Friday, March 11, 2011

በአሰንዳቦ የክርስትያኖች ጥቃትና የአሜሪካው ድምፅ

በአሰንዳቦ የክርስትያኖች ጥቃትና የአሜሪካው ድምፅ

አይደር ከድር በጂማ ዩኒቨርሲቲ የእስልምና ኃይማኖት መምህር ነው። የአሜሪካ ድምፅ ራዲዩ የአማርኛው ክፍል ለቃለ መጠይቅ አቅርቦት ነበር። ጋዜጠኛው አዲሱ አበበ በከፋ ክፍለሃገር (በባንቱስታዎቹ መልካአ ምድር አጠራር “ክልል”) ጅማ አካባቢ አሰንዳቦ በተባለች ትንሽ ከተማ ሰሞኑን ቁጥራቸው “ከአንድ ሺህ በላይ” የሚገመቱ እስላሞች የተካፈሉበት በየገጠሩ ባሉት 28 የክርስትያን መኖሪያ ቤቶችና 59 አብያተ ቤተክርስትያናት ላይ “በጂሃድ” መልክ በማጥቃት ተግባር እንደተሳተፉ በውጭ አገር የዜና ዘጋቢዎች በኩል በርካታ ዘገባዎች የተሰራጩትን ዜናዎች አስመልክቶ የጂማ ዩኒቨርሲቲ የእስልምና መምህር የሆነውን አቶ አይደር ከድር ሁኔታው እንዲገልጽለት ለጥያቄ አቅርቦት ነበር። እኔ የገረመኝ የመምህሩ ክስ ነው። እዚህ አሜሪካን አገር ውስጥ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዩች የተቋቋሙ በየፓልቶኩ በክረስትና እና በኢትዩጵያ ታሪክ የዘላፋ ዘመቻ አለፍ ብሎም ዘረኝነት የተሞላበት ሲያናፍሱና ሲለዛብዱ የሚደመጡ ዋሾች የሚያጉረመርሙት ዓይንት በቪኦኤው በተለይም አዲሱ አበበን የአንድ በተክርስትያን ማህብር ቦርድ አባል መሆኑና ለሃይማኖቱ የሚያዳላ እያሉ የሚዘላብዱት ሙጃሃዲኖችና ጣሊባኖች የሚከስቱን የክስ ዓይነት ቅሬታ መምህሩም አብሮ ያንኑ ቪኦኤ ላይ ቅሬታውን/ክሱን አሰምቷል።

በአዲሱ አበባ የስልክ ጥሪ እንጀምር ፡ በመጀመሪያ አቶ አይደር ከድር በአድማጮች ስም አመሰግናለሁ።የዛው አካባቢ ኗሪ ነዎት፡ ከዚህ በፊትም ሕብረተሰቡን ለማረጋጋት ብዙ እንደሰሩ ሰምቻለሁ፡መምህርም ነዎት ማለትም የእስልምና ትምህርት እያስተማሩ እንደሆነ አቃለሁ፡ባካባቢው ያለው ሁኔታ ቢየስረዱን? አይደር፡ በመጀመሪያ ቪኦኤ ላይ ያለንን Comment ሁኔታ Churchቾቹ መቃጠሉን ብቻ ሳይሆን Churchቹ ለመቃጠሉ ምክንያት የሆነውንም balanace አድርጋችሁ መናገር አልቻላችሁም። Church ተቃጥሏል፤ለመቃጠሉ በዓይናችን አይተናል፡ይኼ ነገር ከተከሰተ ከሰማን ሄድን። እኔ በአይኔ ያየሁት “Church” ተብሎ ያለው የሰበካ ቦታ ተዘጋጅቶ ገዝተው ቦታውን …(?)የሚያደርጉበት ነው። ያው ተከልሎ ብዙ ነገር ተደርጎ ፤ ያን ያክል አይደለም፤ ግቢ ያለው እንደዚያ ዓይነት ነገር አይመስለኝም ። ስንሄድ ተቃጥሏል። አንድ ተቃጥሏል። “አሰንዳቦ” ከተማ ውስጥ ሦስተኛ ደግሞ ተቃጥሏል ግን እኔ በዓይኔ አላየሁም። ይሄ መሆን እንደሌለበትም ለሕዝቡ ተናግረናል ሸሆቹም ኢማሙም ተናግረዋል።…….(?) አቶ አይደር የሚለውን እስተኪ ዘርዘር አድርገን እንመልከት። <<ቪኦኤ ላይ ያለንን Comment ሁኔታ Churchቾቹ መቃጠሉን ብቻ ሳይሆን Churchቹ ለመቃጠሉ ምክንያት የሆነውንም balanace አድርጋችሁ መናገር አልቻላችሁም።>> አብያተ ክርስትያናት እና የክርስትያኖች መኖርያ ቤቶች ከአንድ ሺህ በላይ እስላሞች በጂሃድ መልክ የተካፈሉበት የማጥቃት ዘመቻ መምህር አይደር በአሜሪካ ድምፅ አዘጋጆች ላይ ቅሬታ ማሳደሩ ጥቃቱ የፈጸሙት እስላሞች ወደው ሳይሆን መጀመሪያ ለዚህ ሁሉ ሰበብ ጠብ አንሺዎች ክርስትያኖች ናቸው ለምን ሰበቡን አትዘግቡትም ይላል፡ “ምክንያቶቹ ክርስትያኖች ናቸው” ሲል “በምስክርነት” ጥቃቱ የአጸፋ እርምጃ ስለሆነ ሕጋዊነት እንዳለው ያረጋገጠ ይመስላል። ያውም ፈራ ተባ እያለ <<ከዚያ በሗላ ተናዶ የሰሩት ስራ ትክክል ነው አይደለም እሱ ሌላ ነገር ነው። >> የሚለውን ስትመለከቱ “ትክክል አይደለም” ብሎ ማለት እንኳ መድፈር አቅቶት “ፈራ ተባ ሲል” ክርክር ውስጥ የሚያስገባ “ማኒፒለሽን ቲኦሪ” ውስጥ ይጎተታል። አስገራሚ! አቶ አይደር ከድር በማስከተልም እንዲህ ሲል የራዲዩ ጣቢያው ዘጋቢዎችን ይኰንናቸዋል እንዲህ ይላል።

<<እናንተ ጋር ያለን (ቅሬታ)፤Cause የሆነው 1ኛ ስላልተናገራችሁ ካንድ ወገን ብቻ መቀበላችሁ 2ኛ ያጋነናችሁ ይመስለኛል።>> አዲሱ ጣልቃ ገብቶ “..ተቃጥሏል… (?)፡ የሚል የማይሰማ ድምፅ ሲጠይቅ ይሰማል፡ አቶ አይደር ከድር እንዲ ሲል ይቀጥላል፡

<<መቃጠሉ የሚያጠራጥር አይደለም፤አዎ ተቃጥሏል>> 1ኛ <<መቃጠሉ ግን ይህን ያክል ተቃጥሏል የሚል ግን የተጋነነ ነገር ይመስለኛል።>> 2ኛ <<ሁለተኛ “በክርስትያኑና በሙስሊሙ መካከል ጥላቻ እንዳለ ነው የገለጻችሁት>> ጣልቃ ገብቶ አዲስ አበበ ጥያቄውን እንዲህ ይላል፡

<ጥላቻ እንዳለ ገልጻችሗል ብለዋል፡ ይሄ እንዳለ በሪኮርድ ተቀርጾዋል? አድምጠዋል?>

<<አቶ አይደር ከድር፦አልተቀረጸም፤አልተገለጸም።>>

እንግዲህ አቶ አይደር የእስልምና ሃይማኖት አስተማሪ ነው፤ እስልምና ደግሞ ቁርአኑን ለማንበብ የአረቦች ቋንቋ ማወቅ ስለሚያስፈልግ ስለማላውቅ አንብቤው አላውቅምና “እውነትን” ማስተማር እንደሚገባ የሚያስተምር እንደሆነ ግን እገምታለሁ። ከሆነ መምህር አይደር ከድር ለምን “ባንድ ምላስ ሁለት ራስ” መናገር ፈለገ?

አዲስ አበበ በማከታተል እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፡ ተጋነዋል ያሉትም አድምጫለሁ፡ ምን ያህል ቤተክርስትያኖች እንደተቃጠሉ እርስዎ ሊገልጹልን ይችላሉ?

አቶ አይደር፡ <<ስንት እንደተቃጠለ ገጠርም አካባቢ ስለሆነ ስንት እንደተቃጠለ ማግኘት አልቻልኩም፡ግን እናንተ እንዳለችሁት የተጋነነ አይደለም። ምናልባት 10 ከአስር በላይ..። ከዚህ ውጪ Information ላይኖረኝ ይችላል።>> መረጃ የለኝም ካለ ሌለውን ተመልሶ አጋንናችሁታል ብሎ ሲያሳጣ/ሲከስ/ሲወቅስ ዜናችሁ ተጋኗል ሲል፤ለመጋነኑ መረጃው ይሁ ነው ብሎ መረጃ ካላመጣ “ተጋኗል” ብሎ መክስስ ሁኔታንና ራስን defense mechanism ውስጥ አስገብቶ minimization ጥቃቱን አቃሎ እንዲታይ ሽፋን ፍለጋ መግባት ነው። ባጭሩ “defense mechanism” ማለትም ‘መካድ”/Denial ውስጥ ለመከናነብ ፍለጋ ነው።

ዜናው የሚለው ይህ ጥቃት ሕብረተሰቡን ያካተተ ጥቃት ነው። አቶ ከድር እንዳለው በቤተሰብ ይነት የተነሳ ግጭት አይደልም። የሃይማኖት ግጭት ነው፤ ጥላቻ ነው! ክህደት ማለትም ፈረንጆቹ Denial የሚሉት defense mechanism የክህደት መንገድ Sigmund Freud Ytbalwe የተባለው አውሮጳዊ የስነ ኣእምሮ ሊቅ እንዲህ ያቀርበዋል “ in which a person is faced with a fact that is too uncomfortable to accept and rejects it instead, insisting that it is not true despite what may be overwhelming evidence.” አንድ ሰው ከእውነት ጋር ፊት ለፊት ሲገጥም፤ የማያጠራጥር መረጃ እያየም ቢሆን የፈለገው ይሁን ተቀባዩ ጭብጡ እንደጋሬጣ ስለሚወጋው እውነታውን ላለመቀበል አላምንበትም ሲል ይጋፈጣል።” አቶ አይደር የእስልምና ሃይማኖት መምህር ሆኖም ይህ እውነታ ላለመቀበል ተጋኗል ሲል እንደገና አልተጋነነም ሲል እውነታው እየተጋፈጠውም ቢሆን እንደገና ጥቃቱ ወደ ማሳነስ በመግባት minimization ወደ ሚሉት ክርክር ሲገባ ይደመጣል። minimization - admit the fact but deny its seriousness (a combination of denial and rationallization) ይህ ምን ማለት ነው፡-ድርጊቱን መፈጸሙ (ጸ/ላላ ብሎ ይነበብ) ማመን - የድርጊቱ ከባድነት ግን ማሳነስ” ማለት ነው። በክህደትና በማመን መሃል መዋዠቅ ማለት ነው። ይሄ ደግሞ ለተከሰተው ሁኔታ እጅግ በጣም በሳላ ሚዛን አይደለም። ይህ ምን ለማሳየት ነው? Projection የሚባል ነገር አለ። Projection ከውስጡ የጥፋቱን ከባድነት አምኖ ሃላፊነት ላለመቀበል መሸሽ ነው። ይህ ደግሞ ከላይ እንደተመለከታችሁት - ለጥቃቱ ሰበብ በአቶ አይደር ቃላት “cause”መነሻው ክርስትያኖች መስጊድ ግቢ (?) ሽንት ስለሸኑ ለጥቃቱ “cause”መነሻው ራሳቸው ስለሆኑ እሳለሙ ተናዶ የክርስትያኑን አጥቅቷል ነው የአይደር አባባል። ጭሱ ሳይሆን ሃላፊው እሳቱ ነው። እሳቱ ሳይሆን ሃላፊው ለኳሹ ነው cause ነው፡ causeዙ ደግሞ ክርስትያኑ ነው፡ አናዳጁ ክርስትያኑ ተናዳጁ እስላሙ ስለሆነ “ተከሰተ”። ነው ምመህር አይደር እያለን ያለው።

ሕብረተሰቡ ውስጥ ለ19 ዓመት እየተስፋፋ የመጣው የሃይማኖት እና የጐሳ ግጭት እንደዚህ ዓይነት ዲፌንሲቭ እና ክሕደት በአጠቃላይ በሕብረተሰቡ መንፈስ ውስጥ መኖር እንኳን ለሊቃውንት ለኛ ለተራ ዜጎችም ግጭቱ ቀላል እና ቤተሰባዊ እንዳልሆነ ማረጋገጥ አያቅትም። ፈረንጆቹ እንደሚሉት general existence of denial is fairly easy to verify, even for non-specialists መላት ነው።. ሌላው የገረመኝ የተዋህዶዎቹን ቤተ ጸሎት ልተወውና የፕሮተስታነቶቹ ቤተ ጸሎትም ምምህር አይደር ከድር እንዴት እንዳናናቀው ተመልከቱ ፤ እንዲህ ይላል፡ <<እኔ በአይኔ ያየሁት “Church” ተብሎ ያለው የሰበካ ቦታ ተዘጋጅቶ ገዝተው ቦታውን ጸሎት የሚያደርጉበት ነው። ያው ተከልሎ ብዙ ነገር ተደርጎ ፤ ያን ያክል አይደለም፤ ግቢ ያለው እንደዚያ ዓይነት ነገር አይመስለኝም >> እንዲህ ዓይነት አስበዋሪ ግምገማ ከአንድ የዩኒቨርሲቲ የሃይማኖት ምምህር አንደበት ሊወጣ የሚጠበቅ ነው”? ግቢ ስለሌለው ተቃጣለ የታበለው “Church” ተብሎ ያለ ያን ያክል አይደለም ማለት ምን ማለት ነው”? መስጊዶች ዛፍ የላቸውም፤ ግቢ የሌላቸው መስጊዶችም አሉ፤ ታዲያ ግቢ ስለሌላቸው ያን ያክል አይደለምና ቢቃጠልም “መስጊድ’ መባል የለበትም ማለት ይቻላል? ምንም ይሁን ምንም እነኚ ዜጎች ገዝተውም ይሁን ተከራይተው “ጸሎት የሚያደርሱበት ነው። ሲቃጠል እንደ ቤተክርስትያን አታስቡት ማለት ምን ይሆን ትርጉሙ?

ከዚህ በታች ያለውን የጅማ ዩኒቨርሲቲ የእስልምና ሃይማኖት ምምህር አቶ አይደር ከድር ያለውን ተመልከቱና ፍረዱ፡ እንዲህ ይላል። <<እናንተ! ይሄ ሊከሰት የሚችል ነው አብሮ የሚኖር ሕዝብ በቤተሰብ ጭቅጭቅ ይነሳል፤ በቤተሰብም አባት በልጅ መካከል ቅጭት ሊሆን ይችላል..ይሄ Exeptional እንጂ ሁሌም በሙሰሊሞችና በክርስትያኖች ያለ ልዩነት አይደለም።>> ጂማ ውስጥ በተከታታይ፤ ሐረር ውስጥ በተከታታይ እና ሌሎች ቦታዎች ለ19 ዓመት ሙሉ የተካሄዱ የጎሳ ግጭቶች ዝርዝር እንዘርዝር ቢባል ብዙ ጥራዝ መጽሐፍቶች የሚያስጽፍ ነው። መምህሩ minimization ወደ ሚባለው ጨዋታ ባይገቡ አዋቂነት ነው። በዚህ ድረገጽ ማለትም ኢትዩጵያን ሰማይ ድረ ገጽ ወደ ቀኝ በኩል በመጀመሪያ ረድፍ የተለጠፈው ጅማ ውስጥ በ1998 ዓ.ም በክርስትያኖች ላይ የተከሰተው ጥቃት የተቀረጸው አሰቃቂና አሳፋሪ ቪዲዩ ይመልከቱና (ከዚያ በፊት በርቀት ዘመን የተደረገው አሳፋሪ ስራ ሳናወሳ ማለት ነው፦የቅርቡ እንኳ በወያኔ አስተዳደር የተደረጉት ተከታታይ ጥቃቶችቹ ስንመለከታቸው) ጥቃቶቹ የቤተሰባዊ ግጭት ይመስላሉ? መምህረ ከድር Exeptional እንዳለው እንዲህ በቃላሉ Exeptional ተብሎ የሚገለጽ ነው? አላህ ይማራችሁ! አመሰግናለሁ ጌታቸው ረዳ “የኢትዩጵያን ሰማይ” ድረገጽ አዘጋጅ። ይድረስ ለጐጠኛው መምህር ጥቂት ቅጂዎች አሉ ለማንበብ የፈለጉ በ408 561 4836 ይደውሉ። http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

በአሰንዳቦ የክርስትያኖች ጥቃትና የአሜሪካው ድምፅ

በአሰንዳቦ የክርስትያኖች ጥቃትና የአሜሪካው ድምፅ