Tuesday, December 9, 2008







ኤርትራ ፤ሕገ ወጥ መሳሪያ ፤ዓለቃይዳና ታሚል ታይገሮች ጌታቸዉ ረዳ ካለፈዉ የቀጠለ- ምንጭና የሰነዱ አቅራቢ ኤርትራዊዉ አቶ ሕሉፍ ፈዳይ ንጉሥhttp://asena-online.com/ በትግርኛ ለትግርኛ አንባቢዎች እያስነበቡት ያሉትን የቀይ ባሕር አካባቢ ሁኔታ ወደ አማርኛ በመመለስ ለአማርኛ አንባቢዎች እያስነበብኩኝ ነበር። ዛሬም ከላፈዉ የቀጠለ ኢሳያስ እና የባሕር ዉንብድና ተግባሮች ከሚለዉ የቀጠለ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ ኤርትራ አልቃይዳ፤አሸባሪዉ የሶማሌዉ ቡድን የመሳሪያ ማሸጋገር ተግባር እና የታሚል ታይገሮች ግንኙነት ወዘተ ጉዳዮችን እንመለከታለን። “በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የሶማሌ እስላሞች ማሕበር ታጣቂዎች በኤርትራ መንግሥት ተባባሪነት እና እንክብካቤ ከሶማሌ ወደኤርትራ ከዛም ወደ ሶሪያ ሊቢያ በመጓዝ ወታደራዊ ስልጣና ካገኙበሗላ ወደ ሊባኖስ በመሄድ ከሑዝብላ ታጋዮች ጋር በመዋሃድ የ”ሻሃዳ” ተልዕኮ የሚጠይቀዉን ተግባር በመፈጸም ላይ እንዳሉ የሚያሳይ የተባበሩት መንግሥታት ያወጣቸው ሰነዶች የክስ ጣንወደ ኤርትራ ያመለክታል። (ምናለባት ሻሃዳ ሚለዉ አረባዊ የሃማኖት ቃል ትርጉሙ ለማታወቁት “መጠመቅ፣ በአባልነት መመዝገብ፤-----እንግሊዝ “መምበር-ሺፕ” የሚለዉ አባባል ነዉ- ትርጉም ጌታቸዉ ረዳ)
የመሳሪያ ሽያጭ እና ሽግግርም በሚመለከት ለምሳሌ የ “ህግደፍ” በመካካለኛ ምስራቅ አገሮች ጉዳይ የኤርትራ ተጠሪ በሆነዉ መሐመድ ቓስም ሐመድ የተከናወነዉ የመሳሪያ ግዢ በ14/7/2007 ከኢራን ወደ ኤርትራ በምጽዋ የ አይሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ የተራገፈዉ 125 Shoulder –surface-to air missiles 80፡ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ከሌሊቱ በ2፡45 ሲራገፍ እራሱ በአካል ተገኝቶ ተረክቦታል። በእርግጥ ሰፊዉ የመሳሪያ ሽያጭ ሽግግር ተከናወኑት ቀደም ብሎ በ2006 ሲሆን ፕረዚዳንት አሳያስ አፈወርቅ የ አስመራ ጽ/ቤቱን ዘግቶ ለዚህ ለማሳሪያ ሽግግር ተግባር በቅርብ እንዲቆጣጠረዉ ሲባል ጽ/ቤቱ ከአስመራ ወደ ምጽዋ አዙሮ ነበር።ለዚህ ተግባር በቅርቡ ተከታትሎ እንዲአስፈጽም የመደበዉ የብርጋዴር ጀኔራልነት ማዕረግ ያለዉ ጠዓመ (መቐለ) የተባለዉ ከኢሳያስ አፈወርቅ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያለዉ ኮሎኔል መንግሥቱ ሃይለማርያምን ለመግደል ሁለት ራሱ ሆኖ ዝምባዉዌ ድረስ በመሄድ የከሸፈ የመግደል ሙከራ በማድርግ በ1995 በዝምባቡዌ መንግሥት ፍርድ ቤት ሁለት ዓመት ተፈርዶበት እስራቱን ፈጽሞ ወደ ኤርትራ የተመለሰዉ ነዉ። (Evgueny Zakharove, the owner of Aero lift, an airline with a fleet of ageing Antonov and LLyushin transport aircraft, based in Johannesburg registered in the British Virgin Islands), ባለንብረት ከሆነዉ ግለሰብ እና ብርጋዴር ጀኔራል ጣዓመ፣ ምፅዋ ላይ በ08/2006 ከ19 እስከ 21 ድረስ ያሉት ቀናቶች የቆየ የጋራ ስብሰባ አድርገዉ ነበር።ቅጽል ስሙ “መቐለ” (መቐለ የሚለዉ በአማርኛ ተነጋሪዎች “መቀሌ” በመባል የሚነበበዉ ቃል ነዉ) በመባል የሚታወቀው ብርጋዴር ጠዓመ ጎይተኦም ከኤርትራ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ዉጭ ሌላ ተራ ፓስፖርቶች ማለትም የኢትዮጵያ ፓስፖርት፤ የስዑዲ የኩዌት እና የመሳሰሉት ፓስፖርቶች በመያዝ በአፍሪካ ቀንድ ለሚንቀሳቀሱ ለሶማሌ የእስላማዊ ፍረድ-ቤት ህብረት ታጣቂዎች እና ለታሚል ታጋዮችን የመሳሪያ ሽያጭ እና ማስተላለፍ ስራ ለሚሰሩ ቡድኖች ለመምራት እና ለማስተባበር በኢሳያስ አፈወርቅ የተመደበ ሰዉ ነዉ።
ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ እና በኤቭጉኒይ ዛካሮቭ ፌርማ እና ፈቃድ ኣማካኝነት በብርጋዴር ጀኔራል ጠዓመ አስተባባሪነት 76 ጊዜ በረራ በማካሄድ ከሶቭየት ሕብረት ከዩክረይን ከኢራን ከ ሊቢያ የመሳሪያ የግዢ ጭነት ሲያመላልስ ለዛካሮቭ በተለይም በ12/07/2008 ከቁጥር የበረራ መዝገብ 76496 የ$1.5 ሚሊዮን ዶላር (770.000 ሺሕ ፓዉንድ) በተናጠል በኮንትሮባንድ ዋጋ ሲከፈለዉ፡ 76ቱ ጊዜ በዉጭ ምንዛሬ በማዕከላዊ 114 ሚሊዮን ዶላር (58 ሚሊዮን ፓዉንድ) ተከፍሎታል። ይህ የመሳሪአዎቹን ዋጋ አይጨምርም።ለበረራ ብቻ የተከፈለ ነዉ። በመሳሪያ ሽግግር እና ግዥ ስራ ቀንደኛ ተዋናይ ሌላዉ ክፍል “ቀይ ባሕር የንግድ ተቋም” ተብሎ የሚጠራ ስራስኪያጁ ዛሬ በእስር የሚገኝ “ተክኤ ኪዳኔ” ነበር። በጁላይ 13/2007 ጽ/ቤቱ አስመራ የሆነዉ ኤሪክ ኢንተርፕራይዝ (Moscow and Asmara, the capital of Eritrea, between Aerolift and Eriko Enterprise of Asmara) በመስኮ እና በአስመራ ከተሞች የመሳሪያ ግዥ ስምምነት ተፈራርሟል።ፌርማዉን ከፈረሙት ተፈራራሚዎች “ታደሰ ክታሙ” የተባለ በኤርትራ በኩል ከሞስኮ ደግሞ “ሺቶላይ አንደረንስኪ” ናቸዉ። ሺቶላይ አንደረንስኪ በደርግ ጊዜ ወደ ኢትየጵያ ሲጫን የነበረዉን ማሳሪያ እና ሎጂስቲክ ሲቆጣጠር እና በሃላፊነት ሲያስተዳድር የነበረ የኬጆቢ አባል ነዉ። ይህ የኮንትሮባንድ መሳሪያ ሽግግር ሲደረግ እንዳሁኑ ዝርዝር ኖሮት ግልጽ ባያደርገዉም ዘሳንደይ ታይምስ የተባለ ጋዜጣ በጁላይ ጠቅሶት እንደነበር ይታወሳል።
“…ዛካሮቭ የሚያበራዉ የጭነት አይሮፕላን ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸዉን የብሪታንያ የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸዉ አክራሪ እስላሞች ወደ ኤርትራ እንደልባቸዉ እንዲገቡ እና እንዲወጡ ረድቷል። ዛሬም ቀጥሏል። በረራዉ ከተለያዩ አገሮች ማለትም ማሳሪያ በመሸጥ የታወቁት አገሮች ከዩከረይን ከካዛኪስታን ከኢራን ሞስኮ ቻይና ወደ ሊቢያ እንዲጫን ከተደረገ በሗላ ለማየት እንዲያስችላቸዉ ዓይናቸዉ ብቻ ክፍት በማድረግ ፊታቸዉን በጥምጣም ጭምብል በመሸፈን ማንነታቸዉ የማይታወቅ ሰዎች ከሊቢያ አስከ ኤርትራ ድረስ ታጅቦ መሳሪያዉ እንዲራገፍ ተደርግዋል።
ምፅዋ አይሮፕላን ማረፊያ ከወረደ በሗላ በ ኢሳያስ አፈወርቂ እና በባሕር ሃይሉ አዛዥ ፍጹም ገ/ሕይወት በምስጢር ተጎብኝቶ ርክክቡ ከተከናዋነ በሗላ መንግስት አልባ ወደ ሆነችዉ ወደ ሶማልያ እና ወደ ታሚል ታይገርስ ወደ ስሪላንካ ተሸጋግሯል። ከስር ላይ ሆኖ የመሳሪያዉ ቅብብሎሽና የባሕር መርከቦችን የጠለፋ ዉንብድና የሚያጠናክረዉ፤ የሶማሊዉ “ዳሂር አወስ” ሲሆን የባህሩን ዉንብድና እንደ ዋነኛ የገቢ ምንጭ እና ለዉጭ አገር ምንዛሪ የሚጠቀምበትና ዉንብድናዉን የሚመራዉ ግን የኤርትራዉ ፕረዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ነዉ። ወደ ሶማሊ ሲጫን የነበረዉ ማሳሪያ የሶማሌ ግምባሮች እንደተከፋፈሉ. ጂቡቲ ወስጥ የሶማሊን ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ በወቅቱ ከሶማሌዉ የእስላሞቹ ሕብረት ጊዜአዊ መንግስት ጋር ከነበረዉ ሸኽ ሸሪፍ ጋር ስትነጋገር መሳሪያ ከኤርትራ እደሚያገኙ በDecemebre 2007 ፍንጭ አግኝታ ነበር።የተባበሩት መንግስታት ተከታትሎ መረጃዉን ለማግኘት ዕቅድ እና ፍላጎት ያደረበት መሆኑን ያወቀዉ ኢሳያስ አፈወርቅ አንዳች ዘርዝር ሚስጢር ቢወጣ በሸኽ ሸሪፍ ላይ የግድያ እርምጃ እንደሚያስወስድበት በተዘዋዋሪ ለሸኽ ሸሪፍ እንዲደርሰዉ ስለተደረገ የሚያዉቀዉ ዝርዝር ምሰጢር ከማዝረክረክ አግዶታል። አከታትሎም፤ የአሜሪካ ቴክሳስ ክፈለሃገር የኤፍ ቢ አይ ምርመራ ክፍል ሃላፊ እንደዘገበዉም አንድ በቴክሳስ ከተማ ፈርድ ቤት በሽብር ተግባር በመሳተፍ በጥፋተኛነት ተከስሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ የተፈረደበት የአልቃይዳ አባል በጊዜ የሚፈነዱ ቦምቦችን አያያዝ እና አጠቃቀም የስልጠና ተግባር ሶማሌ ድረስ ሄዶ የሰለጠነ መሆኑን ሲያምን አብረዉት ከኤርትራ መንግስት የተላኩ የቦምብ ጠመዳ ምህንድስና ባለሞያ አሰልጣኞች ትምርቱን ለእሱ እና ለመሰል ሰልጣኞች ያሰለጥኑዋቸዉ እንደነበሩ አምኗል።
ይህንን የሚያረጋግጥ ለልዩ ልዩ ተልዕኮ ኤርትራ ወደ ሶማሌ የተላኩ ሰዎች ኬኒያ ከእስላማዊ ሃይል ሽብርተኞች ጋር በተግባር ተስማርተዉ ከሶማሌ የኢትዮጵያ ጦር ሸሽተዉ ወደ ኬኒያ ድንበር ሲገቡ የያዝኳቸዉ ናቸዉ ለኢትዮጵያ አስተላልፋ ከሰጠቻቸዉ መካከል የሃምሳ እልቅና ማዕረግ የነበረዉ የወታደራዊ መሃንዲስ ባለ ሙያ እና አብረዉትም የተያዙት ጋዜጠኞች መካከል ተስፋልደት ኪዳነ ፤ተስፋዝጊ እና ሳልሕ እድሪስ የማሳሰሉት መያዛቸዉን ኢሳያስ አፈወርቅ ከቲቪ ኤሬ ጋር ባደረገዉ ቃለ መጠይቅ በሽርደዳ መልክም ቢሆን በተዘዋዋሪ ሳይወድ መያዛቸዉን መልስ በመስጠት አምኗል።…ይቀጥላል