Wednesday, June 17, 2009

ሙሉጌታ አረጋዊ ተቃዋሚዉን “ሪሳይክል/ሎች” ናቸዉ አለን?

ሙሉጌታ አረጋዊ ተቃዋሚዉን “ሪሳይክል/ሎች” ናቸዉ አለን? ጌታቸዉ ረዳ http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/
አቶ ሙሉጌታ ማናቸዉ ለምትሉ ሰዎች በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሙያ የስደተኞች ጠበቃ (Attorny)ናቸዉ፣፣ ባለፈዉ ሰሞን ሙሉጌታ አረጋዊ ከዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጋር በነፃነት ራዲዮ ላይ ያደረገዉ የራዲዮ ዉይይት ሰፊዉን ዉይይታቸዉ በመጠኑ ቀንጭቤ ለእይታ አቅርቤላችሁ እንደነበር ይታወሳል፣፣ በዛ ዉይይት ደ/ር አሰፋ ነጋሽ ለጠየቀዉ የጎሳ ፌደራሊዝም ቀያሾች የሆኑትን እነ ገብሩ አስራት ከመለስ ዜናዊዉ ቡድን ሲለዩ የእነ ገብሩ አስራት ቡድን ደጋፊ በመሆን ለጎሰኞቹ ድጋፍ የመስጠቱን ጉዳይ አስመልክቶ ጥያቄ ሲመልስ ‘እኔ የነ ገብሩም ሆነ የማንም ቡድን ደጋፊ ሆኜ አላዉቅም” በማለት አጠንክሮ ለመለሰዉ “አሉታ”፣ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ የነ ገብሩ አስራት እንጃ ደጋፊ እና እምባ አፍሳሽ ሆኖ በዋሽንግተን አካባቢ (ምናልባትም በመላ ዓለም ላሉት የትግራዋዮች ማሕበረሰብ) ለሚኖሩ የትግራይ ማሕበረሰብ ቃል አቀባይ በመሆን ድጋፉን ያስተላለፈበት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ቅጅ እንዳስነበብኳችሁ ይታወሳል፣፣ ዛሬ ደግሞ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ በግንቦት 25/2002ዓ.ም. “ራዲዮ መርሃዊት” በመባል የሚታወቀዉ “የመንግሥት የተቃዋሚዉም ደጋፊም” አይደለሁም ዓይነቱ ‘ዉሉ የጠፋ”-የሙሉጌታ አረጋዊ ዓይነት “የፖለቲካ አቋም”-ያለዉ ድሮ የአንጃዎቹ ጠንካራ ደጋፊ በመሆን ከኢትዮጵያን ኮሜንታተር (ደጀን)ራዲዮ ጋር አብሮ ሲያዘጋጅ መለስ ዜናዊን በቃላት ሲወርፈዉ የነበረ “ሃብቶም ተኽለ”-የተባለ የራዲዮ መርሃዊ (ስድስት ወር እድሜ ያለዉ አዲስ ራዲዮ) አዘጋጅ ጋር ባደረገዉ የትግርኛ ቃለ መጠይቅ፣- ግንቦት7-የተባለዉ ድርጅት የትግሬዉ ማሕበረሰብ በትግሉ ያለመሳተፍ ቅሬታ እና ጥሪ ያስተላለፈዉ የድርጅቱ ጥሪ አስመልክቶ (እንደ ሙሉጌታ እና እና እንደ አዘጋጁ አባባል)ሙሉጌታን ለጠየቀዉ ጥያቄ ሙሉጌታ አራጋዊ ሲመልስ “ትግሬዎች በዉጭ አገር በሚካሄዱ ሰላማዊ ሠልፎች አይሳተፉም፣ ቢሳተፉም በጣት የሚቆጠሩ ናቸዉ፣ - አብዛኛዎቹ መንግሥትን የሚደግፉ ናቸዉ እያሉ ትግራዋይ ባንድ ወገን ትግርኛ ቋንቋ የማይናገረዉ ክፍል ደግሞ በሌላዉ በረት የሚለዩን እነማን ናቸዉ?” እነዚህ “ሪሳይክልድ” የሆኑ ሃይሎች ናቸዉ፣፣ በዉጭ አገር መንግሥትን እንቃወማለን የሚሉት ሰላማዊ ሠልፍ የሚያዘጋጁ ክፍሎች ምን ዓይነት ሰዎች ናቸዉ?(ብልህ ብትጠይቅ) ልንገርህ!?በዚህ በዋሽንግተንና በኖርዝ አሜሪካ የተደረጉ ሠላማዊ ሰልፎች የተከታተለ ሰዉ ሠላማዊ ሠልፍ የሚያደራጁት ሰዎች የተወሰኑ ሰዎች ናቸዉ የሚያደራጁት፣- በተደጋጋሚ!፣፣ “ሪሳይክልድ”- “ሪሳይክልድ!” ሲሆኑ ነዉ የምታየዉ፣፣ በተለያዩ ጊዜ አንድ ጊዜ “መላዉ አማራ” በሌላ ጊዜ “ኢደፓ” አንድ ጊዜ “ኢዲዩፒ” አንድ ጊዜ “ኤ ኤፍ ሲ” አንድ ጊዜ “ቅንጅት” አንድ ጊዜ “አንድነት” ሌላ ጊዜ “ግንቦት 7” እየሆኑ ታያቸዋለህ፣፣ ከመጀመሪያ ጊዜ ከጥንት ጀምሮ ለአስራ ስምንት ዓመት እነዚህ ድርጅቶች ናቸዉ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲቃወሙ የምናያቸዉ፣፣ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ድርጅቶችን የሚመሩትም ቢሆን የሚታወቁት ያዉ አንድ/ሪሳይክልድ የሆኑ የምናቃቸዉ አዲስ ያልሆኑ ሰዎች ናቸዉ፣፣ ሌሎቻችንን በጎሰኛነት ሲከሱን “የአንድነት ሃይሎች ነን” “አንድ ነን” ይበሉ እንጂ እነሱም የምታያቸዉ “አንድ አይደሉም”፣፣ ዛሬ አንድ ይሆናሉ፣ ነገ ሲጣሉ ሲናከሱ ታያቸዋለሁ፣፣ ዋሽንግተን ዲሲ መጥተዉ መኣት ገንዘብ ያዋጣሉ ገንዘቡ የት እንደሚገባ አይነግሩህም፣፣ “የኢትዮጵያ ሕዝብ -ማይነስ - (ሲቀነሰዉ) ተጋሩ” ባንድ ወገን (ቀደም ብየ እንደነገርኩህ)…. (ነዉ ራሳቸዉን የሚያዩት)፣፣ እኛ የምንወክለዉ ትግሬዎች ያልሆኑ የኢትዮጵያ ሕብረተሰቦችን ነዉ ይላሉ፣፣ ስለዚህ እነዚህ ምንድ ናቸዉ “ሪሳይክሊንግ” የሚባል ነገር አለ አደለም?!አንድ ዕቃ ዛሬ ተጠቅመህበት ነገ ትጨፈልቀዉና ሌላ ዓይነት ዕቃ አድረግህ ታወጣዋለህ- ነገር ግን ዉስጡ ያዉ “ሪሳይክልድ” የሆነ ነዉ፣፣ ዉድ ወንድሜ አቶ ሙሉጌታ፤- “ተቃዋሚዉ የአንድነት ሃይል” ትግሬዉን አልወክልም ብሎም አያወቅም፣፣ የትግራይ ገበሬ ኗሪ ሕዝብ በሻዕቢያ ተከብቦ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ ሻዕቢያ ሲኦል ሲያሳየዉ፣ ወያኔ ትግራይ መሪዎች ሻዕቢያን ለብቻቸዉ መቋቋም አቅቷቸዉ በእርስዎ አነጋር “ኢትዮጵያ ማይነስ ትግራይ”የሚሉትን አነጋገርዎ ልጠቀም እና ያ ሃይል ነበር (80ሚሊዮን -5ሚሊዮን “75 ሚሊዮኑ ኢትዮጵያዊ) ዛሬ መለስ እየቦጨቀ ሚጥላት ሰንደቃላማችን ዓይነት ያላት ቀለም የያዘ ሕዝብ እያዉለለበለበ ነበር ወደ ትግራይ መጥቶ ህዝቡን ከመንገላታት ያዳነዉ፣(የምኒሊክ ዓድዋዉ ዓይነት ወገናዊ እርዳታ ተደግሟል)፣፣ ይህ የተቃዋሚዉ ክፍል ነበር ከፍተኛ ድጋፍ፣ አስተዋጽኦ አድረጎ በገንዘብም በፕሮፖጋንዳም በሞራልም በፕረስም የራሱ ቤተሰብና ዘመድ ወደ ባድሜ አስልኮ በደሙ የትግራይን ሕዘብ ከሻዕቢያ ወላፈንና ዉርደት ያዳነዉ፣፣ ታዲያ ይህ ተቃዋሚ እንዴት ሆን ነዉ “ትግራይን አንወክልም ይላሉ” ሚሉን አቶ ሙሉጌታ? መቸ ነዉ እንዲህ ያሉት? በየትኛዉ ፕረስ መግለጫቸዉ? አቶ ሙሉጌታ ንግግሩ ይቀጥል እና “ትገሬዎች ባንድ በኩል፣ የተቀረዉ ኢትዮጵያ ባንድ ጎራ ናቸዉ የሚሉን እንኚህ ሰዎች (ሪሳይክሎች)እነሱ እንደሚሉን “እኛ ትግሬዎች አንድ አይደለንም ይሉናል”፣፣ እንደዚህ የሚባል ነገር የለም፣፣ አንድ ቋንቋ የሚናገር፣ (አንድ ጎሳ)አንድ አይነት ጭንቅላት የለዉም፣፣ “የተገጠመብን” (ፕላንትድ ማለቱ ነዉ) አንድ ዓይነት ተመሳሳይ ራስ (ጭንቅላት/አስተሳሰብ ማለቱ ነዉ)የለም፣፣ ግለሰቦች የተለያዩ ራሶች አሏቸዉ፣፣ እና ትግሬዎች አንድ ናቸዉ ስትል “ጎሰኛነትን ማንፀባረቅ ነዉ”፣፣ ትግራዋይ እንደ አንድ ግለሰብ አድርገህ ማየት አትችልም፣፣ እነዚህ ግን እንዲመቻቸዉ (ጎሰኝነታቸዉን በሽፋን ለማንፀባረቅ ማለቱ ነዉ) “መንግሥትና ሕዝብ ኣንድ ነዉ ይሉሃል”፣፣ መንግሥትና ሕዝብ አንድ አይደለም፣፣ሌላ ቀርቶ የተለያየን ሰዎች ለቃለ መጠይቅ ስንቀርብ እንኳ አንድ ዓይነት አመለካካት አናቀርብም፣፣ ሌላ ቀርቶ የትግራይ ሕዝብ አንድ ነዉ ማለት ቋንቋችን እንኳ ከኣዉራጃ ወደ አዉራጃ ተለያየ ነዉ፣፣ አማራዎችም “The same thing” ናቸዉ፣፣ ዲሲ ያሉት ራዲዮ ጣብያዎች እንኳ ብትመለከት “አንድ ኢትዮጵያ የሚባል አለ፣ነጻነት ለኢትዮጵያ የሚባል አለ፣ ኢትዮጵያዊነት የሚባል አለ፣ ሕብረት የሚባል አለ፣ እነዚህ ሁሉ በአማርኛ ቋንቋ ሚተላለፉ ራዲዮ ጣቢያዎች ናቸዉ፣፣ የእነዚህ ራዲዮ ጣቢያዎች አዘጋጆች፣ በአንድ ሻይ ቤት እንኳ ቁጭ ብለዉ ተስማምተዉ ሊጠጡ የሚችሉ ሰዎች አይደሉም፣፣ Actually,እርስ በርሳቸዉ አንዱ በሌላዉ ዘመቻ ሲያካሂዱ ናቸዉ የሚዉሉት፣፣ እንኳን ለኢትዮጵያ ሕዘብ ሊወክል ቀርቶ አንድ ራዲዮ ጣቢያ ከአንድ ራዲዮ ጣቢያ አዘጋጅ በሰላም ቁጭ ብለዉ መወያት የማይችሉ ናቸዉ፣፣ ስለዚህ አማራዎች የሚባሉትም አንድ ዓይነት አንድነት ያለቸዉ ሰዎች አይደሉም፣፣ በጎንደር በሸዋ ወሎ ሸዋ ያለዉ አማራ አንድ አይነት አመለካከት አለዉ ማለት አትችልም፣፣ የሰዉ ልጅ አፈጣጠር አና አስተሳሰብ ያለመረዳት ድክመት የመጣ እምነት ነዉ፣፣ ስለዚህ እነዚህ የአንድነት ሃይሎች ነን(ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እንቆረቆራለን እንወክላለን)የሚሉት የግል ፍላጎታቸዉን ለማራመድ “የ ኢትዮጵያ አንደነት አንድ ነዉ” ይላሉ፣፣ ልክ የአሜሪካ ሕዘብ ፍላጎት አንድ ነዉ እንደማለት ነዉ፣፣ የአሜሪካ ሕዝብ ፍላጎት አንድ ሊሆን አይችልም፣፣ እንኳን የኢትዮጵያ ህዘብ ፍላጎት አንድ ሊሆን ቀርቶ “የአንድ ቤተሰብ አባል እንኳ የተለያዩ ፍላጎት ስላላቸዉ-አንድ ፍላጎት አላቸዉ ማለት አይቻልም” (በሙሉጌታ አባባል አንድ የሚያደርጋቸዉ ማእከላዊ “የሃገር ህልዉና እና ያገር ፍቅር እና ሉኣላዊነት” ጉዳይም እንደ መናኛ ዕቃ የዕለት ተለት ፍላጎት ሁሉ ሕዝቦች የጋራ እሴት የሆነ የአገር ሕልዉና/ኢንተረስት የተለያየ ፍላጎትና አስተአየት እንዳለን አድርገዉ ወደ ታች ያወርዱናል።ተከብሮ የመኖር ፍላጎት፤ በዉጭ በጠላት እና በዉስጥ ጠላት ስንነደፍ/ስንጠቃ ባድሜ ላይ የታዉ “የጋራ ሕዝባዊ ፍላጎት”የረሱት ይመስላሉ)፣፣ ይቀጥሉ እና ባገር እና ባንደነት ጉዳይ የሚያክል ትልቅ ጉዳይ “ሂፕክሪት ፍልስፍና” ዉስጥ ሲገቢ እንዲህ ይላሉ “ የወንድም የሴትም ፍላጎት እንደዚሁ የተለያየ ፍላጎት አላቸዉ፣፣ እና ትግሬዎች ከኛ ጋር አላበሩም የሚሉት …. Look …(እነሱም አንድ አይደሉም) “ትግሬዎች ለምን ያስፈልጉሃል?ለምን ድ ነዉ ትግሬዎችን ለይተህ ከኛ ጋር አብረዉ ድምፃቸዉን አያስተጋቡም የሚሉት?ስንት አገዉ ይሳተፋል?ስንት ዓፋር ይሳተፋል ስንት ኦሮሞ ይሳተፋል ስንት ሶማልያ ይሳተፋል?ይታወቃል? ለምንድ ነዉ ትግሬዎች ዓይን ዉስጥ የገቡት?ምክንያቱም ትግሬዎች ስልጣን ዉስጥ ስላሉ ከሚል የተነሳ ነዉ፣፣” ይሉና በመቀጠል
ስለዚህ የነሱ ሰዎች (ትግሬዎች-ወያኔዎች ማለታቸዉ ነዉ) ስልጣን ላይ ስላሉ “ተጠቃሚ እስከሆን ድረስ ምን አገባን ይላሉ” ወደ ሚል ትርጉም እንዲመጣ ነዉ ጥረት እየተደረገ ያለዉ፣፣ የተቀረዉ ኢትዮጵያዊ ቅር ብሎት በተቻለ መጠን “ቆስቁሰህ” “እንዲበሳጭ አድርገህ በትግሬዉ ላይ እንዲነሳ ለማድረግ ነዉ”፣፣ስለዚህ ትግሬዎች ለምንድነዉ እኛ ጋር የማይተባበሩት የሚሉት ነገር ፣ መጀመሪያ ነገር “እኛ”የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም ትግሬ ያልሆነ“Non-Tigrayan”የሆነ Populationአንድ-ነዉ-የሚባል (አነጋገር/እምነት) ልክ አይደለም፣፣ ምንም ማስረጃ የለዉም፣፣ እንደነገርኩህ “ቅንጅት እንኳን አንድ አይደለም”፣፣ የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ስትመለከት ራሱ “አንድ” አይደለም፣፣ እነ ልደቱ እና እነ ሃይሉ ሻዉል ቁጭ ብለዉ ሻይ ሊጠጡ አይችሉም፣፣ ሁለቱም ግን ከአንድ ድርጅት የወጡ ሰዎች ናቸዉ፣፣የግንቦት 7 መሪዎች “ትናንት” ምን ይሉን ነበር? Look! ደ/ር ብርሃኑ እስር ቤት ዉስጥ እያለ ጻፈዉ የተባለዉ መጽሓፍ ስትመለከት የሚሰብከዉ ስለ “ሰላም” ነዉ፣፣ አንድ ኣመት ሳይቆይ “ጦርነት” ሲል ያስተዛዝባል። “ምን ዓይነት ሕሊና ነዉ” ትላለህ፣፣ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ “ትናንት ከኢሕአዴግ” ጋር ኖሮ ‘ኢሕአዴግን’ እንዳላደራጀ እና የኢሕአዴግ ወታደር እንዳላደራጀ፣ ዛሬ ዞር ብለህ “የወታደሮችን ቁጥር ዘርዝረህ”-አብዛኛዎቹ “ትግሬዎች” ናቸዉ ብለህ You know የጎሳ መርዝ ለመበተን መሞከር፣ ከአንድ የኢትጵያ አንድነት ለመጠበቅ እታገላለሁ ከሚል ክፍል የሚጠበቅ አይደልም፣፣ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነዉ፣፣….” በማለት “ሂፒክሪት” የሆነ ለሙግት የማያመች “ብር አምባሩ” የተደበላለቀ “ዉሉ የጠፋ” ነገር በመግባት “የወያኔን የጎሳ አደረጃጀት እና ያድልዎ ስራ “ክደኑት” (የወታደሩ ክፍል አብዛኛዉ በትግራይ ታጋይ የተያዘ ቢሆንም -ዝም በሉ!ኢ-ፍትሃዊ ስራ አትዋጉ ነዉ የሚሉን)። አስኪ ከኔ በበለጠ የተረዳችሁት ብትኖሩ ከሰጠዉ መልስ የተረዳችሁት ከሆነ ቀስ ብላችሁ አንብቡትና ለማስመር የፈለገዉ/ብልቱን ያገኛችሁት ከሆነ ተቹበት “እባካችሁ!”፣፣ አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ እኛን “ሪሳይክሎች” ብለዉናል፣ እና አስኪ አንዳንድ በስንት መከራ ደጋግሜ ለመረዳት ሞክሬ ሊገባኝ ያልቻለዉን ለናንተ ትቼ -ጥቂቶቹን በበኩሌ የተረዳሁዋቸዉ አንዳንዳንዶቹን በሚቀጥለዉ በሌላ አምድ ሊሂቁንና እና የትግራይ ህብረተሰብ ያለዉ አንድነትና ልዩነት ልዩ አስተያየት አቀርብላችሗለሁና ያንን በሚመለከት ጠብቁኝ፣፣ እስከ እዛዉ ድረስ ግን አቶ ሙሉጌታ አረጋዊን ለማስታወስ የምፈልገዉ “የተለያዩ ራዲዮኖች/ሚዲያዎች እና የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተለያየ ስም የያዙ ተቃዋሚ ድርጅቶች አለመስማማት ይኑራቸዉ እንጂ- (እርስዎ ሪሳይክሎች- የሚሏቸዉን ማለቴ ነዉ) አብዛኛዎቹ (አሰምርበታለሁ ---- “አብዛኛዎቹ”) ተቃዋሚ ድርጀቶች ልዩነታቸዉ የስትራተጂ ሳይሆን “የታክቲክ”ልዩነት መሆኑን ላስታዉሰዎ እፈልጋለሁ፣፣ ወያኔን እንዴት እናስወግድ በሚለዉ ላይ ልዩነት ያላቸዉ እንጂ “የወያኔ ተቃዋሚም-ደጋፊም”-አይደለንም በማለት አይደለም እየተጨቃጨቁ የሚያዩዋቸዉ፣፣ የትግራዩን ገበሬ ፖለቲካ ዉስጥ ሳናስገባ (ኤሊቱ ነዉና ወሳኙም ለዚህ ጉድ ያደረሰዉም) የትግራዩ ሊሂቅ/ኤሊት እንደ “አሰር ግመል” “ወደ ሌላ እንዳያይ -አይኑ በጨርቅ ተጨፍኖ” ባጭር የገመድ ሉጓም ከቀምበር እንጨት ጋር ታስሮ ባንድ ጠባብ“ክብ”አዉድማ ሙሉቀን ዙርያዋን እየዞረ ሰሊጥ እንደሚጨምቅ ገምል “ደግሞ ደጋግሞ”-በጎሰኞች ጠባብ አወድማ ዙርያ እየዞረ “የወያኔ መሪዎች ወደ አጠመዱለት የጎሰኛነት ወጥመድ” በጭፍን ስለ እነሱ ደህንነት እና ሙሉ ጤንንት “እንባ”-ባደባባይ የሚያፍስ እንደ እናነንተዉ የትግራዩ ኤሊቶች”እንዳልሆኑ ግን በእርግጠኝነት ልነግርዎ እወዳለሁ፣፣ “ሪሳይክለድ!” ሲሆኑ ነዉ የምናያቸዉ በማለት በተለያዩ ጊዜያት አንድ ጊዜ “መላዉ አማራ” በሌላ ጊዜ “ኢደፓ” አንድ ጊዜ “ኢዲዩፒ” አንድ ጊዜ “ኤ ኤፍ ሲ” አንድ ጊዜ “ቅንጅት” አንድ ጊዜ “አንድነት” ሌላ ጊዜ “ግንቦት 7” እየሆኑ ታያቸዋለህ፣፣ ከመጀመሪያ ጊዜ ከጥንት ጀምሮ ለአስራ ስምንት ዓመት እነዚህ ድርጅቶች ናቸዉ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲቃወሙ የምናያቸዉ፣፣ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ድርጅቶች የሚመሩም ቢሆን የሚታወቁት ያዉ አንድ የሆኑ የምናቃቸዉ አዲስ ያልሆኑ “ሪሳይክልድ” ሰዎች ናቸዉ” ያሉዋቸዉን ተቃዋሚዎች አርስዎ እንባ ያነቡላቸዉ “ባለ አንቀጽ 39ኞቹ ዓረናዎች”ላይ እና እርስዎ “ለመቃወምም ለመደገፍም- “ፈራ ተባ” ለሚሉሏቸዉ መለስ ዜናዊንን “ጥይት ሳይተኩሱ” በፖለቲካዉ መስክ እርቃናቸዉን ያጋለጡ እነኚህ “ሪሳይክሊድ-ተቃዋሚዎች”፣-እንጂ የእርስዎ “ቡጥቡጥ-መስመርዎ”(የኔዉ ሃማቱማ እንዳለዉ-“ዝብርቅርቅ ፖለቲካ” )ዎ፣ እንዳልሆነ እንዲገነዘቡት አፈልጋለሁ፣፣ ለመሆኑ -አንዴ “ማገብት አንዴ “ተሓሕት”፣ አንዴ “ህወሓህት” አንዴ “ማሌሊት” አንዴ “ኢህአዴግ” አንዴ “ተሃድሶ” አንዴ “ዓረና” አንዴ “መጻኢት ትግራይ” ወዘተ….እያሉ ለ35ዓመት እስካሁን ድረስ እንደ ነገሥታት በሥልጣን ዙፋን ላይ የሚገኙ የትግራይን ገበሬ እና የትግራይ አዛዉንቶች በእሳት እየለበለቡ “ሲኦል’-ኑሮ እንዲገፋ ምክንያት የነበሩት “ሪሳይክልድ ወያኔዎች” ናቸዉ ለማለት ሳይደፍሩ (ያዉም እርስዎ የነሱ እምባ አዉራጅ ሆነዉ) ዘብ እና አገር በድለዋል እና ከስልጣን ይወገዱ ስላሉ “ሪሳይክልድ ናቸዉ” ማለትዎ ትንሽ ሕሊናዎ አይከብደዎትም? ለመሆኑ ጎሰኛ ስርዓትን የሚያራምዱ፣ የባሕር በራችን የዘጉብን ብሔራዊ ወንጀለኞች “ይወገዱ” ሲባል “እኔ እዛ ዉስጥ አልገባም” “ይወገድ የሚለዉ ቃል “ይከብደኛል” ሲሉ “ሪሳይክልድ ሊባሉ የሚገባቸዉ ”ብሔራዊ ወንጀለኞች እና የጎሳ ነገሥታትዎን“ “ከይወገዱ” በላይ ምን እንዲባል ፈለጉ? የአንድነት ሃይሎች ሊባሉ የቻሉት ወይንም አርስዎ “ኢትዮጵያን የወከሉ መሆናቸሁን ማስረጃ አቅርቡ ቢባሉ መልስ የላቸዉም” በማለት ዉሉ የጠፋ ነገር መከራከርዎ በእዉነት እርስዎ የሕግ ምሁር ነዎት “የሚጠይቁት መረጃ ከወያኔ ወይስ ከዓረና ቢያመጡለዎት ይመርጣሉ?” የአንድነት ሃይሎች መሆናቸዉ የሚጠራጠሩ ከሆነ በምርጫዉ ጊዜ የታየ መረጃ ካላጠገበዎ-ሌላ ምን እንዲቀርብ ይፈልጋሉ? ሌላ ቀርቶ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጅ በብዛት ይኖርበታል በተባሉት አካባቢዎች ሳይቀር “ላንድነት ሃይሎች” እንጂ “ለጎሰኞች” እንዳልመረጠ ይነገራል (መረጃ ባይኖረኝም)፣፣ ስለዚህ ምን መረጃ ይምጣለዎ?ለመሆኑ እርስዎ “የትግራይ ራስ/ጭንቅላት የተለያየ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ የትግራይ ድርጅቶች ልክ እንደሌሎቹ የተለያዩ መስመር/አስተሳሰብ የሚያራምዱ ድርጅቶች አሉዋቸዉ”በማለት ትግራይ ማሕበረስብ ድርጅቶች ዉስጥ ልዩነት እንዳለ ለማመለከት ሞክረዋል (አንድ እንዳልሆንን ለመከራከር ሞክረዋል፣፣ አርስዎ ያልገባዎት ነበር ትንሽ ጣል ላርግለዎት “በትግራይ ዉስጥ በትግራይ ሰዎች/ኤሊቶች የሚመሩ የትግርኛ ተናጋሪ ሰዎች የሚመሩዋቸዉ ድርጅቶች “መሪዎቻቸዉ እና አባሎቻቸዉ” ካንድ ጎሳ የወጡ ናቸዉ!ያንድነት ሃይሎች/ኢትዮጵያዊ ሃይል/ድርጅት ሚባሉት ደግሞ ከተለያዩ ጎሳዎች የተዉጣጡ መሪዎች እና አባሎች ያቀፉ ድርጅቶች ናቸዉ” ለዚህም ነዉ “የአንድነት ሃይል” ነን የምንለዉ፣፣ የኦሮሞ ከሆነ ኦሮሞ ብቻ ነዉ (ኦነግን ለምሳሌ)፣ ሶማሊ ከሆነ ያዉ መሪዉም ተመሪዉም ሶማሊ ነዉ፣ ጉራጌ .ዓፋር አገዉ ትግራይ ወዘተ ከሆነም መሪዉ ያዉ ካንድ ጎሳ የወጣ መሪ እና ካንደ ጎሳ የወጣ አባል ነዉ የሚሰባሰበዉ፣፣ ስለዚህ ልዩነቶቹ ከዚህ ቢነሱ የአንድነት ሃይሉ “ክስ” ቁልጭ ብሎ ሊገባዎ ይችላል፣፣ ኦሮሞዉ “ትግራይ ሶሊዳሪቱ” ዉስጥ አይገባም/ድርጅቱን መምራት አይችልም፣ትግራዩ የዓፋሩን ድርጅት የኦሮሞዉን የጋምቤላዉን ደርጅት የዓፋሩ የአማራዉን ድርጅት መምራት ወይንም አባል መሆን አይችልም፣፣ ምምራት እና አባል መሆን የሚችለዉ እርስዎ አብዛኛዉ ኢትዮጵያን ህብረተሰብ/ህዳጣን መወከሉን “ሰርትፊኬት/መረጃ”ያቅርብ እያሉ የሚጠይቁትን የ “በአንድነት ሃይሉ ዉስጥ ሲደራጅ ብቻ ነዉ!“ ስለዚህ የትግራይ ተወላጆች እንደተቀሩት (እንደተቀሩት የአንድነት ሃይሎች) የተለያዩ ድርጅቶች አሉን፣ ስለዚህም “ባንድ ጭንቅላት የምንጓዝ አይደለንም መወቀስ የለብንም” የሚሉትን “ፍሎሶፊካል -ሂፒክሪት” ክርክርዎ ለየት ባለ በፖለቲካዉ መልኩ ቢመለከቱት ጥሩ ነዉ የሚል ምዕዳን አለኝ፣፣ ከ ዓረና እና ከመለስ ወያኔ ሌላ ምን የፖለለቲካ ድርጅት አለ?ካሉም “ሲቪክ ማሕበራት ናቸዉ” እንሱ ደግሞ ፖለቲካ ዉስጥ አንገባም የማንም ፖለቲካ ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለንም ባዮች ናቸዉ። ታዲያ ምን የሚሉት የተለያየ አስተያየት ነዉ የሚነግሩን? ስለዚህም ነዉ የአንድነት ሃይሉ “አንድ አይነት ሰዎች”ይምሩትም ይኑርትም “ከአንድ ጎሳ” የወጣ አባልና መሪ አይደለም ነዉ እያልን ያለነዉ፣፣ የድርጅት ስራ ለማጠናከር አባሎቹን እና መሪዎቹን በተለያዩ ዘርፎች አሰማርቶ ይለዋዉጣቸዋል እንጂ “እርስዎ ስም እንደለጠፉላቸዉ-“ሰዎች እንጂ” “ሪሳይክልድ እንደሚደረግ ዕቃ” ስላልሆኑ እንደ አለቀ ዕቃ አይጣሉም! የትም አይሄዱም! ሰዎች ናቸዉ! ዜጎች ናቸዉና ሕይወት አላቸዉ በድርጅቱ ዉስጥ መታቀፍ እስከፈለጉበት ጊዜ ታቅፈዉ የአንድነት ሃይሉን እያራመዱ አብረዉ ከድርጅቱ ጋር ያድጋሉ/ይቆያሉ፣ ይመራሉ (ላላ) ይመራሉ(ጠበቅ)፣፣ ድርጅቱን ለረዢም ጊዜ ሳይለወጡ ቦታዉን ይዘዉታል የሚል እሮሮ ካለ “የዲሞክራቲክ ምርጫን” የሚመለከት ጉዳይ እንጂ “ሰዎቹ አምናም ታች አምናም ሰላማዊ ሰልፍ የሚያዘጋጁት እና ተቃዉሞ የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የአንድ አይነት የሰዎች መልክ ብቻ ነዉ የምናየዉ እና ” የኢትዮጵያን የተለያዩ ህዳጣን ሊወክሉ አይችሉም” ማለት የተሳሳተ እምነት ነዉ፣፣ አዳዲስ አባሎች ሊታዩ የሚችሉት እንደ እርስዎ ያሉት ኤሊቶች “ሪሳይክልድ ሰዎች”ሆኑብን ከማለት “ተቃዋሚም-ደጋፊም አይደለንም”ከማለት ወደ አንድነት ሃይሎች ተቀላቅለዉ “የሪሳይክሉን ኡደት”ማዳንም ይጠበቅበዎታልና ወያነ ትግራይ የበለጠ ጉዳት ሳያደርስ ወደ አንድነቱ ጎራ ይቀላቀሉ፣፣ አንድ አይነት ሰዎች ተቃዉሞዉንም ፖለቲካዉንም ለዢም ጊዜ የሚያራምዱት እኮ ደሞዝ ይገኝበታል ተብሎ ሳይሆን ያገር ክብር ተደፍሮ አይተዉ ቁጭት እና አልክ ይዟቸዉ ነዉ “ነፃ እስካልሆንን ድረስ ከመድረኩ አንለይም”እያሉ ያሉት፣፣መድረኩ ላይ ቆመዉ የሚሰደቡ የሚንገላቱ ሚታሰሩ ሚሰደዱት እኮ “የኢሕአዴግን ተቃዋሚም ደጋፊም አይደለሁም”የሚሉት እንደ እርስዎ ዓይነት የትግራይ ሊሂቃን/ኤሊቶች ጥሪ ተደርጎ “አንደባለቅም” “እምቢ” ስላሉ እኮ ነዉ! አሳፋሪዉ የትግራይ አብዛኛዉ ሊሂቅ ጥግ ጥጉን ወደ ወያኔ አዳራሽ መሞቅ ስለመረጠ እኮ ነዉ! ፣፣ አንድ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሆነናል እና እደከምን ነዉ እና አግዙን እኮ ነዉ የጥሪዉ አንኳር? “እኛ” የሚሉት ሃይሎች( መላዉ ኢትዮጵያ “ማይነስ “ትግሬዉ” በራስዎ ቃላት አጠቃቀም) የሚሉት 75 ሚሊዮኖች ከሆኑ እኛ (ትግሬዎች) 5 ሚሊዮን ድጋፍ ለምን ይፈልጋሉ? “ብዙሃኑን የሚወክሉ ከሆነ?ለምን እኛን ፈለጋችሁ? የሚለዉ በጣም አስገራሚ ጥያቄዎ ለሌሎቹ መልስ ቢሰጡበት ትልቅ አነጋጋሪ መድረክ ነዉና ለሰፊዉ አንባቢ ትቼ፣ ባጭሩ ግን ለማለት ምፈልገዉ“75ሚሊዮን ሕዝብ ባድሜ ድረስ ድረስልኝ ብሎ 5ሚሊዮን የትገራይ ሕዝብ ጥሪ ካቀረበ ዛሬ 75ቱ የ5ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ ፈልጎ የትግራይ ሕዝብ ድረስልን ቢል የሚያስቆጣዉና የሚያስከፋዉ የቱ ላይ ነዉ? ወይ ጋዶ! ወይ ቱ ጉዱ! “እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋነታችን እንድንወጣ ጥሪ አታድርጉልን” የሚሉ ከሆነ የታሳሰተ ቅሬታ በጣም አስገራሚም ነዉ፣፣ ለምን ሌሎቹን ጥሪ ሳታደርጉ ነጥላችሁ ትግሬዉን ለወቃሽ ዓይን ሰጥታችሁ እኛን ታስጠሉናላችሁ የሚለዉ “ማምለጫ ቀዳዳ”-{ዲፍነሲቭ -ሉፕ ሆል)አይሰራም፣፣ ወያኔ በግምባር ቀደም የገነባዉ (ከጥፍር እሰከ ራሱ) እኛ ትግራይ ተወላጆች እንጂ የኦሮሞ/አማራ/የሶማሊያ …ወዘተ ታጋዮች/ሕብረተሰቦች/ህዳጣን አይደሉም የገነቡት፣፣ ከገንዘብ አስከ የሰዉ ሃይል ምንጩ ከእኛዉ እና እኛ ብቻ ነበርን፣፣ ኤርትራ ድረስ ሄደን ’20,000 ሺሕ በላይ የትግራይ ታጋይ ይዘን ደሙ እና አጥንቱ እዛዉ አስከስክሰን የኤርትራን ሕዝብ ነጻ ካወጣን፣ ለምን ዛሬ በገዛ አገራችን እና ሕዝባችን ‘እኛዉ በፈጠርነዉ እና በእኛ እና ጉልበት፣ጥረት፣አስተዋጽኦ፣ጥብቅና እና ተንከባካቢነት ያሳደግነዉ ድርጅት “የኢትዮጵያን ህዝብ-እንደ ባእድ ኩፍኛ ሲበድል፤ ሕዝቡ “የፈጠራችሁት ድርጀት እናንተዉ ናችሁ እና “አንድ በሉልን! እባካችሁ ኑ እና አብረን ይህ ግፍ/በደል እናስቁም”ብለዉ ጥሪ ማድረጋቸዉ የሚያስቆጣዉ እምኑ ላይ ነዉ? በስማችሁ እየነገደ ነዉና እናንተን የሚወክል ከሆነ እባካችሁ እናንተን ተባባሪ አድርገን ከመመልከታችን በፊት በጠላትንት እናዳንመለከታችሁ “እኛ የለንበትም” በሉን ‘የለንበትም” የምትሉ ከሆነም አብራችሁን ታገሉ አና ይሄ በትግራይ ስም የሚነግደዉ ድርጅት አብረን እናስወግደዉ “ኑ!” ምነዉ ድምፃችሁ ራቀብን? በማለት ለእርዳታ ጥሪ በማድረጋቸዉ ለምን ትወቅሱናላችሁ?ለምን ለብቻችን/ለትግሬዉ ህብረተሰብ/ኤሊት ጥሪ ታደርጋላችሁ? የሚለዉ “የማምለጫ ቀዳዳ” መዉጫ ይቅርታ የማይደረግበት አጉል “ካብ’ ነዉ፣፣ ለጥሪዉ ምክንያትም መነሻ አለዉ፣፣፣፣ የትግራዩ ኤሊት ለምን እሱ ብቻ “ዓይን ዉስጥ” ይገባል ለሚሉን “ሂፒክርት ክርክርዎ” በሚቀጥለዉ አምዴ ለምን የትግራዩ ኤሊት እና ማሕበረስብ ዓይን ዉስጥ ሊገባ እንደቻለ መልሱ ያገኙታል እና መልሱን ይጠብቁ፣፣ ኤሊቱ የወያኔ ፖለቲካ አራማጅ ሆኖ የትግራይ ሕዝብን “ሳያስበዉ’ የወያኔ ሰለባ’ እና “በኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይን እንዲገባ መጥፎ ሚና ተጫዉቷል” ‘ለጎሳዉ ልዩ እንክብካቡ እና አስተዳደራዊ እና ቁሳዊ አድልዎ አድርጓል ስለተባለ “የኢንተርሃሙዎ’ፖለቲካ ነዉ እያካሄዱብን ያሉት “የትግራይን ሕዝብ ልታስፈጁ ትቀሰቅሳላችሁ”እያሉ ከመለስ ዜናዊ በላይ ሆኑብን እሳ ምነዉ አቶ ሙሉጌታ?!የትግራይ ሕዝብ “ዘርፏል አልተባለ! ዘራፊዉም አድልዎ ፈጻሚዉም “ወያነ” ትገራይ” የተባለ በመንግሥትነት ዙፋን ላይ በሻጥር እና በጠመንጃ ሃይል የተቀመጠዉን ጎሰኛ ድርጅት/ቡድንን ነዉ እየተወቀሰዉ እና ሃላፊነት እየወሰደ ያለዉ! ይሄንን የማቃናት ጉዳይ “አትዝረፍ’-አታዳላ’-የማለት ሃላፊነት በስሙ እየተነገደበት ያለዉ ክፍል በተለይም “ሊሂቁ” ነዉ፣፣ ይህ ከማድረግ ፈንታ “ወደ ተቃዋሚዉ አድልዎ እየተፈጸመ እንዳለ በማስረጃ ስለተከራከረ “ኢንተርሃሙዌ/ ዘር ማጥፋት ዘመቻ በትግራይ ሕዝብ ላይ እያካሄዱ ነዉ ማለት ለጀሮ አይጥምም፣- ጋዶ!! የትገራይ ህዝብም ሆነ ሊሂቁ አንድ ጭንቅላት የለዉም እያለን ያለዉ ሙሉጌታ አረጋዊ ሊሂቁ ባንድ የወያኔ ጭንቅላት አስተሳሰብ ዉስጥ ተጠፍሮ እንደነበር ማስረጃ ለማቅረብ እንዲመቸኝ፣ ወያነ ትግራይ የትግራዋዩን ሊሂቅ እንዴት እንደተጠቀመበት እና ሊሂቁ አስከ ቅርብ ድረስ ወያኔ ትግራይ ለሁለት ሲሰነጠቅ ያለቀሰዉ አሳፋሪና አስተዛዛቢ ልቅሶ እና ያሳዉ የዘቀጠ ሃገራዊ የፖለቲካ ብስለት በሚቀጥለዉ እትም “ትግራይን ለማዉደም ለምን ፈለጋችሁ?“ከትግራዊያን ፕሮፌሽናሎች”የሚል ያስተላለፉት አስቂኝ መልክታቸዉ አንድ ዓይነት ጭንቅላት (በዛዉ በጎሳ አዉድማ ዙርያ) እንዴት ያስቡ እንደነበር እንድትመለከቱት አቀርባለሁ፣፣ለምን ሰብሰባ ላይ በተቃዉሞ አብረዉን አይቆሙም ለሚለዉ ጥያቄ ምን ያህል ልክ እንደሆንን እና ከምን ምክንያት እንደተነሳን ታዩታላችሁ፣፣ ተከታተሉ፣፣ ይቀጥላል….. ጌታቸዉ ረዳ www.Ethiopiansemay.blogspot.com