሪ’ ፖለቲከኛ አድርጎታል።” መስፍን ማሞ (እንስሳት አብዮት) ገጽ 9)።

የግንቦት 7ቱ “ስኩለር” በከፈተው ዘመቻ የጀመረ ይኼው እስከ ዛሬ ድረስ በኢሕአፓ ላይ ዘመቻ የሚያካሂዱ በርካታ ደርጎችና በየፓልቶኩ የተወሸቁ የ“ሳንድዊች ጄነሬሽን” ተከታዮቹ ቀጥሏል።  ኦርዌል “ጥቁር አሞራው ሙሴ” ብሎ የሚጠራው   ሻዕቢያው ሰላይ ጋዜጠኛ ተስፋየ ገብረአብ ሁለት ሦስት ጊዜ በኢሕአፓ ላይ ዘመቻ ሲያናፍስ አንብበነዋል።

‘ጥቁር አሞራው ሙሴ’ በጆርጅ ኦርዌል ገጸ ባሕሪያት ላይ የተጠቀሰው የአቶ ጆንስ (የትልቅ እርሻ ባለቤት ሰው ነው) ታማኝ የቤት እንስሳ ነው። ስራው የአቶ ጆንስን ነጭ ወሬ የሚያሰራጭ የጆን ወኪል ነው። ጆን ማለት ‘ኤርትራ’ የምትባለዋን ትልቅቷን ማሳ በባለቤትነት የያዘ “ኢሳያስ አፈወርቂ” ማለት ነው። ሰሞኑ አንድ ወዳጄ “የብሸፍቱ የማታ ወፍ” ብሎ የሰየመው   ‘ተስፋየ ገብረአብ’ ኢሕአፓን በመዝለፍ ኤርትራን ከደርግ በባሰ እያሰቃያት ለሚገኘው ጨቋኝ መሪ የሰጠውን የቤት ስራ ለማካሄድ  የተለመደው የስለላና የመተንኮስ አገልግሎቱ ማሰራጨት ጀምሯል።  

የተስፋየ ገብረአብ ትውልድ ኤርትራዊ መሆን ድንገት የማታውቁ ካልሆናችሁ ሁላችንም የምናውቀው ነው።ሻዕቢያዎች የተካኑ ናቸው። ሌላ ቀርቶ ሪቻርድ ኮፕላንድን የተጋፈጡ የተዋጣላቸው ሰላዮች ናቸው። ትዝ ይላችል ሪቻርድ ኮፕላንድ ጋር ሲነጋግሩ ኢሳያስ የጠየቀው ጥያቄ እና ያገኘው መልስ? እነሆ አንብቡት  እንዲህ በሎ ነበር፦

“…ኢሳያስም ይህን ፕላን በቲዮሪ ደረጃ ከሰማ በኋላ ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ምን ዋስትና አለው? በማለት ጠየቀ፡፡ አሜሪካኖቹም ፖለቲካ የቁማር ጨዋታ ስለሆነ ቁማር ተጫወትእናንተ የምትፈልጉት ነጻነት ነው፡፡ እኛ ደግሞ የምንሻው የቀይ ባህር ይዞታችን እንዲጠናከር ስለሆነ፣ ይኸው ዋስትናችን ነውብለው
መለሱለት፡፡” (የተስፋይ ጀርጆ በስምምነቱ ላይ አብሮ ስለነበረ በደርግ ጊዜ በምፅዋ ሲምፖዝዮም ላይ የሰጠው የምስክርንት ዘገባ ነው)

ሰማችሁ? ተስፋየ ገብረአብ የኢሳያስ አፈወርቂ ሰላይ ነው። የአሜሪካው የስለላ ድርጅት  ኮፕላንድ የተስፋየ ገብረአብ አለቃ የሆነው ኢሳያሰድ አፈወርቂ ፖለቲካ የቁማር ጨዋታ ስለሆነ ቁማር ተጫወት” እንዳለው ሁሉ ተስፋየም በኢትዮጵያዊነት ስም እና በስነ ጽሑፍ ችሎታው እያምታታ ብዙ የዋህ ሰዉ የቁማር ጨዋታውን እየተጫወተ የስለላ እና አንድነትን የሚያፈርስ የቤት ስራው እየሰራ መሆኑን ከሚሰነዝራቸው አንደበቶቹ ማወቅ ይቻላል።

ይህ ግለሰብ የስለላ ችሎታው በጣም የተካነ ስለሆነ እነ ብርሃኑ ነጋን ተገን በማድረግ “የሳንድውች ጀነረሽን” ወጣቶችን በተዋበ ስነ ጽሑፍ በማኖህለል የስለላ ስራዎቹ በማካሄድ ለዓሊ ዐብዱ እና ለየማነ ማንኪ ስለ ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እና ስለ ወያኔዎች ጉዳይ አጠቃላይ መረጃዎችን በሚመለከት  እንደሚለዋወጥ እና አንደሚያስተላልፍ ከኤርትራ መንግስትም ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ከሚታመኑ ሰዎች የተሰጡንን መረጃዎች ያመለክታል።

ተስፋየ ሁለ ገብ ነው። አማርኛ እና ኦሮምኛ በሚነገርበት ኢትዮጵያ ውስጥ በማደጉ የስነጽሑፍ ችሎታው ለስለላው ስራ አመች ሆኖለታል።በሻዕቢያ በኩል የተሰጠው የጥላቻ ትምህርት ለማሰራጨት በኦሮሞ እና በአማራው ሕብረተስብ መካካል እሳት ለመጫር የቡርቃ ዝምታ በሚባለው ደራሲው ያንጸባረቀው  የእነ ሌንጮ ለታ እና ዲማ ነገዎን ጸረ አማራ የጥላቻ ባሕሪ  “የውሸት ቃላት” ተጠቅሞ ያልሆነ የአማርኛ የቃላት ትርጉሙ በመተርጎም ሕዝብን ለማናቆር እንዴት እንደተጠቀመበት ባለፈው ጊዜ የ“ቀለቤቴን ስጧት”  ደራሲ ወንድማችን “በልጅግ አሊ” የተስፋየ ገብረአብ የቃላት አጠቃቀም ዘዴ ባለፈው ወር በኢትዮላዮን እና በአሲምባ ድረገጾች ላይ በሚገባ ከነትርጉሙ አጋልጦታል።

ሻዕቢያ የሰጠው የጥላቻ መርዝ በትግሬዎች ላይ  እየረጨ ለስለላ የቆመላት በወላጆቹ የትውልድ መንደር ኤርትራ ውስጥ ትዳር መስርቶ የመጀመርያ የበህር ልጁ ያስገኘችለት ስለ ኤርትራ ወታደሮች እና ህዝቧ መጥፎ ነገር ምንም ሳይተነፍስ በትግሬ ገበሬ እና አለቃው ኢሳያስ እንዳስተማረው “የወያኔ ወታደር/ ጭፍራ” በሚላቸው “የኢትዮጵያ ወታደሮች” ባድሜን ነጻ እንዳወጡ እነ የማነ ገብረአብ እና የሻዕቢያ ከፍተኛ ሹሞች ከቢቢሲ የዜና ማዕከላት ባረንቱ ተወሽቀው ዉግያው ሲከታተሉ የነበሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች ደንገት እነሱን ከበው ለመያዝ  ወደ ባረንቱ ሲጠጉ “እነ የማነ ሸሽተው ሲያመልጡ”  ተስፋየ ገብረአብ ያሰራጨው ጸረ ትግራይ ሕብረተሰብ ጥላቻው እነሆ አንብቡት፦

“በቀጥታ ለመናገር ስዬ እየዋሸ ነው። እያጭበረበረ ነው። በጦርነቱ የተቻለውን ሁሉ ሞክረዋል፡፤ ስላልተቻለም ተመልሰዋል! ሌላ ሰበብ ማብዛት ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሰረዊት ባረንቱ ከያዘ በላ ሰራዊቱን አስከትለው 5000 የትግራይን ገበሬ ለዘረፋ አሰማርተዋል። በዚህ ዘረፋ ጀበና እና ማርገብገቢያ ብቻ ሳይሆን ማሳ ላይ የነበረ ጥቅል ጎመን ሳይቀር በአህያ እየጫኑ ወስደዋል።ከዘረፋው በላ ሠራዊቱ ተመልሶ ወጣ። ስለዘረፋው ባረንቱ ሄጄ ከገበሬዎቹ የሰማሁት ሲሆን ከእነዚህ ጋር ሲወዳደር የደርግ ሰራዊት ጨዋ ነበር። ብለው ነግረውኛል።”

እንገዲህ ይታያችሁ። ይህ ሳላይ በረንቱ ድረስ ሄዶ አለቆቹ የሰጡትን የቤት ስራ ለማካሄድ  ከበረንቱ ኗሪዎች አገኘሁት የሚለው “የትግራይ ገበሬ ዘራፊነት ባሕሪ” ለጊዜውም ቢሆን በተስፋየ ገብረአብ ዘገባ አውነት ሆኖ እንቀበለው እና ይህ ሰላይ እውነተኛ ጋዜጠኛ እና ኢትዮጵያዊ ከሆነ “የሻዕቢያ ሰራዊቶች” በትግራይ ገጠሮች ቤተክርስትያናት፤በባድሜ፤ ዛላምበሳ፤አሊቴና እና በበርካታ የድምበር አካባቢ ኗሪዎች ላይ ያደረሱት ጉዳት እና ዘረፋ ለምን አልዘገበልንም? መረጃ አጥቶ ነው እንዳንል ይህ ሰላይ ወደ ውጭ በኬኒያ በጫካ ሸሽቶ (ባይሮፕላን ነኝ የወጣሁ ይላል ፤ውሸት ነው።) የወጣው  ከጦርነቱ በኋላ ነው። ታዲያ ለምን በ5000 የትግራይ ገበሬዎች ላይ “ዘራፊዎች” እያለ ዘመቻውን ማካኼድ መረጠ? ቁጥራቸውስ ማን ሰጠው? ከየት አገኘው?

ተስፋየ ገብረአብ ኤርትራ ሲሄድ አንዴ ‘ለቅሶ ለመድረስ” ነው የሄድኩት ይላል፡፤ አንዴ “መጽሐፌን ለማጸፍ እንዲያመቸኝ እዛው ሄድኩ ይላል” “ኤርትራ ሄዶ “መንዕሰይ’ ለተባለ በእኛ በኢትዮጵያውያን እንዳይጋለጥ ተብሎ በጥንቃቄ የተመረጡ ለስላሳ ጥያቄዎች ተዘጋጅተውለት *በጣም ይገርማችሗል) በትግርኛ ቃለ መጠይቅ አካሂዶ ሲያበቃ ትግርኛ መናገርና ማዳመጥ ችሎታው እያላው -ዱባሩባ ዘመዶቹ ጋር ሄዶ እያለ ገበሬው ጋር የመግባባት ችግር ነበረኝ ይላል”። የውሸቱ ማደናገሪያው ብዙ ቢሆንም፡ ኤርትራ ሄዶ በነበረበት ወቅት በያካባቢው ነፃ ዝውውር ለማድረግ ሲፈቀድለት እዛው የተመለከተው የትግራይ ህዝብ ዘራፊነት ብቻ እንጂ ስለ ኤርትራ ሕዝብ ችግር እና አለቃው በኤርትራ ሕዝብ ላይ ስለሚያካሂደው ዘረፋ፤ጭቆና፤ግድያ እና አፈና እንዲሁም የወጣቶች በባርነት በስርዓቱ የመያዝ ጉዳይ የተነፈሰው አንድም ቃል የለም። ለምን?
እስኪ ይህንን የሻዕቢያ የቤት ስራው ለማሰራጨት በኢትዮጵያውያን የዜና ማዕከሎች እየተጠቀመ የሚያሰራጨው ጸረ ትግሬዎችን አድምጡ፤እነሆ-
 በቀጥታ ለመናገር ስዬ እየዋሸ ነው። እያጭበረበረ ነው። በጦርነቱ የተቻለውን ሁሉ ሞክረዋል፡፤ ስላልተቻለም ተመልሰዋል! ሌላ ሰበብ ማብዛት ለምን አስፈለገ?”  የሚለው የዚህ ሰላይ ፕሮፓጋንዳ እንመርምረው።

ሃይለ ዱሩዕ የተባለው በባድመ ጦረነት ወቅት የሻዕቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ እስር ቤት ገብቶ ሁለቱ ዓይኖቹ ዓይኑ እንዲታወር ሆኖ እየተሰቃየ እንዲሞት ሌት ተቀን ጭለማ ውስጥ ታሽጎ በቆላማ በረሃ እስር ቤት ውስጥ  የሚገኘው “ሃይለ ዱሩዕ”  የተባለው በውሸቱ የታወቀው “አልአሚን” ከተባለ የታወቀው የሻዕቢያ “ዋሾ” ባለስልጣን  ጋር በመሆን አሜሪካ “ሎስ አንጀለስ የኤርትራኖች ፈስቲቫል” ላይ በመገኘት ስለ ነበረው የጦርነቱ አጠቃላይ ሁኔታ እንደተጠበቀው እንደኛ “ማን አህሎ” የጉራ ሱስ የለመዱት ኤርትራኖችን ካሰከራቸው በላ የስልጣን እና የአስተዳደር ህዳሴ ለውጥ ማድረግ አስፈላጊነት ኣብራርቶ ሲያበቃ “ጦርነቱ ባሸናፊነት ወጥተን አከሸፍነው” ብሎ የዋሸው ውሸት ከሕሊናው ጋር እየተምታታበት ስላስቸገረው ያበጠው ይፈንዳ በማለት ለእስር የዳረገቺውን ሊደብቃት ያላስቻለቺው ሃቀኛዋን መራራ ንግግር እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር፡

አስቀድሜ ሰላምታየን አቀርባለሁ። በዚህ ሁለት ወር ውስጥ በኤርትራ ሕዝብ ላይ አንዣበቦበት የነበረው አደገኛ ሁኔታ መክቶ ሸፍኖት የነበረው አደገኛ ዳመና ስላስወገደው እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። በጦርነቱ ወቅት በዓለም መገናኛ ዜናዎች ሲተላለፍ የነበረው እጅግ አስፈሪ እና አሳሳቢ የሕልውና ዋስትናችን አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደነበር የሚያስተጋቡ የጦርነት ዜናዎች ስታዳምጡ

አንዳንዶቻችሁ በሃሳብ ሰመመን ምግብ መብላት እስከማቆም ድረስ እና ከስራ የመቅረት ሁኔታ አጋጥሟችሁ  እንደነበረ የምታውቁት ጉዳይ ነው። ያ ሁሉ የምታውቁት ስለሆነ እኔ ለናንተ ለባለቤቱ አልደግመውም። ችግር ሲያልፍ ተሎ ስለሚረሳ ምናልባት ዛሬ እንደ ቀላል ሊታይ ይችል ይሆናል። በእውነቱ ይህ ጦርነት እጅግ ፈታኝ እና የፈተና ሁሉ ፈተና የመጨረሻ አደገኛ ነበር።
( “ወያነ አብዛ ኩናት እዚኣ አጣላቒየሙና እዮም እንተብልኩ ጋህዲን ሓቂን እዩ።)

 “አጣላቒየሙና” ማለት ባሕር ውስጥ ስትዋኝ ትግል ገጥመህ ጠላትህ አንገትህን ጠምዝዞ ትንፋሽ እስኪያጥርህ ድረስ ባሕሩ ውስጥ ሲያደፍቅህ የሚታየው እና የሚሰማው የትንፋሽ እጥረት ስሜት ማለት ነው። በሌላ አነጋገር “አጣላቒየሙና” የሚለው ቃል ከፍርሃት የተነሳ  ፍርሃት የወለደው የውስጥ ሱሪ የሚፈታተን ክስተት ተከስቶብን  ነበር ማለቱ ነው። “አርበድብደውን ነበር፤መድረሻ አሳጥተውን ነበር” ማለቱ ነው።) ወየኔዎችም እውነት ለመናገር በዚችው ጦርነት እስክንበሰብስ ድረስ አድርገውን ነበር ብየ ስነግራችሁ የታየው ጋሃድ እና እውነት ነው።” “ በጦሩነቱ ወቅት ወያኔዎች ወደፊት  ገፍተው ሰፊ የኤርትራ ቦታዎች ሲቆጣጠሩ የወያኔ ወታደር እየሸሹ ነው እያልን ተቃራኒው ስናሳስታችሁ እናንተም መረጃውን እየተቀበላችሁት እንደነበር በግልጽ ለመናገር እወዳለሁ። እኛ እንደ መንግስት ድክመታችን ካሁኑኑ በግልጽ ተነጋግረን ከላረምን የባሰ ችግር ያመጣል……” ሲል እቅጩን ነገራቸው።

“የጥቁር አሞራው ሙሴ” የተስፋየ ገብረአብ አለቃ ኢሳያስ አፈወርቂም ጀርመን አገር ውስጥ ሕዝብ ሰብስቦ ወያኔዎች ሰፊውን የኤርትራ ቦታ እንዴት ሊቆጣጠሩት  እንደቻሉ ኤርትራኖች ጠይቀውት ሰራዊቱ አሳፋሪ ሽንፈት የገጠመው መሆኑን ሳያመነታ “ይህች ቃል ሌላ ቦታ ለማንም ተናግሬ አለውቅም፤ አሁን ግን ስለጠየቃችሁኝ ነው ይህ አንጀት የሚያሳርር ሽንፈት ለመቀበል እና ለማማን የቻልነው ሲል ” በኢሳያስ አፈወርቂ በድጋሚ የተረጋገጠ ቢሆንም ኢሳያስና ደርግ  ንጉሶች ERITREA: ህግደፍ ደርጊ http://youtu.be/BPQJOBno9Eo ናቸውና ነውና የሚነካው ሃይል እና ባለስልጣን ስለሌለ የሃይለ ድሩዕ ንግግር የሎስ አንጀለስ ገልጽነት ስላልተወደደች “ሃይለ ዱሩዕ”  ወደ አስመራ ከተመለሰ በላ ለእስር ተዳረጎ ሁለቱ  ይኖቹ ታውሮ ጭለማ ውስጥ ታስሮ  እንደነበር እሱን ሲጠብቅ የነበረ የእስር ቤት ጠባቂ  የነበረው “እዮብ ሃብተ ማርያም” የተባለው ወደ ስደት መ ቶ የሰጠው ዜና ያረጋግጣል። መረጃው ለማዳመጥ ይህንን ዜና ከ አልጀዚራ አስተላለፈው ቀፋፊ እና አሳዛኝ ዜና  ዮዩ ቱብ ገብታችሁ Eritrea accused of prisonerabuse  http://youtu.be/mJ3_MlTstiY ያድምጡ።እስካሁን ይሙት ይኑር የሚታወቅ ነገር የለም ።

ታዲያ ሰላይ ተስፋየ ገብረአብ  የወላጆቹ አገር ኤርትራ ድረስ ሄዶ ትዳር መስርቶ የሻዕቢያ ከፍተኛ ባለስልጣን ልጅ አግብቶ ወልዶ ከብዶ አንደሚንደላቀቅባት ገነት ሳትሆን “ሕዝብ በስቃይ ሰንሰለት ታስሮ የሚጮህባት መሬት ነች””። እውነት ይህ ሰው ጋዜጠኛ ነው? የውጭ አገር ባዕዳን ስለ ኤርትራ ሕዝብ ችገር ሲዘግቡ እሱ ትዳር መስርቶ ኤርትራ ውስጥ ኑሮ መስርቶ ሲዝናናባት ምን ዓይነት ሕሊና ሲኖሮው ነው?  የሕዝቡ ስቃይ በሩቅ ሆነን እኛኑን እያንገበገበን፤ ይህ አድርባይ ግን የህዝቡን ስቃይ ለማራዘም እዛ ለመኖር አሳብ አለኝ፤ስደት አንገፍግፎኛል ሲል “ከስደት ይልቅ ኤርትራ የምትሻለው መሆኑን ሲዘላብድ ታደምጡታላችሁ”። ተስፋየ ገበረአብ ስለ አለቃው የኢሳያስ አገር ቢደብቀንም፤ ታዋቂው ዘፋኝ ኤርትራዊው ተወልደ ረዳ “ካተሰማ” በሚያስመስለው በታወቀው ጎርናና ማራኪ ድምፁ በትግርኛ እንዲህ ሲል በሙዚቃ ቃናው ነግሮናል።
(ኣቦይ ኣደይ ካንዶ ረጊምኩማ ዛብርኽቲ ዓደይ
ክጋደል ወጺኤስ ተሰዲደ ኣንታ ናዓይስ ዳሓን ይኹን ጊደይ፡
ዘሕዝነኒ ዘሎስ ቶም ውላደይ።
ኣታ መኒኻ!
ካራ ዝሳሓልካ መሕረዲኻ
ገመድ ዝተታዕካ መሕነቒኻ
ሓለንጊ ሰቢሕካ መግረፊኻ
ብደም ዓሊስካያ ገዛኻ።
የማነ ባርያኳስ ነጊሩ
ዓፍራ ከይትረግጹ ክትሰግሩ።
ዳዊት ደጊሙዋ ትማሊ
መን እዩ ተሓታቲ ባሃሊ”)

ትርጉም፡
(“አባት እናቴ ይቺ የተባረከች አገር ረግመት ይሆን  እንጂ
ባልተሰቃየች እንዲህ ባለ ጉድ እንዲህ ባለ ጎጂ
እታገላለሁ ብየ ሜዳ ወጥቼ
ቀረሁ ተሰድጄ።
የኔስ ምንም አይደል እያየሁት ነው እንዳለየሁ አይቼ
እኔ የሳዘነኝ የነኛ ልጆቼ
ሰማህ! ማነህ አንተ! ቢላዋ የሳልክ ማረጃህ
ገመድ የተበተብክ ማነቅያህ
አለንጋ ያዘጋጀህ መግረፊያህ
በደም የረጨሃት አገርህ።
የማነ ባርያ እንኳ አስጠንቅቆ ነበር እንዳትሻገሩ
እሻገራለሁ ስትሉ አረፋ ረግጣችሁ ገደል እንዳትገቡ።
ዳዊትም ደግሟታል ያቺው ማስጠንቀቂያ
ለዚህ ሁሉ ጉድ ማን ነው ተጠያቂው?)

በማለት ዝነኛው ተወልደ ረዳ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ዘፍናል። ስለ ግጥሙ ለማብራራት ያህል። እታገላለሁ ብለን በወጣትነታችን በረሃ ወጥተን አርጅትን ኤርትራን ነጻ አወጣን። ነፃነት መጣ ስንል የተመኘነው ሁሉ የማይጨበጥ ጉም ሆኖብን የባሰ ጭቆና አስከተለችብን።  በነፃይቱ ኤርትራ መኖር ስላልቻልን በስተ እርጅና ወደ ስደት አመራን። ያ ሁሉ በኛ መድረሱ  ቢከነክነነም ፤ይባስኑ የወለድናቸው ወጣት ልጆቻችን ወደ ባሰ ባርነት እና ሲኦል መግባታቸው አንጀት ያሳዝናል።

ይህ ሁሉ በደል በራስህ ላይ እንዲፈጸም ምክንያት የሆነበት ምክንያ የሰው ደም መስዋእትነት የመጣውን ስልጣንና ነፃነት ጥቂት አምባገነን ግለሰዎች ስልጣን ሲቆጣጠሩት “ስልጥን ለሕዘቡ መልሱለት”” ብለው በሚሉ ዜጎች ላይ “ጸረ ኤርትራ” እየታበሉ ለግፍ ሲዳረጉ ተው ስትባሉ፤ አብራችሁ አምባገኖችን “አይዞህ፤ግፋ” እያላችሁ እያንጨበጨባችሁ ለብዙ አመታት አገልግላችሁት “አሁን በማይነቃነቅበት ደረጃ ደርሶ” ሕዝቡ “ተዳክሞ” ለዚህ ውርደትና ተገዢነት ከደረሳችሁት በሗላ አሁን ተመልሶ “በራሳችሁ ላይ” ዱላውና ግድያው አዞረው። ለዚህ ግፍና ጉድ ተጣቂው ማን ይሆን?

የማነ ባርያ እና የአረፋ ጉዳይም ስለሚለው ግጥምም “የማነ ባርያ" የተባለው አሁን በሕይወት የሌለው አውቅ ኤርትራዊ ዘፋኝም “ወደ ኤርትራ እንዳትሻገሩ ፤የማይታያችሁ አረፋ እግራችሁ ስር አለ፤ ስትረግጡት ገደል ነው ተጠንቀቁ” (ባጭሩ ምን ማለቱ ነው ወደ ነፃይቱ ኤርትራ አገራችን ወደ ገነቲቷ አገራችን እንዳለን ብላችሁ ወደ እዚህ ብትመጡ የሚያገኛቸሁ እጣ ፈንታ “ሞት” “ውርደት” አፈና እና “እስር ቤት” ስለሆነ ወዮላችሁ! ብሎ ኤርትራ ሂዶ አስመራ ውስ  ከመመሞቱ በፊት በዘፈን መለክ ስለ ኤርትራ ስርአት ሁኔታ አስጠንቅቆ ነበር። ማለቱ ነው።በይበልጥ የተወልደ ረዳ ይህ ዘፈን እና ሌሎቹ ለዛ ያላቸው ዘፈኖቹ ለማዳመጥ የሚከተለው አድራሻ በዩ ቱብ ገብታችሁ አዳምጡት። (ተወልደ ማለት የኤርትራ ኢትዮጵያዊው “ካሳ ተሰማ” ወይንም ሱዳናዊው “አብደል ከሪም አልካብሊ” ነው።  ewelde Redda - Brikti Adey http://youtu.be/08h0V3xYiP8

ይህ ጉድ በሚዘፈንላትና በሚነገርላት፤ ከዛች የምድር ሲኦል ለማምለጥ አብዛኛው ነብስ ያወቀው ኤርትራዊ  በሚሸሻት የሰቆቃ እና የሽብር መሬት  ኤርትራ” ውስጥ ነው ተስፋየ ገብረአብ እየተንደላቀቀ በየባረንቱ እየተዟዟረ የሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ እየነዛ በግንቦት 7 እና በጸረ ትግሬ ፓልቶክ ክፈሎች እየተንጨበጨበለት ነጭ ሃሰቱን ሲነዛ የምንሰማው።

አብዛኛው ጊዜ የሻዕቢያ ባለስልጣኖች እና የሻዕቢያ ተከታዮች ትኩረታቸው እና ጥላቻቸው የሚሰነዝሩባቸው ከወያኔ ባለስልጣናት ይበልጥኑ በገብሩ አስራት እና በስዩ አብርሃ እንዲሁም በትግራይ እንደሆነ እስካሁን ታወቃላችሁ የሚል ግምት አለኝ።ሰላዩ ተስፋየ ገብረአብም በነዚህ ሦስት ሰዎች አረጋሽ ገብሩ እና በስየ ላይ ነው ትችቱ በሃይለኛ ትኩረት የሚያተኩረው ሁሌም ነው። በጣም የሚገርመው የሻዕቢያው ሰላይኢትዮጵያዊ አይደለህም ይሉኛል ፤ዜግነቴ ማንም አይሰጠኝም አይነጥቀኝም፤ የብሸፍቱ ልጅ ነኝ! ይላል። “የብሸፍቱ ወፍ” ይበሉት ሌላም ሌላም እሱ እንዳለው ኢትዮጵያዊ ነኝ ካለ ማንኛችንም ለመንጠቅ መብት የለንም። ግን እራሱ የሰውን መብት ካልጠበቀ ሌላው እንዴት የሱን ኢትዬጵያዊነት ሊጠብቅለት ይጠብቃል?
የሚከተለውን አንብቡ፦
"Seyene never been Ethiopian.” ECADEF PAL TALK ROOM. 

ስየ ከእስር ቤት ወጣ፤ ከዚያ በኢትዮጵያዊነት አለ። እሱ ከእስር ቤት ወጥቶ ኢትዮጵያዊነት ስላለ “ኢትዮጵያዊ” ሆነ ማለት አይደለም”  (source  Tesfaye Gebre Ab Second book Interview with ECADF Part 1 ) አደመችሁት?

ሰፋ ባለው አነጋገሩ  ምን እንዳለ ልድገምላችሁ፡

.“ ..ቀደም ብየ እንደገለጽኩት ኢትዮጵያዊነቴን ማንም ሊሰጠኝ ወይንም ሊከለክለኝ አይችልም። አገር ውስጥ እንዳልገባ እከለከል እሆናል፤ የውስጥ ስሜቴን ግን መንጠቅ የሚችል አንድም ሰው የለም! ማነው ያ ከልካዩ በመሰረቱ?! ምን ዓይነት ሥልጣን አለው ያ ከልካዩ? ከየት ነው የመጣው ያ ሰውየ? እሱ እራሱ ምንድ ነው? ምን አደረገ ለዛች አገር? እኔ የብሸፍቱ ልጅ ነኝ “ኢትዮጵያዊ ነኝ”። (source Tesfaye Gebre Ab Second book Interview with ECADF Part 1 Ethio Tube)  

እንግዲህ ፍረዱ። ይህ ሰላይ የሱን መብት የሚነጥቅ በጽኑ ይኮንናል፤ እሱ ግን የስየን ኢትዮጵያዊነት ዜጋ እንደፈለገው በፈለገው ፓል ቶክ ሩም ገብቶ መጋፋት ፤መንጠቅ መብት እንዳለው ይናገራል። ይህ ሰው የሻዕቢያ ሰላይ” ብሎ ሰው ሲለው ያንሰዋል? ይከፋዋል?

አዲስ አበባ ወያኔን ሲያገለግል በነበረበት ወቅት ወያኔን እና ሻዕቢየን ተማምኖ “እኔ እኮ ኤርትራዊ ነኝ! ወላጅ አያቶቼ እንዳንተው ዓይነቱ ጋላ 100 ነበሯቸው! ለፍዳዳ ኦሮሞ! ሲል አሁን በጤና ቀውስ ታሞ የሚንከራተት አንድ ጋዜጠኛ ሲጠጡ በስካር መንፈስ ጠግቦ ሲደናፋ ከተሰደበው  የሰሙት ሰዎች አሁንም በሕይወት አሉ። ያውም በኤርትራዊ ጋብነት በወያኔ አይዞህ ባይነት ተማምኖ የሺ ጥላ ኮኮብ የተባለውን አስደብድቦ ከሰራው  አፈናቅሎታል ብለው በሰፊው ታሪኩን የሚያውቁ  ሰዎች ነግረዉኛል።

ወየኔ ጋር ሆኖ “ነፍጠኛ” እያለ እየጻፈ በአማራው ላይ ሲቀልድ ነበረ ብዙ በደል ያደረሰ ይህ የሻዕቢያ ሰላይ የወያኔ ምስጢር አውቃለሁ ባይነቱ በስየ አብርሃ ላይም ሲደነፋ አድምጡት። እነሆ፡

“ስየ ‘አታስፈራሩን፤ እንድናወጣው አታስገድዱን” ሲል ለነ መለስ ዜናዊ ማስፈራሪያ ሲናገር ሰምተነዋል። ስየ አብርሃ የሚያውቀው ምንም ምስጢር የለም። ቢኖሮው እስካሁን አይቆይም”” ሲል በጸረ ትግሬ አጫፋሪ ተቃወሚ ፓል ቶክ ሩም ውስጥ ሲዘላብድ ሰምታችሁታል። በሌላ ቀን ደግሞ ይህ ባለበት አንደበቱ  ፡ እንዲህ ይላል፦

ለመናገር ስለማልፈልግ ነው እንጂ እነ ስዬ ለእኔ የነገሩኝ ብዙ ነገር አለ” 

ስየ የሚያውቀው ምስጢር የለም ይላል። በሌላ ቀን ደግሞ “ለመናገር ስለማልፈልግ ነው እንጂ እነ ስዬ ለእኔ የነገሩኝ ብዙ ነገር አለ” ይላል። ምስጢር ከማያወቅ ሰው እንዴት “የማይገለጽ ብዙ ምስጢር አገኘ?” ይህ ሰው የሚዘላብደው በጥንቃቄ የሚናገረው ብትከታተሉት እኮ እጅግ አስገራሚ ፍጡር ነው።

እኔ አገር የለኝም። ይላል። በነፃነት እንደልቡ ትዳር ይዞ ልጅ ወልዶ በየባረንቱ እና በየገጠሩ እየተዘዋወረ የትግራይን ሕዝብ ስም ለማጉደፍ የሚጫጭረው የስለላ ስራው ሲያጠናክር ጓደኛው የ ኢ ኤፍ ኤም ድረ ገጽ እና የኢሳቱ የአውሮጳው ዋናው ሰው ክንፉ አሰፋ የተባለው ጋዜጠኛ ተስፋየ ገብረአብን ለቃለ መጠይቅ አቅርቦ ትዳር አለህ?ብሎ ሲጠይቀው። ምንድነው ያለው? ታስታውሳላች ? “የለኝም!”ነበር ያለው፡፤ ሃቁ ግን የሚከተለው ነው፤፡

ጥቁር ጫካ የተባሉ የዚህ ጉደኛ ሰላይ የአስመራ ህይወቱ እንዲህ ሲሉ ይፋ ያደረጉልንን ምስጢር እነሆ፦


አንዳርጋቸው- አስመራ ከሄደ በሗላ አስመራ ያሉትን ብዙ ኢትዮጵያዉያን እየዞረ ቢያነጋግር ኖሮ ብዙ ሊማርና ብዙ አባላት ሊያገኝ ኢችልም ነበር። አስመራ ያሉት ኢትዮጵያውያን የሚሉት አንዳርጋቸው እንዳይታወቅ የሙስሊም ቆብ ለብሶ ይዞራል። ታጋይ እኮ ሰው መስበክ እንጂ መደበቅና ከሰው መራቅ ኩራት ነው ወይስ ምንድነው ይሉ ነበር፡

አንዳርጋቸው ይባስ ብሎ አብዛኛውን ጊዜ የሚዝናናውና የሚውለው ከተሰፋዬ ገብረአብ ጋር ሆነ። ራሽኑ ከያረጋል ኢማምና ከአለበል አማረ ጋር ሲጣላ እቃውን ይዞ ጠቅልሎ ከተስፋዬ ገብረአብ ቤት መኖር ጀመረ። አቶ አንዳርጋቸው ያሳለፋቸውን ተከታዮቹን ኢትዮጵያውያንን ንቀት ካልሆነ ተስፋየ “ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት” መሆኑን በደምብ ያውቃል።ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕቢያ መረጃ መሆኑን ያውቃል። ታዲያ አብሮ መኖር ምነድነው?

የቆየ ጓደኝነት ኖራቸውም እንኳ የትግል መሪ ተራ ታጋይ ቢሆንም ለሀገር እና ለወገን ሲባል እንኳን ጓደኛን የወለዱትን ልጅና ሚስት ባጠቃላኢ ቤተሰብ እየተኙ እርግፍ አድርጎ መተው ያስፈልጋል።

ተስፋዬ ገብረአብ ታዲያ የግንቦት 7ን ምስጢር ከአንዳርጋቸው እየለቀመ ጠዋት ጠዋት ለሻዕቢያ መረጃ ቢሮ ማድረስ ስራው ነው።እኛ ተስፋየን ስናገኘው በጥንቃቄ ነው። ኢትዮጵያውያኖችን ሲቀርብ  የመጀመሪያ ወሬው ስ ኤርትራ ያለህን አመለካከት ለማወቅ ይጥራል። ለዚገህም ተስፋዬ ወሬ ሲያወራ እራሱን ኢትዮጵያዊ አድርጎ እኛ አገር እንደዚህ እንደዚህ ነው፤ እዚህ አገር ግን እንዲህ እንዲህ ነው፤ እያለ፤ አስመራ ውስጥ ደስተኛ እንዳልሆነ ኤርትራውያንንም እንዳማይፈልጋቸው እያማረረና እያጣጣለ ነው ወሬ የሚጀምረው።


ሁለተኛም ስያወራ ስለ እነ ስየ ውሎና ሁኔታ እንጂ ስለ እነ መለስ ወይንም በረከት እና ስብሓት ምንም ትዝ አይሉትም። እነ ስዬ የተሳሳቱተን ተገንዝበው ወደ ህዝብ ጎራ መቀላቀላቸው ለሻዕቢያ በጣም ቆጭቷቸዋል። እና ኢህ ነገር በጣም ኢገርመኝ ነበር።ምክንያቱም ከፖለቲካ ተገልለው መኖር ለጀመሩት ግለሰቦች ሻዕቢያ ለምን ቦታ ሰጥቶ ወሬ ያወራል በሚል ይገርመኝ ነበር። ታዲያ ይህ ጉዳይ ወደ 1098 አጋማሽና መጨረሻዎቹ እንድመለስና እንዳስታውስ አደረገኝ።

ከዚያ በፊትም በሗላም መሰለኝ፤ ሁላንም እንሰማው የነበረውን እነ መለስ በሓንሽ ደሴት ጦርነት አሳብበው መሳሪያ ለሻዕቢያ ሰጡ እና ነገር ግን እነ ሃየሎም ለምን ይሰጣል ተብሎ ተቃወሙ ፤ተጨቃጨቁ። እንዲሁም እን መለስ ለሻዕቢያ የካሳ ገንዘብ ሰጡ ተባለ። ታዲያ እነ ስየ፤ሓየሎም እና ቡድኖች “ኤርትራውያን ከኛ በላይ እየዘረፉ ፤እየተንደላቀቁ ነው፤ ከተገነጠሉ በሗላ ምን መብት አላቸው ብለው ጭቅጭቅ ውስጥ ገቡና በቡድን ተከፋፈሉ የሚል ወሬ ተሰማ። በሗላ ወሬው እውነት ሆኖ ብቅ ብሎ ከባድመ ጦርነት ወዲህ ጠርቶ ወጣ።


ያውም እነ ስየ እና ገብሩ ኤርትራን ስናስገነጥል ስርዓት አልተከተልንም፤ ስለዚህ ሁለት ወደብ ስንሰጥ አንደኛው ማለትም ዓሰብ ለኛ መቅረት አለበት ፤የኛ ሕጋዊነት መጠበቅ አለበት  ብለው ተከራከሩ። ህዝቡ ስለ ዓሰብ ባለቤትነቱ ተስፋ ቆርጦ ተናዶ ጉዜ ሲጠብቅ የነበረውን ቀዝቅዞ የነበረው የዓሰብ ወደብ ጥያቄ እንደገና አቀጣጠሉት። በጦርነቱም ወቅት ዓሰብን ከሻዕቢያ ነጥቆ መያዝ እንደሚችሉ በማያጠራጥር መልኩ አስመሰከሩ።

ቀስ ብለው ኢትዮጵያዊ አጀንዳ መያዛቸው አስመሰከሩ። ታዲያ ወደ ኢትዮጵያዊነት አጀንዳ መቀላቀላቸው ሻዕቢያዎችና ተስፋየ ገብረአብ እንደ ጉድ ይቆጠቁጣቸዋል። እነ ስየን እንድንጣላ የማይሰብኩትና የማያደርጉት ነገር የለም።ታዲያ ተስፋየ እላይ የተዘረዘሩት ነገሮች እራሱ ያነሳና ውይይይት ይጀምራል። አንድ የዋህ ከተገገኝ እውነት መስሎት የልቡን ይዘከዝካል፡ያች ሁሉ ጠዋት ሻዕቢያ ቢሮ ትደርሳለች።

ተስፋዬ እስካሁን ድረስ በግንቦት 7 ላይ ትርጉም ያለው ጉዳት ባያደርስም፤ ግንቦት7ን ለመቦርቦርና ለማዳከም በሻዕቢያ በኩል ታዝዞ በእንዳርጋቸው በኩል ገብቷል። አሜሪካ  እና አውሮጳ አንዳርጋቸው ሰራት አቋቁሞ እያዋጋ ነው እየተባለ እሱ ግን አስመራ ከተስፋዬ ቤት እየኖረ የደራሲው ማስታወሻ እየፃፈ ነበር። ይባስ ብሎ መጽሐፉ ግንቦት 7 ሊያሳትመው ነው የሚል ስንሰማ፤ እኔ በበኩሌ ግንቦት 7 አንዲህ ባለ ስራ ውስጥ እንደ ድርጅት እንዲህ ባለ ውሳኔ ገብቶ አያሳትምም ብየ ተከራክሬ ነበር። መሰንበት ደግ ነው፤እውነትም መጽሐፉን አሳትሞ ለገበያ አበቃው።”

ይሉና የጥቁር ጫካ ጸሐፊ፤ በመቀጥል እንዲህ ይላሉ፤

“ተስፋዬ አማራውና ኦሮሞው ሕብረተስብ ለማጨፋፍ የቡርቃ ዝምታ የሚለው መርዙን ሲጽፍ ብዙ ሰው ገረመው።ለመሆኑ የታሪክ ሰው ነው ፤ጋዜጠኛ ነው? ምንድ ነው? እኛ የምናውቀው በደርግ ጊዜ የደርግ ካድሬ ለመሆን የማርክሲስተን ትምህርት ጨርሶ  በወታደራዊ ክፍል መዝመቱን እና የተማረው ማርክሲሲዝም አንድ ወር እንኳ ሳያስተምርበት በወያነ ተማረከ። ወዲያውኑ በሻዕቢያና በወያኔ የዘር ብሔር ፖለቲካ “የጥላቻ ካድሬ” ተካው። ታሪክ መጥፎም ይሁን በጎ የባሎያው እንጂ በካድሬ መጻፍ ንቀት ነው።

ተስፋዬ ከወያኔ ሲባረር መጨረሻ የተባረረ እሱ ነው። ክንፈ ከሻዕቢያ ጋር ድሮ የነበረው ግንኙነት ባያውቅ ኖሮ “ውጣ” አይለውም ነበር።

ተስፋዬ የቡርቃ ዝምታ ሴራው እንዳሰበው ሳይሆን የተቆጨው ተስፋዬ እና በወቅቱ ከሗላው የነበሩ የሻዕቢያና የወያኔ ሰዎች አሁን ደግሞ በደራሲው ማስታወሻ ላይ አማራን ከአደሬ፤ከትግሬ ጋር ቂም እንዳለውና እንዲጨፋጨፍ የሚቀሰቅስ ፕሮፓጋንዳ አወጣ። አይ ግንቦት 7! አሁን እስቲ  እዚህ መጽሐፍ ላይ እጃቸውን ያስገቡ? ያውም ከተስፋዬ ጋር!

ግንቦት 7 የህን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማፋጀትና ለመበታተን የሻዕቢያ ወኪል ሆኖ ለ20 ዓመት የሰራውን አሁን በበለጠ እየገፋበት ያለውን ተስፋዬን ማስጠጋቱ ትርጉሙ ምንድነው?
ተስፋዬ በኢሳት ቴሌቪዥን እንግዳ ሆኖ በቀረበ ጊዜ ሲጠየቅ የመለሰው መልስ የሚገርም ነበር።  ትዳር አለህ ወይ?” ተብሎ  ሲጠየቅ “የለኝም” ብሎ ዋሸ።

ወገኖቼ ተስፋ ገብረአብ “ሚስት” አለው። የሁለት አመት ዕድሜ የሚቃረብ ልም አለው። የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ “የፀጥታ አማካሪ” የሆነው የአቶ ዮናስ የሚባለውን ባለስልጣን ልጅ አግብቶ አንድ ልጅ ወልዷል። ይህንን ምስጢር ኢትዮጵያውያኖች አንዳያውቁት ለመደበቅ ይሞክራል። የተስፋዬ አማች ማለትም አቶ ዮናስ ማለት የኢትኦጵያውያን ተቃዋሚዎች ከሚያሽከረክሩት ባለስልጣኖች አንዱ ነው። ሰውየው ከእነ ኮሎኔል ፍጹም የበለጠ ለኢሳያስ ታማኝ ነው። ግማሽ ቢወሮውም “ቤተ መንግስት ውስጥ ነው”።”
ሲሉ ጥቁር ጫካ ጸሓፊ የተስፋዬ ገብረአብ ሰላይነትና የደበቀውን ሚስጢር በማያሻማ መረጃ አቅርበውልናል።

በጣም የገረመኝ ግን ይህ “ጥቁር አሞራው ሙሴ” ኢሕአፓዎች የኮለኔል መንግስቱን መጽሐፍ አባዝተው በኢንተርኔተር መለቀቁን አንጀቴ አረረ መከሰስ አለባቸው ከሚሉት ጋር ተጨምሮ ሲያጫፍር የራሱን መጽሐፍ “ያውም ከመታተሙ በፊት” የኢትዮ-ሚዲያው ባለቤት አብርሃ በላይ  የተስፋየን መጽሐፍ ስካን አድርጎ በኦን ላይን ለሕዝብ በነፃ ሲበትነው፤ጠበቃው አለማዮህ ገብረማርያምም ሆነ እራሱ ተስፋዬ ገብረአብ ይሁን የጋዜጠኞች ተጠሪ ነኝ የሚሉን  ድምጻቸው ለብዙ አመት ከሚዲያ ተሰውሮ የነበሩት አቶ ክፍሌ ሙላት እና መሰሎቻቸው  ያኔ  ምንም የክስ ድምፅ ወይንም አሁን ስለፕሬስ መብት እና ባለቤትነት መብት… ወዘተ.. ወዘተ….እንደሚጽፉት ቅሬታ በአብርሃ በላይ ሳያሰሙ ‘ዛሬ ኢሕአፓዎች በመንግስቱ መጽሐፍ ላይ አብርሃ የሰራውን ተመሳሳይ ድርጊት ሲፈጽም ኢሕፓን “አይንህ ላፈር” እያሉ በ ሖ ሖ!! መጮህ  ምክንያቱ ምን ይሆን? ጋዜጠኞች እና የሕግ ጠበቃዎች እንዲህ ባለ የቡድንተኛነት እና የወገንተኛነት ጨዋታ ውስጥ ሲዘፈቁ ማየት ትንሽ አያፍሩም? አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ editor www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com   









_