Tuesday, November 9, 2010

የዳመናው አገር By Getachew Reda

የደመናው አገር (ጌታቸው ረዳ)
GETACHEW REDA Editor Ethiopian Semay
መናው አገር (ጌታቸው ረዳ)

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር(አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ(ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/

ይህ ግጥም ወያነ ትግራይ ወደ መንበረ ሥልጣን ወጥቶ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በላ የጎሳ ፖለቲካ ነድፎ እርስ በርሳችን በጥላቻና በቂም በቀል የጎሪጥ እየተያየን የቋንቋ አደረጃጀት በተከተሉና ባልተከተልነው መሃል ሲታይ የነበረ እጅግ አሳዛኝና አስፈሪ የጥላቻና የመሰዳደብ ዓየር ሰፍኖ በነበረበት የመጀመሪያው ዓመት እና በተለይም ከዚያ ተከትሎ ለ7 ዓመታት ወያኔዎች ከኤርትራ ባንዳዎች ጋር በመሻረክ አማራውንና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማና ታሪክ ጸሓፊዎችን እንዲሁም በተለይም አፄ ምኒሊክንና አማራውን በጠላትነት እንዲታዩ ወያኔ ትግራይ በረሃ ውስጥ (1) ተጋድሎ ትግራይ በልዎ እቲ ዓሻ ኣምሓራይ (2) ንዓወሽ በሉ ዙ አድጊ ኣምሓራይ (3) ይኺድ ንዓዱ… እና የመሳሰሉ ፀረ አማራ የወያኔ ዘፈኖችን በግልፅ ሲያሰራጫቸው ነበረውን የጥላቻ ቅስቀሳው በተግባር በመተርጎም አጀንዳው አደርጎ የተነሳው ጥላቻውን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎች በተለያዩ ጠባብ ብሔረሰቦች በቢላዋ እና በሳንጃ አንገታቸው እየተቆረጠ ከነበሩበት እና ከቄያቸው ወደ ትውልድ መንደራችሁ ሂዱ እየተባሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል። በወቅቱ ትግሬዎች ሆነን የሻዕቢያ ጊላ (ባርያ) የሆነውን ወያኔን ያልደገፍን ትግሬነታችን ተገፎ “የሸዋ ትግሬዎች” (ሽዋውያን ተጋሩ) እያለ ትግሬነታችን ሲነጥቀን፤ በአንፃሩ ከወያኔ ያልተናነሱ አንዳንድ ጠባብ አማራዎችና የኦነግና የመሳሰሉ ጎሰኞች የትግራይን ሕዝብ ሲዘረጥጡ አልፎም ከትግሬ ጋር ጋብቻ እንዳታደርጉ የሚል ቅስቃሳ ሲደረግ እነሱንም በግልፅ ስቃወም ትገሬ በመሆኔ እኔኑም አብረው ትገሬ ትገሬ ነው እያሉ “የወያኔ የሻዕቢያ ዘር” እያሉ በየ ሚዲያው ሲሰድቡኝ በመሃል ለሃቅ በመቆሜ አንተምና አንተም ተው አንተም ተው ባልኩኝ ቁጥር የደረሰብኝ ዘለፋ እጅግ ኣሳዛኝ ስለነበር፤የተሰማኝን ብቸኝነትና ቅሬታ ለታሪክ የዘገብኩት ግጥም ነው። ግጥሙም በትላልቅ መጽሄቶች ታትሞ ነበር። ዛሬ በራሴ መጽሓፍ ለማስረጃ ተካትቷል። ግጥሙም እነሆ። ለጎሳ እና ላጥንት ለሥጋ ዝምድና ላገር ልጅ ለወንዝ ልጅነት ሳይሆን ለሰብአዊነትና ለኢትዮጵያዊነት በመቆሜ ሞት አይቀርምና እኔ በሥጋ ብሞትም ታሪክ ዘግቦታልና የቆምኩላትን አገሬ ኢትዮጵያን ግን ለጊዜው ቢያዳክሟትና ቢዘልፏትም መግደል ግን ከቶ አይቻላቸውም። እሷን ለመግደል ለ18 ኣመት የተለያዩ መርዞች ተቀምመው ሁሉም አልሰራ ሲላቸው ጠላቶቿ ዛሬ የሷን የሺዎቹ ዘመናት ታሪክ ማመመን እየዳዳቸው ነው (ስዩም መስፍን የመቶ ዓመት ታሪክ ሲላት የነበረው ከባድሜ ጦርነት በየ3000 ዓመት ታሪክ አለን ሲል ያለውን አድምጡ) ወጣቱ “ልደቱ አያሌው” በምርጫው ክርክር ወቅት ወያኔዎችን ያሳፈራቸውና (ድሮ ምኒሊክ ከሃዲ ሰትሏቸው የነበረ ዛሬ ይመስገነው እግዚአብሔርና ታሪክ ለምርጫ መጠቀሚያ ብላችሁም ይሁን … ለግል ምክንያታችሁ “አፄ ምኒልክን ጀግና ነበሩ” ሰትሉ ለመጀመሪያ ጀሮኣችን አድምጠናል;
ለወደፊቱም ሌላ ታሰሙን ይሆናል። ያለውን ታሪክ ምስክርነት አድምጡ።) ኢትዮጵያ የረዢም ሂደት ክንዋኔ እንጂ ወያኔዎች እንደሚሉት በቀላሉ የምትናድ፤ የኮሎኒ፤ የብሔር ስበስብ ፤አርቲፊሺያል”ስላልሆነች “አትሞትም”። ጠላቶቼ እኔንም ሆነ አገሬን ሊገድሉን ከቶ አይቻላቸውም። ሊገድሉት የማይቻላቸው ወደ ግጥሜ ይዤኣችሁ ልግባ።

                                           
የዳመናው አገር (ጌታቸው ረዳ)
አንተም ታገስ አንተም ተው ባልኩኝ ቁጥር፤
ይጠሩኛል በነሱ ጎን ለምስክር።
ለሓቅ ስናገር አያምራቸው፤
ይመድቡኛልሸዋዊያን-ተጋሩ” (የሸዋ ትግሬዎች) ከሚሏቸው፤
ሌላኛውም ካልሄድኩ በመንገዱ፤
ያወርድብኛል የስድብ ንዳዱ።
የወያኔ የሻዕቢያዘር ይለኛል፤
መድረኩ ሁሉ ይዘጋብኛል፤
የቋንቋ ፍራቻም አገር አጥቅቶታል፤
ትግሬና አማራው ሌላዉም ሌላውም በሩቅ ይተያያል
መዞር አልተቻለም፤መንደር በዘር ታጥሯል።
ንቡም ቢሆን ጨንቆት እምባ ቋጥሯል ዓይኑ፤
አይዞህ እንዳልለው ዓይኔ ብሷል ካይኑ።
በዚህ ናፈቅኩኝ፤አገር እንዳለው ሰው አገሬን ናፈቅኩኝ፤
ቀና ስል ወደላይ የጭጋግ ጉም ታየኝ፤
ልቤ አስሬ መታ ማመንም አቃተኝ፤
አየሁኝ ዳመና የጥንት የሚመስል፤
ይዞ ያገር ካርታ አብሮ የሰው ስዕል፤
ባተኮርኩኝ ቁጥር ይጠጋኛል፤
ደብዘዝ ይልና አንዳንዴም ይጎላል፤
ልዝነብ! ልዝነብ! ይላል፤
ዘንቦ ላይዘንብ ጠብ! ጠብ!.... ጠብ!... ጠብ! ይላል፤
ቀዝቃዛም አይደለም ቆዳ ያቃጥላል።
ቆዳየን ለማየት ዞር ብል ላንዳፍታ፤
ተሰወረ ጉሙ ካይኔ በእፍታ።
አሻቅቤ ሰማዩን ብቃኝ በአንክሮ
ሳይታወቀኝ አየሁት መሬት ወርዶ እፊቴ ላይ ተገትሮ፤
የሰዉ እግር በእግረሙቅ ተሸንክሮ።
ብጎነታትለው ልፈታው
እግረሙቁን ልሰብረው
ጮኹብኝ በገደል ማሚቶ ከበቡኝ በግራ ቀኝ መጥተው
አትንካው አሉኝ እኔም መነካካት አልተው።
ነፃ አውጡት ፍቱለት ወይ ልፍታው ብየ በጠየቅኩኝ
ትግሬ ነህ አማራ? አሉኝ ማንን እምስላለሁ? አልኩኝ።
አይመስልም እንዴ ቆዳየ ቆዳችሁ?
ለምን እንዲህ ጠየቃችሁ? ብየ ጥያቄያቸውን በጥያቄ መለስኩኝ
ማመን ሲያቅተኝ የምለውን ሲጨንቀኝ፤
ገርገጭ ሲል እግረሙቁ ተሰማኝ
በግራ ጎተቱት፤በቀኝ አዋከቡት፤አጋር የለው አማኝ።
አለቀሰ! አብሮት ያለው ካርታም ተላቀሰ
አለቀሰ! አለቀሰ! አለቀሰና እኔኑም ጭምር አስለቀሰ።
ተሰናበተኝ እንደታሰረበጉምወጣ ታጅቦ ወደ ሰማይ
አብሮት ጭልጥ አለ ካርታውም አይታይ።
በዝግታ ይጓዛል፤
አንዴ ወደፊት አንዴ ወደኃላ ይዋልላል።
ኮበለለ ኦሮማይ! ሄዷል ስል እንደገና ተሰበሰበ
ይዘንብ እና አብሮት ይወርድ ይሆን ስለው አልዘነበ።
በጉምይጎተታል
አየሁት ደብዛውን እንዴ ይከስላል
አንዴ ይጎላል
ወይ አይሟሟ ወይ አይረጋ፤ ጎልቶ ላይጎላ ባየር፤
ይዋልላል በጉም የደመናው አገር።///-///