Friday, April 17, 2009

በወያኔ ቀዉስ አንቆዝምም “ዕልል!” እንላለን እንጂ!

በወያኔ ቀዉስ አንቆዝምም “ዕልል!” እንላለን እንጂ!
(ከትዝታችን ማህደር) ጌታቸዉ ረዳ
(…በወያኔ ቀዉስ “ቆዝሙ” የሚሉን ክፍሎች “በወያነ ቀዉስ አንቆዝምም ዕልል እንላለን እንጂ!” ወያኔ ከተንኮታኮተ ሀገር ትተረማመሳለች ብለንም እንቅልፍ አናጣም፣ ሀገር እየተተረማመሰች ያለቺዉ በወያኔ ነዉ።ገዢዎች ሥልጣናቸዉን ለማራዘም ሁሌም እኛ ከወደቅን ስምነተኛዉ ሺህ መጣ ማለታቸዉ ተለመደ ነዉ…)
ባለፈዉ ከትዝታችን ማህደር አማዳችን ወያኔ ለሁለት ሲሰነጠቅ በመላ ዓለም የሚኖሩ በተለይም በዚህ በአሜሪካ ሃገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የተሰማቸዉን ሃዘንና ድንጋጤ አቅርቤላችሁ ነበር። ድርጅቱ ለሁለት ከተገመሰ በሗላ አንጃ ለተባለዉ ቡድን ማለትም ለእነ ገብሩ አስራት ደህንነት ምንኛ እንደተጨነቁ/እንደተጠበቡ አይተናል። በዚህ አምድ ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወያኔ በቀዉስ መመታቱ ምንኛ እንደተደሰቱ እና በየጋዜጣዉና ራዲዮኑ ዕልለታቸዉን እንዳስተጋቡ እና መጽሄቶችና ጋዜጦች በጣም እጅግ በበርካታ የደስታ ደብዳቤ መግለጫዎች እንደተጥለቀለቁ እናስታዉሳለን። ለተለያዩ መጽሄቶችና ጋዜጦች የተላኩ የደስታ ምግለጫዎች በጣም ብዙ በመሆናቸዉ ድብዳቤዎችን ከማቅረብ ይልቅ ባጠቃላይ የህዝቡን ወቅታዊ ስሜት ያንጸባረቀዉ የሃዋርያዉ ጋዜጣ “ከዜና ባሻገር”-አምደኛ መስፍን ታምራት ከናይሮቢ የዘገበዉን ሀተታ ለትዝታችን አምድ መርጬ አቅርቤላችሗለሁ። ወደ ሗላ ተመልሰን በወቅቱ ተዘገቡትና የታዩት ሁኔታዎች ስንመለከት አሁን ላለነዉ ሁኔታ አመላካች በመሆናቸዉ፣ በጥሞና እንድናጤናቸዉ ይረዳናል። መብሩክ አለህ ከሪም፣ፈጣሪ ይመስገን፣ ወደ አድባሩ ወደ አተቴዉ ዘምበል ላለላችሁትም በዚያዉ ባመቻችሁ ደስ ኢበላችሁና መብት መጠበቅ አለበትና የዚህ ዓይነት እምነት ለሌላችሁ ደግሞ በምታምኑበት ዓላማ ሆነ ሕዝብ ስም ለሀላችንም እንኳን ደስ አለን ። የመቶ ዓመት የቤት ሥራ ሰጠናቸዉ ብለዉ የትግራይ ትግርኚ ትምክህተኞች በጨፈሩብን በአጭር ጊዜ ዉስጥ እርስ በርስ ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀዉ ሲደካክሙ ለማየት በቅተን ተደስተን ሳናበቃ እነሆ የሃገርና የሕዝብ ጠላት የሆነዉ ወያኔ ጭራሽ ሊያንሰራራ በማይችልበት ደረጃ እርስ በረስዩ ተንከረባብቷል።ተስላችሁ የነበራችሁ ሳይዉል ሳያድር ክፈሉ! በዚህ ዓምድ ባለፈዉ ወር ሳይቀር ወያኔ በዉስጣዊ ቅራኔ እየተተራመሰ መሆኑን ጠቁመን ነበር። ሰብሓት ነጋ የእሳት አደጋነት ማለትም የቅራኔ አብራጂነት ሚና እየከሸፈ ራሱም ራሱም የችግሩ አካል ሆኖ እየተነከሰና እየቦጨቀ በመምጣቱ የወያኔ ቅራኔ ሊደበቅ ከማይችልበት ደረጃ ደርሶ በ አደባባይ ፈነዳ። አለቃችሁብን ብለዉ የተላቀሱት የወያኔ ደጋፊ ትግራዉያን እዉነት አላቸዉ። “በወያኔ ተስቆበታል ግን ደምበኛዉ ካካታ ጀመረ እንጂ አላከተመም” ዛሬ የፈነዳዉ የወያኔ ቅራኔ መብሰልሰል ከጀመረ አመታት ቢያልፍም ግጭቱን አከረረዉ ከሻዕቢያ ጋር የተፈጠረዉ ቅራኔ መሆኑን ግልፅ ነዉ። የወያኔ አንጃዎች በምንም ጊዜ ሆነ ቢሆን ስላሉት በደል ፀፀት ተሰምቷቸዉ እንታረም ብለዉ ባነሱት ክርክር ተጋጩ አይደሉም።ከኢትዮጵያ አንፃር ሁለቱም አንጃዎች የሚፈይድ ፕሮግራም ወይንም አመለካካት የላቸዉም ። በጠባብ የትግራይ ትምክህተኞች ዘንድ የተፈጠረዉ ግጭት ማን ይበልጥ ወያኔ እንጂ ማን ንስሃ ገብቶ ክህደትን ትቶ ኢትዮጵያዊ ልሁን በሚል አይደለም። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን በጠላት ጎራ የሚከሰት ክፍፍል በደፈናዉ እሰየዉ ተብሎ የሚተዉ ሳይሆን እንዳይረግብ የሚረባረቡበት ነዉና በመለስ አንጃና በእነ ስየ አንጃ መሃከል የተከሰተዉ ቅራኔ እንዳይዳፈን መስራት አስፈላጊ መሆኑን ይታያል። ከዝንጀሮ መረጣ በዳኝነት መቀመጡ አስደሳች ስራ ባይሆንም በአጭር ጊዜም ደረጃ ቢሆን የአንዱ አንዱን ማሸነፍ በተመለከተ የሚጠቅመዉን አይቶ በዚሁ መሰረት ዘምበል ያለ ስራን መስራት አስፈላጊ መሆኑ ይታያል። ወያኔ ገና ከዘመነ “ሕንፍሽፍሽ” ቅራኔዉ ጀምሮ የተፃራሪ የትግራይ ነፃ አዉጭ ድርጅትን (ቲኤልኤፍ)ን-ሲገድልም ሆነ በኢሕአፓ ላይ ጦርንት ሲከፍትና ሗላም ማሌሊት ብሎ እነ አረጋዊና ግደይን ሲያባርር የታየዉ በሞላ ይህ ድርጅት ልዩነትን የዉስጥም ሆነ የዉጭ በጭረሽ ማስተናገድ የማይችልና ከግድያ ሴራ ዉጭ ምንም መፍትሄ የማይታየዉ መሆኑን ነዉ። ይህ ሀቅ ሆኖ እያለ እነ ስየ ላይ የሚበትኑት ወረቀት ላይ ሰፍሮ ሚታየዉ አንድም የእንዚህን ግለሰቦች የማይታረም ወያኔነት ሲያሳይ (ጸረ ዲሞክራሲ ከየት ድንገት ከየት መጣብን ይሉናል!)-በሌላ በኩልም ጅልነታቸዉንም ያረጋግጣል። ለነታምራት ላይኔ ይቅርና ለነተክሉ ሃዋዝና በገዳርፍ ሱዳን በሰንጢ ተቆራርጦ ለተገደለዉ የወያኔ የጀዳ ወኪል (ያሲን)ያላየዉ ዲሞክራሲ ዛሬ በድንግት ከየት እንዲወለድ እንደጠበቁ ያስጠይቃል። ፀረ ዲሞክራሲ የሆነዉ መለስ ብቻዉን ሳይሆን የወያኔ አመራር በሞላ መሆኑን ለህዝባችን ምስጢር አይደለም ። ይሁንላችሁ ብንል እንኳ ባለፉት 10አማታት ብቻ ሳይሆን ገና ከጫካዉ መለስ አላግባብ ሥልጣንን ከዓባይ ፀሃየ በእጁ አስገብቶ መገኘቱ ነዉ። ይህንን ሂደት ደግፈዉ ሲያጫፍሩ የነበሩት እነ ስየ እና ገብሩ ለሦስተኛ ጊዜ የከዳዉ ሐሰን ሺፋን፣ ወላዋዩን ዓባይን ትተን)ራሳቸዉ ናቸዉ። የትኛዉ የወያኔ ዲሞክራሲ ደምቆ ታይቶ ነዉ ጉባኤ ይጠራ፣ ነፃ ዉይይት ይካሄድ የሚሉት?በዘረፉት ገንዘብና ምቾት ኣእምሮአቸዉን ስተዉ ነዉ?ፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች በፖለቲካዉ ገቡ፣ አፈና አካሄዱ ሲሉን አስከ ዛሬ የት ነበሩ?አሰፋ ማሩ በማን ጥይት ተገደለ?ተስፋየ ታደሰ በማን ሰንጢ ተቆራረጦ ተገደለ? ፕሮፌሰር አስራት በማን ታሰሩ? እነ ጸጋየ ገብረመድህን በማን ታፈኑ? አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በማን ተደበደቡ.ተሳደዱ፣ታሰሩ?ጋዜጠኛች ለምንና በማን ከረቸሌ ወረዱ?እነ ዶክተር ታየ፣ አበራ የማነአብ፣ ፊታዉራሪ መኮንን ዶሪ፣ ወዘተ በማን ታሰሩ?ያዲስ አበባ መስጊድና የጎንደር አደባባይ እየሱስ ፍጅት የማን ነዉ? ወያኔ ባሁኑ ጊዜ በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሰስ የሚችል ነዉ?-አርባ ጉጉ ምሰራቅ ወለጋ ወዘተ ለዚህ ተጠያቂዉ መለስ ብቻ ነዉ?በህዝብ ላይ ሲደረስ የቆየዉ ግፍ ዛሬ በአድራሾቹ ላይ እየደረሰ ከሆነ ልናዝንላቸዉ ለምንስ ይጠብቃሉ?ከርቸሌ ያለዉ ታምራት ሳቅ ሰቅ እያለዉ ሰሞኑን ቢቸገር ማን ይፈርድበታል? የአሁኑ ቀዉስ ለትግራይ ተወላጆች በተለይም ለምሁራኑና በባዕድ ሀገር ላሉት የወያኔ ደጋፊዎች በሞላ አዲስ ዕድል ሰጥቷቸዉ ነበር-ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ሳያወላዉሉ ለመሰለፍ። ሊጠቀሙበት ቀርቶ ከምናዉቀዉና እጅ እጅ ካለን አነጋገርና ትንተና እንኳን ጭራሽ መራቅ አልቻሉም። ቢያንስ እስካሁን። የትግራይ ጠባብ ብሔረተኝነች አባወራ ነን ባዮቹን እነ ስየን በጭፍኑ ደግፈዋል ። ደግፉም እያሉ ኢትዮጵያዊያኑን ይወተዉታሉ።ምን አህል ቢንቁን ነዉ?የኢትዮጵያ ጠላት መለስ የሚባል ግለስብ ሳይሆን ጠባብ ብሄረተኛነት የተባለዉ ቫይረስ ሲሆን-የዚሁ በሽታ ተሸካሚዎች ደግሞ “ኢ አር ፖሲቲቭ” ወይም የሻዕቢያ ቡችላዎች የሚባሉት እነ መለስ ብቻ ሳይሆኑ ወያኔ በጥቅሉ ነዉ። ፀረ ኢትዮጵያ የሆነዉ የትግራይ ጠባብ ብሔረተኝነት ከተነሳ ደግሞ -የዚሁ አስከፊ እምነት ተሸካሚዎችና አስፋፊዎች ከሚባሉት ቀንደኞቹ ዉስጥ በእነ ስየ ገብሩ ጎራ ተሰለፉት ሁሉ ይገኙበታል። ሕገ ወጥ ታምራት ላይኔ በሕገ ወጥ ሲወገድና ለፓርላማቸዉ ቧልት ተጋልጦ መሳቂያ መሳለቂያ ሲደረግና ከዚያም አልፎ ለዚሁ ጠንሳሽና አካሂያጅ መለስ ብቻ ነበር? የእነ ተወልደ፣ዓባይ ሚና ምን እንደነበር ሁላችን ስለምናዉቀዉ ያኔ ያልታየዉን ዲሞክራሲ ዛሬ ጠፋ ቢሉን ከመሳቅ ሌላ የምናደርገዉ አይኖርም። የትግራይ ምሁራንና የወያኔ ደጋፊ የሆኑት የዚሁ አካባቢ ተወላጆች በጊዜዉ ተጠቅመዉ የወያኔን ፀረ ሕዝብነት አዉግዘዉ የመላ ሕዝብን ጥያቄ ደግፈዉ ከሕዝብ ጎን ካልቆሙ በስተቀር መለስን አዉግዘዉ ስየን ሲደግፉ መለስ ካሸነፈ የወያኔና የትግራይ የበላይነት ይበልጥ ይጎዳል ብለዉ ተጨንቁ ከሚል ሌላ መደምደሚያ መድረስ አንችልም። አንድ የኢትኦጵ ጋዜጣ በአንክሮ እንደጠየቀዉ ሁሉ “በተለያዩ የኢትኦጵያ ክፍሎች ተበታትነዉ በንግድና በመሳሰሉ ስረዎች ላይ የተሰማሩትና በአብዛኛዉ ተመችቷቸዉ ሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች እንደ ኤርትራዉያን “ወደ አገራችሁ ቀጥሉ” የማይባሉበት ያፈሩትን ሃብት ጥለዉ ወልደዉ ከከበዱበት ወግ ማዕረግ ካዩበት ተዋርደዉ ላለመባረራቸዉስ “ከወያኔ ጉዞ” አንፃር ዋስትናቸዉ ምንድነዉ? ምን ዋስትና? ስየና ገብሩን ደግፉ እያሉ እስከቀጠሉና ለትግራይ በላይነት እስከቆሙ ድረስ ለወያኔ የመጣ በነሱም ላይ እንዳይከሰት መቸስ ዜጎቻችን ናቸዉና እጅግ እንሰጋለን። ። ምክንያቱም ወያኔ አብቅቶለታል።ሟርት ሳይሆን ሀቁን መናገራችን ነዉ።የዛሬ ጠዋቱን ሳይሆን የነገ ቀኑን። የመንግሥት ሥልጣንን በተመለከተ ለመለስ ፈረሱም ሜዳዉም ተለቅቆ ስለከረመ ዛሬ በቀላሉ መንጠቅ አይቻልም።መለስ ሃይሉን ለማደላደል እየተራዋጠ በሌላ በኩል ደግሞ አማራጮች አሉት።ታረቁ ብለዉ ሳይጠሯቸዉ ታረቁ ብለዉ አማላጅ የሆኑትን (ጳጳሱ፣ ሰለሞን ዑንቋይ፣ ደጃዝማች ዘዉዴ ገብረስላሴ ወዘተ)“የባልና ሚስት ጠብ አይደለም”-ብሎ ዘግቷል።ጉባኤ ካልጠራሕ እያሉ የሚንጫጬት ሁሉ እነ ስየን ከከወነ በሗላ ሊጠራላቸዉ ይችላል።ካልሆነም በመቀሌ ሆነ በአዲስአበባ የካድሬዎች ስበሰባ እንዳሳያቸዉ-ሁሉ የራሱን ምርጦች ሰብስቦ እነ ስየ ባሉበት የፈለገዉን ዉሳኔ ሊያስወስንባቸዉ ይችላል። በእነ አረጋዊና ግዴይ አድርጎታልና። ባለፈዉ ሰሞንም ደግሞታል።በወኔ ቢሱ ታምራት ላይኔም ፈፅሞታል። ይህንን ቲያትር የ ኢሕአዴግ አባል ነን ባይ ተለጣፊዎች እንዲደግፉት ማድረግ አይሳነዉም። እነ ስየን ዛሬ ቢያስር የሚከተለዉንም ተቃዉሞ ከተነገወዲያዉ እርምጃዉ ጋር አመዛዝኖ ያዋጣናል ሚለዉን መዉሰዱ አይቀሬ ነዉ። የስየና ገብሩ አንጃ ከሰነዶቹ እንደታየዉ ሁሉ ዛሬም ከወያኔዉ ካቴና ባለመላቀቃቸዉ “ወያኔያዊ ሕዝባዊነትና ዲሞክራሲያችን ጠፋ ይሉናል”።ሰፋ አድርጎ ሕዝብን ሊያስደምጥ ሆነ ባዲስ መልክ ሕዝበን ሊቀሰቅስ ባለመቻሉ ራሱን ነጥሎ ለበለጠ አደጋ አጋልጧል። መድረኩን አጥብበዉታል::በወያኔ ዙርያ ሊወያዩና ችግሩን ፈትተዉ በቀድሞ መንገድ ሊቀጥሉ ነዉ የፈለጉት።በዚህ ዳንስ ደግሞ አንገትም ሆነ ወገብ እየሰበቁ መሽከርከሩን ሞያተኛዉ መለስ ከማንም በበለጠ ያዉቀዋል፣ ይችልበታልም። ቀዉሱ ስላልተጠናቀቀ ካዩትና ካለፈዉ ተምረዉ ሌላ እርምጃ ይወስዳሉ ወይ?ይችላሉስ ወይ?የሚለዉ ገና በመጠኑም ቢሆን ተንጠልጥሎ ያለ ጥያቄ ነዉ። ምንስ ሲቀናጣ በትሩን ወርዉሮ ፍለጋ ይገባል እንደተባለዉ መለስን በራሳቸዉ ላይ ካፈናጠጡና በሥልጣንም ካባለጉት (እሱም በገንዘብና በሥልጣን ካባለጋቸዉ በሗላ)ዛሬ መለስ ያላግባብ በፀጥታና በፖሊስ ሃይል ወይንም በመንግሥት ሥልጣን ተጠቀመ ብለዉ ዋይ! ዋይ! ቢሉ መሰረታዊ ሀቁን የሚለዉጥ አልሆነም። መሰሪዉ መለስ ከደደቢት ጀምሮ ልክ እንደነ ዓባይ ለሳሕሉ ሰዉየ ያደረ ቢሆንም ሻዕብያን በተመለከተ የነበረዉ አቅዋም ሁሉ በአንድ ሰዉ ሊላከክ የሚችል አይደለም። ሻዕቢያን ተቃዉመዉ በነ ገብሩ አስራትና በነ ሐሰን ሹፋ የተሰቃዩ ትግራዉያን ለዚህ ምሳሌ ናቸዉ። መለስ ወደ ሻዕቢያ ካዘነበለና አብዛኛዉ የወያኔ መሪ “እንደሚሉን”አሱን “ይቀወሙት” ከነበረና እነ ስየ “አለ” የሚሉን “ዲሞክራሲያዊ” አሰራር የወያኔ ባህልና ልምድ አሰራር ከነበረ ታዲያ “ለምን መለስ ፍላጎት ብቻ የበላይ ሆነ?” ለሀገራችን መጠቃትና ገና ከጥዋቱ መከፋፈል መሽመድምድ ተጠያቂዉ ወያኔ ነዉ ወይስ አንድ ግለሰብ?-የልዩነት ነጥቦች ተብለዉ የቀረቡት አጥጋቢ ሆነ አሳማኝ ሆነዉ አይገኙም። ወያኔና ሻዕቢያ የተጣሉት በባድሜ አልነበረም። እነ ገብሩ ስየ ወዘተ ከሻዕቢያ ጋር የተጋጩት በሃገራዊ ሉዓላዊነት ሳይሆን ባኮኖሚ በጥቅም ጉዳይ ነዉ::የወያኔ አዲስ ወጥ ከበርቴ ያለምንም ፉክክር ኢትዮጵያን መበዝበዝ በመፈለጉ የኤርትራን ኢኮኖሚያዊ ቋንጃ ሊቆርጥ በመነሳቱ ነዉ ዋነዉ መንስኤዉ። እንኳን ለምናዉቃቸዉ ኤርትራዊያን ቀርቶ ለሱዳን ለኢራን ሳይቀር ያገራችን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሰጠዉ ወያኔ በጥቅሉ አልነበረም?ከዚያድ ባሬ ጋር ተፈራርሞ ግማሽ ኢትዮጵያን የምዕራብ ሶማሌ ያለዉስ መለስ ብቻ ነዉ?ለዚህ ሁሉ መለስ መለስ ብቻ ከተባለ ዉሸት ከመሆኑ ሌላ እነ ስየ በወያኔ አለ የሚሉትን ዲሞክራሲ የጋራ አማራር አለመኖሩን አረጋጋጭ ይሆናል። መለስ ዜናዊ የአያቱ የባንዳዉ አስረሱን ቅርስ አንግቦ ሀገራችንን ሊሸጥ ሊያዋርድ ከመጀመሪያዉ የተነሳ ስለሆነ እሱን በተመለከተ ብዥታን አላስተናገድንም። ደቡቡን .ዓፋሩን ባጠቃላይ ሕዝቡን ያስለቀቀሱት እነ ቢተዉ የመለስ አማካሪ የነበሩትን ተወልደና ዓለምሰገድ፣ ገብሩና ስየ የትግራይ ትገንጠል ማኒፌስቶን ፣ዓባይ ፀሃየ ወዘተ ዛሬም “ትግራይ ዓደይ”ከሚሉት ዘፈናቸዉ ሳይርቁና ኢትዮጵያዊነታቸዉን ለማደስ “ፍርጥር አድርገዉ”-“በአጥፍተን ነበር ግለሂስ ሳያጅቡ”እነሱ ይሻላሉ ብሎ መፈረጅ ለጤነኛ ኢትዮጵያዊ ከባድ ነዉ። የእነሱ መጠናከር ማለት ባለፉት አስር አመታት ያየነዉ ዘረኝነት ተጠናክሮ መቀጠል ማለት ነዉና ነዉ። ወያኔ በቀዉስ ሲታመስ የአገሪቱ ነፃነት እየተቃረበ መሆኑን ሲያመለክት፣ በወያኔ ቀዉስ “ቆዝሙ”የሚሉን ክፍሎች “በወያነ ቀዉስ አንቆዝምም ዕልል እንላለን እንጂ!”ወያኔ ከተንኮታኮተ ሀገር ትተረማመሳለች ብለንም እንቅልፍ አናጣም፣ ሀገር እየተተረማመሰች ያለቺዉ በወያኔ ነዉ።ገዢዎች ሥልጣናቸዉን ለማራዘም ሁሌም እኛ ከወደቅን ስምነተኛዉ ሺህ መጣ ማለታቸዉ ተለመደ ነዉ። በዚህ ማስፈራሪያ ወያኔ ይቆይ የሚል ካለ መቸም በወያኔ ስር ቀንበር ያለ ለመሆኑ ያጠራጥራል።ሃገር የምትከፋፈለዉና ለከፋ አደጋ የምትጋለጠዉስ የወያኔ አገዛዝ (በመለስ ሆነ በእነ ስየ”) ባለፈዉ ይዘቱ ከቀጠለ ብቻ ነዉ ። ቀዉሱ ሌላዉ ጫና ሰጥቶ ግልጽ ያደረገልን ነገር ቢኖር ዘረኛዉ ወያኔ በሙስና እንደተጨማለቀና በዘመድ አዝማድ አሰራር እንደሚያምን ነዉ ። የወያኔ ባለስልጣኖች እርስ በርስ የተዛመዱ ከመሆናቸዉ ሌላ (የጻድቃን ገብረተንሳይ ሚስት የስብሐት ነጋ ዘመድ ስትሆን፣ የወያኔ ማ/ኮ አባል ትርፉ ኪዳነማርያም የዓባይ ወልዱ ሚሰት ናት፣ የተወልደ ቦታ የተሰጠዉ ዓባይ ወልዱ የእነ ስየ አንጃ አባል የአዉዓሎም ወልዱ ታናሽ ወንድም ነዉ፣ ሙሉጌታ አለምሰገድና አለምሰገድ ገብራምላክ ዘመዳሞች ናቸዉ።የቅዱሳን ነጋ ማለትም ስብሓት ነጋ እህት ባል የትግራይ ሃላፊ ተብሎ በመለስ የተሾመዉ ጸጋይ በርሐ ነዉ፣ ወዘተ….። የዉልደት ቦታ ክፍል ባይኖርም የምርጦቹ ዓድዋዎቹ በሌሎቹ ዘንድ ተቃዉሞ ማስከተላቸዉ አልቀረም።ይህም። ይህም የቤተሰብና የጠባብ ክልል አልፎም አሰላለፍ ጉዳይ ደግሞ ከቀጣዩ ችግር አንጻር ቦታ ያለዉ ነዉ። እንደተለመደዉ ባዕዳን የሃገሪቷን ቀዉስ ይዘት መረዳት ያቃታቸዉ ከመሆኑ ሌላ የእነ ስየ እንጃ የወያኔ ዝቅተኛና መካካለኛ ደረጃ ካድሬ “ሁላችንም እኩል ነን”ባይ ቅዠታም አስተሳሰብ ለማስተናገድ ሲሉ አጼነትን (ሓፀይነት)ን ማዉገዝና የካዱትን ርዕየተ ዓለምንም ሟጯጯህ በመምረጣቸዉ ባዕዳኑ መለስን ለዘብተኛና የካፒታሊስት ተንከባካቢ ብለዉ ሲፈርጁት እነ ስየን ደግሞ በአክራሪ ግራነት (ማለትም አደገኛነት)ፈርጀዋቸዋል።ያም ሆኑ ይህኛዉ ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃን ያስታዉሰናል። ዕልል ሲያንስ ነዉ። ባጭሩ የቀዉሱን ሂደት ስንገመግም “በባእድ ሀገር የሚገኙ በርካታ ትግራዊያን የእነ ስየን አንጃ ደግፈዋል ለዚህም መሰረቱ የትግራዋይነት የበላይነት መቀጠል ፍላጎትና ፀረ-ኤርትራነት እንጂ ለኢትዮጵያ አዲስ ነገር በመመኘት አለመሆኑ ግልጽ ነዉ’’። በዚህ አንጻር መፈክራችን በሀገር ጉዳይ ሕዝብ ይወስን፣ ወዘተ… የሚል መሆን አለበት። የወያኔ ጉባኤ ተካሄደ አልተካሄደ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ሊሆን አይገባም የዚች ታሪካዊ ክብር ሀገር ዕጣም በወንበዴና ከሃዲ መንጋ ጉባኤ ሊወሰን ሲሞከር ዝም ብለን ማየት የለብንም። ይህ ብቻ አይደለም ቀዉሱ በር ከፍቷል።ዶክተር መስፍን ወልደማርያም “ወያኔ ከፈተዉ”ያሉትን የ “ዲሞክራሲ በር”ማለቴም አይደለም።የተከፈተዉ በር ወያኔን መወጠርያ ትግልን ማፋሚያና ከሆነም ወያነን ጠራርጎ ከታሪክ ትቢያ መቀላቀልያ ነዉ።ከዚህ ባሻገር ደግሞ በወያኔ የንግድ ተቋማት ላይ ዕቀባን ማወጅ የወያኔ ኩባንያ ያመረተዉን ልብስ ላለመልበስ ቢራዉን ላለመጠጣት፣የመሬት ምሪቱን አለመግዛት፣አገር አቀፍ አድማ ተግባራዊ መሆን ይገባዋል።በአንጃ ተከፋፍለዉ ሲፋጁ መገላገል ሳይሆን ስለት ማቀበልና ቀዉሱ በፈጠረልን ቀዳዳ ሁሉ መጠቀም ይኖርብናል መለስ በበኩሉ በሥልጣን ለመቀጠልና ሀገራችንን ለማጥፋት ጥረቱን ቀጥሏል።ብርሃነ ገብረክርስቶስ በአሜሪካ ያሉትን ትግራዊያንን በመለስ ዙርያ ማሰለፉ አቅቶት አብዱል መጅድን አጅቦ አዲስ አበባ ተመልሷል።ሁለቱም ለሹመት ታጭተዋል ይሉናል።ለናይሮቢዎቹ የትግራይ ተወላጆችም ተወልደ ገብሩ (?)ተመድቧል አሉ። ኢትዮጵያዉያንን በሞላ የሚያናግር ግን አስካሁን አልተገኘም።ማን ከቁም ነገር ቆጥሮን! ሀገራችን ተቀምተን መሳለቂያና መጫወቻ ከሆንን አስር ዓመት አልፎ የል?።//-/ ከኢትዮጵያ ሰማይ ኤዲተር-- /- ዛሬም አንቀጽ 39ኙን አንግቦ “ኣለና!!!!” ብሎ ብቅ ያለዉ የእነ ገብሩ አስራት “ዓረና ትግራይ”እና የትግራይ ወንድሞቻችን “ዕልልታ”-ከላይ ያነበብነዉ ማህደር ስታገናዝቡ በወቅቱ ለነገብሩ ደህንነት የሳሱትን ወንድሞቻችን ዛሬም አንቀፅ ሰላሳ ዘጠኝን አንግቦ ብቅ ሲልላቸዉ ድጋፋቸዉ ለምን እንዳልነፈጓቸዉ መረዳት ትችላላችሁ። እነሱ ብቻ ሳይሆኑ መድረክ ተብየዉ “አዲስ ዕቃም” አንቀጽ 39 ይዞ ብቅ ሲልለት አቅፎ መደገፉ “ለኢትዮጵያ አዲስ ነገር መመኘት አለመሆኑ ግልጽ ነዉ።ምስጢሩ ግልጽ ነዉ፣ “ትላንት”-መለስን የአስመራ ቅጥረኛ ስላሉ “ዛሬ”-የወያኔ መንጋ ስለደገፉ ተቃወሚ ብለን-ከምር-መዉሰድ ይከብዳል!መልካም ፋሲካ ይሁንላችሁ! http://www.ethiopiansemay.blogspot.com/