Saturday, July 19, 2008

For Your File

ለማስታወሻዎ! ለዛሬ ከወያኔ ማህደር የምንመለከታቸዉ አንዳንድ ማስታወሳዎች አቶ ገብረመድህን አርአያ በረሃ ዉስጥ የወያነ ሓርነት ትግራይ ታጋይ በመሆን 12 ዓመት የድርጅቱ የፋይናንስ ዋና ሐላፊ እና በድርጅቱ የሕክምና ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ሆነዉ ተመድበዉ ሲያገለግሉ ቆይተዉ የወያኔን ጸረ ኢትዮጵያዊነት መሰሪ ሥራዎች እንገፍገፎአቸዉ በወቅቱ ለነበረዉ የደርግ መንግሥት ሰጥተዉ በነበሩበት ወቅት ለኢትዮጵያ ራድዮ ጋዜጠኛ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ አንዳንድ ነጥቦችን እያነሳን አዲስ የወያነ ጀሌ በመሆን እያገለገሉት ያሉትን የወያኔን ማንነት ያላወቁ አዳዲስ ተከታዮችና ወጣቶች እንዲያዉቁት ይረዳቸዉ ዘንድ ድርጅቱን ከምያዉቁት ነባር ታጋዮች የሰጡትን ተጨባች መረጃዎችን እነዲመረምሩትና እንዲማሩበት ይሄዉ አቅርበናል።

ድርጅቱ ማን ፈጠረዉ? እንዴት ተፈጠረ? ለምን ተፈጠረ? ለሚለዉ ጥያቄ አቶ ገ/መድህን አርአያ እንዲህ ብለዉ በመለሱት መልስ እንጀምር። ድርጅቱ የተፈጠረዉ በቀድሞዉ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ ትመርታቸዉን ሲከታተሉ በነበሩት በጥቂት የትግራይ ተዎላጆች ነዉ። ማለትም በ65-67 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ነዉ። በዋናነት ድርጅቱ የመሰረተዉ አሁን የት እንዳለ የማላዉቀዉ “መለስ ተኽለ”የተባለ ተማሪ ነዉ። መለስ ተኽለ <ከሻዕቢያ> ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስለነበረዉ ፤ከሻዕቢያ ጋር ተነጋግሮ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ፤ ድርጅቱን የሚመሩና ሚመሰርቱ እንዳንድ የኤርትራ ተወላጅ የሆኑትንና ትግራይ ውስጥ የኖሩትን መልምሎ አሰባሰበ። ወይንም እነሱ እንዲደራጁ አደረገ። ከነዚያ ዉስጥ ግደይ ዘርዓጽዮን አክሱም ያደገ በትዉልድ ኤርትራዊ፤ መለስ ዜናዊ ትክክለኛ ስሙ “ለገሠ ዜናዊ” የኤርትራዊዉ የደጃዝማች አስረስ የልጅ ልጅ፡ እና የመሳሰሉት ኤርትራዊያንን አሰባስቦ ለማስመሰያ ከትግራይ እንደነ አረጋዊ በርሄ ያሉትን የትግራይ ተወላጆች በሽፋን የትግራይ ድርጅት ነዉ እነዲባል ቀላቅለዉ ስብሰባ አደረጉ። ማሕበር ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ (ማገብት) የሚል ድርጅት አቋቋሙ። አብዛኛዎቹ ኤርትራዊያን መሆናቸዉን ገልጫለሁ።በሽፋን ማገብትን ከመሰረቱ በሗላ ብስለታቸዉ ዝቅ ያለ እንዳንድ ሰዎችን በማሰባሰብ በ1967 ጥር ላይ ወደ ሻዕያ ሄዱ። አስፈላጊዉን ትምህርት ከተቀበሉ በሗላ ትግራይ ዉስጥ ሄዳችሁ መንቀሳቀስ ትችላላችሁ ተባሉ። የኤርትራዉ ተወላጅና በሻዕቢያ ዉስጥ ከፍተኛ አመራር የነበረዉ “ሙሴ ባራኺ” እንዲሁም አሁን በህወሓት ዉስጥ ከፍተኛ ቦታ ያለዉ ሰዉ “ጃማይካ” ተብሎ የሚጠራዉ “የማነ ኪዳነ” ሁለቱም በሃላፊነት ድርጅቱን እንዲመሩት ሆኖ ትግራይ ዉስጥ ገቡ። ድርጅቱ ተመሰረተ። ድርጅቱ የሚመራዉ ሻዕቢያ ባወጣለት ፕሮገራም ነዉ። ፕሮገራሙ የሚለዉ “ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም።ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት።ስለዚህ መገንጠል አለባት።ኤርትራን ነጻ ለማዉጣት በመላ ሃይላችን እንቀሳቀሳለን።አስከመጨረሻ ደማችን አናፈሳለን።የትግራይ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክን አንመሰርታለን።>> የሚል ፕሮግራም “አረጋዊ በርሄ” ከኤርትራ ይዞት መጣ። አሱ ይዞት ይምጣ አንጂ አሱም አንዳነድ ጥያቄዎች ነበሩት። ጥያቄዎቹ በመነሳታቸዉ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ትርምስ ተፈጠረ። ይህ ደግሞ የራሱ ታሪክ አለዉ። ባንድ ቃል ከመጀመሪያ አስከ አሁን ድርጅቱ (ህወሃት) የራሱ ነጻ አመራር የሌለዉ፤ ድርጅቱን ከሻዕቢያ በተላኩ የሻዕቢያ ታጋዮች እንዲመሩት፤እንዲቆጣጠሩትና አንዲአቋቋቁሙት በተላኩት “በሙሴ ባራኺ እና በየማነ ጃማይካ” የተፈጠረ ነዉ ማለት ነዉ።

ሲሉ የህወሓት አመሰራረትና ማን እንደመሰረተዉ ግልጽ አድረገዉታል።አርስዎ ወደ ህወሃት በምን ምክንያትና አንዴት ገቡ? ለሚለዉ ጥያቄ አቶ ገ/መድህን ሲመልሱ፦

በመጋቢት1968 ዓ/ም ነዉ የገባሁት። በ1966 ዓ/ም አረጋዊ በርሄን መቀሌ አግኝቸዉ ድርጅት ለመመስረት አስበናል፤ ቀስ በቀስ ለምታቃቸዉ የትግራይ ልጆች ንገራቸዉ አለኝ። በዚያን ጊዜ ብዙም የፓለቲካ ዕዉቀት አልነበረኝም፡ በጭፍን ዓይን <<ትግራኢ ትገነጠላለች የትግራይ መንግሥት አናቋቋቁማለን>> ነበር ያሉኝ።አሁን ፤አሁን ነገሩን ሳስበዉ እንዴት ይህነን ጠባብ ስሜት ልናራምድ ቻልን የሚለዉ ጥያቄ ራሴን ይመታኛል>> መንፈሴ ይረበሻል። በ1966 ዓ/ም የካቲት 11 እንቅስቃሴዉ ሲጀመር ስራየን ትቼ አነሱን ፍለጋ ወደ በረሃ ሄጀ ነበር። ወደ <ሻዕቢያ> ሄደዉ ስለነበር አላገኘሗቸዉም። በዚየዉ ዓመት ክረምት ላይ ገጠር ቤተሰቦቼን ለመጎብኘት ከጓደኞቼ ጋር አንድ ሠርግ ላይ “አረጋዊ በርሄ እና ሥዩም” አገኘሁዋቸዉ።የት ጠፋህ? አሉኝ።

ስለ ድርጅቱ እንቅስቃሴ መንገዶቹን ከገለጹልኝ በሁዋላ ፤ለጥቂት ጊዜ ከተማ ዉስጥ እንድቆይ ተነገረኝ። በ1968 መጋቢት ከነሱ ጋር ተቀላቅየ በረሃ ገባሁ። በዛዉ ዓመት ማለት በ1968 ዓ/ም አረጋዊ በርሄ በፐሮግራሙን አስመልክቶ አንድ ጽሁፍ አቅርቦ ነበር። ጽሑፉም እንዲህ ይላል << ስለትግራይ የመብት ጥያቄ ብቻ ማንሳትና መዋጋት ጠባብ ብሄረተኝነት ስለሆነ ለትግራይ ብቻ ማለት የለብንም፤ በውዩስጥና በዉጭ የሚኖር የተማረዉ ክፍል አይቀበለንም ።ጠባብ ብሄረተኞች ናችሁ ብሎ ሊያገልለን ይችላል። ያስመታናልም።>> የሚል ነበር።<<በስተራተጂ ደረጃ ብሔራዊ ትግል እንደ ስልት ሆኖ ተቀምጦ በእኩልነት የምትመሠረት ኢትዮጵያን ማዋቀር እንደ ዓላማ በፕሮግራማችን ዉስጥ መግባት አለበት።>> ብሎ ነበር።

ከዚያ በሗላ ለማንም ሳያማክሩና ሳያዉቀዉ “ዓባይ ጸሃየ፤ መለስ ዜናዊ እና ስብሓት ነጋ” ወደ ሱዳን በመሄድ <<የ1968 ማኒፌስቶ>> የሚል ጽሁፍ ይዘዉ መጡ። አረጋዊ በርሄ በማኒፌስቶዉ ላይ ያቀረበዉን ኢትዮጵያን በእኩልነት እንመስርት የሚለዉን ሃሳብ ሰርዘዉ <<የትግራይን ሪፑብሊክ መመስረት አለብን፤ የምንታገለዉም ለዚህ ነዉ። ሁለተኛም ብሔር ብሔረሰቦች ተገንጥለዉ የየራሳቸዉን መንግሥት ማቋቋም አለባቸዉ። እኛ ስለ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ እኩልነት ብሎ ነገር አንታገልም። ከፕሮግራመችን ዉጭ አድርገነዋል።>> የሚል ጽሁፍ ይዘዉ መጡ።

በረሃ ላሉት ሁሉ ተበተነ እንደ እነ <ኢሕአፓ> ያሉ ቡድኖች አገኙት። ኢሕአፓ <የትግራይ ወያኔ ጠባብ ብሔረተኝነት የተጠናወተዉ በመሆኑ ኢትዮጵያን ሊያፈራርስና ሊቆርስ ነዉ> ለሚለዉ ክሳቸዉ ማስረጃ አገኙ። በዚህ ጊዜ በነመለስ ዜናዊ የተጻፈ ማኒፌስቶ ሌላ ያልተበቀዉ አቀባበል ጠበቀዉ። በህወሓት ዉስጥ የነበሩ ያንድነት ታጋዮች<<ማኒፌስቶዉ ሲዘጋጅ ጉባኤ ተጠርቶ የተወሰነ ነዉ ወይንስ እንዴት ነዉ? በኢትዮጵያ የእኩልነት ትግል ማካሄድ ከንቱ ነዉ ተብሎ የተጠቀሰበት ምክንያት እንዴት ነዉ?>> የሚል ጥያቄ መጣ። በጣም አስገራሚዉ ነገር ደግሞ ጽሁፉ ዉስጥ << በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ እኩልነት ብሎ መታገል ትልቅ ተራራ እንደመግፋት ያህል እልቂትን የሚያስከትል ነዉ።>> ይል ነበር ማኒፌስቶዉ። <<ኢትዮጵያ የሚል ነገር መነሳት የለበትም። እና ለትግራይ ብቻ ተዋግተን ነጻ ካወጣን በሗላ ትግራይን መንገሥት ማቋቋም አለብን።> አሉ። ሁኔታዉ እየተብላላ ፤በ1969 ድርጅቱን አናጋዉ ። <<የህ ጠባብ ብሔረተኝነት ነዉ፡ ማኒፌስቶዉን አንቀበለዉም።ተቀብለን ብንታገል ጠባብ ብሔረተኞች ናቸዉ ተብለን በ ኢትዮጵያዊያን እንወገዛለን-እንመታለን>> በማለት ከፍተኛ ተቃዉሞ ተቀሰቀሰ።

እንደሚታወቀው ከ23 ከፍተኛ አመራሮች 16ቱ እርተራ ተወላጆች-ናቸዉ።አመራሩን አብዛኛዎቹ ኤርትራዊያኖች ስለሆኑ ለስሙ ብቻ በመአከላዊ ኮሚቴ ዉስጥ አረጋዊ በርሄ ብቻ ነበር። ይህ ደግሞ የነሱን አላማ ለማቀላጠፍ ተብሎ የታሰበ ነዉ>> በማለት ብዙ ታጋይ ተነሳባቸዉ። ግማሹ ወደ መንግሥት እጁን በመስጠት ግማሹ ወደ ሱዳን ሄደ። የድርጅቱ ሃይል ብበዛት ተናጋ፤ተከፈለ። በአመራር ላይ የነበሩ አንድ ነገር ሳያደርጉ እርምጃ እንዉሰድ አሉ።ከሻዕቢያ ህወሓትን ለመመስረትና ለመምራት የመጡ በድርጅቱ ዉስጥ ያሉ ሻዕቢያዎች ሁኔታዉን ከኤርትራዉ የመንካዕ እንቅስቃሴ አነጻጸሩት።

ዓባይ ፀሃየ እና መለስ ዜናዊ የሚሰሩት ደባ ተቃዉመናል በማለት ለኢትዮጵያዊነት ዓላማ በመቆም እንቅስቃሴ ያደረጉ የሚከተሉት ሰዎች የማኒፌስቶዉን ተጻራሪዎች ተብለዉ በሌሊት ታፍነዉ እርምጃ-እንዲወሰድባቸዉ ተደረገ። ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል። መምህር ዳዊት (ዓዲ ግራት) ዑቕባዝጊ በየነ (አክሱም) ሕንጻ ሽፈራዉ (ሽረ) ውርቅነህ ሐጎስ (ዓድዋ) አጽብሃ ዳኘዉ (ዓድዋ)፤በርሐ ጦማለሁ (ዓድዋ) መንገሻ በላይ (ሽረ) ዓባዲ ደገፍ (እንደርታ) ሙሉጌታ አብራሃ (እንደርታ) አልማዝ አስፋዉ (እንደርታ) ኪዳነ ግርማይ (እንደርታ) ሐዱሽ ዮሐንስ (ዓዲ ግራት) ጥቂቶቹ ናቸዉ።

እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በድርጅቱ ሊከሰት የቻለበት ምክንየት በስልት እና በስትራተጂ ደረጃ ኢትዮጵያን የሚያካትተዉን በእኩልነት ያካተተ ፕሮግራም “ስንኩል” ፕሮግራም ነዉ በማለት ዉድቅ ስላደረገዉ ነዉ።

የሚከተለዉን ደግሞ በጥሞና ያንብቡ። የህወሐት አመራር ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በሻዕቢያ እነደተያዘ ተገልጿል። ኤርትራ ለማስገንጠል እንደሚታገል በማሌሊትና በማኒፌስቶዉ አስቀምጦታል። ትግራይ ሪፑብሊክም እመሰርታለሁ ይላል። አንደገና ኤርትራና ትግራይ በማዋሃድ “የትግራይ ትግርኚን መንግሥት የመመስረት ነገርም አለ። ድርጅቱ በኤርትራዊያኖች መያዝ ዋናዉ ዓላማ የኤርትራን ጉዳይ ለማስፈጸም ነዉ?

አቶ ገብረመድህን አነዲህ ይላሉ።

ወያነ እና ሻዕቢያ አባትና ልጅ አነደሆኑ አብራርቻለሁ። ወያነ ከጎንደር ሰቲት ሁመራን፤ጠለምትንና ወልቃይትን በስፋት፤ ከወሎም እንዲሁ ራያና ቆቦ አስከ አሸንጌ ድረስ ያለዉን አካልሎ በካርታ አስገብቶ ይዞታል። በወያነ አነጋገር ይህ << ትግራይ ትግርኚ> በማለት ይጠራል። በ1974 ዓ/ም ቀደም ብሎ የወጣዉ <ፈደረሽን> የሚል ጽሁፍ የ “ትግራይን ሪፑብልክ የመመስረት ጉዳይ እንዳለ ሆኖ፤አስፈላጊ ከሆነም ኤርትራ ነፃ ከወጣች በሗላ የትግራይ ህዝብ ከኤርትራ ጋር በፌድረሽን መንግሥት አንድ ግዛት መመስረት ይችላሉ>> ይላል። አመራሩን የያዙትም ይህነን ዓለማ ለማራመድ ነዉ።

የሚከተሉት ሁለት አስገራሚ አንደኛዉ በመለስ ዜናዉ የተፈፀመ ወንጀል እና ሌላኛዉ ደግሞ ድርጅቱ በወያኔ መሳፍንቶችና በተረዉ ታጋይ የነበረዉ የአድልዎ የምቾት ልዩነት የተጠቀሰዉን ልጥቀስና በረሃብተኛዉ ሕዝብ ስም የተገኘዉ ገንዘብና እህል እምን ላይ ያዉሉት እንደነበር እንመልከትና በዚሁ እንሰነባበት። ለድረቅ የመጣዉ እህል ለምን አልታደለም? ለሚለዉ አቶ ገ/መድህን አነዲህ ሲሉ ይመልሱታል።ሱዳን ዉስጥ ይኖር የነበረ ሰዉ አብዛኛዉ ይህ ጉዳይ ያዉቀዋል። ለርዳታ የመጣዉ እህል አብዛኛዉ በፖርት ሱዳን በኩል ነዉ። እርዳታ እህልና ሌላም ዕቃ በገፍ በመምጣቱና የፖርት ሱዳን ወደብም በማጣበቡ፤ደጋግመዉ አንሱልን ይሉ ነበር።

ያ ሁሉ እህል ወደ ትግራይ የሚያመላልሱ ብዙ ካሚዮኖች ነበሩ። አስፈላጊ የሚሆናቸዉን ከያዙ በሗላ ከዚያ ዉስጥ የረባ ለህዝብ አልሰጡም። ትግራይ ዉስጥ ለታጋይ ሰራዊቱ ቀለብ ከተከማቸ በሗላ <<ዋንዛ>> በሚል የኮድ መጠሪያ በብዙ ሚለዮን ብር ለሱዳን ነጋዴዎች ተሸጠ። የሱዳን ነጋዴዎች በእርዳታ የተገኘዉ እሀል ከህወሓት እጅ ለመሸመት ይሽቀዳደሙ ነበር። እኔ ገቢዉን ገንዘብ ብቻ ነበር የምቆጣጠረዉ። ከእጄ ሲገባ የነበረዉ የሱዳን ፓዉንድ ቁጥሩ ትዝ አይለኝም። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ነዉ ገቢ የሆነዉ። ከዚህ ገቢ የወያኔ ታጋይ ሠራዊት ያገኘዉ ነገር የለም። በሙሉ ለወያኔ አመራር አባላት መዝናኛ ነዉ የሆነዉ።

አንድ ነገር ልጥቀስ፤ በዚያ ጊዜ የኔ አለቃ የፖሊት ቢሮ አባል ገብሩ አስራት የሚባለዉ የልብ በሽታ ስለነበረበት ወደ ዉጭ አገር ለሕክምና ይሂድ ተባለ።40,000 (አርባ ሺህ) ዶላር ስጠዉ ሚል ትዕዛዝ መጣልኝ። በጥሬ ገንዘብ አርባ ሺህ ዶላር ቆጥሬ ሰጠሁት። አርባ ሺህ ዶላር ለአንድ ሰዉ በሚከፈልበት ወቅት የትግራይ ሕዝብ እንደ ቅጠል ያለ ምንም እርዳታ እየረገፈ እንደነበረ መታወቅ ይኖርበታል። ህዝባዊ ነኝ የሚለዉ ወያኔ ህዝባዊ አለመሆኑ ይህ አያረጋግጥም? ሲሉ አቶ ገ/መድህን ጠይቀዋል።

እዉነትም ባቶ ገ/መድህን መረጃ መሰረት፤ አሁን እየታየ ያለዉ በሕዝብ ስም እተደረገ ያለዉ የወያነ ትግራይ ኤሊቶቹ/መሳፍነቶቹ ፤በንቅዘት የመበስበሱ ሁኔታ እንታገል ነበር ሚሉትን የበረሃ ኑሮአቸዉ ምን ይመስል አንደነበረ ወለል አድሩጎ ያሳያል። ተወለደ ወልደማ ፤ገብሩ አስራት እና ብዙዎች ከህዘቡ ለህክምና እና ለትምህርት እተባለ ከድሃዉ ገበሬ የተለቀመዉ የግብር ገንዘብና ከራሃብተኛዉና ከመንግሥት ባንክ የተዘረፉ ሀብቶች፡ መሳፍንቶቹ ሲታመሙ ዉጭ ድረስ ሄደዉ እንዲታከሙ መታከሚያ ዶላር ይሰጣቸዉ እንደነበር የታወቀ ነገር ነዉ። ገብሩም ሆነ ተወለደ ወልደማርያም እና ሌሎቹ ወደ ህወሐት በረሃ ሄደዉ ባይቀለቀሉ አገር ዉስጥ ከወላጆቻቸዉ ጋር ቢኖሩና ቢታመሙ አርባ ሺህ ዶላር የሚአክል ገንዘብ ከወላጆቻቸዉ አግኝተዉ እንግሊዝ አገር፤ ጀርምን፤ አስራኤልና ሳዉዲ-ዓረብ ወዘተ…. ሄደዎ ይታከሙ ነበር ብላችሁ ትገምታለችሁ? በፍጹም፡ አይታሰብም።

በመጨረሻም በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እራሱ በተገኘበት፤ በተሳተፈበት የተፈጸመ የብዙ ሰዉ ሕይወት የጅምላ ግድያ ወንጀል እንመልከትና በዚሁ ላብቃ

አንድ ነገር ልጥቀስ በማለት አቶ ገ/መድህን አርአያ እነዲህ ይላሉ። <በ1975 ዓ/ም ከየት ቦታ እንደተማረኩ ባላዉቅም ከሰባ በላይ ምርኮኞች ነበሩ። ለመግደል ተፈለገ።<<ሳይናይድ>> የሚባል መርዝ አለ።ከቀመስከዉ ትሞታለህ። ያበደን ዉሻ መርዙን በስጋ ላይ ጨምረህ ብትሰጠዉ ዉሻዉ ይሞታል። ራሱ መለስ ዜናዊ ለሕክምናዉ የቴክኒክ ክፍል ሃላፊ ለነበረዉ ለአባዲ መስፍን መርዙን እንዲልክለት መመርያ አስተላለፈ። የህወሓት የእስርቤቶች ሃላፊዉ የነበረዉ ብስራት አማረ ወደ አባዲ መስፍን ሄዶ መርዙን ማለት ሳያናይዱን ይዞ መጣ። የቴትራሳይክሊን ዱቄት ካፕሱል እየከፈተ ከካፕሱሉ ዉስጥ የታሸገዉን መድሃኒት ዱቄቱን እያራጋፉ በምትኩ መርዙን ማለት በሳዮናይድ ሞሉና ካፕሱሉ በፊት እንደነበረ አደረጉት። ሁሉን ነገር ካስተካከሉ በሗላ በአካባቢዉ የመነንጃይተስ በሽታ ስለገባ እንዳትታመሙ ይህን መድሃኒት ዋጡ ብለዉ ሰጡዋቸዉ። ዉሃ ከሚጠጡበት እንስራም ጨመሩበት። መድሃኒቱን እንደዋጡ ሁሉም ረገፉ። በመለስ ትእዛዝ እራሱ ባለበት እነዚህ ሰዎች አስፈጀ>>። ይላሉ አቶ ገ/መድህን።

ማን ያዉራ? የነበረ፤ ‘ማን ይናገር’? የቀበረ። አቤቱ ፤ሁሉን የምትችል የሰማዩ ጌታ እነኚህስ ነብሰገዳዮች በየትኛዉ ቀንህ ትፈርዳቸዉ ይሆን? ሱፍ ለብሰዉ፤ አምሮባቸዉ፤ ተዉበዉና ባገልጋዮች ታጅበዉ ጉዳቸዉን በማያዉቁ የዓለም መሪዎች መሃል ጋር የክብር መንበር ተሰጥቶዋቸዉ ሰዉ መስለዉ ስለ የሰዉ ልጆች ችግር ሲወያዩ፤ በትእዛዛቸዉና በ እጃቸዉ ሕይወታቸዉ ያለፈች፤ በሰማይ ቤታቸዉ ሆነዉ በመስኮቱ ብቅ ብለዉ ወደዚቸዉ ምድር እተመለከቱ የሚታዘቡዋቸዉ አእላፍ ሙታኖች ይች ምድር ምንኛ እንደቆሸሸች ይታዘቡ ይሆን? አገሬ ሆይ! የሚያደርጉትን አያዉቁትምና ይቅር በያቸዉ።//---// ጌታቸዉ ረዳ

ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ 2000