Tuesday, September 16, 2008

The Third wave and the unsolved Eritrean and ethiopian issue






ይድረስ ጥያቄየ ለአቶ ክፈሉ ታደሰ
እና
ለተቀራችሁት የኢሕአፓ አመራሮች ከጌታቸዉ ረዳ የኢሕአፓ ከፍተኛ መሪ የነበሩት አቶ ክፍሉ ታደሰ በኢሕአፓ ዲሞክራሲ የህዋ ሰሌዳ ተለጥፎ ያዳመጥኩት “የፓል-ቶክ” ቃለ መጠይቅ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ብዙ ትምርቶችና ካሁን በፊት ተደብቀዉ የቆዩ አንዳንድ ምስጢሮች ሳይቀሩ ለሕዝብ ይፋ ያደረጉበት መድረክ ነበር።እንዳዳምጠዉ ለጠቆመኝ ወንድም አመሰግናለሁ።

ከዚህ በታች የማቀርበዉ እላይ በጠቀስኩት መድረክ ተገኝቶ ኢሕአፓ ስለ ኤርትራ ጉዳይ የነበረዉ አቋም እንዲያብራራ ሲጠየቅ የሰጠዉ ምላሽ የተሸፋፈነ ከመሆኑ አልፎ ኢሕአፓ በፕሮግራሙ አስፍሮአቸዉ የነበሩትን ኤርትራን በሚመለከቱ ጉዳዮች ለምን በቀላሉ ሊያልፈዉ እንደፈለገ አልገባኝም።
የሶማሌዉን ክብደት በመስጠት ጠለቅ ያለ ማብራርያ አሰጣለሁ ብሎ በይደር ለሌላ ቀን ቀጠሮ ሲያስመዘግብ፤ ሕሊናችንን ሁሌም የቀለበዉና ለወደፊቱም ከህሊናችን ላንዳፈታም ቢሆን በቀላሉ የማይታየዉን የኤርትራ እና-የኢትዮጵያ ጉዳይ ኢሕአፓ የነበረዉ ግንኙነትና እንዲሁም ለወደፊቱ ኢትዮ ጵያ ምን ዓይነት ስልት ብንከተል በልጆቿ ባንዳዎች እና በዓለም ዙርያ ባሉት ጠላቶቿ ሴራ እየተደረገባት ካለዉ ግፍ በእንዴት ፍትህ ልትቀዳጅ እንደምትችል ካለዉ ሃበታም ልመድ እና ዕዉቀት መግለጽ ነበረበት እላለሁ። ያ አላደረገም። ወንድሜ አቶ ክፍሉ “ሦስተኛ መስመር” የሚለዉ የኢሕአፓ መፍትሔ ምን እንደሆነ ስላላብራራዉ በእኔ በኩል በፍጹም ምን ማለት እንደሆነ አልጨበጥኩትም።
እንደ አባባሉ “ሦስኛ መስመር” ከሞላ ጎደል ቅንጅት የተከተለዉን ዓይነት መስመር እንደሆነ ነካክቶታል።የኤርትራ ጉዳይ በሕዝብ ድምጽ (በሁለቱም ህዝቦች መካከል?) መፈታት አለበት ሚባል ከሆነም እዚያ ሊያደርሱ ሚያስችሉንን የትግል ስልቶች “3ኛ-መስመር” የሚባለዉ ነገር ካሁን በፊትም ሆነ አሁን የዘረዘረዉ ነገር ስለሌ ያንኑን ማብራራት ነበረበት። አስካሁን ድረስ መፍትሄ ያላገኘ ለወደፊቱም ከፍተኛ የግጭት መንስኤ የሚሆነዉን የኤርትራ እና የእኛዉን ጉዳይ ህዘቡ በተለያየ ስልት ተሰልፎ መፍትሔ አጥቶ “አልቦ ስልት” ሲዋዥቕ 3ኛ መስመር እንዴት “ብቸኛ” መፍትሔ መሆን እንደሚኖርበት ግልጽ አንዲሆን ጋባዦቹ ተመልሰዉ ጥያቄዉን ብየነሱት መጠቆም እሻለሁ።

ያስ ባልከፋ፡ወንድሜ አቶ ክፍሉ ለኤርትራ ጉዳይ ተጠያቂዎቹ ንጉሱ እና ደርግ ሲያደርግ 3ኛዉን መስመር ሙያ ላይ ቢዉል ዓይነተኛ እና ብቸኛ የግጭቱ መፍትሔ ፍትሕ አመንጭ ይሆን አንደነበር በሙሉ ድፍረት አስቀምጦታል። ኤርትራን በሚመለከት የንጉሱ ሹማመንት የተከተሉት/የፈጸሙት/ ስለቶች እና ያስተዳደር እርምጃዎች ባንዳንድ ሁኔታዎች የሰላም እና የፍትሕ መብት ተጻብኦ እንደነበር ባይካድም፡ ኢሕአፓ በትግሉ እና በስልቱ እንዲሁም በፕሮገራሙ ላይ የፈጸማቸዉ አንዳንድ ስሕተቶች እንደነበሩት ሁሉ ንጉሱም በዛ መልክ ባስተዳደራቸዉ የታየዉ የትግል ስልት እና ድክመት “የጥላቻ እና መለያያ መንገድ ያስተናገደ ወይም በር የከፈተ” ተብሎ መወንጀል ተገቢ አይመስለኝም።

የጥላቻ ፖለቲካ መነሻ እና ፈጣሪዎቹ/አስተናጋጆቹ ዓረቦቹ እና ዓረቦች ነን ብለዉ ጸረ ክርስትያን ሃይማኖት እና ጸረ ኤርትራዊያን-ክርስትያን የቆሙት ጸረ-ኢትዮጵያ “ቪቫ-ኢታሊያ- (ፕሮ-ኢታልያ-የጣልአን ደጋፊ)” እና በምዕራባዊ ቆላ ተወለጆች የራቢጣ አል ኢስላሚያ/ጀብሃ..ሓራካ… እስላሞች እና በሗላም በትዕቢት የተወጠሩ ሲ.አይ. ኤ ያደራጃቸዉ የክርስቲያን ጎሰኞች እነ ኢሳያስ አፈወርቂ የመለያየት እና የጥላቻ በር ከፋቾች ምክንያት የሆኑት እንጂ ንጉሡ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ?
ዛሬ ኤርትራ የምትባል የድሮዋ “ምድሪ ባሕሪ”- “ባሕሪ ነጋሲ”-“ባሕረ-ነጋሽ” “መረብ ምላሽ”…..” ዛሬ ለኤርትራ መገንጠል እንደዋነኛ ተከሳሽ ሆነዉ በየመድረኩ እየተከሰሱ ያሉት ንጉሱ በትግላቸዉ ባስመለሷት ኤርትራ ተመልሰን መዉቀሳችን ሊገባኝ አይችልም።ኤርትራ ከኢትዮጵያ በፌደረሽን ትቀላቀል ብለዉ 46 አገሮች ድምጽ ሰጡ። ኮሚሽኑም ኤርትራ ሄዶ ሕዘቡን ስሜት ይዞ የወሰነዉን ታዉቁታላችሁ።በፌደረሽን ለጊዜዉም ቢሆን (10ዓመት) ትተዳደር አሉ እንጂ ለወደፊቱ ከኢትዮጵያ ጋር እንዳትዋሃድ የሚል እኮ የለበትም። ከሕዝባችን ጋር እንዋሃዳለን ብለዉ ዉሳኔ ያሳለፉትም እኮ “ትዋሃድ ብለዉ የደነገጉት” ንጉሡ ሳይሆኑ የኤርትራ ምክር ቤት ማንም ተጽዕኖ ሳያደርግበት ፍጹም በሆነ ዲሞክራሲ ተመርቶ መዋሃዱን እንፈቅዳለን ሲል ህዳር 5 ቀን 1955 ዓ.ም ውሳኔ አሳለፈ። ውሳኔዉ ለኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርቦ በዚህም ፓርላማ ዉስጥ ከ250 የሕዝብ እንደራሴዎች 25ቱ የኤርትራ ሕዝብ እንደራሴዎች 25ቱ የኤርትራ እንደራሴዎች ናቸዉ። ከ125 የሕግ መወሰኛ አማካሪዎች 5ቱ ኤርትራዊያን ነበሩ።ከነሱ መሃል አንድም እንኳ የተቃዉሞ ድምጽ አላሰማሙ።ብለዉ ከፓርላማዉ እና በዉሳኔዉ ውስጥ ተካፈሉት ምስክሮች አሉ።(የአፄ ሃይለስላሴ ታሪክ -ደራሲ ብሪሁን ከበደን ይመልከቱ)-;-
ታዲያ ይህ ሕጋዉ መድረክ ጥሰወዉ በጉልበት ፍትሕን ለመዳጥ የተነሱ ለዓረብ ያጎበደዱ ህሊናቸዉ የሳቱ “ወገኖቻችን” እነ አድሪስ ዓዋተ በፈጠሩት ጥላቻ እና ጦርነት በምኑ ስሌት ንጉሡ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ። ጦርነት የጀመሩት ንጉሡ ሳይሆኑ በዉስጣቸዉ እንኳ መስማማት አቅቷቸዉ የሃይማኖት ፤የነገድና የቡድን ግጭት ፈጥረዉ ቢያነስ 17 ዓመት እርስ በርሳቸዉ “እስላሕ”፤- “ኮሚቴ-ተጋደልቲ”- “ሱሉሳዊ- ሓድነት( ሱሉሳዊ -ሓድነት-ኢሳያስ የነበረበት አንጃ ነዉ) እያሉ ገና ጃብሃዎች ትግሉን “ሃ” ሳይሉ ራሳቸዉ የፈጠሩት የመገዳደል እና የጥላቻ ፖለቲካ እንዴት ተኩኖ ንጉሱ ለጥላቻዉም ሆነ ለመለያየቱ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ?
የደርግ ሠራዊት አመራር በማጣቱ አንጂ ጥያቄው እኮ የአገር እኮ ነዉ።ወደብ እኮ ነዉ። “የመኖር” ወይንም “አለ-መኖር” የባሕር በር ጉዳይ ባለቤትነት ጉዳይ ጥያቄ እኮ ነዉ። የተካሄደዉ ትግል እኮ አበሻነታቸዉ በጣሉ አዉደሐዋሪያቸዉ እና አዉደ ዓመታቸዉ በፈረንጂኛዉ የሚቆጥሩና ከሚያከብሩ አበሾቹ ወገኖቻችን ብቻ አልነበረም።ትግሉና እና ጦርነቱ እኮ የተካሄደዉ ከራቢጣዎቹ ብቻ ሳይሆን ከትልልቆቹ፤ከጥንት ጠላቶቻችን ከ ዓረቦች ጋር እና ከፈረንጆች ጋር ጭምር ነበር!
ኤርትራን እንደገና ከራሷ ደም እና አጥንት ጋር ያዋሃዷት የንጉሱ ጥረት ታክሎበት እኮ ነዉ። ታዲያ አሳቸዉ ባሰመለሱት አንዴት ተመልሰን አስነጠቁን ብለን በግምባር ቀደም ተወቃሽ እንወቅሳቸዋለን? ምድሩ የተወሰደዉ በ1881 ዓ.ም ሲሆን በተወሰደች በ66 ዓመት በ1945 ዓ.ም ነዉ። የ አክሱም ሃዉልት ያን ያህል ዓመት በጣሊያን ይዞታ/አገር ቆይቶ ወደ ቦታዉ ዛሬ ሲመለስ 60 ዓመት በጣሊያን እጀታ ነበር እና ሃዉልቱ የኢትዮጵያ ንብረት ቅርስ መሬት ድንግያ አፈር ዕዉቀት እና ታሪክ ቢሆንም በሬፈረንደም በሕዝብ ድምጽ ለጣሊያኖች ወይም ለእኛዉ ለባለንበረቶቹ ይወሰን እንዴት ማለት ይቻለናል? የተበታተነዉን ሕዝብ የሰበሰቡ፤ያገናኙ ናቸዉ። ጥፋት አድረገዉ ነበር? አዎ! በሰዉ ሕይወት ወንጀል እና የመብት ረገጣ ፈጽመዉ ነበር? አዎ! ማን አለ በዚያ የስህተት ጎዳና ያልተሸጋገረ የፖለቲላ መሪ?

ኦጋዴንም በተወሰደ በ1923 በ21 ዓመቱ በ1947 ዓ.ም አስመለሱት።

ጋምቤላም የተወሰደዉ በ1894 ዓ.ም ሲሆን በተወሰደ በ56 ዓመት በ1950 ዓ.ም ወደ ህዝቡ ተቀላቀለ።
በጠላት ተወስደዉ የነበሩት የተበታተኑ ህዝቦቿ ያስመለሱት ንጉሱ የጦርነቱ ቀስቃሽ እና የመለያየት ቆስቋሽ ተደርገዉ መታየት በእዉነቱ አዲሱ ትዉልድ የተሳሳተ ታሪክ ከማስተማር አልፈን “ኤርትራዊያኖቹ ከተጠያቂነት” ነጻ አድርጎ እንደ “ተበዳይ” አድርጎ የሚያቀርብ ሰዕል ይመስለኛል።ያ መቀጠል የለበትም።

እንዴ እኛም እኮ አግዚሃርን እኮ መፍራት ተገቢ መሰለኝ። እኛም እኮ ያስረከቡንን መጠበቅ ወይም ማስመለስ ቢያቅተንም ጦርነቱ በከፋ (160 ሺሕ ሕዝብ ለሞት ተዳርጓል) ከንጉሱ በሗላም ከነፃነታቸዉ በሗላም ዛሮም እኮ ቀጥሏል። ንጉሱ አንዴት ተኩኖ የድክመት ማምለጫ ሁሎም እንጠቀምባቸዉ? ሃጥያት እኮ መፍራት ተገቢ ነዉ።

ንጉሱ ያደረጉት የኮሎኒ/የቅኝ አገዛዝ/አያያዝ ሳይሆን ከኛዉ አስበልጠዉ እነሱን ተንከባክበዋል። ታሪኩ በትክክል ይጻፍ። ጣሊያን ከ4ኛ ክፍለ በታች እንዳይዘልቁ ሲያደርግ ንጉሱ ኤርትራዊያኖችን በገፍ ዉጭ አገር ሄደዉ በነጻ እንዲማሩ አድርገዉ አስካሁን ድረስ የሚኖሩበትን ተንደላቃቂ ኑሮ እና እዉቀት ለግሰዋቸዋል።የጥላቻ እና ፖለቲካ በር ከፋቾቹ አነሱ እንጂ ንጉሱ ሊሆኑ አይችሉም።ስለዚህ ተጠያቂነቱ ለሁሉም ቢዳረስ ድርሻ ድርሻዉን ቢያነሳ ጥሩ ነዉ፡የሚል አመለካከት አለኝ።
ለነገሩ 3ኛዉ መስመር የሚባለዉ የቱ ነዉ?ኢሕአፓ የተከተለዉ 3ኛ መስመር የተባለዉ በ1976 ዓ.ም ለኤርትራ መፍትሄ ብሎ ያወጣዉ የሚከተለዉስ ይጨምራል? እሱ ከሆነ እንዴት ከንጉሱ ይልቅ በ1976 ስለ ኤርትራ ጉዳይ መፍትሔ የተባለዉ የኢሕአፓ ፕሮግራም መፍትሄ እና ተመራጭ ሆኖ አቶ ክፍሉ አስካሁንም ቢሆን 3ኛዉ መስመር በተግባር አልዋለም ቢዉል ኖሮ ሰላም እና መፍትሄ ያመጣ ነበር ማለቱ ሊገባኝ አልቻለም።
ኢሕአፓ አወጣዉ ከተባለዉ ሰነድ ልጥቀስ።

መጋቢት 1976 የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም;(በጥራዙ ሽፋን ላይ የሚታየዉ እርእስ- )
በዉስጥ ገጾቹ ደግሞ እንዲህ ይላል ልጥቀስ፦

"የጭቁን ብሄሮች የራሳቸዉን ዕድል በራሳቸዉ የመወሰን መብት/አስከመገንጠልና የራሳቸዉ የሆነ ነፃ መንግስት አስከማቋቋም ድረስ/ መከበር እንዳለበት ማስተማርና መታገል እንዳለብን ሁሉ ጭቁን ብሔሮች በፈቃደኛነትና በእኩልነት ከጨቋኙ ብሔር ሠፊዉ ሕዝብ ጋር መዋሃድ እንዳለባቸዉም ማስተማርና መታገል አለብን…"
 
"….በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለ23 ዓመት ሲካሄድ የቆየዉንና አሁንም እየቀጠለ ያለዉን የኤርትራ ህዝብ የነፃነት ትግል መደገፍ ትክክልና ተገቢ ነዉ።አሁንም ኢሕአፓ የኤርትራ ሕዝብ ሚያካሂደዉ የነፃነት ትግል ይደግፋል።..."

በዘሁ ፕሮግራሙ ኢሕአፓ ስለ ብሔሮች ምን ይላል? ገጽ 23-24 አንቀጽ አራት ቁጥር 1-4 እንዲህ ይላል;--
1- "ጭቁን ብሔሮች ሁሉ ያላቸዉን የራሳቸዉን ዕድል በራሳቸዉ የመወሰን/አስከ መገንጠል ድረስ/ ሙሉ መብት አዉቆ ወዲያዉም ፈቅዶ መዋሃድ በሚለዉ መርህ መሠረት የሚፈልጉትን ዓይነት የሕብረት/መንግሥት በእኩልነትና በወንድማማችነት እንዲያቋቁሙ የፖለቲካ ትግል ያካሂዳል…"
 
ብሎ እንደነበር የሚታወስ ነዉ። ከተሳሳትኩ ልታረም። እላይ የተጠቀሰዉ 3ኛ መስመር ከሚባለዉ አንዱ እንደማይሆን ደግሞ ተስፋ አለኝ።3ኛ መስመር የጀመረዉ ያኔ ከሆነ የሚያነጋግር ይመስለኛል። በሗላም በ1976 የቀረበዉ እላይ የተጠቀሰዉ አስከ መገንጠል ጉዳይ በዲሞክረሲያ በ1982 “አንዳንድ ማብራሪያ” ብሎ ባወጣዉ የማሻሻያ ሃሳብ አቅርቦ

 "… የኤርትራን ጥያቄ በመገንጠል ደረጃ ሳይሆን ከቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ጋር በተሳሰረና ከቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕድል ጋር በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ዉስጥ በተቆራኘ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኝ ማድረግ፤ለዘለቄታ ሰላም፤ለዘለቄታ የሕዝብ ጥቅም ለጋራ ብልፅግና አስፈላጊና ገሃድ የሆነ ምርጫ ይሆናል…" በማለት በዲሞ/ቅፅ 15፡ ልዩ ዕትም ገፅ 14 አርሞታል።
የንጉሡን በኤርትራ የተከተለዉ ፖሊሲ የሚጻረር የኢሕአፓዉ 3ኛዉ መስመር እንደ መፍትሄ ሆኖ የቀረበዉ በ1976ዓ.ም ነዉ ወይስ በ1982ዓ.ም? ይሄ የማሻሻያ ፕሮግራምም እኮ ቢሆን ኤርትራኖቹ አይቀበሉትም።ለአንዴም ለሁልም ባሕራችሁን ነጥቀናል፤ ተዘግታችሁ ኑሩ። እያሉን ነዉ። ታዲያ 3ኛዉ መስመር እየተባለዉ ያለዉ በኤርትራዊያኖች በኩል ሰሚ ካጣ “መፍትሄዉ” ከጉልበት ሌላ ምን ሊሆን ይችልላል ብላችሁ ትገምታላችሁ? ይህ “ዲሞክራሲ” የሚባል ወይንም “የሕዝብ ድምፅ” የሚሉት በወረቀት የተኳኳለ በግብር የማይዉል ፤በዚህ ነባረዊ ዓለም የማይሰራ ምን ቢደረግ ይሻላልል ትላላችሁ? ገራገር ያገሬ የኢትዮጵያ ልጆች አስከ መቸ ድረስ ገራገሮች ሁናችሁ እየተበደላችሁ አገርን ያክል ወደብን ያክል ተዘግቶባችሁ ዲሞክራሲ የሚባል ጠንቋይ ፍትህ ይዞልን በወርቅ ሳህን ይመጣል እያላችሁ ልትኖሩ ነዉ? ወይ አገሬ ዳር ድምበርን እና ወደብን ሚስት እና አገር ዲሞክራሲ ይወሸማቸዉ ብለዉ ፍትሕ በዛ ብቻ ይገኛል ብለዉ የሚዋዥቁ አዲስ ትዉልዶች ካሉ ለመጠቆም ከንጉሡ አንደበት እንዲማሩ አንድ ነገር ልበላችሁ።

(”…ወይ ጉድ? የዚህ ዓለም ሁኔታ የሚያስገርም ነዉ። በግፍ ከተወሰደብን ከራሳችን መሬት ተቆርሶ ወደ በሕር መተላለፊያ በር አንዲሰጠን ስናመለክት መልሱ ወደፊት ይታሰብበታል ሆነ።በዚህ አኳሗን የተወሰደብን መላዉ ግዛታችን ይመለስልን ብለን ጠይቀን ቢሆን ምን ልንባል ኖሯል?...”)

ውስጣቸዉ የነደዱት ንጉሥ ተፈሪ መኮንን። (የኤርትራ ጉዳይ -ዘዉዴ ረታ)
ይህ ሁኔታ በጥልቀት ሲጠና ዛሬ የኤርትራ ነፃነት ያረጋገጠዉ “ዲሞክራሲ” የሚባል ጠንቋይ አንደነበር አስመስለዉ ዛሬም የሄንኑ Dimocracy የሚባል ጠንቋይ አገር እና ወደብ ያስመልሳል የሚሉን

“የዲሞክረሲ” ምሁራን፦ ንጉሱ ከገጠማቸዉ የተለየ ዓለም እየኖርን እንደልሆንን ፖለቲካዉ ለእምቦቆቁላዉ በስሜት ለሚጋልበዉ ላልበሰለዉ ወጣት እናስረክበዉ የሚሏችሁን አዛዉንቶች ለምን መምራት አልቻላችሁም ብላችሁ ብትጠየቋቸዉ ምንኛ ደግ ነበር? ዲሞክራሲ የሚባል ጠንቋይ ወይም 3ኛዉ መስመር የሚባለዉ መመሪያ ሽማግሌዎቹ ካወቁበት በስሜት በቅሎ የሚጋልበዉ የዘመኑ ወጣት መሪ ሆነዉ እየገሩ ካላሳዩት በምን ልምዱ ይጋልበዉ? እያየነዉ! ለመሆኑ አንደዛሬዉ ዓይነቱ “ሊጥ” “ቡሆ” የሆነ ወጣት ታይቶስ ተሰምቶስ ይታወቃል?

በጣም የሚገርመኝ ነገር፦ በንጉሱ ምክንየት ኤርትራኖች እኛ ያላገኘነዉን ክብር እና ዲሞክራሲ አገኙ አንጂ እንደተበደሉ ተመስሎ ፤”ተገፉ፡ አስራቅናቸዉ፤እንዲርቁን በር ከፈትንላቸዉ….” እየተባለ የሚነገረዉ ስህተተኛ ፕሮፖጋንዳ/ቅስቀሳ በቀና ኢትዮጵያዊያን መደገም መቆም አለበት እያልኩ “የኤርትራ ጉዳይ” ታሪክ ፀሃፊዉ ክቡር አቶ ዘዉዴ ረታ ከተናገሩት ልጥቃስ እና በታለቁ ዲፕሎማት በአክሊሉ ሀብተወልድ ምሬት ትምርታዊ ንግግሮች ልሰናበታችሁ።
"ኤርትራዊያን ወንድሞቻቸችን ለሃምሳ ዓመታት የጣሊያን ቅኝ ሆነዉ ከተሰቃዩ በሗላ፤ ለዓሥር ዓመታት በእንግሊዝ ወታደራዊ አስተዳደር በተያዙበት ዘመን ኢትዮጵያዊነታቸዉን ለማረጋገጥ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት” ብለዉ ያን ሁሉ መከራና ፈተና ለምን ሲሉ እንደተቀበሉ፤ በመጨረሻም እናታችን ነሽ ብለዉ ከኢትዮጵያ ጋር ከተዋሃዱ በሗላ፤ምን ቢጎድልባቸዉ መገንጠልን እንደመረጡ ፤ምን ቢበደሉ እናት ኢትዮጵያን እንደጠሉ ታሪክ የሚያቀርብላቸዉን ጥያቄ በወጉ መመለስ ያለባቸዉ እነሱ ናቸዉ። {ዘዉዴ ረታ-የኤርትራ ጉዳይ ገፅ 10}

"…ሀገሬ ኢትዮጵያ በዓለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።…..ኢትዮጵያ ያለፉት ታሪኮቿ በትክክል እንዳስረዱት፤ለነፃነቷና ለመንቷ፤በኮሎኒያሊስቶች ጣሊን ጋር በየጊዜዉ ስተዋጋ፤ያሸነፈችዉ ብቻዋን ነዉ። የተጠቃቺዉም ብቻዋን ስለሆነ፤አገሬ መቸዉንም ለሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም።ዛሬም ሆነ ነፃነቷን ለመጠበቅ፤ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊዉን ዝግጅት ማድረግ ያለባት፤እሷ ራሷ ብቻ ነች።…" {አክሊሉ ሀበተወልድሕዳር 21 ቀን 1949 ዓ.ም}