Thursday, April 26, 2012

በደም የተቀባ ከበሮ መደለቅ ያስነውራል!

ድረስ ለጎጠኛው መምህር (አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (this is diffrent book/story that is defferent than the Amharic indicated) (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com የካቲት11 የህ.ወ.ሓ.ት. Cosa Nostra ኮስታ ኖስትራ” የተመሠረተበት ወር ነው። ክላኖቹ የካቲትን በውሸት ከበሮ ያጅቡታል። ለዚህ አምዳችን ለመረጃ ማገናዘቢያ ያመች ዘንድ ሲዋሽ እየዋሸ መሆኑን ገጽታው በቀላሉ የሚጋለጠብት በየወያኔው መሪ ውሸት በመለስ ዜናዊ ንግግር ልጀምር። ባለፈው አንድ ወር ሆኖታል ካልተሳሳትኩ ወያኔ እራሱ “ነጋዴ ሌባ” ሆኖ መላ ቅጡን ያሳጣው የገበያ እና የምርት ምስቅልቅል ለማረጋጋት የአዲስ አበባ መስተዳድር እያለ የሚጠራው የነጋዴ እና የአምራች ክፍል ግንኙነት ሲተነትን ምን ያህል ከፍታዊ (ከፍታዊ ማለት በወያኔ ትርጉም ምን ማለት እንደሆነ ባላውቅም ጋዜጠኛው ከፍታዊ ይለዋል) እና ግልጽነት ምን ደረጃ ላይ ነው? እንዲሁም በጉዳዩ በቂ ጥናት እንደተረገ ነው በተደጋጋሚ የሚገልጸው…በዚህ ያለዎት አስተያየት ምንድነው?ሲሉ ቱልቱላው የወያኔ ተቀጣሪ ጋዜጠኛ እንዲያብራራለት ጌታውን ይጠይቀዋል። ግልጽነት ማለት በወያኔ ቃል “ውሸት ድብበቆሽ”እንደሆነ ከማሕደሩ የምታውቁት ነውና መተንተን አላስፈለገኝም፡ ለመነጋገር የፈለግኩት ከራሱ የውሸት መልስ ለዛሬው ርዕስ ምን ያህል እውነታ አለው ከሚል ነውና ፤የመለስ ዜናዊ የተለመወደው አጭበርባሪነት ይኼው ሲመልስ እንዲህ ይላል “… ጥናቱ ሲደረግ እኔም በሩቅ ሁኜ ስከታተለው የነበረው ጉዳይ ነው፡ በጥድፍያ ያልተደረገ ጉዳይ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።ለማወቅ የሚቻለው ሁሉ ለማወቅ ጥረት እንደተደረገም እርግጠኛ ነኝ። ግልጽነት በሰፈነበት ሁኔታ እንዲከናወንም ማንኛውም ነገር ከፈትሓዊነትና ከግልጽነት አኳያ አስተማማኝ እንዲሆንም አስፈላጊ ዝግጅት እንደተደረገ አውቃለሁ።ይኼም ሆኖ ሰው የሚሰራው ሥራ ከስሕተት ነፃ ይሆናል የሚል በእርግጠኝነት መናገር አልችልም።ስለሆነም መጀመርያ ስሕተት እንዳይኖር እንዳልኩት ከአስራ ስምንት ወራት በላይ የፈጀ ጥናትና ጥንቃቄ የሞላበት አሰራር መከተል ነው መጀመርያ ስህተትን ለመቀነስ። የህም ሆኖ ስሕተት ሊኖር ስለሚችል ተበደልን የሚሉ ወገኖች ሊደመጡበት የሚችሉ ሥርዓት መኖር አለበት።እና እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት እንዲኖር ተደርጓል፤ አዲስ አበባ ለይ። ስሕተት ለመኖሩ የማውቀው ነገር የለም፤ ምክንያቱም አይኖርም ብየ ተስፋ አደርጋለሁ፡ምክንያቱም በቂ ጥንቃቄ ተደርጓል፡ነገር ግን እንዳልኩት ከሰው ስሕተት መኖሩን ሁሌም ጥርጣሬ መያዝ ስላለብን ምናልባት ስሕተት የተሠራ እንደሆነ በስሕተት የተጎዱ ወገኖች ተጎድተው እንዳይቀሩ የሚደመጡበት የቅሬታ ሰሚ ስርዓትም መኖር አለበትና ያ ስርዓት አለ።ስለዚህ በሁለም መልኩ ጥንቃቄ የተደረገበት ነው ማለት ይቻላል።”ስል ቅንድቡን ገትሮ ሳያፍር ዋሽቷል ልድገመው “ዋሽቷል”! ስሕተት የተሠራ እንደሆነ በስሕተት የተጎዱ ወገኖች ተጎድተው እንዳይቀሩ የሚደመጡበት የቅሬታ ሰሚ ስርዓትም መኖር አለበትና ያ ሥርዐት አለ”የምትለዋን ውሸቱን አትርሱ እና እሷን በሕሊናችሁ ይዛችሁ ወደ ሚቀጥለው ልዩ ዝግጅት ልውሰዳች። እውን ወያኔ የተጎዱ ወገኖች ተጎድተው እንዳይቀሩ የሚደመጡበት የቅሬታ ሰሚ ስርዓት ክፍት አድርጓል?መኖር አለበት ብሎስ ጭራሽኑ አምኖ ያወቃል?ያ ሥርዐትስ አለ የሚለው የት እና መቸ የተመሰረተ? ለእንዴት አይነት ተጎጂ ክፍሎች ነው “የሚደመጡበት ሰሚ ሰርዐት አለ” እያለ ቅንጣት ሃፈርትሳይሰማው የሚዘላብደው?”እሱና መሰል የህ.ወ.ሓ.ት ገራፊዎች ጫካ ውስጥ በማን ያህለኝነት በመርዝ ግድያ የተካፈለበት ወንጀልና የራሱ ነብሰ ገዳዩች ማጭድ አግሎ በእሳት የሰው ልጆች ሲጠብሱበት የነበረው ወንጀልና በሺዎች የተገደሉ ንፁሃን ነብሳት የሚደመጡበት “ልዩ ፍረድ ቤት የሚፈቅድ ሥርዐት አቋቁም ተብሎ ትግራይ ውስጥ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ስርዓቱን ሲጠይቁት ለምን ፈርቶ ተምቦጅቡጆ እምብየው አለ?” ንጹህ ሰው ከሆነ ለምን ፈርቶ እምቢ አለ? ንጹህ መሪና ድርጅት ፍርድ ቤት ይፈራል? በመርዝ ግድያ የተካፈለበት የራሱ ወንጀል እንዳይታወቅበት ይሆን? የተጣለበት ሳይታወቅ በወያኔ ሽብርተኞች እና ገራፊዎች ተደብድቦ ተቃጥሎ በየጥሻው ተጥሎ የቀረው የሰው ሕይወት ወያኔ ምስጢሩን ይዞት ለምን ዝም ይላል? ለምንስ ሕግ ይፈራል? መቸስ ነው፤ ለምንስ ነው ድርጅቱ የፈጸማቸው ወንጀሎች ልክ እንደ ደርጎች ልዩ በጀት ከፍቶ በሕግ እራሱንም እንዲጠየቅ ልዩ ፍርድ ቤት ለማቋቋም እምቢ ብሎ በፍርሃት ሁሌም እያጭበረበረ መኖር መረጠ?ይህ ሁሌም በየአመቱ የካቲት የምጠይቀው ጥያቄ መለስ እስክያገኝ ድረስ የዛሬ የካቲት 11ቀን አክባሪዎች የማጭበርበሪያ ከበሮአችሁን መሬት ላይ አስቀምጡና ጆሮኣችሁን አቅንታችሁ ለዚህ ጥያቄ መልስ ስጡ! በደም የተቀባ ከበሮ መደለቅ ያስነውራል! የካቲት እያሉ ውሸታቸውን ለመደበቅ በፍርሃት ከበሮ የሚዘሉ ፈሪዎች የየካቲት ጉድ እነሆ ‘ጉዳቸውን እዩልኝ፡- ይህ ሰነድ ጋህዲ ከተባለ አቶ አስገደ ገብረስላሴ በጻፈ መጽሐፍ ቁ-2 ገጽ 131 135 ከትግርኛ ወደ አማርኛ የተረጐምኩት ነው። ጽሑፉ በቅርብ ጊዜ ለመታተም ዝግጅት ላይ ካለው አዲስ መጽሐፌ የተቀነጨበ ነው። ሰላይ ብለው ወይንም ሻምበል ተኽላይ ብለው የሰየሙት ሰላይ ከሌሎች ታጋዩች እና የዓይን ምሥክሮች እንዳረጋገጥኩት (በይድረስ ለጎጠኛው መጽሐፌ ውስጥ ከአቶ (ፊታውራሪ)ገዛኢ ረዳ ጋር በተደርገው ቃለ መጠይቅ የቀረበውና እኔም በግል ከሳቸው ጋር ባደረግኩት ውይይት እና ከሌሎችም ልጁ የአስራ ሁለት ዓመት ወይንም ከዛ በታች የሆነ ታዳጊ ህፃን ነው።ይኼም በራሳቸው በወያኔዎች የተለያዩ የራዲዩ ቃለ መጠይቆች ባደመጥኳቸው ላይ ሰላይ እየተባለ ያለው ገና “ልጅ እግር”እንደሆነ አንዳንዱ 14አንዳንዱ ትንሽ ልጅ አንዳንዱ 15ነው እያሉ ነው የገመቱት (ለዚህም ነው ወያኔዎች የዲማው “ማንጁስ” ወይንም የዲማው ጩጬ (ህፃን)ብለው የሚጠሩት።ለዝርዝሩ ይድረስ ለጐጠኛው ምምህር መጽሐፌ ስለሚገኝ ያንብቡ)። ቢሆንም በአስገደ ገብረስላሴ አባባል አሁንም ከወደ መጨረሻ ዘገባው ሻምበል ሲለው የነበረው ሰላይ ከ20 ዓመት ዕድሜ በታች ሲል እራሱ አስገደም ቢሆን አረጋግጧል። እንደ ፊታውራሪ ገዛኢ ቃለ መጠይቅ ሕጻንት ልጆች በስለላ እየተጠረጠሩ ሲያዙ ምንም የማያውቁ እንነበሩ አብረው ታስረው ከነበሩት ህጻናት ጋር ለመረዳት እንደቻሉ ተናገረዋል። ብርሃነ መስቀል የተባለው ህጻንን ሲገርፉት የማያውቀው ነገር አዎ በል ስላሉት አዎ ሰላይ ነኝ እያለ አመድ አክስቱን ለጎብኘት መጥቶ ያረፈበት ቤተስብ ሁሉ ሲጠቁም የነበረውን ታሪክን ያጠነዋል፡እዛው መጽሓፌ ላይ ተዘግቧል፤ እሱን ማንበብ ነው።} ለማንኛውም ሻምበል ተብሎ የተጠራው የሻምበል ተኽለ የስለላ ታሪክ እና የወያኔ መሪዎች አረመኔነት እንከታተል።}ወያነ ትግራይ መስርተው በእግሩ ካስቆሙት አንዱ የሆነው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ እንዲህ ይላል፦ ጊዜው የካቲት 5/1968 ዓ.ም. በየአውራጃው፤ወረዳዎች፤ከተሞች ድርጅታዊ ሥራዎችን ስናከናውን ቆይተን ሌሎቻችንም ተራራ ጉቡታው ላይ አንዳንዶቻችን ከረፋዳው የፀሐይ ቃጠሎ ለመጠለል “ላሓይ” ከተባለ ዛፍ ጥላ ሥር ቁጭ ብለናል፡አንዳንዶቻችንም ቂጣ እንጋግራለን ሌሎቻችም “ብርኩታ” (በፀሓይ ሙቀት በጋለ ድንጋይ ላይ የሚጋገር ዱቡልቡል ደረቅ ዳቦ (ክርሰፒ ብሬድ) ማለቱ ነው ብርኩታ ሲል የጋህዲ ደራሲ) በማር ቀብተን እንበላለን፤ሌሎችም እንዲሁ ቂጣ በቅቤ ፈትፍተው ይበላሉ፤ እንደሰታለን፤ እናወራለን፤እንስቃለን ደስ የሚል ሁኔታ!ይኽ ደስታ ወደ ሃዘን የሚለወጥ ድንገተኛ ክስተት ከላይ በተጠቀሰው ዕለት የተ.ሓ.ሕ.ት. (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ) አመራር አባለት፡ 1. በረሁ በርሄ ማ/ኮሚቴ 2.አስፋሃ ሐጎስ መ.ኮሚቴ 3.ስዩም መስፍን ማ/ኮሚቴ 4.አገአዚ ገሰሰ መ/ኮሚቴ 5.ሙሴ ተኽለ መ.ኮሚቴ 6.ግደይ ዘርአጽዩን ማ/ኮሚቴ 7.አባይ ፀሃየ ማ/ኮሚቴ 8.ስብሐት ነጋ ታጋይ 9.ህቡር ገብረኪዳን ታጋይ 10.ቆቋሕ ፀጋይ ታጋይ 11.አጽብሃ ዳኘው የ5ኛ ምድብ የሕክምና ሓላፊ እና ሌሎች የተቀባበለ ጠመንጃ ወድረው በዛው ባለንበት በዲማ ማርዋ በሥልጠና ላይ የሚገኙ ሰልጣኝ ታጋዩችን እየያዙ ወደ እስር ቤት ማስገባት ጀመሩ። ከዛ የታሰሩት እነኚህ ሰልጣኝ ታጋዩችም በጣም ጨካኔ በተሞላበት ከባድ ግርፍያ (ቶርች)እና ድብደባ ውስጥ አስገቧቸው።የተገረፉትም እንድንጠብቃቸው ወደ እኛው አመጧቸው። እዛ በሕክምና ተመድበን የነበርን ታጋዩችም የገረፏቸውን ታጋዩች እንድናክማቸው በሙሴ አማካይነት መመርያ ተሰጠን። ሌሎች በጣም በከባድ ምርመራ የተገረፉ ታጋዩች ደግሞ በወቅቱ የሕክምና ሓኪም የነበረው ዶ/ር አታኽልቲ ቀጸላ ሰው እንዳያያቸው በምስጢር በተከወለ ሥፍራ እያከማቸው ነው።እኛ ምን እንደተገኘ ምን ትርኢት ውስጥ እንደገባን ግራ ገብቶናል። ስለ ሁኔታው የነገረን ወይንም የሚናገር ሰው የለም። ደንግጠናል፤ክው ብለን ምን እንደገጠመ ማወቅ አልቻልንም።በድንጋጤ ተወርረን ተጨንቀናል። ከላይ ስም ዝርዝራቸው የተጠቀሱ ገራፊዎቹ እኛ ወደ ተቀመጥንበት አካባቢ ብቅ ሲሉ ሁሉም ታጋይ በሽብር ተውጦ እርስ በርሱ አንገቱና ዓይኖቹ ‘ዞር ዞር’ ፍጥጥ’ ‘ፍጥጥ’ “ቆልመመም” እያለ እርስ በርሱ ይተያያል፤ ግን ድምጽ ኮሽ አትልም አይነጋገርም።ሁኔታው ምን እንደሆነ የነገረን የለም፤ ተጨንቀናል። ቀን ወደ 5፡00ሰዓት አካባቢ አንዳንዶቻችን ደፍረን የምትሠሩት ሥራ ተቀባይነት የለውም ማቆም አለባችሁ፤ የሚል ተቃውሞ አሰማን። እነሱም ሰጉና ስዩም መስፍን፤በሪሁ በርሄ እና ሙሴ ወደ እኛ በመምጣት ስለ ሁኔታው ገላጻ አደረጉ። እንዲህ ሲሉም ስለ ሁኔታው ምንነት ነገሩን “ሻምበል ተኽላይ” የተባለ የደርግ ሰላይ የሚያዛቸው ብዙ ሰላዩች ወደ እኛ በምስጢር ሰርገው ገብተውብናል። እነሱን ነው እየመነጠርን እየያዝን ያለነው። አሁንም ምንጠራውና ማጣራቱ ይቀጥላል። የምንጠረጥረው ሰው ሁሉ እንይዘዋለን ይዘን እንመረምረዋለን አሉ።ታጋዩ የባሰ ተደናገጠ። አንዳንዶቹም ‘ሁኔታው ረጋ ባለ መንፈስ ብትከታተሉት ይሻላል እንጂ ይዛችሁ ከመረመራችኃቸው መሃል ውስጥ ፍጹም ወደ እዛ አቅጣጫ የማይታሰቡ የማንጠረጥራቸው ናቸው፤ ስለዚህ ወደ አደገኛ ግርፍያ ውስጥ ባትገቡ ጥሩ ነው።ያዝነው የምትሉት ሰላይ እያታለላችሁ እንዳይሆን በጥንቃቄ ረጋ ብላችሁ ሁኔታውን አጣሩ ቢሉም አመራሮቹ ማሰራቸውን ቀጠሉበት። ቆየት ብለው ለሻምበል ተኽላይ ጥብቅ የሆነ ጭካኔ የሞላበት ከባድ ምርመራ ውስጥ ሲያስገቡት “እኔ የተላክኹበት ምክንያት ታጋዩ እረስ በርሱ እንዲባለ፤ ድርጅቱ ውስጥ ብጥብጥ/ግርግር እንዲነሳ አድርግ ተብየ ነው ከደርግ የተላክኩት፤ስለዚህም ነው ተናገር ስትሉኝ ሁሉንም ታጋዩቻችሁ ለመጠቆም የፈለግኩት አላቸው። ያም ሆነ ይህ ሰላዩ የጠቆማቸው ሰዎች በአመራሩ እጅ እየተገረፉ የሞቱ ታጋዩች አሉ፤አንዳንዶቹም ሕሊናቸው የቀወሰ አሉባቸው፤አንዳንዶቹም በድብደባ ብዛት ጥርሳቸው የወለቀ/ተሰበረ፤ ዱላ እና ካራ በእሳት እየጋለ ሰውነታቸው በእሳት የተጠበሱ አረ ስነቱ ጉድ ተብሎ ይታወሳል! ከጊዜ መርዘም ብዙዎቸን ብረሳም ለምሳሌ እስከ አሁን የማስታውሳቸው በወቅቱ ያለ ሃጥያታቸው በወያኔ አመራሮች በምርመራ ውስጥ የተደበደቡ እሳት የተቃጠሉ የሞቱ ጎዶሎ አካል የሆኑ ሰዎች ስም ዝርዝር ለመጥቀስ ያህል፡ 1.ግደይ የተባለ ታጋይ (ትውልዱ ሽሬ አውራጃ ጣቢያ ኣርዓዳ) በግርፋት የሞተ 2.ያሬድ (ሽሬ እንዳስላሴ) በእሳት በዱላ የተገረፈ 3.ብርሃነ ገብረስላሴ (ሸሬ እንዳስላሴ) በዱላ፤ በእሳት የተገረፈ 4.ወዲ ገቲራ(ሽሬ እንዳስላሴ ወረዳ ዓዲ አውላዕሎ) የተገረፈ 5.ካብራል (ዓድዋ ከተማ) በግርፋት ብዛት አካለ ጐደሎ የሆነ 6.ይሳቕ ቆማጥ (ዓድዋ አውራጃ) የተገረፈ 7.ሉቃስ ተፈሪ (ዓድዋ አውራጃ) የተገረፈ 8.ነጋሽ ተፈሪ(ሸሪፎ) (አኽሱም አውራጃ) በድብደባ ብዛት ጥርሱ የተሰበረ 9.ወዲ ሓኔታ (ዓጋመ አውራጃ) በግርፋት የሞተ 1o.አሰፋ ተስፋይ (ዓጋመ አውራጃ ዓዲ ግራት) የተገረፈ 11.ማርታ (ዓጋማ አውራጃ ዓዲ ግራት) ከባድ ምርመራ ተካሂዶበት የተገረፈ 12.መኮንን ዓሊ ሹም (ሽሬ አውራጃ ማይ ዕባራ) የተገረፈ 13.ዘርኡ በዛብሀ (ዓጋመ አውራጃ ዓዲግራት) ሌሎች 15 የሚሆኑም ታስረው ነበር ግን ግርፋት አልተፈጸመባቸውም። ከላይ ተዘረዘሩት ታጋዩች ግን በዱላ እና በእሳት ገላቸው እየተጠበሰ ከባድ ምርመራ እና ግርፋት እየተፈፀመባቸው ገላቸው ቆስሎ ፀሓይ ላይ ተዘርረው የዋሉበት ቀንም በር።ተዘርረው የተመለከተናቸው ልናክማቸው ብንሞክርም አክሟቸው ሳትባሉ እንዳታክሟቸው ስለተባልን ምንም ማድረግ አልተቻለም። በጣም ሚገርመው ደግሞ አዳዲስ ታጋዩች ወደ ትግሉ ተቀላቅለው ስለነበር ይኸንን ጉድ ሲመለከቱ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ።ተረብሸው በቁም “ሽንታቸው”የለቀቁ ነበሩባቸው። ማናቸውም ታጋይ የተጠቀሱት መርማሪዎች በአጠገቡ ሲያይ ይደናገጥና ይረበሽ ነበር። አስረው የገረፏቸው ሰዎች ምንም ውጤት ሳያገኙባቸው ከቀሩ በኃላና ሰላዩም የተልእኮው ሚና እንደፈጸመ ከነገራቸው በኃላ በከባድ ምርመራ ተገርፈው በሽንትና በዓይነምድራቸው ተበላሽተው ሕሊናቸው የሳቱ ከለቀቁ በሗላ፤ በእሳት እየተጠበሱ ገላቸው ቆስሎ ጸሐይ ላይ ተጥለው ገምተው የነበሩት ታጋዮችም ለደ/ር አታኽልቲ ቀጸላ፤ለስየ አብርሃ እና ለእኔ እንድናክማቸው መመርያ ሰጡን። ይህ ሁሉ አሸባሪ ተግባር ከፈጸሙ በሗላ ታጋይ በሞላ ሰብስበው “ተሳስተናል፤ረጋ ማለት ነበረብን፤መቸኮል አለነበረብን፤ይቅርታ”ብለው ይቅርታ ከጠየቁ በኃላ አንዳንዱ ፍርሃት ውጦት የነበረው ታጋይ መረጋጋት ጀመረ፡ እነዚያ ድብደባ የተፈጸመባቸው ታጋዩች ግን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሌሊት ሌሊት በእንቅልፋቸው ኩፉኛ ይባንኑ ነበር።ከእነዚያ አዳዲስ ምልምሎች አንዳንዱ “ኣይ!አይሆንም ይቅርብን፤ አንታገልም፤ወደ ቤቶቻችን እንመለሳለን”ብለው እምቢ አሉ። አንዳንዶቹም በስንት ልመና ተለምነው ታገሉ። ነግር ግን እንደ እነ ብርሀነ ገብረስላሴ እና ወዲ ገቲራ የመሳሰሉት ግን እንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤አንታገልም! ብለው ትግሉን ጥለው ተመልሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ። ህ.ወ.ሓ.ት.ከባድ ምርመራ አስገብቶ የዜጎችን ፍትሓዊና ሚዛናዊ ፍርድ ሳያጣራ መግረፍ የጀመረው ማርዋ ዲማ ላይ የጀመረው ሳይሆን ከዛ በፊት በ1968ዓ.ም.ሴሮ በተባለ አካባቢ አምበሳ የሕዝብ ማመላለሻ አብቶቡስ ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩት እንዳጋጣሚ በእጃቸው ስቲንገር የተባለ 40ጎራሽ ጠመንጃ ይዘው የነበሩ “ጥዑመ ልሳን ተክለሃይማኖት” የተባሉ ጠንቋይ (ብሏቸዋል ደራሲው- ግን ደብተራ ለማለት ይመስለኛል ምክንያቱም ሰውየው መሪጌታ ናቸውና)ትውልዳቸው በሽሬ አውራጃ ሰለኽለኻ ወረዳ ዓዲ ሐበሳይ ሲሆን፤ ያኔ አቡቶቡሷን ስናቆማት ስለተታኮሱን፤እሳቸውን አስረን ወደ ምስራቅ ትግራይ አካባቢ ከኛው ጋር ወሰደን እስርቤት ከነበሩት ከግምባር ሓርነት ትግራይ መሪዎች ከእነ ዮሐንስ ተ/ክለሃይማኖት ጋር ጨመርናቸው።እነ መምህር ዩሐንስ፤ ኤፍሬም፤ወዲ ሻለቃ ሃይለሚካኤል፤ወዲ አባ ጎበዝ እና ሌላ ስሙ የዘነጋሁት ሽፍታ ለረዢም ጊዜ በመታሰራቸው ጊዜ ስለረዘመባቸው፤ እነ መምህር ዩሐንስ ሲጨንቃቸው መሪጌታውን በምትሃታቸው ችሎታ ከእስር የሚያመልጡበት ብልሃት እንዳለ እንዲረዷቸው አማከሯቸው፤መሪጌታ ጥዑመ ልሳንም ጠንቋይ (ምትሃተኛ)ስለነበሩ (ደራሲው ደብተራ ለማት ጠንቋይ ስላለ ጠንቋይ እያልኩ ጽፌዋለሁ) በእግረሙቅ በታሰሩት እግሮቻቸው ላይ እግረሙቁ ላይ ሽንታቸውን ሸንተው እግረ መቁን በስራይ/በምትሃት ሊፈቱት እንደሚችሉ መርጌታ ጥዑመ ልሳን ያማክሯቸዋል። መሪጌታም ድጋማቸውን ካከናወኑ በሗላ ሽኑበት ብለው ሲጨኑበት እግረሙቁ አልበተን አልፈታ አለ። በዚህ ወቅት መሪጌታ እና መምህር ዩሐንስ ሲንሸዃሸኩ በወቅቱ እነሱን (እስረኞቹን)ዘብ ቆመው ሲጠብቋቸው የነበሩት ተረኞች እነ ስብሓት እነ ሕቡር፤እና ዓወተ ያዳምጧቸዋል። እነሱም ለአመራሮቹ ለእነ አጋአዚ ይነግሯቸዋል። ከዛ እነ ስዩም መስፍን ከዘበኞቹ ጋር ሆነው ማጭድ በእሳት እያጋሉ ለነ መምህር ዮሓንስ ለነ መርጌታ ጥዑመ ልሳን እና እዛ ላሉ እስረኞች በሙሉ በእሳት እያቃጠሉ መላ ሰውነታቸው ገሸላለጧቸው። በጣም አሰቃያሚ ትዕይንት ነበር።በእሳት እያጋዩ ግፍ በተሞላበት የጭካኔ ምርመራ ስለመረመርዋቸው ለማከሙ አስቸጋሪ ነበር። የህ.ወ.ሓ.ት አማራር በባዶ 6 እስረኞች አያያዝ በእነ መርጌታ ጥዑመ ልሳን እና በእነ መምህር ዩሐንስ የጀመረው የግፍ እና አረመኔ ምርመራ፤ከዛም ሻምበል ተኽላይ በፈጠረው ቀውስ ምክንያት ሰከን ብለው ሁኔታዎችን ባግባቡ ከመያዝ ይልቅ ከደርግ ጭካኔ አምልጠው ለመታገል የመጡትን ታጋዩች ሳይቀሩ አሰቃቂ ምርመራ በላያቸው ላይ (በማን አለኝነት)በመፈጸም የሞት፤የአካል እና የሕሊና ቀውስ ማውረድ በድርጅቱ ታሪክ ላይ ጠባሳ ትቶ ያለፈ እጅግ አሳፈሪ ድርጊት ነበር። በህ.ወ.ሓ.ት የምርመራ አረመኔ አያያዝ የተነሳ ደርግ ብዙ ብርጌዶች አሰማርቶ ድል ማግኘት ያልቻለው ከሃያ አመት ዕድሜ በታች የሆነ አንድ ትንሽ ልጅ አሰማርቶ የህ.ወ.ሓ.ት. ታጋይ ሠራዊት በራሱ መሪዎች እንዲገረፍ፤እንዲገደል እንዲበተን ከማድረጉ በላይ የህ.ወ.ሓ.ት ጭካኔ ከዓጋሜ ሕዝብ ጋርም ሆድና ጀርባ አድርጎ እንዲቆራረጥ አድርጎት ነበር። የህ.ወ.ሓ.ት ደጋፊዎች የነበሩ እንደ እነ አቦይ ወልደማርያም የተባሉ አዛውንት ገበሬ ሰላይ ናቸው ብሎ ሻምበል ተኽለ ስለጠቆማቸው ከነ 4 ልጆቻቸው ባለቤታቸው ጨምሮ 6ታቸው ታስረው በእሳት እየጠበሱ ስለገረፏቸው አከላታቸው እንዳለ ስለተገሸላለጠ የዓጋመ ሕዝብ ይህን ወሬ ስለሰማ ወደ ህ.ወ.ሓ.ት እንዳይጠጋ ሰጋ። ሰለዚህም በዚህ ሰበብ ሕዝብና ህ.ወ.ሓ.ት ተራራቀ፤መተማመን ታጣ። በሰበቡም ለሠራዊታችን ዕድገት እንቅፋት ፈጠሮ ነበር። ህ.ወ.ሓ.ት ከስህተቱ ተምሮ የቅራኔ አፈታት መንገድ ከማበጀት እና ሰዎች በምህርት መልቀቅ ፈንታ በሞት (እና በእሳት እየጠበሰ )መቅጣት ስራየ ብሎ ተያያዘው። ተቃዋሚን እና ተጠርጣሪን በሞት ቅጣትና በድብደባ ማሰቃየት በእነ ዩሐንስ እና ጥዑመ ልሳን “ሀ” ብሎ የጀመረው አረሜናዊ እርምጃ ዲማ ማርዋ ላይም በሰላይ ሻምበል ተኽላይ እና ሌሎችም የሞት ፍረድ ተፈርዶባቸው በዲማ ማርዋ በየጥሻው ተጥለው የቀሩ ብዙ ናቸው። (ጋህዲ ቁ 2፦ አስገደ ገ/ስላሴ) አስገደ ገ/ስላሴ ይህን ካለ በሗላ “የተከበራችሁ አንባቢዎች ሆይ በሰላይ ሻምበል ተኽላይ ምከንያት (በህ.ወ.ሓ.ት አመራር አረመኔ ባህሪ- “ቅንፍ” የተጨመረ) ህ.ወ.ሓ.ት ውስጥ ብዙ ስቃይና ምርምራ ተደርጎ አካላተቻው እና ህይወታቸው እንዳጡ ተመልክተናል። ከዚህ በሗላ የ ህ.ወ.ሓ.ት ባዶ ሽድሽተ 06 እስር ቤት ያንኑ ይደግመው ይሆን? ይልና ከጠየቀ በሗላ “እንከታተል” በማለት እጅግ የከፋ ግፍ እና ምርመራ ኢሰብአዊ እና የዲሞክራሲ አፈና በባሰበት መልኩ በሰፊው አቅርቦታል። እንግዲህ ዛሬ የ.ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች መንግሥት ከሆኑ በሗላ የቀጠሉበት የግድያ የግርፋት እና አረመኔ እርምጃዎች ሁሉ መቸ እንደጀመረ ለማስረዳት ከላይ ከመግቢያው የጠቀስኩት ይህን የቆየ ማንነታቸው ዛሬ ለሚታየው አፈና እና ግድያ እንዲሁም ጭካኔ ከጫካ የመጣ እንደሆነ በመረጃ አቅርቤላቸሗ ለሁ። ዛሬስ መንግሥት ከሆነ በኃላ የፈጸማቸው ኢሰብአዊ እና አገራዊ ወንጀሎች እንዲሁም ስርዓቱ ከበረሃ አምጥቶ በሕዝቡ ላይ ጭኑ ከዘረጋው በሗላ የስርዓቱ ቱባ ቱባ ሃላፊዎች ዛሬ ሥልጣን ላይ ቁጢጥ ብለው ክራባት አስረው ንፁህ ሸሚዝና ውድ ውድ ገበርዲን ለብሰው ሰው መስለው ከዓለም መሪዎች ጋር ቁጭ ብለው በስዕለ ድምጽ (ቲቪ) ለዓለም ሲታዩ እጃቸውና፤ አፋቸው፤ፊታቸው በደም ንጣሪ ሲጨማለቁ እንዳለነበረ ሁሉ ያን ጉዳቸው ሸፍነው ጸዳድተው ሽቶ ተለቅልቀው የዋህ አገልጋዩቻቸውን ሲያሞኙ ስታዘብ በጣም አድርጎ ይኸ ዓለም ይገርመኛል። ይኼ ነው የካቲት!!!!!!!!!! በዚህ ግድያ በዛው ወንጀል አረመኔነት የተጓዘ ተጠያቂነት የሌለው የካቲት ማለት የኼ ነው!አይ ፈጣሪ ሁሉም ችለህ ማየት እስከ መቸ? ተሎ ውረድ እንጂ አምላክነትክን አመስክርና ሽቶ የተቀቡት ደም ደም የሚሸቱት ፍጡሮችህን ውሰድልንና አቃጥለው ገርፈው ረሽነው የገደሏቸው የሞቱትን ቆፍረን አውጥተን ዳግም መቃብራቸው ተሰርቶ ሙሾ እና ሃዘን ይደረግላቸው እንጂ! እራሱ የገዳላቸው የት እንደቀበራቸው ሳይነግረን ሸሽጎ፤ በሕግ አልዳኝም ብሎ በየአመቱ በፈርሃት ተውየጦ ሲምቦጀቦጅ ለፍርሃቱ ሽፋን ደርግ የገደላቸው ብቻ ለፖለቲካ ንግዱ ሲል አስቆፍሮ ሕዝብን እያስለቀሰ እስከ መቸ?የገደላቸው ፍጡራን የት እንደቀበራቸው በየትኛው ጣሻ ብልን እንፈልጋቸው አምላኬ?ብዙ እናቶች እኮ ፍርድህ እንዲፈጥን እየጠበቁ ነው:ከሰው ስሕተት መኖሩን ሁሌም ጥርጣሬ መያዝ ስላለብን ምናልባት ስሕተት የተሠራ እንደሆነ በስሕተት የተጎዱ ወገኖች ተጎድተው እንዳይቀሩ የሚደመጡበት የቅሬታ ሰሚ ስርዓትም መኖር አለበትና ያ ስርዓት አለ። ይላል መለስ ዜናዊ። አውን የተጎዱ ወገኖች ተጎድተው እንዳይቀሩ የሚደመጡበት የቅሬታ ሰሚ ስርዓት ኖሮ ሰው ከተጣለበት ጉድጓድ እየተቆፈረ የሚያሳይ የሚያስለቅሰው የስክሪን ካሜራ በነሱ ጣሻ ላይ ያነጣጠረው መቸ ነው?መቸስ ነው በትግራይ ጫካ ላይ ቁፋሮው ሲጀመር የሚነጣጠረው?አይ የካቲት የስንቱን እናት አስለቀስሽ የስንቱን ደም ጠጣሽ? ፍርሃቱ ነው ዝምታው? ጥያቄው ይኼው ንገሪን እንጂ? ደም የተቀባ ከበሮን መደለቁ እስከ መቸ? Getachew Reda

No comments: