Sunday, March 27, 2011

ለዳዊት ዳባ

ከአዘጋጁ፡ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የሚለው በስሕተት ስለሆነ በስህተቱ ምትክ ዳዊት ዳባ ተብሎ ይነበብ>በዛው ሰሞን “አልጄ” የተባለ የሦስትዩሽ ድርጅት ጥምረት በኢትዩጵያዊነቱ የማያምን ውጪአዊ የሆነ ድርጅት ለአርባ ዓመት ብረት ታጥቆ ኢትዩጵያን ለማጥፋት የተሰለፈ እራሱን “ኦነግ” ብሎ ለሚጠራ ሕዝብን ለመበተን ማንኛውንም አስነዋሪ ድርጊት የፈጸመ ተራ የሽፍቶችና የፋሽስቶች መንጋ ለኢትዩጵያውያን የቀመመው መርዝ ተመልሶ እራሱን ሲበክለው ተከፋፍሎ በየፍርድ ቤቱ ሲጯጯሁና ሲጓተት ከርሞ ለይስሙላ አንድነት ፈጠርን ሲሏችሁ ሞኞቹ አልጄዎችና እነ ዳዊት የመሳሰሉ የተቃዋሚ አባል ቡድኖች ከመቸውም በላይ ደስተኞች ሆነናል በማለት ፕሮፓጋንዳችሁን ለሕዝብ አስነብባችሗል።

እስኪ ዛሬ ደግሞ “ትግሉን እየተካሄደበት በአለው መንፈስ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኞች ነን” በሚለው አቡጊዳ በተባለው መሰል ድረገጹ እንድናነብለት የለጠፈልንን የዳዊት ከበደን “ከመቼው በላይ” (ከመቼውም በላይ ሲል ማለት ከ20 ዓመት ሙሉ ከተደረጉት ትንቅንቅ ትግሎች የበለጠ ዛሬ አመርቂ ደስታ እንደተሰማው ነው እየገለጸልን ያለው ) ደስተኛነቱን የገለጸልንን እስኪ አንዳንዶቹን እንመርምራቸውና እውን “ከመቼውም በላይ ያስደሰተው ምን ይሆን?” ብለን አንድ ባንድ እንሂድባቸው።

“ካብ ክልተ ጥንሲ ከይትሕጎሲ” የሚለው የትግርኛ ምሳሌ ከዳዊት የደስታ ስሜት አንድ ሆኖብኝ ነው ምሳሌው ያስታወሰኝ (እንዳትደሰቺ ከሁለት ሰው አንድ ጽንስ አርግዢ። (ላለመሰደሰት ፍላጐት ካደረብሽ ከሁለት ሰው ባንድ ቀን አርግዢና ‘የኔ ነው የኔ ነው’ ብጥብጡ ራስ ምታት ይሆንብሻል ማለት ነው።- ናይት ሜየር የሚሉት ፈረንጆቹ ማለት ነው)ነገሩ ሳስበው፤ ዳዊት በተጠቀሰው ርዕስ ተሞርኩዞ ያስተላለፈው እንድምታ ስለ ኦሮሞ ነፃ አውጪ አንድነት ከመቸውም ቢሆን ተደሰቱ ሲለን፤ባንድ በኩል ደግሞ ትግሉን አቅጣጫ የማስያዝ ድፍረት እንዲኖረው ያስገነዝባል። ስለ ኦኖጎቹ ግልጽ ሲሆን ስለ ትግሉ አቅጣጫ ማስያዝ ሲናገር አዲስትዋን ኢትዩጵያን “ለመውለድ” ይመስለኛል።ብሩህ ተስፋ፤ ሰላም፤ ከዘረኛነት የጸዳች ጠንካራና አንድነት የሰፈነባት ኢትዩጵያ እንድትረገዝ ከተፈለገ << እንዴ?>> እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል? ኦንግ ነው አዋላጁ ወይስ ኢትዩጵያውያን? የሚል ጥያቄ ያስጭራል። ኦነግ ኢትዩጵያዊ ነኝ ሲል አልተደመጠም፤አልተነበበም ፤አላወጅም። ታዲያ ሁለት ተቃራኒ ሃይላት አንዱ አፍራሽ አንዱ ገምቢ በሆነበት ወቅት “ኦነግ” ና “ኢትዩጵያውያን” ነን የሚሉ ቡድኖች ሲቀላቀሉ አገሪቱ የምታረግዘው ጉድ ምን፡ይሆን? መጪው ዘመን የሚያጠላብንን <<ፍራቻ ወይ እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት ያላቸው የድርጅት ሰዎች ባሁኑ ሰዓት ሕዝብን ቢያወያዩ የሚማሩበት ይሆናል።>> ይለናል ወንድሜ አቶ ዳዊት ።

ወንድሜ ዳዊትን ለመጠየቅ ከራሱ ምስክርንት ልነሳ።

(1ኛ) <<የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት አመራሮች የነበረባቸውን ውስጣዊ ችግር ላይ መፍትሄ ሰርተው በአንድ ሆነው ለመታገል ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ችግሮቻቸው ላይ መፍትሄ ሰርተው በአንድ መቆማቸው ብቻ ሳይሆን አቋማቸውን አለዝበው ከሌሎች ኢትዩጵያዊ ድርጅቶች ጋር ትግላቸውን ማቀናበር ጀምረዋል።>> የሚለው ዳዊት ማስረጃው የት አገኘው? “በኦነግና በኢትዩጵያዊ ቡድኖች በአንድ ቆመው ለመታገል ስምምነትና እንቅስቃሴው ኦነግ አቋሙን “ማለዘቡ” የምትጠራጠሩ ሰዎች ፍራቻችሁ እና እርግጠኛ ያልሆናችሁ “ፈሪዎችና ተጠራጣሪዎች” ሕዝቡን ብትጠይቁ ትማሩበታላችሁ ይለናል፡ ታዲያ ሕዘብ የሚለው አድራሻ የት እንደሚገኝ ባላወቅም ወደ ሕዝብ ከመሄዴ በፊት ዳዊት እንዲመልስልኝ የምፈልገው “በየትኛው የኦነጎች መግለጫ ነው አቋሜን አለዝቤአለሁ ያለው?” ለምን እንዋሻለን? እንዳንዋሽ በሕዝብ ስም ማሃላ ገብተናልኮ! እኔ የማውቀው የኔ እህት ጠላና ጠጅ ወይንም ቅራሪ እቤታችን ስትጠምቅ ኰምጠጥ ሲል እናቴ እህቴን ምነው አስኰመጠጥሺው? እንዲለዝብ ማር/ሱካር አስልሺው ወይንም ድፍድፍ ጨምሪበት በማለት የኰመጠጠው ጠጅ/ጠላ/ቅራሪ ለዘብ እንዲል ታደርገው ነበር። ሲለዝብ ግን ለቅምሻ ለዘብ ብሎ በማርነቱ ምላስን ያሞኝ እንጂ ኮምጣጣነቱ መቼም ቢሆን አሁንም አንጀት ውስጥ ሲገባ ኮምጣጤ መሆኑን አይተወውም።ስለዚህ አቶ ዳዊት በየትኛው መንገድና ትርጉም ነው ኦነጎች ለዘብ ብለዋልና እቀፍዋቸው እያለን ያለው? እኔን ካላመናችሁ ሕዘቡን ጠይቁት ከሕዝቡ ትማራላችሁ ይለናል። በድርጅት ውስጥ የግድ አልታቀፍክም ካልተባልኩ በስተቀር “ሕዝብ” ከሰሩት የድምር ቀመር አንዱ’ኮ እኔ ነኝ።ይህ ከሆነ ኦነግ መለወጥ ቀርቶ ለዘብተኛ ሆኛለሁ ሲል አልሰማሁም አላነበብኩም ለዘብተኛ የሚባሉ ምንና ምን አቋማቸው እንደሆኑ ዘርዝሮ አልነገረንም፤አላወጀም። ለዘብተኛ ለመሆኑ ምንድ ነው ትርጉሙ?

ኦነግ በጥሪው ወረቀት ያስነበበን <<ድል ለኦሮሞ ሕዘብ>> እንጂ ለኢትዩጵያ ሕዝብ ሲል አልተደመጠም። ዳዊትም የሚነግረንን የኦነግ ለዘብተኛነት በይበልጥ ቢያብራራልን በተሻለ ነበር። ከዓይን የሚፈጥን ከውሃ የሚቀጥን የለም ይላሉ ትግሬዎች፤ ስለ ኦነግ ለዘብተኛነት ለኢትዩጵያዊነት ምን እርባና እንዳለው ባይገልጽልንም እንዲህ ዓይነት ፈጣን የሆነ ፕሮፓጋንዳ ከምናይበት “ፈጣን ዓይን” የፈጠነ ይመስለኛል። ከምናይበት ዓይን የፈጠነ ነገር ደግሞ ማየት ስለማንችለው ሳይታየን “ይሄውና ቆሞ አይታይችሁም?” ቢለን ዓረቦቹ “ስሒር” ወይንም የእኛኑ ግዕዝ “ምትሐት” የሚባለው ድግምት ሊደገምብን የተከጀለብን ይመስለኛል።

ወንድሜ ዳዊት ስለ አንድነት ፓርቲ አመራሮች ባንድነት መቆም ተስፋ ማድረጉ የራሱ ስሜት በመሆኑ ከመቼውም በላይ ከተደሰተ እንኳን ደስ ያለህ እለዋለሁ።( እናቴ “ሳሪሃ ማሪሃ” የምትለው ዓይነት “ነገር ሳላበዛ” ማለቴ ነው)። ኢሳት ስለሚባለው በተቃወሚ ግለሰዎች የተቋቋመ አዲስ የህዋ/ሳተላይት የቴሌቪዥን ትግሉ ላይ ያበረከተው አስተዋጽኦ ሊኖር የሚችል ቢሆንም “በመለኪያነቱ” መለኪያ እና ተወዳዳሪ እንደሌለው ወንድሜ አቶ ዳዊት ከበደ አስነብቦናል። እኔ በዚህ በኩል “ሳሪሃ ማሪሃ” ሳላበዛ ባጭር ማርኛ የምገልጽበት ቃላት ያለኝ ቢሆንም “በእንተ ሞጐጐ አንጭዋ ትሕለፍ” (ምጣድ ላለመስበር ዱላ ሳልሰነዝርባት አይጧ አንዳሻት መንገዷን በኩራት ትቀጥል ነው) የሚለው የትግርኛው ብሂል ተገንዝቤ በጣቢያውን የተቀላቀሉ አንዳንድ ዜጎችን ላለመንካት ስል ተቆጥቤ “ወዲህ ቢሉት አራት ወዲያ ቢሉት አራት” የሚል ከየት እንደመጣ የማይታወቅ ሳይንሳዊ አነጋገር አለ! የሚሉትን ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እኛ ትግሬዎች “ወጮ ተገልበጥካዩ ወጮ” “ወጮ ቢገለብጡት ወጮ” የምንለው ዓይነት ነው “ኢሳት” የሆነብኝ።

ጣቢያው ደግሞ ደጋግሞ የሚጋብዛቸው የክብር እንግዶቹ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የትግልና የአገር ላገር የኡደት (ዙረት ልበለው?) ጓደኞች የሆኑት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግምባር አዛውንቶችን ነው። አዛውንቶቹ በተከታታይ ያስተላለፉት መልክት በጣም ነዋራ እና ስድ የሆኑ ያልታረሙ አነጋገሮችን በኢትዩጵያ ታሪክ፤ባሕል፤ ደምብ፤ ትውልዶችና በነገሥታቶቿ ላይ ትንሽ ሳይሸማቀቁ የስድብ ውርጅብኝ ሲያወርዱ ነበር የተደመጡት። ከዕድሜአቸው አኳያ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሳይኖራቸው የዘለፋና የውሸት የክሕደት ምላሳቸው በኢትዩጵያ ሕዝብ ትውልድና ታሪክ ውጭ አገር ተጠልለው የሚሰነዝሩት አስነዋሪ ንግግር ጣቢያው ምንም ሳይሰማው ኢትዩጵያንና ታሪኳን እንዲዘረጥጡ ያለ ገደብ በመፍቀድ ወደ ኢትዩጵያ ማስተላለፉ የሚያሳዝን ስራ እንጂ ከመቸውም በበለጠ ተወዳዳሪነቱ የሚሞገስበት ስራው ምን እንደሆነ ለኔ አልታየኝም።

ለ19 ዓመት የተካሄደው ትግል ሳስተውለው በተለያዩ ዋሾች እንድንማረክ የተጠመደብንን ወጥመድ በማወቅ ይሁን ካለማወቅ ቀስ በቀስ ያንኑን የ1983ቱን የዋህንት እየደገምነው እንደሆነ ምልክቶች እየታየኝ ናቸው። እውነት እንድትደበቅ አስተዋጽኦ እያደረግን እኮ ነው። ብዙ ሕይወት ያጠፉትን እንደ መላዕክት እንዲታዩ ሽፋን እየሆንን እኮ ነው። ለምን? ከሰይጣኖች ጋር ፍቅር ይይዘናል? እንዴት እንገላገላቸው እንጂ መልሰው መላልሰው እንዲገድሉን እንዴት እንዘጋጅላቸው ይባላል? ጥርስ ለሌለው የማይናከስ ጯሂ ውሻ እንዴት እንምበርከክለት? ያኦነግ መሪዎች በውሸት ዓለም በዚህ ውጭ አገር ተጠልለው ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ሲያስተምሩ እንጂ እራሳቸው እንደ መሪ ጫካ ሄደው እንደጡበት ለሚማግዱት የገበሬው የኦሮሞ ልጅ ትግሉን እያሳዩት በግምባር ተሰልፈው ሲሞቱ አላየናቸውም። የሚኖሩት በውሸት ዓለም ለሥጋቸው ተስግብግበው ነው እየኖሩ ያሉት። ሕዝብን በሃሰት እየሰበከ እራሱ እሳት ውስጥ ሳይከት “የ ኦሮሞ ነፃ አውጪ ተወካይ እና መሪ ነኝ ሲለን” ሃሳዊ መሲህን ማክበር እኮ በባህላችንና በሃይማኖታችን ያስነውራል? ለፍቅር የማይገዙ ጥላቻን መመሪያቸው የሚያደርጉ፤አገራችን የዋሾች ደሴት እንደትሆን በፍጥነት እንዲራቡ እያደረግን ነው። አሳዘኝ!

አሁንም ክቡር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ወዳሉት ድንቅ አባባል ልመልሳችሁ። <<…ኢትዩጵያ የእውነት አገር አልሆነችም፤ከሀምሳ ዓመታት በፊት አንድ የሕንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በዕጣ የንግግር ውድድር ላይ <<በሕንድ አገር ውስጥ በፍቅር መውደቅ>> የሚል የመነጋገሪያ ርዕስ ደረሰው፤ በሕንድ በዚያን ጊዜ ፍቅር የሚባል ነገር አይታወቅም ነበርና የሚናገረው ቢጠፋው “ፍቅር ከያዛችሁ ከሕንድ አገር ጥፉ!>> አለ። እኔ ግን መጥፋት አልሰብክም፤እውነትን እስክታገኙ ድረስ አትረፉ! ቆፍሩ! እውነት ነፃ ያወጣችሗል ተብሏልና>> ይላሉ።

ኦነጎች እስካሁን ድረስ ለኢትዩጵያ ፍቅርም አክብሮትም የላቸውም። ከኢትዩጵያ ጋር ፍቅር የያዛችሁ ከኦሮሞ ምድር ውጡ የሚሉት ለኛ ብቻ ሳይሆን ኦሮሞውቹንም ጭምር ነው። በፍቅር መውደቅ አያውቁምና “ ከኢትዩጵያ ጋር ፍቅር የያዛችሁ ሁሉ ከምድሪቱ ጥፉ” ነው የሚሉን። አይገባችሁም እንዴ!

ኦነጐች “ለዘብ” ያለ አቋም ይዘው መጥተዋል እያለን ያለው ጋዜጠኛው ወንድሜ አቶ ዳዊት ፤ ኦኖጎች ለዘብተኛ ብለው ይዘውት የመጡትና የመፍትሄ አቋም ብለው እርስ በርስ ካናከሳቸው አንደኛው “ለዘብተኛ” የተባለው ያልተውት አቓማቸው እኛኑን (በኦነጎች አባባል እኛ “አማራ አጐዎችና እኛ አጎብ ትግሬዎች (አቢሲኒያን ይሉናል”) ነፃ አንዲያወጡን (ከነጭ መሆን ወደ ጥቁር ኦሮሞነት እነሱ ኩሽ\ የሚሉትን ዜግነት) ለኛ “ለነጮቹ” የሚታገሉልን አንዱ ትግላቸውን ለወንድሜ ለዳዊት ላስነብበው ይሄውና፦ <<Genuine Ethiopian renaissance is the reversing of the negative 3000 years Abyssinization of the Cushites. Liberation of Agew-Amhara and Agew-Tigrai from this negative impact should be accompanied by the re-Cushitization movement; i.e the Oromo liberation movement should include the liberation of these two highly Abyssinized nations and to help them be re-Cushitized.>> ይሉናል ኦኖጎች። እንግዲህ እኛኑን አማራዎችና ትግሬዎች ከአቢሲኒያዊነት (አቢሲኒያ ማለት በኦኖጎች ኢትዩጵያ ላለማለት የሚጠቀሙበት በኛ የማይታወቅ ጌቶቻቸው ያስተማሯቸው የተሰጠን ስም ነው) ወደ “re-Cushitized” ዜግነት ነፃ እንዲያወጡን ነው ብያንስ “ኮሎኒያሊስቶች” ከሚሉን ሌሎቹ የነሱ ቡድኖች በለዘብተኝነት የቀረበው አንደኛው ይህንን ይመስለላል።

ይህ ፋሺስታዊ እና የደነቆረ የወረበሎች ምጥቀት ስናስበው በጣም አስቂኝ ከመሆኑ የተነሳ “ቁቤ” የነደፉላቸው የውጭ ጌቶቻቸውና ተባባሪዎቻቸው ያሰተማሯቸውን “ኢትዩጵያውያን” <<ጥቁሮች>> አይደለንም ነው የሚሉት የሚለው ጊዜው ያለፈበት ውሸት ያስተጋቡበት ለዘብተኛ የተባለው አቋማቸው አንዱ ይሄ ነው። ይሄ ደግሞ በኛ እንደበት ብንናገረው ስለማይመቻቸው በጥቁር አሜሪካኖች መሪ በማልካም ኤክስ ኢትዩጵያ የጥቁር ሕዝቦች ተምሳሌት የተከበረ ሕዝብ መኖርያ መሆኗንና የኦኖጎችና የሻዕቢያ ጌቶች የሚዘላብዱትን በእኛ የተዘረጋው ስም አጥፊ ዘመቻ ውሸት መሆኑን ካንደበቱ ያለውን ላስነብባችሁ ልሰናበታችሁ።

<< So, I went through Khartoum to Addis Ababa, Ethiopia, which is a wonderful country. It has its problems, and it's still a wonderful country. Some of the most beautiful people I've seen are in Ethiopia and most intelligent and most dignified, right there in Ethiopia. You hear all kinds of propaganda about Ethiopia. But any time a person tries to tell you as they've told you and me, that Ethiopians don't think they're the same as we are, that's some of that man's manufacturing. He made that up ...They are just as friendly towards us as anybody else is." (G. Breitman; By any means Necessary,(London: 1985), p. 142 >> ጌታቸው ረዳ - ሳንሆዘ አሜሪካ። http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

getachre@aol.com