Tuesday, October 27, 2009

“ተክሌ” በሻዕብያ ፍቅር የተነደፈዉ የግንቦት 7(ቱ) ወጣት

ተክሌ” በሻዕብያ ፍቅር የተነደፈዉ የግንቦት 7(ቱ) ወጣት

አንደኛዉ ፎቶግራፍ ከሃዲዉ አብርሃም ያየህ አስመራ ዉስጥ የኦሮሞ የሲዳማ እና የኦጋዴን ነፃ አዉጪ መሪዎች ነን ከሚሉት ጋር በመሆን በክብ ጠረጴዛ ከሻዕብያ ራዲዬ ጋዜጠኛች የቀረበለትን ቃለ ምልልስ ሲያደርግ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ሲሆን፤ ሌላኛዉ በሻዕብያ ባለስልጣናት ቀናነት የተማረከዉ የግንቦቱ ወጣት ተክለሚካኤል አበበ ፎቶግራፍ ነዉ። ወጣቱ ECAD- Forum እተባለ የሚጠራ የህዋ ሰሌዳ (internet) አዘጋጅ ነዉ፣፣ ይህ ወጣት የሚያዘጋጀዉ ሌላዉ የሕብረተሰብ መወያያ መድረክ ቅጥ ባጣ የስሜት ስካር እና በተለያየ የዘረኝነት ሱስ የሰከሩ መድረኩን የአራዊቶች ሜዳ የሚያስመስሉት የተለያዩ “Hard Core” የሚሏቸዉ ዘረኞች የሚርመሰመሱበት Ethio discussion Forum(?) እየተባለ የሚጠራዉ ፓልቶክም እንደሰማሁት ከሆነ የሚቆጣጠረዉም እሱ ይመስለኛል፣፣ (“በፓልቶክ መድረክ ስትጮህ የሰማሗት አራዊት” በሚል ጽሁፍ 5ሚሊዬን ትግራይ ሕብረተሰብን በስድሳአምስት ሚሊዬን ኢትዬጵያዉያን የማጥፋት ዘመቻዋ ቅስቀሳ ስታካሂድ የሰማሗት አንዷ ከመድረኩ የማትጠፋ ሁሌም በስሜት የምትከንፍ የዚህ መድረክ የዘወትር ሞተር መሆኗን የተቸሁበት ያ ፎረም እንደነበር ይታወሳል)፣፣ በዓለም ዉስጥ ተወዳዳሪ የታጣለት ሯጩ ኢትዬጵያዊዉ ጀግና የቀነኒሳ በቀለን፤የመኢአዱ መሪ ኢ/ር ሃይሉ ሻዉልን፤ የኢትዬጵያ ሕዝብ አካል የሆነዉን የትግራይን ሕዝብ እናጥፋ የሚሉት ጋጠወጦች በዛዉ መድረክ መሆኑን ከተቀዱት ድምፆች ያረጋግጣሉ። ወጣቱ የግንቦት 7 ቁንጮ ወጣት ነዉ፣፣ “ልጅ ተክሌ” ከሚል ስም ጀምሮ አያሌ የብዕር ይሁን የዕዉነተኛ የመጠርያ ስሞች አሉት፣፣ አለፍ ብሎም በቅርቡ የግንቦት 7 መሪዉ “አምታታዉ በከተማ/ዶ.ር ብርሃኑ ነጋ” ዳለስ/ቴክሳስ ዉስጥ ስብሰባ ሲጠራ ይህ ወጣት (“ልጅ ተክሌ”) ከሚኖርበት ካናዳ ቫንኩቨር ለስብሰባዉ ሲገኝ “እኔ እንኳ “ደጃዝማች ነት ነበር ደስ የሚለኝ ሆኖም “ዳላሶች” የፊታዉራሪነት ማዕረግ፣ መጠርያ ሸልመዉ ላኩኝ በማለት የብዙ ማዕረግ ስሞች ሁሉ የያዘ አስገራሚ “የዘመነ” ወያኔ ወጣት ነዉ፣፣ ወጣቱ ካገር ሲወጣ ኬንያ ዉስጥ ግራ ተጋብቶ ሁሌም ሲያለቅስ በኢትዬጵያዊነት ተንከባክበዉ ለዚህ ያደረሱት የኛ ልጆች ሲነግሩን አሁን ከሚፎክረዉ አንጀት የተለየ ነበር ብለዉኛል። ያን ለባለ ታሪኮቹ/አዋቂዎቹ ልተዉና ይህ ወጣት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማር (ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ መባሉ ኩነኔ ነዉ ተብሏል በማሃይሞቹ ዉሳኔ አባባል) ብርሃኑ ነጋ አስተማሪዉ እንደነበር እና የግቢዉ ተማሪዎች ከፍተኛ አመራር አባል እንደነበር በጻፋቸዉ መጣጥፎች ነግሮናል፣፣ ለኛ ግራ በገባን ፣ እሱ በሚያዉቀዉ ምክንያት ብቻ ዋሺንግተን ድረስ ሄዶ (ዋሽንገተን ኢትዬጵያ ያዘጋጁት ስብሰባ ለመካፈል ነበር የሄድኩት ይለናል፣-) በሺዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዬጵያ ቤተሰቦች እና ወታደሮች በሻዕብያ እና በቅጥረኛዉ ወያኔ ወታደራዊ የሽምቅ ዉግያ ቅንብር በምድሪ - ባሕሪ/ ባሕረ-ምድር (ኤርትራ) ዉስጥ የተገደሉበትና ለዘግናኙ እና ለዚያ የግድያዉ ወንጀላቸዉም ሻዕብያዎች ደስታቸዉን በያመቱ የሚገልጹበት ፌስታ/ፌስቲቫል የሚሉት እሻዕቢያ ድግስ በአካል በመገኘት በቅርቡ ወጣቱ በድረ ገጹ ባሰራጨዉ ቪዲዬ ላይ ከሻዕቢያ ጋር ፍቅር መነደፉን እና በሻዕቢያ በዓል/ፈስቲቫል/ድግስ አዘጋጆች እና የድግሱ አዳራሽ ስፋት፣የጨፋሪዎቹ የኤርትራዉያን ቁጥር እንደ አሸን የመብዛቱ ትዕይንት ከመገረሙ አልፎ፣ የሻዕቢያን ሰብአዊነት፣ ለኢትዬጵያ በጎ አሳቢነት እና ቀና መሆን መስበክ የጀመረበትን “ኢትዬጵያዊነትን” እና ኢትዬጵያዊ ክብር” የሚነካ አሳፋሪ “የፖለቲካ ሽርሙጥና” የተሞላበት ፖለቲካዊ መልዕክት ማስተላለፉን ስመለከት- ከኬንያ ኤርትራ ድረስ ተጉዞ ‘የአርበኞች ግምባር የሽምቅ ተዋጊ” አመራር አባል የነበረዉ በሻዕብያ ሰቆቃ ሕይወቱ እንዳለፈች የሚነገርለት የሕግ ተማሪ እና ያዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሊቀመንበር የነበረዉ የጌታቸዉ ተስፋዬን በሻዕቢያ እና በሻዕቢያ አሽከሮች የሞሞቱን ጉዳይ ቅንጣት ያለቆረቆረዉ ይህ “ዘመናይ” የሻዕቢያ በጎነት ለመስበክ የሻዕቢያ ነገረ-ፈጅ ሆኖ ብቅ ሲል ሕሊና ላለዉ ዜጋ እጅግ አስገራሚ ነዉ፣፣ ዘግየት ብየ በጣም በቅርቡ ያነበብኩት ተስፋየ ገብረአብ የተባለዉ ደራሲ ስለ ኦነግ ሲንገበገብ ሳናብብ የተሰማኝን ያንጀቴን መቃጠል አብሮ ከዚህ ልጅ የሻዕብያ ቀናነት ሲሰብክ ሳዳምጥ “አገሬ ሰዉ ያጣሺዉ” የሚለዉን የንዋይ ደበበን ዜማ የጆሮየን በር ሲያንኳኳ ይሰማኛል። በዛዉ ሕሊናየ በማይወጣዉ አቀበት ዉስጥ ገብቶ ይጨልማል። የኢትዬጵያን ረቪዉ ድረገጽ አዘጋጅ የሆነዉ ኤልያስ ክፍሌ ስለሻዕቢያ በጎነት እና ስለ ነብሰ ገዳዩ እና ጸረ ኢትዬጵያ የሆነዉ የሻዕቢያዎቹ “ትልቁ ወረበላ” ኢሳያስ አፈወርቅ የኣመቱ ሰዉ ሆኖ በኤልያስ መመረጡና በድረገጹም አሸብርቆ በመሰበኩ በአብዛኛዉ ኢትዬጵያዊ እንደተኮነነ እና ከመድረኩ እንደተገለለ የሚታወቅ ነዉ፣፣ የወጣቱ አስገራሚ ነገር - በኤልያስ ክፍሌ የተገረመዉ ጆሮአችን ሳያጋግም የሻዕብያ ቀናነት መስበክ የመጀመሩን ዘመቻዉ ስመለከተዉ፣ ተቃዋሚዉ ክፍል “በአፍቃሬ ሻዕብያ” የተበከለ መሆኑን አመላካች እንደሚሆን መጠራጠር አይቻልም፣፣ ወጣቱ የለጠፈዉ የአዉዲዬ-ቪድዬ ቅስቀሳ ስንመለከተዉ ስለ ኢትዬጵያ ጉዳይ የሻዕቢያ አሳቢነት፣የዋህነት፣ተባባሪነት እና ቀናነት ሰበካዉ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በወጣቱ ብቻ ተወስኖ የቀረ ቅስቀሳ አልነበረም፣፣ ከግንቦት 7 መሪዉ ከብርሃኑ ነጋ ጀምሮ የዛሬዉ የግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተጠሪ እና ድሮ የበየነ ጴጥሮስ “የደቡብ ሕዝቦች” ፓርቲ የዉጭ ተጠሪ የነበረዉ “ኤፍሬም ማዴቦ” ተባለዉ ግለሰብም ከሻዕቢያ ቀርቶ ከሰይጣንም ጭምር እንተባበራለን በማለት “የፖለቲካ በራቸዉም እንደ ሸርሙጣ ቤት-“ለማንም ክፍት” መሆኑን” በኩራት ሲገልጹ በዛዉ ቪዲዬ ይደመጣል፣፣ (ወጣቱ የሻዕብያ ዲፕሎማቶች ተገናኝቶ የታዘበዉ ቀና አስተሳሰባቸዉን የገለጸበት ድጋፉን የኤፍሬም ማዴቦን ቃለ መጠይቅ የሚለዉን ያዳምጡ) ፣፣ እንደዚህ ያለ የማሳሰቢያ መልዕከት ሳስተላልፍ አንዳንድ ሰዎች የሚያንገራግሩ አይታጡም፣- የተለመደ ባሕርይ ነዉ፣፣ አብራሃም ያየህ ስለ ሻዕብያ ደግነት ስለ ኢትዬጵያ በጎነት መቆርቆር መስበክ ሲጀምር በየመጽሄቱ እና ጋዜጣዉ እንዲሁም በኢንተርነቱ ተቃዉሞየን እና ማስጠንቀቅያየን እንዲሁም ዉግዘት እንዲደርስበት ሳስገነዝብ ብዙ ስድብ እና ዘለፋ እንደደረሰብኝ ፋይሌ ዉስጥ ለታሪክ ያስቀመጥኳቸዉ ጽሁፎች እስካሁን ድረስ አሉ፣፣ ‘ወጣቱ” በዚህ አሳፋሪ ክህደት እና ሰበካ ዉስጥ ራሱን ሲከትት የመጀመርያ ይፋ ማስጠንቀቅያ ስገልጽም እሚያጉረመርሙ የድርጅቱ አባሎች እንደሚኖሩ የታወቀ ነዉ፣፣ ታሪክ ቀን/ፍርድ እና ሃቅ ቢያዘግሙም ሄደታቸዉ ያጠናቅቃሉ፣፣ ሂደቱ ሲጠናቀቅ አጉሮምራሚዎችም ሆኑ የሻዕብያ በጎ እና ቀናነት ሰባኪዎችም አብራሃም ያየህ የሃፍረት ጋቢዉ ተከናንቦ መደበቂያዉ ዉስጥ ገብቶ ከመድረኩ እንደተሰወረዉ ሁሉ፣ እንኚህም ከጊዜ ሂደት አሰሩን/ኮቴዉን መከተላቸዉ የማይቀር እዉነታ ነዉ፣፣ ዉድ ወገኖቼ፣- መቸም አገራችን አሳፋሪ መድረክ ዉስጥ እንዳለች ለብዙ ኣመታት ብገነዘብም፣ በቅርቡ የራስ መንገሻ ስዩም የትግራይ ጉብኘታቸዉ ራዲዬ መርሃዊት የተባለዉ ዋሺንግተን ዲሲ የሚገኝ የትግርኛ ራዲዬ ጋር ያካሄትን ቃለ መጠይቅ ካዳመጥኩ በሗላ እና ልዑሉ የተጠቀሙባቸዉ የወያኔ ትግራይ የአፓርታይድ ክልሎች መጠርያ “ቃላቶች” (የአማራ ክልል ትግራይ ክልል….ወዘተ ወዘተ……..) እያሉ እና እንዲሁም ለወያኔ ትግራይ ባንዳዎች ያላቸዉ ከበሬታ “የትግራይ መንግሥት መስተዳድር ፕረዚዳንት “ክቡር” ጸጋይ በርሄ፣ “ክቡር” ጠቅላይ ሚኒስቴር……..”ክቡር”.,,,,,”ክቡር”,,,,፣) በማለት ታሪክ አጉዳፊ የወያኔ ባንዳዎች የፈጸሙዋቸዉ መንግስታዊ እና ልማታዊ ጠቅላላ የሥራ አፈጻጸም ግምገማቸዉ በአድናቆት ሲገመግሙ እና ባንዳዎቹ ላደረጉላቸዉ እንክብካቤ እና ያሳይዋቸዉ ፍቅር በክብር አጅበዉ ያስጎበኛቸዉ ስፍራዎችን በሚመለከት ሲገልጹ ፣ በሺዎቹ የልዑሉ (ኢዲዩ) አርበኞች ተዋጊዎች እና በሺዎቹ የሚቆጠሩ የትግራይ ታላለቅ ሰዎች እና ዜጎች በግፍ የገደሉ እና ያጠፉ ለፍርድ መቅረብ ነበረባቸዉ “የወያኔ ትግራይ ባንዳዎች” በሰብአዊነት እና በአገር ወዳድ አሳቢነት በበጎ ቃላት “ሲከምሯቸዉ” ቃለ መጠይቃቸዉን ሳዳምጥ ግራ የገባዉ ጀሮየን እንዴት እንደማጽናናዉ ሳስበዉ ይበልጥኑ ያች አገር በብዙ ልጆቿ እንደተከዳች እና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሳስበዉ እጅግ ያሳስበኛል፣፣ ልዑላን ተብለዉ ከጀግኖች ዘር የተገኙ ያገሪቱ ዋርካዎች ለጠላት እጃቸዉ ሰጥተዉ ወደ “ክህደት በረት” ዘልለዉ ሲገቡ በሌላ በኩል ደግሞ የኢዲዩ አርበኞቹ ጎንደሬዉ እነ “አጣናዉ ዋሴ” (የጋደኛየ የአዳነ አጣናዉ ወላጅ አባት እና የማዉቃቸዉ ለጋስ፣ ደፋር፣ጭምት አባት መኖራቸዉን በቅርብ ስለማቃቸዉ! “ልጃቸዉ አዳነ የት እንዳለ አላወቅኩም እንጂ”) በክብር ተጀንነዉ ይህች ብስብስ ዓለም በጀግነንተ እና በኩራት ሲያልፏት በማየቴም የሞተዉ ሃሞቴ ተጽናንቶ ሳይ ይህች አለም በምን ብዕር መተርጎም እንደሚቻልም ይገርመኛል፣፣ ዛሬም አገር ያድናነሉ የምንላቸዉ ከእኛ በዕድሜ ያነሱ እና በጉልበት የጠነከሩ ወጣቶች ወደ አሸናፊዎች እና ወረበላዎች በረት እጃቸዉን እየሰጡ ተምበርክከዉ ወረበላዎችን ለእርዳታ ድረሱልን እያሉ ሲለማመጡ ደጃፋቸዉ ድረስ እጅ እየነሱ ሲጠይቁ፣ ያገሪቷ የወደፊት መጻኢ ዕድል አስቸጋሪ እና ክፉ ሕይወት ይሆን? ብየ ራሴን አስጨንቃለሁ፣፣ ወጣት ‘ተክሌ” አንዳንድ ሰዎች ከዚህ በፊት በብዙ ሁኔታዎች ሲጠረጥሩት ካነበብኳቸዉ በዝግ/በዟሪ ኤልክትሮኒክ ከሚላኩልኝ መልዕክቶች/ ደብዳቤዎች መገንዘብ ችየ እንደነበር ባዉቅም፣ ልጁ ከስሜት አለ-መቆጣጠር እና ከዕድሜ ተለምዶ ማነስ ሊሆን ይችላል በሚል መተቸቱ ቸል ብየ እንደነበር አስታዉሳለሁ፣፣ የልጁን ዘብራቃነት መታዘብ የጀመርኩት የሆላንድ አገር ኗሪ ሃኪም ዶ/ር አሰፋ ነጋሽን አብዛኛዉ በዉሸት የጦቆረ ጽሁፍ በድረ ገጹ እንዲለጠፍ ፈቅዶ ስመለከት እና በዛዉም እንደረካበት ሳስተዉል፣ ለልጁ ያለኝን አመለካከት በቅርብ እና በጥሞና እንድከታተል አስችሎኛል፣፣ ከጥቂት ጊዜ በሗላ ልጁ በቪዲዬ ቀረጽኳቸዉ ቃለ መጠይቅ አደረግኩላቸዉ እያለ የሚያቀርባቸዉን እና የራሱ ጽሁፎችን ሰከታተል እያደረ የወጣቱ ዉዥምብራምነት እና ወዴት እያዘገመ እንደሆነ ፍንጭ አገኘሁባቸዉ፣፣ በዚህ በቅርቡ ተከታታይ ከዳላስ አስከ ቫንኮቨር (?) የግንቦት 7 ሰብሰባ ዘገባዉ ሲያትት “ኤርትራ መሄድ እንዴት እንደናፈቀኝ ታወቃላችሁ አይደል?” ብሎ አንባቢን ሲጠይቅ “ብዙዎቻችን አንባቢዎቹ “በአግራሞት ነበር ሰቅዞ ያስያዘን”፣፣ አባባሉም ምን እንደሆነ በፎሮሙ እንዲያብራራልን የጠየቅነዉ ነበርን፣፣ ከጠያቂዎቹም አንዱ እኔ ነበርኩ፣፣ ወጣቱ በሻዕብያ እንደተነደፈ ከብዕሩ አጣጣል ስጠረጥር የነበረዉን እንቆቁልሽ መልሱ በቅርቡ በራሱ ዌብ ሳይት “ኢካድ-ፎረም’ በበለጠ ይፋ አድርጎ ሲያቀርበዉ ፣ ”ክዉ” ብየ ነበር የቀረሁት፣ (ለወደፊትም በቀጣይ በቪድዩዉ ይቀርባል ብሎናል)፣፣ የ “ተክሌ”ን ክንብንብ መገለጥ ድንገተኛ ተጓዳኝ ሆነዉ ሳገኘዉ፣ እዉነትም ይሄ ተቃዋሚ የሚባል “በአፍቃሬ ወያኔ እና በሻዕብያ” የተበከለ መሆኑን መረዳት ያስቻለኝ መረጃ አንዱ ይሄዉ የተክሌ በግልጽ ወደ ሻዕበብያ በረት መግባት እና ስለ ሻዕቢያ ወረበላዎችና ዝና በጎነት ሰበካዉ የመጀመሩ ጉዳይ “ኤልያስ ክፌሌን” የተካዉ አዲሱ የግንቦት 7 ወጣት “አፍቃሬ ሻዕያ” ነዉ ማለት እንችላለን፣፣ ከዚህ ሌላ ምን ማለት ይቻላል? //-/ www.Ethiopiansemay.blogspot.com