Tuesday, July 19, 2011

በማይጨው ጦርነት ያፈርከውስ አንተና ባንዳዎች! (ለዶ/ር ብርሀኑ ነጋ መልስ) ጌታቸው ረዳ

 በማይጨው ጦርነት ያፈርከውስ አንተና ባንዳዎች!

(ለዶ/ር ብርሀኑ ነጋ መልስ)
ጌታቸው ረዳ
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከቅንጅት መፍረስ ጀምሮ የድርጅትም ሆነ የግሉ በሕዝብ ፊት የሚጽፋቸውም ሆነ የሚናገራቸው ነገሮች እርስ በርሳቸው የሚጣረዙ እንደሆኑ ልብ ብላችሁ የተከታተላችሁት ዜጐች የምታውቁት ጉዳይ ስለሆነ ዝርዝር ውስጥ አልገባም (ዝርዝሩን ለሚፈልግ ስለ ብርሃኑ የጻፍኳቸው ጽሑፎች በዚህ በኢትዮጵያ ሰማይ ድረግጽ ፈልጎ ማንበብ ነው።

ሰሞኑን እንደተከታተላችሁት የግንቦት 7 መሪው ብርሀኑ ነጋ እና በስተእርጅና ከኦነግ ጋር አዲስ ፍቅር የያዘው መሆኑን የገለጸልን ሌላው ዶ/ር ደግሞ ጌታቸው በጋሻው አብረው ከኦነጐች ጋር በየቦታው በመዞር በዓለም ውስጥ አሉ በሚባሉት ውድ ሽቶዎች (ርፉም/ኮለን) ታጥቦ የማይለቀውን የኦነግን ክርፋት ሸፋፍኖ “ስጋኹ ወደሙ” ሚያቆርብ ቄስ ይመስል በየአዳራሹ “እንደምን ዋለችሁ?” በማለት የኦነግ ማንነት በመካብ ኢትዮጵያውያኖችን “በባዶ እጅ ቆመው የሚፈክሩ ባዶ እጅ ፎካሪዎች!!!!!” በማለት የኢትዮጵያን ልጆች ሲዘልፍ ኦነግን ሲያሞግስ አድምጠናል። “ቆሞ ባዶ እጅ ፎካሪ” ተብሎ በጌታቸው በጋሻው አየተዘለፈ ያለው ኢትዮጵያዊ እኮ ጌታቸው በጋሻው ዘንግቶት እንደሆን አንጂ  “ጠመንጃ ይዞ አርባ ዓመት ሙሉ የባዶ እጅ ፈካሪዎችን አገር ለመማረክ አንዴ አስመራ እንዴ ኬኒያ አንዴ ሶመሌ፤ አንዴ ጫካ ውስጥ ሲርመሰመሱ የመሸባቸው የጌታቸው በጋሻው አርበኞች የኦነግ መሪዎች ጠመንጃቸው “ባዶ እጁ ለቆመው ፎካሪ” አስረክበው በመፈርጠጥ “አስመራ፤ሜኔሶታ እና ስዊድን” የመሸጉ መሆናቸው ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው ማወቅ አለብህ።

ካወቅከው ደግሞ “ወገቤ ቁርጥማት ይዞኛል” ካላልክ በስተቀር እነሆ ሜዳው እነሆ ፈረሱ ኦነግን በመምራትም ሆነ በማማከር እና በማመስገን ከኢሳያስ አፈወርቂ እሻላለሁ ካልክ ጠበንጃቸውን ጥለው በመፈርጠጥ ክራባት አስረው ያሜሪካ ባቀላባ እየገመጡ በየዳራሹ ከብርሃኑ ነጋ ጋር በጉራ የሚያደነቁሩንን አርበኞችህ ኦነጎችን እንድትመራቸው እና የደነቆረው ጀሮአችንም እረፍት ያገኝ ዘንድ” ኦነጎችህ ይዘህ እሺ ካሉህ እንደገና ኢትዮጵያ ውስጥ ኼደው “ነፍጥ አልባ፤ሕዝብ አልባ ባዶ እጃቸው ቆመው የሚፈክሩ” የምትላቸውን ኢትዮጵያውያኖች  እንዲሞክሯቸው እንድትመራቸው ጥሪያችንን እናስተላልፍልሃለን። ቢሞክሩትስ ቢሆን ያው አንተ እንዳልከው “ደግሞ ደጋግሞ የማይሰራ ነገር በዚህ አገር ምን እንደሚባል አንተ እና ኦነጐችህ ታውቁታላችሁ አይደል?” ፕፍ! ዋይ አነ ጓል ሓጎስ! ትል ነበር ወላጅ እናቴ እንዲህ ያሉት የከረፉ ጉረኞችን ወፍጮ ቤት እህል ስታስፈጭ የሚደነፉ ሰዎች ስትሰማ!
አሁን “በቀላሉ ጡሮታ አልወጣም” ወደ የሚለንን “የተራራ ተፈላሳፊው” ወደ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንመለስ። ሰሞኑን አርሊነግተን- ቨርጂኒያ የሚቀጥለው ገበያቸው ሚውለው ደግሞ ዋሺነግተን ዲሲ ልንዞር ነው እያሉ ነው። ኦነግን ለማሻሻጥ እንደ ‘ማጂላን’ ዓለም ሙሉ ሊዞሩ ነው ማለት ነው። መዞር የማይቻላቸው “ባዶ እጃቸውን ቆመው በሚፎክሩ የፎካሪዎች አገር በተባለችዋ ኢትዮጵያ ብቻ ነው መዞር የማይችሉት እንጂ ሁሉም ቦታ ይዞራሉ! ”ባይችሉም ወኪላቸው እስክንድር ደስታ የተባለ የነ አረጋሽ አዳነ ዛሬ ደግሞ የነ ኦነጐች እና የነ ኦብነጐች አድማቂ ኮሜንታተር ወደ መሆን እየቃጣው እያለው የድሮው የሚኒሊክ መጽሔት አዘጋጁ እስክንድር ሊያሻሽጥላቸው ዝግጁ ነውና ብዙም የሚጨነቁ አልመሰለኝም። ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውም እስክንድር ነጋን የኦሪት ራዕይ የሚያይ ነብይ አስመስሎ በምሳሌ ሲመስለው አድምጠናል። ሃሎ! ሃሎ! አጼ ሚኒሊክ በምትክዎ ሰዎቹ ገብተዋል፤እያደመጡኝ ነው?!
40 ዓመት በስብሶ የከረፋ የኦነግ ፖለቲካና የሻዕቢያ ሴራ ለመሸጥ ገዢን ለማፈላለግ ከሚንደፋደፉት “የ1983ቱ የወያኔ ሁለተኛ ዙር አስፈጻሚ ቡድን” የሚመስሉ ጥቂት ሰዎች መካካል ብርሃኑ ነጋ ነው። ብርሃኑ በቨርጂና አርሊነግተን ውስጥ ስለ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊነት ምንነት ሲጎነታትል አድምጠነዋል። ‘ዛሬ..”ይላል ብርሃኑ ነጋ ንግግሩን ሲጀምር፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ሚያሰኘንን እና ማንነታችንን ልጎነታትል ነው የመጣሁት፡ ሲል ይጀምርና ታሪካችንን ማንነታችንን ከሚያወቀው በላይ አወቅሁ ብሎ መጎንተል ብቻ ሳይሆን ሲዘልፈን ዋለ። ፈረንጅን የዋህ እና ቅናት እና ምቀኝነት የሌለው ፍጡር አስመስሎ (ያውም በቅናትና በምቀኝነት በጥላቻ እና በቁሳዊ ውድድር መሪዎቻቸውን እና ዜጎቻቸውን ግጠው ጨርሰው የሌላውን ዓለም ሕዝብ የሚጨፈጭፉትን እኩይ ፍጡራንን እኮ ነው በማወዳደር የሚዘልፈን) እያሞጋገሰ ኢትዮጵያዊነት ባሕሪን ግን ያበሻቀጠበትን እና ሌሎችን የመሳሰሉ በክፍል ሁለት ሐተታየ በሚቀጥለው ሳምንት እመለስባቸዋለሁ።
ለዛሬ ግን የማይጨውን ጦርነት “ያፈርንበት ጦርነት” በማለት በማያወቀው ታሪክ ወይንም ኦነግን ለማስደሰት ወይንም ሌላ መልእክት ለማካሄድ ይሁን መላ ቅጡ በማይታወቅ ሁኔታ አባት አርበኞቻችንና በኩራት የታገሉለትን ጦርነት “ያፈርንበት ጦርነት” ሲል የተሳለቀበትን የማይጨው ጦርነትን እንመለከታለን። የብርሃኑ ነጋ የምሁርነት ችሎታው የት እንደሆነ ሳሰላስል አቶ አስተዋይ በቀለ የተባሉ ጸሐፊ አሲምባ ድረገጽ ላይ የጻፉትን አንብቤ ሙሉ ሌሊት ልቤ እስኪፈርስ ያሳቁኝን ጽሑፋቸው አስታወሰኝ እና እስኪ ላንባቢዎቼ ላካፍል አልኩኝ፡ ይኼውና አይ ምሁር ! የትነው የምትሄደው ሲሉት እንኳራሴን ልቆረጥ ነው’ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይቁረጠውና ምን አለበት ፀጉሬን ልስተካከል ነው ቢል እውነቱን ቢናገር ? ይሉና

እንደ ሙታን ያልነቃና ከብሔር/ብሔረሰብ ቁራኛ ያልተላቀቀ ድንባዣም ምሁር የሰለጠነና ያወቀ መስሎት እንደ ኋላ - ቀር የከሰል ባቡር ጥቁር ጢስ እየተፋ አገርን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ሰንደቅ ዓላማን ጥላሸት ይቀባል፡፡

እውነትም አይ ምሁር! ብረሃኑ ነጋ ንግገሩ የከፈተው በለመደበት አሽሙር ነው። እኛ እና እሱ የምንባባለውን ስለምንግባባ፤ሌላው አድማጭ ሰለ ምን እያወራ እንዳለ ላይገባው ይችል ይሆናል። ኢትዮጵያውያኖች ዲፈንሲቭ ናቸው፤ ታሪክ ነካሾች ናቸው፤ወደ ላ እንጂ ወደ ፊት መመለከት አያወቁም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ “ኮነተስትድ” ነው ወዘተ..ወዘተ ሲለን እና በማያውቀው ሲፈተፍት አዳራሽ ውስጥ የነበሩት ተጎንታዮቹ የማንጨብጨብ በሽታ ስላላቸው ሲጎነተሉም ያንጨበጭቡለት ነበሩ። እንኳን ታሪክ “አስሬ ዲሞክራሲ እያለ የሚያወራው የማይጨበጠው የማሞኝያ “Myth”ም ቢሆን “ኮንተስትድ” መሆኑን አላወቀውም። ይህ ሁሉ ሲጐነታትለን ብርሃኑ የረሳት እና ያላብራራት በርከት ያለ አሃዝ ያለው በውጭ  አገር የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሲሰደብም፤ሲጐነተልም አንገትህ ለመቁረጥ እየመጣሁብህ ነው ሲሉትም፤ሰንደቃላመውንም ሲሰድቡበት ያንጨበጭባል። በመዳፋቸው ሥር የተደበቀ ያልታወቀ የሚያሰጨብጨብ በሽታቸው ከምን የመነጨ እንደሆነ ብርሃኑ እዛቺው ደርሶ ለምን እናዳልነገርን አልገባኝም። አበሻ ተጠራጣሪና ምቀኛ ነው ይበለን እንጂ የዋህነቱን ከሚያንጨበጭቡለት “ገራ ገሮች” ለምን ማስተዋል እንደተሳነው አልገባኝም።

አፍ ይበሉበታል እንጂ ግፉ አይናገሩበትም” ይላሉ ወላጆቻችን። ብርሃኑ ነጋ እና የቺካጐ ኮሌጅ መምህር ጌታቸው በጋሻው ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊነትን ሲዘረጥጡ ሰንብተዋል። ብርሃኑ ነጋ እንኳን እና የማይጨው ጦርነት ለማወቅ ቀርቶ 14 ዓመት ሙሉ አፍንጫው ስር ተቀምጦ ዜጎች በሰቆቃ ሲያሰቃይ የነበረውን የወያኔ ሥርዓት  እንኳ ዕውቀት አልነበረውም። ወያኔ እስረኛን ቶርች/ሰቆቃ ሚፈጽም መንግሥት መሆኑን ገና ዛሬ እስር ቤት እንደ ገባሁ የሚሰቃዩ ሰዎች ሲጮሁ ከስየ አብርሃ ጋር ሆነን ክፍላችን ውስጥ ሳዳምጥ ነው ለመጀመሪያ ጊዜየ ነው ያወቅኩት” ሲል መጽሐፉ ውስጥ የጻፈ የወያኔ ማንንት የላወቀ የምሁር ደንቆሮ ከስንት ዓመት በፊት የተከናወነውን ስለ ማይጨው ጦርነት በማውራት “ያፈርንበት ጦርነት”- ሲል አወቅኩ ብሎ “ኢትዮጵያዊነትን” በመጎንተሉ እገዛ አድርግልን ያሉትን እገዛ ለማድረግ ሞክሯል። 

ዛሬም ሰሞኑነ ኦነግን በማሻሻጥ ረድፍ የተያዘው ዘመቻ ስንመለከት ሁለተኛ የወያኔ ዙር ታሪክ ለወደፊቱ የሚደገም ይመስላል። ትዝ ይላችሁ እንደሆነ በ1928 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ከወራሪው ኢጣሊያ ጋር በተደረገው ጦርነት ንጉሡ ከማይጨው ጦርነት በመሸሽ ሕዝብን ለጠላት አገርን ለውርደት አጋልጠው ሰጥተዋታል፤ በታሪካችን ከጦርነት አውድማ የሸሸ መሪ ማየት የመጀመሪያው ንጉሥ ናቸው በማለት ከእርሱ በፊት የጣሊያን ፕሮፓጋንዳ አራጋቢዎችና ሌሎችም ለየግል ምክንያታቸው ውዥምብር ሲነዙ የነበሩትንም ተመሳሳይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያደርጉ ተደምጧል። ታሪኩ ግን ሐቅ ሆኖ መመዝገብ አስፈላጊ ስለሆነ፤ ንጉሡ የተሳተፉበትን ጦርነት በሌሎች ወገኖች በኩል የተዘገቡትን የታሪክ ሰነዶች አፈላልጎ ማንበብ ነው። በመጪው መጽሐፌም ይህንኑ ስላካተተ በዛው መመለክት ነው። "ከማይጨው (የሰሜኑ) ጦርነት በፊት ንጉሡ ቆራሔ (ምሥራቅ) ላይ ከጣሊያን ጦር ጋር ገጥመው ድል ማድረጋቸውን እንደመነሻ አድርገን ጠላት በእግር ጦር አልሆንለት ሲል ጥቅምት 23 ቀን 1928 ዓ.ም. ቦምብና መትረየስ የጫኑ 20 አይሮፕላኖችን በማሰለፍ ቆራሄ ላይ ብዙ ጀግኖችን በአይሮፕላን ገድሏል። ከነሱ መሃል አገራቸውን ኢትዮጵያን ሲከላከሉ በውጊያ ላይ የሞቱት  ጀግና ግራዝማች በላ ደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሰማያት የማዕረግ ስም ለመሥጠት ጂጂጋ ተመልሰው በመሄድ የደጃዝማችነት ማዕረግ ሠጥተዋቸው ተመለሱ። ንጉሡ ከነፃነት በላም ለሟቹ ጀግና ለደጃዝማች አፈወርቅ ወልደሰማያት መታሰቢያ እንዲሆን ጂጂጋ ላይ ሐወልት አቆሙላቸው። ሐወልቱ ግን ወያኔዎች መንግሥት ሆነው ሥልጣን ከያዙ በበወቅቱ የወያኔ የፌደራሉ ፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ብልግና በተሞላበት አንደበት ሲዘልፍና ሲያበረታታ የነበረው ላ ወያኔን ከድቶ አሜሪካ አገር ጥገኝነት ጠይቆ ዛሬ የኦነግ ደጋፊ ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው ሐሰን አሊ” እና የሽግግሩ መንግሥት የጉባኤው አባሎች የነበሩ ሶማሌዎችም ኦሮሞዎችም አንዳንድ የደቡብ ሕዝቦች (የሃዲያ ተወካይ አቶ…መስቀሌ) እና የመሳሰሉ ተወካዮችም እየተፈራረቁ አዳራሹ ውስጥ የአገሪቱን ታሪክና የአገሪቱን ሰንደቃላማ "የነፍጠኛ የክርስቲያኖች ባንዴራ" “ይኽች ሰንደቃላማ በዓለም ፊት አዋርዳናለች” (አንድ በዕድሜ የሸመገሉ የኦሮ ተወላጅ ባስተርጓሚ እየተናገሩ ነበር እንዲህ ያሉት። ታሪኩን ለማየት ኢሳት ቲቪ የተባለው መገናኛከታሪክ ማሕደርበሚል ርዕስበዩ ቱብኢንተርኔት http://youtu.be/qJU_R8lEn5w ላይ የለጠፈውን በመክፈት ያድምጡ። ) እያሉ በመዝለፋና አፀያፊ ስላቅ በመሳለቅ በወያኔ ጋሻ ጃግሬነት ሲጋጋሉ የነበሩት በጫካ ደመነስ የሚጓዙ እነኚህ የዘመኑ የወያኔ ሶማሌዎችና ኦነጎች ለደጃዝማቹ የቆመውን ሐወልት በ1983 እንዲፈርስ አድርገዋል።





ይህ ፀረ ኢትዮጵያና ጸረ አርበኞች ዘመቻ የተሠራ አልበቃ ብሏቸው መሪያቸው መለስ ዜናዊ የኢትጵያን ሰንደቃላማ “ጨርቅ” እያለ “የነፍጠኞችን አሳፋሪ ተረት እና ታሪክ  የመላ አገሪቱ ሕዝቦች ታሪክ አድረገው ሲያቀርቡ…” እያለ መለስ ዜናዊ  ሲያሾፍ “የአክሱም ሐወልት ለወላይታው ምኑ ነው?” ብሎ በቀደደላቸው የአገር ማዋረድ ሴራ፤ ሶማሌዎቹ እና ኦሮሞወቹም ፓርላማ ተብየው ተሰብስበው ‘እነዚህ ጀግኖች አባቶቻችን አያቶቻችን የምትሏቸው የኔን አባቶችና አያቶቼን የገደሉ አይደሉምን?” እያሉ የአገሪቱን አንድነትና ደህንንት ከጠላት ጋር ተዋድቀው በመከራ የገነቡትን የኢትዮጵያ አርበኞችን ሲቦጭቁና ሲሰደቡ የፈቀደ እና በጦርነቱ ወቅት ጠላት ገድለው አገር እስከብረው የተሠውበት የጀግኖች ሐውልት ማስታወሻ እንዲፈርስ ተደረገበትን ታሪክ ስናስታውስ የዛሬውን የብርሃኑ ነጋ  በኩራት ብዙ ጀግና የተዋጋበትን የማይጨውን ጦርነትን “ያፈርነበት ጦርነት” በማለት የወላጆቻችን ገድል አንኳስሶታል።

አዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል መለስ ዜናዊ ጋር ታምራት ላይኔ ጋር ሆኖ ዊስኪ ሲያንቃርር እነ ታየ ወልደሰማያት እነ አሰፋ ማሩ እነ አበራ የማነ አብ እነ ፊታውራሪ ዶሪ እነ ፀጋየ ገብረመድህን ደብተራው….የመሳሰሉ ጀግኖች እስር ማጎርያ ቤት ጨለማ ውስጥ ሲሰቃዩ እሱ ክራባት አስሮ አምሮበት ሸራተን ሲዝናና ሙዚቃ አምሮት ሲወዛወዝ ከርሞ ዛሬ የማይጨው ጦርነትና ታሪካችነን ሲያንኳስሱብን ያዳመጠውን የዱርየዎች ዘለፋ እራሱን ሳያሳፍረው አሁን ጀግኖቻችንን አፈርንባቸው እያለ ያንኳስስ እንጂ የኢትዮጵያውያን ጀግኖች በማይጨው ጦርነት ላይ ተመብርክከው ሳይሆን ቆመው ነበር የሞቱት። መረጃውን “The rape of Ethiopia” 1936 by A J Barker published 1971 ስንመለከት ያለ አይሮፕላን በባዶ እግራቸው በእሾህ እና በጠጠር ድንጋይ እየተወጉ፤ ዛፍ ላይ ወጥተው የኤርትራውያን ባንዳዎችን እና ጣሊያኖችን አምባላጌ እና ባካባቢው በመትረየስ ያርበተበቱበትን የጀግኖች አንደበት እዚህ አስፈላጊ ስለሆነ ልጥቀስ እነሆ ተከታተሉኝ።

Massacre at Lake Ashenge ከሚለው እንጀምር “…As the causality rates soared and major battles continued to be lost, Ethiopian peasant spiders began to drift back to their villages. Haile Selassie was forced to launch a great attack, led by himself. From 7am to 8am Haile Selassie’s men kept up a furious onslaught brilliantly supported by the fire of a few machine guns and batteries they had.  The battle continued to sway backwards some of the Italian forward positions were over run. But, they were bombed by Regia Aeronautica and harassed by several thousand Azebo Gallas who swooped down like a voltures. When the Ethiopian worriers picked up their weapons to mrach  south towards Lake Ashange and Quaram, few of them has tested food for more than thirty-six hours. Italian bombers had prevented any supplies getting through to them by bombing and spraying poison anything which moved and by spraying the roads and tracks leading to Mai Chew. It was no longer a war for the Italian airmen-it was a game…it was a massacre…(une victoire de la civilisation ,pp 45). Indeed it was a massacre, when the evening closed in and the last of the planes flew back to Makalle, the plain of of Lake Ashange was strewn with thousands of corpses. ..”

ይልና ታሪክ ዘጋቢው ሲጽፍ ስለ አንድ ጀግና ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ በማይጨው እንደ ብርሃኑ ነጋ አገላለጽ ያፈርንበት ሳይሆን በክብር የኮራንበት ጀግንነታችን እንዲህ ሲል ታሪክ ጸሃፊው ይተነትናል “That evening, Haile Selassie sent a message to his wife: from five in the morning until seven in the evening our troops attacked the enemy’s strong positions, fighting without pause. We also took part in the action, and by the grace of God remain unharmed. Our chief and trusted soldiers are dead or wounded. Also our loses are heavy, the enemy too has been injured. The Guard fought magnificently and deserves every praise…”

The Negus had a good reason to be proud of his troops. One captured Ethiopian with bullet wound in the head who was interrogated by the Italians obviously had not long to live. But he faced his captures with dignity.

Who are you? He was asked
“THE COMMANDER OF A THOUSAND MEN”
why don’t you lie down on that stretcher? The Italians don’t do not harm their prisoners” 
“I PREFER TO DIE ON MY FEET. WE SWORE TO THE NEGUS THAT WE WOULD CAPTURE YOUR POSITIONS, OR DIE IN THE ATTEMPT. WE HAVE NOT WON, BUT WE HAVE DIED. LOOK!
The Ethiopian pointed to the valley littered with corpses.” (The Rape of Ethiopia 1936 A j.Barker)

እንግዲህ አስታውሉ፡ ባይሮፕላን ቦምብ እና ከሰማይ የሚረጭ መርዝ ምክንያት እየተጠቃን ባናሸንፍም ላገራችን እና ለንጉሳችን የገባነውን ቃል አክብረን መሞት ክብር ነውና በቁም እንጂ ተምበርክከን አንሞትም! ወሳንሳ ላይ ተጋድሜ አልሞትም እንደቆምክ በክብር እሰናበታለሁ! ያለውን የማይጨው  ጀግኖች ወላጆቻችን የገድል ታሪክ በውጭ ጸሐፍት ተጽፎ በኩራት ስታነቡ  ብርሃኑ ነጋ በጀግኖቻችን “አፍረናል” የሚል የቅጥረኛ ዝባዝንኬው ምንን ያመላክታችል? ተሸነፍን የሚል ከሆነም የመሸነፋችን ምክንያት ከላይ የሚታዩት የባንዳዎች ፎቶግራፋ እና ሰላዮች እንዲሁም ካይሮፕላን መርዝ እና አንድ ጊዜ 9፣ 15፣18 ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ባይሮፕላን ላይ የኤፕሪት ውሃ/መርዝ የሚረጭ መኪና ጭነው ሰፊ በሆነው አገር ላይ ሞትን ከሚያመጣ ከረቂቅ የዝናብ መርዝ ሲሸሽ በረሃብ ተጠቅቶ ጦርነት አድክሞት የሚጓዛው ጀግና መንገድ ላይ ጠብቀው ብልቱን ሲሰልቡትና ሲያርዱት የነበሩትን ለወራሪ ጣሊያን ያደሩ ኦሮሞዎች  ምክንያት መሆኑን ማወቅ ነበረበት።"የሰውን አገር ሊቀማ ነፃነት ገፍ ከመጣው የጋራ ጠላት ጋር ሲዋጋ ቆይቶ ድል ሁኖ ለሚመለስ ወገን እህል ውሃ ማቀበል ይኸውም ቢቀር መንገድ መርቶና ሸኝቶ መሰደድ ሲገባ ቁስለኛ ተሸክሞ በደከመ ጉልበቱ በተራበ አንጀቱ የሚጓዘውን ሠራዊት

በየቦታው እያደፈጠ መግደል ይቅርታ የማይሰጠው የጭካኔ እና አገርን የመክዳት ገበን/ወንጀል ነው።ታድያ ማፈር ያለበት ማን ነው? ከጠላት ጋር ያበረው አገሩን የወጋ ከሃዲ አይሁዳ ወይስ ሳይንበረከክ ቆሞ እየተዋጋ የሞተው? ከብርሃኑ ነጋ እና ምሁር ነኝ እያሉ ከሚለፋደዱት ሁሉ መልስ እንጠብቃለን።  

 እንደው ለነገሩ የ አፄ ሃይለስላሴ ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው ክቡር አቶ በሪሁን ከበደ እንዲህ ይላሉ “ይህንም የመሰለ ታላቅ ጦርነት የተደረገው የወታደርነት ክብር እንዳይዋረድና የኢትዮጵያም የዠግንንት ታሪክ እንዳያድፍ ለመጋደል ነበር እንጂ የድሉ አክሊል በጣሊያን እጅ የሆነው ጣሊያን በብሬቪና በቶሪኖ ፋብሪካ አቋቁማ መድፍ መመትረየስ ታንክና ቦምብ የጋዝ መርዝና አይሮፕላን በሠራ ጊዜ ነው። እንዲያው ለነገሩ ኢትዮጵያና ኢጣሊያ ጦርነት ካደረጉት ጀምሮ በማይጨው የተደረገውን የመሰለ ጦርነት ከቶ ተደርጐ አያውቅም ይባላል። …አንድ የጦር አይሮፕላን ሳይኖራት የገጠመቺው 7ወር ሙሉ የተዋጋችው በ7ኘው ወርም ድል ለመሆን የበቃችው በሠራዊት ብዛት በመሳሪያው ጥራት በሰማይ ላይ በሚወርደው በቦምብ ጉዳት ሳይሆን “በዓለም በተከለከለ የመርዝ ጢስ እንደዝናብ በማዝነቧ ነው። ይህንንም ጢስ ያዘነበችው  ጦርነት ለማድረግ በተሰለፈው ሠራዊት ብቻ ሳይሆን በሰላማዊ ሕዝብና ሳር ነጭተው ውሃ ተጐንጭተው በሚኖሩት የቀንድና የጋማ ከብቶች ጭምር ነው።የፈረንሳይን የሚያህል ትልቅ መንግሥት በጀርመን ወታደር ድል ሁና የተወረረችው በ63 ቀን ነው። ሌሎቹም አውሮፓ አገሮች የተወረሩት ከዚህ በአነሰ ጊዜ ነው። ይኸውም ጣልያን በኢትዮጵያ ላይ እንዳደረገችው የመርዝ ጢስ ሳይረጭባቸው ነው።”
ደ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህ ታሪክ ያውቀዋል? ያፈርንበት የማይጨው ጦርነት ምኑ ላይ ነው? ጀግንነት ቢወረስ (በወ/ሮ ሠናይት ሃይሌ) የተጻፈ መጽሐፍ ብርሃኑ ነጋ አንብቦት ይሆን? ወላጆቻችን የነገሩን ታሪክ ሌላ ብርሃኑ ነገ አርሊነግተን ድምጽ ማጉያ ይዞ ስለ ኦነጐች ደላላ ሆኖ በአሻሻጭ የሚዘላብደው የማንነታችን ጉንተላው ሌላ። እውነትም አይ ምሁር! እስኪ ልድገማችሁ በዚህ አስቄአችሁ ልሰናበት። አይ ምሁር ! የትነው የምትሄደው ሲሉት እንኳራሴን ልቆረጥ ነው’ ይላል፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ ይቁረጠውና ምን አለበት ፀጉሬን ልስተካከል ነው ቢል እውነቱን ቢናገር? አይ ምሁር! እውነትም አይ ምሁር! አመሰግናለሁ።ጌታቸው ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ getachre@aol.com