Tuesday, November 2, 2010

ወሮበላዎች የመቀሌ ኗሪዎችን እያስጨነቁ ነው!

ይድረስ ለጎጠኛው መምህር(አማርኛ) $25.00 እና ሓይካማ (ትግርኛ) $15.00 መጽሐፌን ለመግዛት ዕድሉን ያላገኛችሁ ካላችሁ በሚከተለው አድራሻ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ Telephone (408) 561 4836 (Getachew Reda P.O.Box 2219 San Jose, CA 95109) getachre@aol.com http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/ ወሮበላዎች የመቀሌ ኗሪዎችን እያስጨነቁ ነው! ከጌታቸው ረዳ www.ethiopiansemay.blogspot.com getachre@aol.com November 1, 2010 ጥቅምት 2010 ባለፈው ዓመት አቶ ዜናዊ አስረስ (የመለስ ዜናዊ አባት) በ2002 ዓ.ም (ታመው በማጋገም እያሉ ማለትም አንድ ዓመት ከሞሞታቸው በፊት)ድሃይ ትግራይ ለተባለ መቀሌ ከተማ የሚታተም የትግርኛ መጽሄት የሰጡት ቃለ ምልልስ በኢትኦጵያን ሰማይ (በኔው ዌብ ሎግ)ከትግርኛ ወደ አማርኛ ተርጉሜ ላንባቢአን አቅርቤው ነበር። በወያኔ አስተዳደር ፍትሕ የተበላሸ እና የአስተዳደሩ ብልሹነት የድሮ የመሳፍንቶች/ንገሥታት/ጉልተኞች/ፊውዳሎች..ስርዐትን የሚያስታውስ የአቆርቋዦች አስተዳደር መሆኑን ከወያኔው መሪ ወላጅ አባት አንደበት ለማስረጃ ዘግቤላችሁ እንደነበር ይታወሳል። ያን ባጭሩ ትውስታችሁን እንደገና ለማስታወስ በዚህ ልጀምርና ዛሬም የመቀሌ ከተማ ጋንጎችና ሌቦች/ዘራፊዎች/ነብሰ ገዳይ ወንጀለኞች “ፍትሒ”(ፍረድ ቤት)እየተባለ ከሚጠራው “ወያነ-ዊ”የዳኞችና የአቃቤ ሕጎች ስብስብ እያስጨነቁት እንደሆነ በጥቂቱ አንድ ልበላችሁና በሚቀጥሉት ሳምንታት ትግራይ በወረበሎችና በፍትሕ ዙርያ የተኮለኮሉ የፍትሕ ክፍል (ፖሊሶች/አቃቤ ሕጎች/ዳኞች…)ጉበኞች-ምክንያት ኗሪዎችና ጎብኚዎች እየተርበደበዱ(ተሪፋይድ)እንደሆነ አቀርብላችሗላሁ። ጠቅላላ ዘገባ እስካቀርብ ድረስ የወያኔ ፍትሕ ለመመመዘን ያመች ዘንድ ፓልቶክ ውስጥና “ኢቲቪ”ተብሎ ከሚጠራ እና ከወያኔ ከበሮ መቺዎችና ቱልትላ ካድሬዎቹ እንደሚነገረው ሳይሆን እውነታው እነሱ ከሚሉን የተለየ መሆኑ “እርኩስና ከሃዲ”የሆነ ፍጡር ትተውልን ከተሰናበቱት የመለስ ዜናዊ ወላጅ አባት አቶ ዜናዊ አስረስ ምስክርነት እንጀምር። <….ሰዉ ላይ ታች ሲል አንዳይቸገር ፤ከሚኖርበት አካባቢ ጉዳዩ እየፈጸመ፡ እሥራው ላይ እንዲውል፤ ረሃብ አንዲወገድ ከሚል አኳያ ስልጣን ለወረዳ ተሰጠ። አሁን የወረዳ ባለስለጣኖች ወደመላአክትነት ተለወጡ።ሰው መሆናቸውን ዘንግተውት ወይንም የሕዘቡ አገልጋዮች መሆናቸውን እረስተው፤ ፈጣሪ አድራጊ እኛው ነን፡ዞባ (አውራጃ) አይቆጣጠረንም በማለት ሉጋም እንደሌለዉ ፈረስ ሆነዋል። መጥፎ ሀኔታ ነው ያለው።በተለይም በማዘጋጃ ቤት፤ ፖሊስ፤ወረዳ በኩል ሕዝቡ ሲያማርር ነው የምትሰማው። ምከንያቱም፤ የሚጠይቃቸዉ ተቆጣጣሪ የለም። አጠቃላይ ስልጣን ለነሱ ሰጣቸዉ። መነሻ ሃሰቡ ጥሩ ነው፤ ሰው እንዳይደክም፤ ላይ-ታች እንዳይል፤ በያለበት አቅራቢያ ውሳኔዎች እንዲያገኝ ፤ነዋሪው ጊዜ ሳያባክን ወደየ ሥራው ወደ ንግዱ ፤ወደየ እርሻው እነዲሰማራ ታስቦ ነው። ሃሳቡ ጥሩ ነው። ግን ቁጥጥር የለውም፤ እንዳሻቸው ይሆናሉ። ለዞባው (ለአውራጃዎቹ) አይሰማም/አያከብርም። ለምሳሌ የዓድዋ ወረዳ ያባረረው ሰራተኛ፡የእንትጮ ወረዳ ይቀጥረዋል። እንትጮ ያባረረው፡ ዓዴት ይቀበለዋል። አንድ ሌባ እሌላ በፈለገዉ ቦታ ሄዶ ይቀጠራል፦በሌብነት ተገልሎ አይኖርም። ምን ነበር? ምን ታሪክ ምን ሬከርድ አለዉ? በምን ምክንያትስ ተባረረ? ብለው አያጣሩም። ….. <…..አንድ ሰው አለ፦ በሌብነት አራት ጊዜ በአራቱም ቦታዎች እተባረረ የተቀጠረ።ወደ ስለጣን!ሌላውን እንተው’ና አኔ የማወቀው አንድ ሰው እንኳ ከእንትጮ ተባርሮ ወደ ዓዴት ላኩት፤ከዚያ ተባርሮ አሁን ደግሞ ወደ ዓድዋ መ’ቷል። አንግዲህ ይታይህ፡ አንድ ሰው ጥፋት ከፈጸመ ጥፋተኛ ነው። በተለይ በሕዝብ አስተዳደር። በየቢሮዉ በሕዝብ አያላገጡ መኖር አይቻልም።እግዚአብሔር ለአዳም ሕግ ሲደነግግለት እፀ በለስ እንዳትበላ በሎታል፡ሲበላ ጊዜ ኮነነዉ። ደሃይ፦ ከቡር አባት ዜናዊ አሁን ወደ አዲስ ሚለንየም ገበተናል፤ከዚህ ሚለንየም ምን ይጠብቃሉ፤ምንስ ይመኛሉ? አባት ዜናዊ፡-ወደ 2000 ዓ/ም መድረሱ በራሱ ድል ነው።በቀጣዩ ግን ይህ መንግሥት የገዛ ራሱን ሹማምንቶቹ ቁጥጥር ያድርግ። ተጠየቂነት ይኑር፤ በተለይም በወረዳ አካባቢ። ያጠፋ፤የበደለ፡ ችሎታ የጎደለዉ መገለል አለበት! ያኔ ጥሩ ዘመን ይሆናል። ጥፋተኛውን ሳይቀጡት እነደነገሩ ቸል ብለውት ሲያጓትቱት ይውሉና መጨረሻ ይለቁታል። ከዚያ በሗላ መጥቶ ወቃሾቹን እራስ እረሳቸውን ይኮረኩማቸዋል። እንዲህ ያለው አሰራር ካልተሻሻለ ተስፋ የለውም። ………ህዋሓት ለሁለት ሲከፈል፤ የትግራይ ህዝብ ሊፈጭ (ችግር ውሰጥ ሊወድቅ) ነው ብየ ተጨነቅኩኝ። የኔ ጉዳይ ሳይሆን ያስጨነቀኝ፤ መለስ ፖለቲካው ውስጥ ስላለ አደጋ ቢደርስበት አኔ መቸውንም ዝግጁ ነኝ። ያስጨነቀኝ ግን ትግራይ አደጋ ውስጥ ይወድቃል ብየ እጅግ ተጠበብኩኝ። አሁንም ቢሆን እኔ ህወሓት እንድትኖር የምፈልገዉ ለራሴ ለግል ብየ ሳይሆን፤ የትግራይ ሕዝብ ለህወሓት ሲል ደሙን አፈስሶ፤አጥንቱ ከስክሶ፤ልሊቱን መዉጫ መግብያ መንገዶችን እየመራ ማሳየት፤ በቀን ሲጠማቸዉ ዉሃ ምግብ፤ማረፍያና መጠለያ በመስጠት አሁን ወዳለንበት ደረጃ አደረሳቸዉ። ያገኘዉ የረባ ጠቀመታ ግን የለም። በወረዳ፤በማዘጋጃቤቶች ቢሮክራሲ ተተብትቦ ፍትህ በማጣት አየተበሳጨ፤እያማረረ ነዉ ያለዉ። መሬት ካንደኛዉ ነጥቀዉ ለሌለኛዉ ይሸጡለታል። በዛም አነሱም (እንደዛም እየሆነ) ድርጅቱ እንዲቆይ እፈልገዋለሁ። የትግራይ ሕዝብ እየቸገረውም ቢሆን ችግሩ እየቻለ ይኑር፤ ከነሱ የተሻለ አመራር ሌላ አያገኝም። የበቁ መሪዎች እንዲሆኑ ራሱ እግዚአብሄር ይርዳቸዉ። በተለይመ አሁን ለየወረዳው የተሰጠዉ ስልጣን ተቆጣጣሪ ቢደረግለት መልካም ነዉ። <… ለምሳሌ በማዘጋጃ ቤቶች በኩል እየተደረገ ያለዉ፡ ላንዱ ሰጥተዉት ቤት ለመስራት መሰረት ተጥሎበት በመሰራት ሂደት ላይ የሚገኝን ቤት አስቁመው፤ በስሕተት ነበር የሰጠንህ አና ስራዉን አቁም በማለት ከሱ ነጥቀዉ ለሌላ ሰዉ ይሸጡታል። በዚህ አሰራር ተጠያቂዉ ማን ነዉ? እነደዚህ ላለ አሰራር ለሚሰራ ባለስለጣን ጠያቂ የለዉም። አንደዚህ ያለ አሰራር እየተሰራ እያዩ አንዴት ተኩኖ ነዉ ዜጎች ከዉጭ አገር መጥተዉ የግንባታዉ ተካፋዮች ሊሆኑ የሚችሉት? ላንዳንድ ሰዎች ደግሞ በማለት የቀሙታል። ሰለዚህ በየወረዳዉ፤በፓሊስ አና በማዘጋጃቤት ፈትሕ የሚባል የለም። እገዚአበሔር ያሳይህ፦ ማዘጋጃቤት ለአንድ ፎቶ ኮፒ ሦስት ብር ያስከፈላሉ። እዉጭ ብታደረገዉ ግን ሚፈጅብህ ሃመሳ ሳንቲም ብቻ ነዉ። ስልጣን እንደ ጠመንጃ ተጠቅመዉ ይዘረፉታል፡ ዘረፋ ነዉ! ዓይን የሌለዉ ዘረፋ! ኦ! እበክህን በቃኝ ይበቃኛል፤ ደከመኝ፤ ብትለዉ ብተለዉ ጉዳዩ የሚያለቅ አይሆንም፤ ተዘርዝሮም አያልቅ> ነበር ያሉት። ዛሬም የፍትሕ ያለሕ እያለ ለ17 ዓመት የሚጮኸው ሕዝብ በሌቦች እና በመንደር ጋንጎች ቁጥጥር ስር ሆኖ የተሻለ መንግሥት እንዲመጣለት እየተማጸነ እንሆነ አንዳንድ ጥቆማዎች ይገልጻሉ። እጅግ ከተማኑ ምንጮች ያውም ለሥርዓቱ ከፍተኛ ቦታ ተመድበው ከሚያገለግሉ ክፍሎች መረጃው እንዳገኘሁት ከሆነ- መቀሌ ከተማ ለብዙ ኣመታት በጫት ሱስ ወጣቶች እንደተበከሉና በእፅ ሱስ ምክንያት የተነሳ ብዙ ትዳር በመፈረስ ላይ እንዳለ ይጠቁማሉ። በቅርቡ የደረሰኝ መረጃ ደግሞ ከተማዋ በሌቦችና በጋንጎች (ወመኔዎች) ቁጥጥር እንደሆነችና ወመኔዎቹ በየቀበሌው የተለያዩ የየራሳቸው ጋንጎች (ዘራፊ ክፍልና መቺ ክፍል/ደብዳቢ) በማሰማራት እንደ ወታደራዊ የዕዝ ሰንሰልት ተሰማርተው ኗሪውና ጎብኚው ክፍል ስጋት ላይ እንደጣሉት ያመለክታል። በትግራይ ርዕሰ ከተማ በመቀሌ ከተማ ውስጥ ባለፉት ስርዓቶች እነኚህ የከተማ ወመኔዎች መኖር ቀርቶ ወፎችና አሞራዎች እንኳ ሲዞሩ ወቅታቸውንና ያየሩን ጠባይ ተሞርክዘው ነበር ተፈጥሮን እያስዋቡ የሚዞሩት። ዛሬ ወያኔ ተግራይ ፍትሕ አሰፈንኩ ሰላም አነገሥኩኝ ባለበት በተመጻደቀበት የውሸት ሥርዓቱ “የመንደር ወመኔዎች”(ጋንጎች)እና ሌቦች ከያኔ የፍትሕ አካላት ጋር በመመሳጠር ድር/ሰንሰለት/ግንኙነት ፈጥረው ከዘረፉት ንብረትና ገንዘብ “ጉቦ”በመሥጠት የተዘረፈውና የተደበደበው ሰላማዊ ኗሪ አቤት ባለ ቁጥር ወረበላዎቹ ለስሙ ተይዘው በሳልስቱ በነፃ እንዲለቀቁ ይደረጋል። ይህ በታም እገራሚ ሊሆነን አይችልም። ካሁን በፊት በራሴ ዘገባ ከመቶ ዓለቃ አበረ መኮንን በአዲስ አበባ ባንድ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ ክፍል ሃላፊና የጣቢያ አዛዥ በነበሩበት ጊዜ የወያኔ የፖሊስ ኮሚሽነሮች እና ደሕንንት ባለሥልጣናት ጋር እንዲሁም ካንዳንድ ሚኒስቲር ደኤታዎች ጋር በመመሳጠር “በመንግሥት ጠመንጃ/መሳርያና መኪና፤እንዲሁም ደምብ ልብስ፤ሕጋዊ የፀጥታ /ፖሊስ መታወቂያ ሠነዶች” በመያዝ በየነግድ ቤቱ፤ቡና ቤቱ፤ሱቅ እና በመብራት መንገዶች መኪዎችን አስቁመው በመደዳ የተሳፋሪውን ገንዘብና ሰዓት በማስወለቅ እየረፉ ያሰቃዩት እንደነበረና በዚህም ሲያዙ ከላይ አስቸኳይ ማስጠንቀቂአና ማስፈራርያ በስልክ እየተደወለ እንዲፈቱ ይደረግ እንደነበረ የስም ዝርዝራቸዉና ከደርጊቱ ጋር ታሪኩ (የቃለ መጠይቁ ዘገባ)አቅርቤው እንደነበር ይታወሳል።ዛሬም ትግራይ ውስጥ ይሕ ሰንሰለት እንዳዲስ ታድሶ ኗሪዎች በወመኔዎች እየተርበደበዱ እንዳሉ ከሚታመን ምንጭ አረጋግጫለሁ። ዝርዝሩ በቅርቡ የማቀርበው ብሆንም፤ በጣም የሚገርመው የወያኔ አስራር “ፖሊሱ ሌባን ምርመራ ውስጥ ደብድቦ ምስጢሩን እንዲያወጣ እንዲያደርግ አይፈቀድለትም። ወያኔን የሚቃወም የፖለቲካ ሰው ከሆነ ግን ቶርች/ድብደባ ውስጥ በማስገባት ምስጢሮች እንዲወጡ ከውስጥ ለውስጥ ከበላይ በላስልጣኖች ሰንሰለታዊ ምስጢራዊ ግንኙነቶች /ትዕዛዞች ይተላለፋሉ ( በዓረና ትግራይ ደጋፊዎች የተፈጸመው ግድያና ወከባ የታዘብነው ጉዳይ ልብ ይለዋል)። በዚህ ጉዳይ ሌቦችና ወመኔዎች እንደማይደበደቡ ስለሚያውቁ የፈለገውን አድርገው ሲያበቁ ከካዱ ሌላ ቴክኒካዊ ምርመራ አይደረግም፡፤ ሌባው/ወመኔው በቂ ማስረጃ ቢቀርብለትም -ፖሊሱ መብት ስለሌለው ዳኞችና አቃቤ ሕጎቹ ሌባውን/ጋንጎቹን (ወመኔዎቹ) በነፃ እንዲለቀቁ ያደርጋሉ። ሌባ/ጋንግ/ወመኔ ላጭር ጊዜ ታስሮ እንዲፈታ ሲደረግ -የፖለቲካ ተቃዋሚ ሆነ በጥርጣሬ ሲያዝ ግን እንግልቱ ከባድ እና አስቸጋሪ እንደሆነ ታወቋል። የዮሓንስ የአሉላ አገር ባሕሯ ተዘግቶባት በታሪካዊ ጠላቶቿ እጅ ወድቃ ካንዱ ወደብ ወዳንዱ በኪራይ ስትንከዋለል የዮሓንስ ከተማም ወረበላዎች ሲርመሰመሱባት ማየት እጅግ አንጀት ያበግናል፤ያሳዝናል! አይ ወያኔ መጨረሻ ምን አድርገኸን ትሄድ ይሆን? getachre@aol.com www.ethiopiansemay.blogspot.com or Google search (Ethiopian Semay)