Thursday, April 10, 2008

“Arena” Should Stop Hatching TPLF’s Decadent Egg!




Please read the article with Ge’ez Unicode fonts at Geez Unicode.com (it is free and works with MS words)

“ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን።

አሁንም አሁንም መንደርተኝነቱ አልለቅ ብሎናል።በጣም ክፉ በሽታ!! ከተመሰረተ ስድስት ወር ያስቆጠረው ከአፍቃሬው የኤርትራዉ ቡድን ከነመለስ ዜናዊ ይልቅ የተሻለ መርሃ ግብር ይዞ ይመጣ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀዉ የእነ ገብሩ አስራት ፤ “ዓረና ትግራይ” ጋሽቦ የወጣዉ የ30 ዓመት አረማቸውን ይዞ እንደና ብቅ ብሏል። ። ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት ግብ እንታገላለን በማለት በግንቦት 21 አና 22 / 2000 ዓ/ም ትግራይ ዉስጥ በመቀሌ ከተማ “ሚላኖ” (ባልታጣ ሥም) ተብሎ በሚጠራዉ ሆቴል ባካሄደዉ ጉባኤ፡ አስቀድሞ በወየኔ የተነደፉትን አንቀጾችና በተለይም አንቀጽ 39ኙ የኮሚኒሰቶች አገር የማፈራረስ መርሐ ግበሩን “በአልተገደበዉ” መብት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ጉባኤዉ በተነጋገረባቸዉ በለ6 ዋና ዋና ነጥቦች በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈዉ መግለጫዉ በኢትዮ- ሚድያ ፤ በደቂ አሉላ እና በአይጋ ድረ-ገጾች ለጥፎታል።

“ኢትዮ ሚድያ” በተባለዉ ድረገጽም < ቅንጅት ናችሁ፤ ጠላት ናችሁ…… እያለን ነዉ> ሲሉ ዓረናዎች እሮሮአቸዉ እያሰሙ ነዉ ሲል ዘግቧል። አዲስ ሆነብን’ሳ እንዴት ነዉ ነገሩ?! ተቧድኖ መሰዳደብ የጀመሩት ገና አሁን አይደለም እኮ። በመሰዳደቡ ሁሉም አልተሰናነፉም። የቸገረን ነገር “ለመሰዳደቡ” መሰረት የሆናቸዉ ልዩነታቸው ግን በኢትዮጵአዊነት ዙርያ ያጠነጠነ ትኩረት ያለመሆኑን ሳያሳስበን አልቀረም። አሁን እተሰደብን ነዉ እያሉት ያለዉን መሰረታዊ ቅራኔያቸዉን አስኪ ወደሗላ መለስ ብለን ጸሐፍት የዘገቡዋቸዉንን ለዉይይታችን መነሻ ያመቸን ዘንድ እንቃኝ።

“በፓለቲካዊና በማህበራዊው ዘርፍ ተንሰራፍተዉ የሚገኙት የኢትዮጵያ አስከፊ ችግሮች ከወያኔ የዘር ፍልስፍና ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ” (አታልቅስ ነዉ ሚያስለቅሰኝ - አሸኔ ጌጡ ዜጋ ጥር - የካቲት 1994)። ሁለቱም ይሄንን አይጋሩትም። ረዢም ገለጻ የሚፈልጉ አስከፊ የሚባሉት የአገሪቷ ችግሮች መሀንዲሶቹም፤ወያኔዎች ሲሆኑ፤ ወያኔዎች የምንላቸዉ ደግሞ ሁለቱንም ቡድን የሚያጠቃልል ሁለቱም የሚኩራሩበት ድርጅት ነዉ።

የዓረና ኮሚኒስቶች አሁንም እንምራችሁ እያሉን ያለዉን መንገዳቸዉ ከነ መለስ ዜናዊ አቋም አይለይም። አሁንም ድሮም በበሰበሰዉ አንጃዉ (በመለስ አንደበት) እና በተምበርካኪዉ የቤተመንግሰቱ ቡድን (በአንጃዉ አነጋገር መሰረት) ያኔ ካሰራጩዋቸዉ ጽሁፎች መረዳት እንደተቻለዉ የፖሊሲ ልዩነት አልነበረም።
ልጥቀስ < እነ አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ ችግር በዘር ላይ ከተመሰረተ አድሎአዊ ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ የሚል አመለካከት የላቸዉም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በይዘቱ ከደቡብ አፍሪካዉ ዘረኛ ሥርዓት ያልተለየ ዘረኝነት መሰረት ያደረገ አስከፊ ሥርዓት መመስረቱን አየቀበሉም። ዛሬም ዘርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት፤የወዳጅና የጠላት ትንተና አለ። ትመክህተኛና ጠባብ በሚሉት ሃሳቦች ዙርያ ምንም አይነት አስተሳሰብ ለዉጥ የላቸዉም። በዚህም አቋማቸዉ ከነመለስ ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸዉ ፀባቸዉም መሰረታዊ ቅራኔ አለመሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። (አሸኔ ገጤ - አታለቅስ ነዉ የሚአስለቅሰኝ) አቶ ያሬድ ጥበቡም በዜጋ መጸሔት ቁጥር 11/1993 ባስነበቡት መጣጥፍ እነ ተወለደ (ያሁኑ ዓረናዉንም ጨምሮ) እንዲህ ብለዉ ነበር ፦ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” (ተወልደ ወልደማርያም)። በእወነቱ እነ ተወለደ እና እነ ገብሩ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ አንድነት አዛኞችና ተቆረቋሪዎች ናቸዉ? የሚከተለዉን ከ አቶ አሽኔ ገጤ (አታልቅስ ነዉ ሚአስለቅሰኝ መጣጥፍ) ስለ አንጃዉ ዘረኝነት አና እንካስላንትያ ስድብ የተለዋወቱባቸዉን ባሕርያቶቻቸዉን የተዘገቡትን እንመልከት፦ <በረከት ወደ ተጠናወተዉ አፍራሽ ሚና ስንመለስ የሚያናፍሰዉ ነገር….የራሱን ዘር ማጥራት ቅሬታ መነሻ በማድረግ የመለስን መልክት ይዞ ብብእዴን ፖሊት ቢሮ በኩል ሰፊ እነቅስቃሴ ማድረጉን ነዉ>።< …….. ህወሓትን እንደ ድርጅት ከትምክህተኞችና ከሻዕቢያ ፕሮፓጋንዲስቶች ባልተናነሰ ማጥላላት ነበር የተያያዘዉ። ህወሐት ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ ፤ካድሬዎቹ እንደፈለጉ ሲሆኑ ምንም ዓይነት እርምጃ እንደማይወስድ አድርጎ ለማቅረብ በስፋት ተንቀሳቅሷል።>> (ሪፖርተር መጽሔት ቅጽ 5 ቁጥር 39)

አንጃዎቹ - ስለ ድርጅታቸዉ ምንነት አንዴ አምባገነንት ለብዙ አመታት ነፍሶ በሆደ ሰፊ አቻችለን አዚህ ድረስ ደርሰናል ሲሉን፤ አንዴ ደግሞ ህወሓት ፈላጭ ቆራጭ አይደለም ገና አሁን ነዉ ዱብ ዕዳዉ የመጣዉ ሲሉ እያደመጥናቸዉ ነዉ። <<ወያኔ ግለሰብም ሆነ የድርጅትን ፖለቲካን የሚመዝነዉና ሚለካዉ በዘር ነዉ። ኦሮሞዉን ጠባብ ብሔረተኛ፤ አማራዉን ትምክህተኛ በማለት ። ለምሳሌ << ከትምክህተኞቹ ድርጅቶች ባልተናነሰ ሁኔታ>> ያሉት፤የአማራዉን ህዝብ ከዘር ማፅዳት መአት ለማዳን (አቅሙ ባይኖሮዉም እንኳ) ሲባል የተቋቋመዉን “መ አ ህ ድ” ን ለመጥቀስ ተፈልጎ ነዉ>። (አሸኔ ጌጤ)። በኢትዮጵያ ዙርያ ያጠነጠነ ፀብ አይደለም የልኩት ለዚህ ነዉ። ከዛ አኳያ አንጃዉን የመሩት አቶ ተወልደ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” ሲሉ <፤ለማይወዷት ለማያከብሯት ለማይቀበሏት ለማይፈልጓት ኢትዮጵያ ህወሓቶች (እነ አቶ ተወልደ ጭምር) ተቆርቋሪ ናቸዉ ማለት ተጨፈኑ እናሞኛችሁ አይነት ቀልድ ነዉ> (- አቶ አሸኔ ጌጤ- አታልቅስ ነዉ የሚያስለቅሰኝ ፡ዜጋ መጽሔት)።

የ “ዓረና ትግራይ” መስራቾች እነ ገብሩ አስራት፤ አዉዓሎምና እና አረጋሽ አዳነ ትናንት በረከትን- ዘረኛ፤ አዲሱና ተፈራን- ተጎታች፤ መለስና ሌላዉን የህወሃት መአከላዊ ኮሚቴ አባላቱን -ተምበርካኪና ጥገኛ . ሲሉት የነበረዉን ቡድን ፤ዛሬ “ጠላቶች ናቸሁ ፤ቅንጅቶች ናቸዉ…..አለን” ቢሉን ፤እኛኑን ምሰኪኖች ሲሰዳደቡ ግራ ለማጋበት ካልሆነ ፤እየተጓዙበት ያሉበትን ጎዳና፤መዝሙራቸዉና ሰንደቃላማቸዉ ያዉ የተሓህት ነዉ።በዚህ ከቀጠሉ የሚያስቡት የመጨረሻ ግባቸዉ በምናቸዉ እንወቅ ? <ኢህአዴግ ምን እንደሚያስብ ሳይንስም እግዚአብሔርም አያዉቀዉም> ብለዉታል እኮ ደ/ር መረራ ጉዲና።

ከፕሮግራሙና ከታሪክ ጀርባዉ ከ’ዚያ ሁሉ ትርምስና ትምህርት በመቅሰም ከወያኔ ወጥዉተዉ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገዉ የኢደፓ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ያደረግነዉ ጥፋት ከልምድ ማነስ ነዉ..” አያሉ የቅርታ መሳይ እንዳልጠቃቀሱ ሁሉ አሁን ተመልሰዉ አገርን ለመገንጠል የኮሚኒስቶች ሕግ ስራ ላይ ያለገደብ ለማዋል በጽናት እታገላለሁ ብሎ አንቀጽ 39ን በአዋጅ የሚደነግግ የትግራይ ተወላጅና ድርጅት በትግራይ ስም “ዓረና ትግራይ” ሲሉ ከተደራጀዉ “ኤርትራዊዉ ወየነ ትግራይ” ለይይተን የምንቀበለዉ መንገድ ከቶዉኑ በምኑ?።

በአጽንኦት ዛሬም የምለዉ፡ የነስብሐት ነጋ ፕሮግራም በዓረና ፓርቲ ስም ተግበራዊ እንዳይሆን ሀቀኛ የትግራይ ተወለጆች የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ መቀጠል ይጠበቅባቸዋል። ዛሬም ማንም ይሁን ማንም ከመንደርተኞች፤ ጋር ያለዉ ቅራኔ ዛሬም ነገም ለወደፊቱም ትግሉ በአነድነት ሃይሎች በኩል በሰፊዉ ይቀጥላል። ሞት የማይቀር ጽዋ ነዉ፤ ግን ታሪክ የእያንነዳንዳችን ስራ እየዘገበ ነዉ! የትግራይ ሕዝብና በተለይም ምሁሩ ክፍል ይህንን የታሪክ ሴራ ሰብሮ መዉጣት ይጠበቅበታል።

ከ7 ዓመት በፊት የተስተጋቡት ድምጸች ዛሬ ተመልሰን ብናስተዉላቸዉ፡ እነ ገብሩ ከተሓህት ሲነጠሉ ያኔ በአገር ዉስጥ በሚታተሙ መጸሄቶች ላይ የኔ ጽሁፎችን ተከታተላችሁ ከነበረ፤ቡዱኑ ቢነጠልም ያዉ ወየነ የሚሸተዉ ባህሪዉ እንደማይለቀዉ “ሃሎ! ሃሎ! መቐለ ድዩ? ሃሎ ማዞርያ! ሃሎ!ሃሎ መቀሌ ነዉ? ….” በሚል በዜጋ መጽሄት ላይ ስተነበይ። አብሮም፤ ወያኔዎች ለሁለት ሲነጠሉ በዉጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በጋራ እና በተናጠል ካዉሮፓ ፤ከካናዳ እና ከሰሜን አሜሪካ ያስተላለፉዋቸዉን በታሪክ የተመዘገበ አሳፋሪ ያቋም መግለጫዎቻቸዉ ከትችት ጋር አቅርቤ ነበር።

አብዛኛዉ የትግራይ ተወላጆች ለአንጃዉ ለእነ ገብሩ ቡድን ድጋፋቸዉን ና የነበራቸዉን ከበሬታ በየመግለጫቸዉ ገልጿዋል።ዉጭ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ወያኔዎች ለሁለት በመነጠላቸዉ ምክንያት ለምሳሌ ከስያትል የትግራይ ተወላጆች በሚል የተላለፈዉ የእንግሊዝኛዉ መግለጫ ብንመለከት፦

“አንቀጥቅጥ ብርድ ይዞ ከወደሰማይ እየቀዘፈ የመጣ ነፋስ ቆፈን መና አስቀርቶናል፡ብርድ ብርድ ብሎናል፤ቀፍፎናል። በዚህም አልተደሰትንም ፤ከፍቶናል። የተለየዉ የማአከላዊዉ አባሎችና አመራሮች ወደስልጣናቸዉ ባስቸኳይ ይመለሱ>>፤ ብሎ ሲደመድም ፦

ከሚድዌሰት ዩ፤ኤስ ኤ የትግራይ ተወላጆችም የተላለፈዉ በተመሳሳይ እንዲህ ብሎ ነበር፡-

<< ስለመሪዎቻችን መከፋፈል ምንኛ እነደተሰማን ቃላት ኖሮን ለመግለጽ ብንታደል ጥሩ ነበር፤ግን ቃላትም ተፈልጎ ሊገልጸዉ አልተቻለም። አጠቃላይ ግን የመሬት መደርመስ ያህል ተሰማን። ስሜቱ መንፈሳችንን ገነጣጥሎታል፤ደንግጠናል፤ወና ነገር ፤አነዳች ነገር ሆነናል ፤ ተከድተናል ፤ተዋርደናል፤አፍረናል እጅግ ተቆጥተናል። የፈለገዉ ዓይነት ምክንየት ቢኖርም እነደዚህ ዓይነት መዓት ለማየት በቂ ምክንየት ነዉ የሚባል ነገር ሊያሳምነን አይቻለዉም።ይህ ዕብደት ነዉ። የናንተ የመሪዎቻችን መተክያ አይገኝለትም።>>

ይህ ሁሉ ድንጋጤ እና ከበሬታ የሰጥዋቸዉ ምክንያት በግላችን የተቆጠበ አስተያየት ቢኖረንም፡የህወሐት መስራች አንዱ ከነበሩ. በሎስ አንጀለስ አሜሪካ ዉስጥ ሚኖሩት አቶ ሃይሉ መንገሻ ግን በዉጭ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ፤ያኔ ለአንጃዉ ያሳዩት ያልተቆጠበ አክብሮትና ለድጋፋችዉ ዋና ምክንያት የሚከተለዉ እነደነበር ይገልጻሉ።

<” አሁንም በነመለስ የተወገዱት የህወሐት ማአከላዊ ኮሚቴ አባላት እዚህ ሁኔታ ላይ ያደረሳቸዉ መለስ ብቻ ሳይሆን አብረዉ የፈጠሩት ኢ-ዲሞክራሲያዊ ብቸኛ ድርጅት መሆኑን አምነዉ ከዚህ በመማር ሰፊዉን ኢትያጵያ ህዝብ ሊያሳትፍ የሚቻልበትን ከልብ ከተነሱ’ና ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመስራትም ከቻሉ ያሁኑ ፍርክስከስ አዎንታዊ ገጽታ ይኖረዋል። በነገራችን ላይ በዉጭ አገር ያሉት የትግራይ ተወላጆችም እርዳታዉንና ድጋፉን የሚለግሱላቸዉ በዚህ መንገድ ይጓዛሉ ከሚል ጽኑ እመነት ነዉ።”>> (ሃይሉ መንገሻ አትኦጵ መጽሄት ነሓሴ 1993 ዓ/ም)

ታድያ በአቶ ሃይሉ እላይ እንደተመለከተዉ፡ አንጃዉ አሁን ይዞት ብቅ ያለዉ የወየኔዉ ማኒፌስቶ አንቀጽ 39ኝን ያክል አበጣባጭ የጠላት ፕሮግራም ተይዞ ለአንድነት ከሚታገሉ ህብረ ቢሄር የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪል ማሀበሮች ጋር እንደ ወያኔዎች በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ ሊዳርጋዉ ካልሆነ በቀር አብሮ ሊያራምዳቸዉ ይችላል? የትግራይ ተወለጆች ላንጃዉ መቆርቆርና ለድጋፋቸዉ ምክንያት ያ ከነበረ ይህንን በጽናት እንታገልለታለን እያሉለት ያሉትን የጣልያኖቹን አንቀጽ 39 የፕሮግራም (ቅጂ) ይዞ የተነሳዉን “ዓረና”ሊቀበሉት ይችላሉ? አብረን የምናዉ ይሆናል።

“ዓረና” ከስሙ አንጻር “አንድ የመሆንን” ነጋሪነትን ያሳያል። አንድነት ለማን? ከእነ ማን ጋር? በየትኛዉስ አገራዊ ፖሊሲ? በ ወያኔዉ አንቀጽ 39? ወያኔንና መለስን በብዙሃን ኢትዮጵያ ያስጠላዉ እና በታሪክ ትቢያ ዉስጥ እንዲመዘገብ ያደረገዉ “ዋነኛዉ ሴራዉ” እኮ ይህንኑ ዓረናዎች ተግባራዊ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን የሚልለትን አንቀጽ 39ኙን ነዉ! ታድያ ወየኔ የምንታገል ክፍሎች ዓረናን እንዴት እንደወዳጅ ድርጅት ቆጥረን ስለሱ በጎነት ማስተማርና የጋርዮሽ ህብረት ማቀናጀት የታሰባል? መገንጠል እንዴት የዲሞክራሲ መፍትሄ እና አማረጭ ምንጭ ሊሆን ይታሰባል? የኢሳያስ ኤርትራ ተገንጥላ አሁን የት ነዉ ያለችዉ? አረናዎች ሊነግሩን ይቻላቸዋል?

መለስ ዜናዊ የኮሚኒሰቶች “እስከ መገንጠል “ያለገደብ” መርሖ ለማተራመሻ መገልገያ (means) በመጠቀሙ ኦኖጎች እና ሌሎች ጠላቶች እየጠየቁት ያሉትን የመገንጠል ዓላማ፤ያንኑ አንቀጽ “ያለ ገደብ” እንሰጣለን ብለኸናል ነዉ ፀቡ።ኦኖጎች የሚሉት ፤አገር የማፍረስ መብት “ያለ ገደብ” የሚለዉን ”ተፈራርመናልና ያለገደብ ለግሰን”፤ ነዉ -እያጋጫቸዉ ያለዉ ነገር። ግጭቱ ስለ ዲሞክራሲ ሳይሆን “ያለ ምንም ገደብ የመገንጠል መብት ጥያቄ ነዉ” ።በዚህ የደረሰዉ ኪሳራ ይታያችሁ።ክፍለ ሀገሮቹን ካስራ አራት በላይ ገነጣጥሎ በአዳዲስ አምባገነን ኤሊቶች ሕዝብን ማሰቃየት የዓረና ትግራይ “አዲሱ የዲሞግራሲ አብዮት” ሌላዉ ገጽታዉ ነዉ። በዘህ አኳያ፤ አሁን እየተገባዉ ያለዉ ጉዞ፡”ትብስን ሰድጄ ትገድድን አመጣሁ!” የሚሉትን ዓይነት ወደ ሦስተኛዉ ዙር ጉዞ እየመሩን ይመስለኛል። ይህ ሁሉ እየሆነዉ ያለዉ እነ ገብሩ አስራት ፤እነ ነጋሶ ጊዳዳ “የኢትዮጵያን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ከጠየቁ በሗላ” መሆኑንም ይበለጥኑ ይገርማል።

እነ ገብሩ ከዚያ ካንገት በላይ ፀፀት በሗላ “አሰከ መገንጠል” የሚለዉ ፖሊሲያቸዉ ፤ያዉም “ዛሬ የአማራ ገዢ ትግራይንና ሌለዉን ባልጨቆነበት”፤ “እኩል ሆነናል ባሉበት አፋቸዉ ባለንበት ዘመን” ፤ “ሸዋዊያን ተጋሩ በስደትና በመቃብር በሉበት” ዘመን” ተመልስዉ ዛሬ ለመገንጠልና ለማስገንጠል በጽናት እንታገላለን እያሉን ያሉትን ዲሞክራሲያዊ አብዮታቸዉ፦ ከ1971-1981 ተብሎ ፤ ተብሎ “እመቢ” ያላቸዉ የመገንጠሉ ሴራቸዉ ዛሬ በዓረና ትግራይ ስም ትግራይን ገንጥሎ መሸሸግያ ምሽግ ለማበጀት ይመስላል። አይደረግም እንዳትሉ።ማስገንጠል መብታቸዉ ከሆነ መጠራጠርም መብታችን ነዉና አስኪ እንጠራጠር። ያልተመነጠረ ተጠረጠጠ! ስንትስ ጊዜ እንመንጠር? ብንጠራጠርስ ይፈረድብናል?ተጎድተናል፤ተከድተናል እኮ! ምጽዋ ላይ አፍአበት ላይ ለኢርትራኖች ወግነዉ እኛኑንና እኛነታችንን ገድለዉ፤ ወደብ አልባ እኮ ነዉ ያስቀሩን። ሆ! አሁንም ያለማፈራቸዉ፤ ድፈረቱ! ድፍረቱ!።

ሁለት ምርጫ ይዘዋል።- ማተራመስ ወይንም መገንጠል፦ ”የስብሓት ነጋ ያስር ዓመት (1971-1981) የህወሓት ሊቀመንበርነት ዘመን እንኳ የመገንጠሉን ፍላጎት በትግራይ ሕዝብና በታጋይ አእምሮ ዉስጥ ማስረጽ ስላልቻለ በኢህአደግ ስም ሚኒሊክ ቤተመንግስት ዉስጥ ሆኖ አገሪቱን ማተራመስ መርጧል” (ሃይሉ መንገሻ የተሓህት መስራች አባል።ኢትኦፕ ነሐሴ 1993 ዓ/ም ከተደረገዉ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)።

ወያኔ- “በኢህአዴግ” ስም አገሪቱን ማተራመስ ከቻለ አንጃዉ በ“ዓረና” ስም በፈረቃ ሊገዙን በሚችሉበት ዘዴ እያመቻቹን ይሆን የሚል ጥያቄ ይታየኛል። ከጥዱ ወደማጡ እንዳይከቱን ያስገነዘቡንን አቶ ሓይሉ መንገሻ ሲቀጥሉ፦<በዘመነ ሕንፍሽፍሽ (ትርምስ) ብዙ ንጹሃን ታጋዮች በወገንተኝነትና ጎጠኝነት ሳቢያ ያለቁት ንጹሃን የትግራይ ታጋዮችና ታገልንልህ እየተባለ የሚመጻደቁበት የትግራይ ሕዝብ ስፍር ቁጥር የለዉም።……….አሁንም የመለስን መንግሥት ሊቋቋሙት የሚችሉት እነዚህ አሁን የተወገዱት መሆናቸዉ አይካድም። ሆኖም ትግላቸዉ ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን ከሌሎች የህብረ-ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ዘለቄታ ሰላም እነዲሰሩ መታገል ይጠበቅባቸዋል>>
(ሃይሉ መንገሻ - ከላይ ከተገለጸዉ መጽሄት ቃለ መጠይቅ )

በጎጠኝነት በዘመነ ሕንፍስፍሽ (ትርመስ) ያለቁት የትግራይ ተወላጆች ተሪክ፤- ዛሬ ዓረናዎች ለመጠቀም ያልፈጉትን አጋጣሚ ያገኙትን የሕዝቡ ቸርነት፤ይቅር ባይነት ተጠቅመዉ ታሪክና ታሪካቸዉን በይቅርታ የታጀበ ኑዛዜ ሊነግሩን በተገባቸዉ ነበር። አልታደሉም! ኑዛዜዉ ቀርቶብን ጭራሽኑ አገር የመበተናቸዉን ፤የፋሽስቶችና የኮሚኒስቶች ርዕዮት አጀንዳቸዉን አንቀጽ 39ኝን እንደ ዋናዉ የመታገያ አጀነዳቸዉ ይዘዉ ተመልሰዉ ብቅ ማለታቸዉ የባሰዉ የንቀታቸዉ ብዘት ያሳዝናል።

በነዚህ ጎጠኞች ያለቁት የንጹሃን ደም ማን ይናገር? ለጠፉት፤ ለተሰወሩት፤ ማን ይቁምላቸው? እዉነታዉ እነዳይገለጽ ሲሸፋፍኑ ከርመዉ አሁን ለፍትሕ እንታገላለን ሲሉ ትንሽ ሐፍረት እነኳ አልተሰማቸዉም! ያኔ ባለፈዉ ሰሞን <“ስየ” በኔ ታሪክ ሳይሁን እኔ በምናገራቸዉ ብቻ እንወያይ> ሲለን አድናቆታቸዉን ለግሰዉ ”የኢትዮጵያ ቅርስ” (ሶቨኒር) ነዉ ብለዉ ሸኙት።የሰራነዉ ጉድ አትነጋገሩ፤ እኛ በምንሰጣችሁ አጀንዳ ብቻ ተነጋገሩ ብሎ አነጃዉ ክፍል ሲለን፤ “እኛ ወያኔዎች አይደለንም አንተ በፈለግከዉ አጀንዳ መነጋገር የምትችለዉ ከወያኔዎች ጋር እንጂ ከኛ ከተጎጂዎች ጋር ሊሆን አይችልም፦…. አዳምጡኝ እያልከ እንዳለኸዉ የኛኑንም ስሞታ አዳምጥ፡….. ብለዉ ለተካራከሩ ዜጎች “ኤክስትሪሞች” ብለዉ የሰደቡን በተቃዋሚነት የቆሙ ታዋቂ ግለሰዎች ሰዎች አሉ። ንቀት?!

ተማርኩ የሚለዉ የትግራይ ዜጋም ብሔራዊ ክህደትለፈጸሙ አምባገነኖች ሽንጡን ገትሮ በሙታኖች ስም ወደ ህግ ማቅረብ አልቻለም። ይህ ቸልተኝነታቸዉን ፤የምን አገባኝነትን ወላዋይ ባህርአቸዉን ስናጋልጥ የማይወዱን አሉ። ይህ ቸልተኝነትና የምን ቸገረኝ ራቅ ብሎ ተመለካችነት ባህሪያችንን በመታዘብ ዛሬም እየናቁን መንደርተኞቹ አንቀጽ 39ን “ያለገደብ” ለመተግበር ይሄዉና ተዘጋጅተዋል። አንድ በሉ! ሁለተኛዉ ታላቁ ሴራ ደግሞ ይመጣል - ጠብቁ! ታድያ አገሪቱን ማን ያድናት? አቶ ሃይሉ መንገሻ እነደላዩት “ኢህአዴግን መታገል የሚችለዉ የተነጠለዉ ቡድን ከሆነ” የተቀረዉ ተስፋ ቢስ ሙሁር ወደባረያ ተገዢነቱ ለሁለተኛ ዙር መዘጋጀት ይኖርበታል። አልያም ሙሁሩ አገሪቷ መታገድ ካልቻለ፡- አቶ ሃይሉ መንገሻ እንዳሉት <<ሠራዊቱ የምትታመሰዉን አገር ያድናት”>> (ሃይሉ መንገሻ ኢትኦጵ ነሓሴ 1993 ዓ/ም) ሙሁሩ ምንተሕፍረቱን አጋለጦ ወታደሩ ሕዝቡን እንዲያድን ሲማጸን፤ እኛ ያልተማርን ዜጎች እግዜር ከመአቱ ራሱ ያድነን ከማለት ሌላ ምን እንበል?

<<ይህ አዲስ ቡድን፡ መለስንና አንዳንድ ደጋፊዎቻቸዉን የተወሰነ ፖሊሲዎችን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንቅናቄዎች ስለነቀፈ ብቻ ኢትዮጵያዊ አጀነዳ ማንሳቱን ለማረጋገጥ እንችል ኢሆን? “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት” ዓላማ እንዳለዉ ለማየት እፈልጋለሁ>> ጸጋየ ገ/መድህን አራአያ ቅጽ 9 ቁትር 6 1994 ጦቢያ -በፈረቃ ሊገዙን ባይመኙ!)

“ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን። ለኢትዮጵያ አንድነትና ቤተሰባዊነት ትናንት ቆመናል፤ ዘሬም ነገም በጽናት እንቆማለን።ቁጥር ስፍር የሌላቸዉ በወያኔ ጎጠኝነትና ማን አለብኝነት የተረሸኑ ታጋዬችና የትግራይ ገበሬዎች ደም አሁንም ይጮሃል።”ኢትዮጵያ” ለዘላም ትኑር!
ጌታቸዉ ረዳ ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ
አሜሪካ መጋቢት 2000 ዓ/ም-/-

“Arena” Should Stop Hatching TPLF’s Decadent Egg!

ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን። አሁንም አሁንም መንደርተኝነቱ አል ልለቅ ብሎናል።በጣም ክፉ በሽታ!! ከተመሰረተ ስድስት ወር ያስቆጠረው ከአፍቃሬው የኤርትራዉ ቡድን ከነመለስ ዜናዊ ይልቅ የተሻለ መርሃ ግብር ይዞ ይመጣ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀዉ የእነ ገብሩ አስራት ፤ “ዓረና ትግራይ” ጋሽቦ የወጣዉ የ30 ዓመት አረማቸውን ይዞ እንደና ብቅ ብሏል። ። ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት ግብ እንታገላለን በማለት በግንቦት 21 አና 22 / 2000 ዓ/ም ትግራይ ዉስጥ በመቀሌ ከተማ “ሚላኖ” (ባልታጣ ሥም) ተብሎ በሚጠራዉ ሆቴል ባካሄደዉ ጉባኤ፡ አስቀድሞ በወየኔ የተነደፉትን አንቀጾችና በተለይም አንቀጽ 39ኙ የኮሚኒሰቶች አገር የማፈራረስ መርሐ ግበሩን “በአልተገደበዉ” መብት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ጉባኤዉ በተነጋገረባቸዉ በለ6 ዋና ዋና ነጥቦች በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈዉ መግለጫዉ በኢትዮ- ሚድያ ፤ በደቂ አሉላ እና በአይጋ ድረ-ገጾች ለጥፎታል። “ኢትዮ ሚድያ” በተባለዉ ድረገጽም < ቅንጅት ናችሁ፤ ጠላት ናችሁ…… እያለን ነዉ> ሲሉ ዓረናዎች እሮሮአቸዉ እያሰሙ ነዉ ሲል ዘግቧል። አዲስ ሆነብን’ሳ እንዴት ነዉ ነገሩ?! ተቧድኖ መሰዳደብ የጀመሩት ገና አሁን አይደለም እኮ። በመሰዳደቡ ሁሉም አልተሰናነፉም። የቸገረን ነገር “ለመሰዳደቡ” መሰረት የሆናቸዉ ልዩነታቸው ግን በኢትዮጵአዊነት ዙርያ ያጠነጠነ ትኩረት ያለመሆኑን ሳያሳስበን አልቀረም። አሁን እተሰደብን ነዉ እያሉት ያለዉን መሰረታዊ ቅራኔያቸዉን አስኪ ወደሗላ መለስ ብለን ጸሐፍት የዘገቡዋቸዉንን ለዉይይታችን መነሻ ያመቸን ዘንድ እንቃኝ። “በፓለቲካዊና በማህበራዊው ዘርፍ ተንሰራፍተዉ የሚገኙት የኢትዮጵያ አስከፊ ችግሮች ከወያኔ የዘር ፍልስፍና ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ” (አታልቅስ ነዉ ሚያስለቅሰኝ - አሸኔ ጌጡ ዜጋ ጥር - የካቲት 1994)። ሁለቱም ይሄንን አይጋሩትም። ረዢም ገለጻ የሚፈልጉ አስከፊ የሚባሉት የአገሪቷ ችግሮች መሀንዲሶቹም፤ወያኔዎች ሲሆኑ፤ ወያኔዎች የምንላቸዉ ደግሞ ሁለቱንም ቡድን የሚያጠቃልል ሁለቱም የሚኩራሩበት ድርጅ nwu። አሁንም ድሮም በበሰበሰዉ አንጃዉ (በመለስ አንደበት) እና በተምበርካኪዉ የቤተመንግሰቱ ቡድን (በአንጃዉ አነጋገር መሰረት) ያኔ ካሰራጩዋቸዉ ጽሁፎች መረዳት እንደተቻለዉ የፖሊሲ ልዩነት አልነበረም።
ልጥቀስ < እነ አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ ችግር በዘር ላይ ከተመሰረተ አድሎአዊ ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ የሚል አመለካከት የላቸዉም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በይዘቱ ከደቡብ አፍሪካዉ ዘረኛ ሥርዓት ያልተለየ ዘረኝነት መሰረት ያደረገ አስከፊ ሥርዓት መመስረቱን አየቀበሉም። ዛሬም ዘርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት፤የወዳጅና የጠላት ትንተና አለ። ትመክህተኛና ጠባብ በሚሉት ሃሳቦች ዙርያ ምንም አይነት አስተሳሰብ ለዉጥ የላቸዉም። በዚህም አቋማቸዉ ከነመለስ ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸዉ ፀባቸዉም መሰረታዊ ቅራኔ አለመሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። (አሸኔ ገጤ - አታለቅስ ነዉ የሚአስለቅሰኝ) አቶ ያሬድ ጥበቡም በዜጋ መጸሔት ቁጥር 11/1993 ባስነበቡት መጣጥፍ እነ ተወለደ (ያሁኑ ዓረናዉንም ጨምሮ) እንዲህ ብለዉ ነበር ፦ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” (ተወልደ ወልደማርያም)። በእወነቱ እነ ተወለደ እና እነ ገብሩ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ አንድነት አዛኞችና ተቆረቋሪዎች ናቸዉ? የሚከተለዉን ከ አቶ አሽኔ ገጤ (አታልቅስ ነዉ ሚአስለቅሰኝ መጣጥፍ) ስለ አንጃዉ ዘረኝነት አና እንካስላንትያ ስድብ የተለዋወቱባቸዉን ባሕርያቶቻቸዉን የተዘገቡትን እንመልከት፦ <በረከት ወደ ተጠናወተዉ አፍራሽ ሚና ስንመለስ የሚያናፍሰዉ ነገር….የራሱን ዘር ማጥራት ቅሬታ መነሻ በማድረግ የመለስን መልክት ይዞ ብብእዴን ፖሊት ቢሮ በኩል ሰፊ እነቅስቃሴ ማድረጉን ነዉ>።< …….. ህወሓትን እንደ ድርጅት ከትምክህተኞችና ከሻዕቢያ ፕሮፓጋንዲስቶች ባልተናነሰ ማጥላላት ነበር የተያያዘዉ። ህወሐት ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ ፤ካድሬዎቹ እንደፈለጉ ሲሆኑ ምንም ዓይነት እርምጃ እንደማይወስድ አድርጎ ለማቅረብ በስፋት ተንቀሳቅሷል።>> (ሪፖርተር መጽሔት ቅጽ 5 ቁጥር 39) አንጃዎቹ - ስለ ድርጅታቸዉ ምንነት አንዴ አምባገነንት ለብዙ አመታት ነፍሶ በሆደ ሰፊ አቻችለን አዚህ ድረስ ደርሰናል ሲሉን፤ አንዴ ደግሞ ህወሓት ፈላጭ ቆራጭ አይደለም ገና አሁን ነዉ ዱብ ዕዳዉ የመጣዉ ሲሉ እያደመጥናቸዉ ነዉ። <<ወያኔ ግለሰብም ሆነ የድርጅትን ፖለቲካን የሚመዝነዉና ሚለካዉ በዘር ነዉ። ኦሮሞዉን ጠባብ ብሔረተኛ፤ አማራዉን ትምክህተኛ በማለት ። ለምሳሌ << ከትምክህተኞቹ ድርጅቶች ባልተናነሰ ሁኔታ>> ያሉት፤የአማራዉን ህዝብ ከዘር ማፅዳት መአት ለማዳን (አቅሙ ባይኖሮዉም እንኳ) ሲባል የተቋቋመዉን “መ አ ህ ድ” ን ለመጥቀስ ተፈልጎ ነዉ>። (አሸኔ ጌጤ)። በኢትዮጵያ ዙርያ ያጠነጠነ ፀብ አይደለም የልኩት ለዚህ ነዉ። ከዛ አኳያ አንጃዉን የመሩት አቶ ተወልደ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” ሲሉ <፤ለማይወዷት ለማያከብሯት ለማይቀበሏት ለማይፈልጓት ኢትዮጵያ ህወሓቶች (እነ አቶ ተወልደ ጭምር) ተቆርቋሪ ናቸዉ ማለት ተጨፈኑ እናሞኛችሁ አይነት ቀልድ ነዉ> (- አቶ አሸኔ ጌጤ- አታልቅስ ነዉ የሚያስለቅሰኝ ፡ዜጋ መጽሔት)። የ “ዓረና ትግራይ” መስራቾች እነ ገብሩ አስራት፤ አዉዓሎምና እና አረጋሽ አዳነ ትናንት በረከትን- ዘረኛ፤ አዲሱና ተፈራን- ተጎታች፤ መለስና ሌላዉን የህወሃት መአከላዊ ኮሚቴ አባላቱን -ተምበርካኪና ጥገኛ . ሲሉት የነበረዉን ቡድን ፤ዛሬ “ጠላቶች ናቸሁ ፤ቅንጅቶች ናቸዉ…..አለን” ቢሉን ፤እኛኑን ምሰኪኖች ሲሰዳደቡ ግራ ለማጋበት ካልሆነ ፤እየተጓዙበት ያሉበትን ጎዳና፤መዝሙራቸዉና ሰንደቃላማቸዉ ያዉ የተሓህት ነዉ።በዚህ ከቀጠሉ የሚያስቡት የመጨረሻ ግባቸዉ በምናቸዉ እንወቅ ? <ኢህአዴግ ምን እንደሚያስብ ሳይንስም እግዚአብሔርም አያዉቀዉም> ብለዉታል እኮ ደ/ር መረራ ጉዲና። ከፕሮግራሙና ከታሪክ ጀርባዉ ከ’ዚያ ሁሉ ትርምስና ትምህርት በመቅሰም ከወያኔ ወጥዉተዉ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገዉ የኢደፓ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ያደረግነዉ ጥፋት ከልምድ ማነስ ነዉ..” አያሉ የቅርታ መሳይ እንዳልጠቃቀሱ ሁሉ አሁን ተመልሰዉ አገርን ለመገንጠል የኮሚኒስቶች ሕግ ስራ ላይ ያለገደብ ለማዋል በጽናት እታገላለሁ ብሎ አንቀጽ 39ን በአዋጅ የሚደነግግ የትግራይ ተወላጅና ድርጅት በትግራይ ስም “ዓረና ትግራይ” ሲሉ ከተደራጀዉ “ኤርትራዊዉ ወየነ ትግራይ” ለይይተን የምንቀበለዉ መንገድ ከቶዉኑ በምኑ?። በአጽንኦት ዛሬም የምለዉ፡ የነስብሐት ነጋ ፕሮግራም በዓረና ፓርቲ ስም ተግበራዊ እንዳይሆን ሀቀኛ የትግራይ ተወለጆች የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ መቀጠል ይጠበቅባቸዋል። ዛሬም ማንም ይሁን ማንም ከመንደርተኞች፤ ጋር ያለዉ ቅራኔ ዛሬም ነገም ለወደፊቱም ትግሉ በአነድነት ሃይሎች በኩል በሰፊዉ ይቀጥላል። ሞት የማይቀር ጽዋ ነዉ፤ ግን ታሪክ የእያንነዳንዳችን ስራ እየዘገበ ነዉ! የትግራይ ሕዝብና በተለይም ምሁሩ ክፍል ይህንን የታሪክ ሴራ ሰብሮ መዉጣት ይጠበቅበታል። ከ7 ዓመት በፊት የተስተጋቡት ድምጸች ዛሬ ተመልሰን ብናስተዉላቸዉ፡ እነ ገብሩ ከተሓህት ሲነጠሉ ያኔ በአገር ዉስጥ በሚታተሙ መጸሄቶች ላይ የኔ ጽሁፎችን ተከታተላችሁ ከነበረ፤ቡዱኑ ቢነጠልም ያዉ ወየነ የሚሸተዉ ባህሪዉ እንደማይለቀዉ “ሃሎ! ሃሎ! መቐለ ድዩ? ሃሎ ማዞርያ! ሃሎ!ሃሎ መቀሌ ነዉ? ….” በሚል በዜጋ መጽሄት ላይ ስተነበይ። አብሮም፤ ወያኔዎች ለሁለት ሲነጠሉ በዉጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በጋራ እና በተናጠል ካዉሮፓ ፤ከካናዳ እና ከሰሜን አሜሪካ ያስተላለፉዋቸዉን በታሪክ የተመዘገበ አሳፋሪ ያቋም መግለጫዎቻቸዉ ከትችት ጋር አቅርቤ ነበር። አብዛኛዉ የትግራይ ተወላጆች ለአንጃዉ ለእነ ገብሩ ቡድን ድጋፋቸዉን ና የነበራቸዉን ከበሬታ በየመግለጫቸዉ ገልጿዋል።ዉጭ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ወያኔዎች ለሁለት በመነጠላቸዉ ምክንያት ለምሳሌ ከስያትል የትግራይ ተወላጆች በሚል የተላለፈዉ የእንግሊዝኛዉ መግለጫ ብንመለከት፦ አንቀጥቅጥ ብርድ ይዞ ከወደሰማይ እየቀዘፈ የመጣ ነፋስ ቆፈን መና አስቀርቶናል፡ብርድ ብርድ ብሎናል፤ቀፍፎናል። በዚህም አልተደሰትንም ፤ከፍቶናል። የተለየዉ የማአከላዊዉ አባሎችና አመራሮች ወደስልጣናቸዉ ባስቸኳይ ይመለሱ>>፤ ብሎ ሲደመድም ፦ ከሚድዌሰት ዩ፤ኤስ ኤ የትግራይ ተወላጆችም የተላለፈዉ በተመሳሳይ እንዲህ ብሎ ነበር፡- << ስለመሪዎቻችን መከፋፈል ምንኛ እነደተሰማን ቃላት ኖሮን ለመግለጽ ብንታደል ጥሩ ነበር፤ግን ቃላትም ተፈልጎ ሊገልጸዉ አልተቻለም። አጠቃላይ ግን የመሬት መደርመስ ያህል ተሰማን። ስሜቱ መንፈሳችንን ገነጣጥሎታል፤ደንግጠናል፤ወና ነገር ፤አነዳች ነገር ሆነናል ፤ ተከድተናል ፤ተዋርደናል፤አፍረናል እጅግ ተቆጥተናል። የፈለገዉ ዓይነት ምክንየት ቢኖርም እነደዚህ ዓይነት መዓት ለማየት በቂ ምክንየት ነዉ የሚባል ነገር ሊያሳምነን አይቻለዉም።ይህ ዕብደት ነዉ። የናንተ የመሪዎቻችን መተክያ አይገኝለትም።>> ይህ ሁሉ ድንጋጤ እና ከበሬታ የሰጥዋቸዉ ምክንያት በግላችን የተቆጠበ አስተያየት ቢኖረንም፡የህወሐት መስራች አንዱ ከነበሩ. በሎስ አንጀለስ አሜሪካ ዉስጥ ሚኖሩት አቶ ሃይሉ መንገሻ ግን በዉጭ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ፤ያኔ ለአንጃዉ ያሳዩት ያልተቆጠበ አክብሮትና ለድጋፋችዉ ዋና ምክንያት የሚከተለዉ እነደነበር ይገልጻሉ። <” አሁንም በነመለስ የተወገዱት የህወሐት ማአከላዊ ኮሚቴ አባላት እዚህ ሁኔታ ላይ ያደረሳቸዉ መለስ ብቻ ሳይሆን አብረዉ የፈጠሩት ኢ-ዲሞክራሲያዊ ብቸኛ ድርጅት መሆኑን አምነዉ ከዚህ በመማር ሰፊዉን ኢትያጵያ ህዝብ ሊያሳትፍ የሚቻልበትን ከልብ ከተነሱ’ና ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመስራትም ከቻሉ ያሁኑ ፍርክስከስ አዎንታዊ ገጽታ ይኖረዋል። በነገራችን ላይ በዉጭ አገር ያሉት የትግራይ ተወላጆችም እርዳታዉንና ድጋፉን የሚለግሱላቸዉ በዚህ መንገድ ይጓዛሉ ከሚል ጽኑ እመነት ነዉ።”>> (ሃይሉ መንገሻ አትኦጵ መጽሄት ነሓሴ 1993 ዓ/ም) ታድያ በአቶ ሃይሉ እላይ እንደተመለከተዉ፡ አንጃዉ አሁን ይዞት ብቅ ያለዉ የወየኔዉ ማኒፌስቶ አንቀጽ 39ኝን ያክል አበጣባጭ የጠላት ፕሮግራም ተይዞ ለአንድነት ከሚታገሉ ህብረ ቢሄር የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪል ማሀበሮች ጋር እንደ ወያኔዎች በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ ሊዳርጋዉ ካልሆነ በቀር አብሮ ሊያራምዳቸዉ ይችላል? የትግራይ ተወለጆች ላንጃዉ መቆርቆርና ለድጋፋቸዉ ምክንያት ያ ከነበረ ይህንን በጽናት እንታገልለታለን እያሉለት ያሉትን የጣልያኖቹን አንቀጽ 39 የፕሮግራም (ቅጂ) ይዞ የተነሳዉን “ዓረና”ሊቀበሉት ይችላሉ? አብረን የምናዉ ይሆናል። “ዓረና” ከስሙ አንጻር “አንድ የመሆንን” ነጋሪነትን ያሳያል። አንድነት ለማን? ከእነ ማን ጋር? በየትኛዉስ አገራዊ ፖሊሲ? በ ወያኔዉ አንቀጽ 39? ወያኔንና መለስን በብዙሃን ኢትዮጵያ ያስጠላዉ እና በታሪክ ትቢያ ዉስጥ እንዲመዘገብ ያደረገዉ “ዋነኛዉ ሴራዉ” እኮ ይህንኑ ዓረናዎች ተግባራዊ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን የሚልለትን አንቀጽ 39ኙን ነዉ! ታድያ ወየኔ የምንታገል ክፍሎች ዓረናን እንዴት እንደወዳጅ ድርጅት ቆጥረን ስለሱ በጎነት ማስተማርና የጋርዮሽ ህብረት ማቀናጀት የታሰባል? መገንጠል እንዴት የዲሞክራሲ መፍትሄ እና አማረጭ ምንጭ ሊሆን ይታሰባል? የኢሳያስ ኤርትራ ተገንጥላ አሁን የት ነዉ ያለችዉ? አረናዎች ሊነግሩን ይቻላቸዋል? መለስ ዜናዊ የኮሚኒሰቶች “እስከ መገንጠል “ያለገደብ” መርሖ ለማተራመሻ መገልገያ (means) በመጠቀሙ ኦኖጎች እና ሌሎች ጠላቶች እየጠየቁት ያሉትን የመገንጠል ዓላማ፤ያንኑ አንቀጽ “ያለ ገደብ” እንሰጣለን ብለኸናል ነዉ ፀቡ።ኦኖጎች የሚሉት ፤አገር የማፍረስ መብት “ያለ ገደብ” የሚለዉን ”ተፈራርመናልና ያለገደብ ለግሰን”፤ ነዉ -እያጋጫቸዉ ያለዉ ነገር። ግጭቱ ስለ ዲሞክራሲ ሳይሆን “ያለ ምንም ገደብ የመገንጠል መብት ጥያቄ ነዉ” ።በዚህ የደረሰዉ ኪሳራ ይታያችሁ።ክፍለ ሀገሮቹን ካስራ አራት በላይ ገነጣጥሎ በአዳዲስ አምባገነን ኤሊቶች ሕዝብን ማሰቃየት የዓረና ትግራይ “አዲሱ የዲሞግራሲ አብዮት” ሌላዉ ገጽታዉ ነዉ። በዘህ አኳያ፤ አሁን እየተገባዉ ያለዉ ጉዞ፡”ትብስን ሰድጄ ትገድድን አመጣሁ!” የሚሉትን ዓይነት ወደ ሦስተኛዉ ዙር ጉዞ እየመሩን ይመስለኛል። ይህ ሁሉ እየሆነዉ ያለዉ እነ ገብሩ አስራት ፤እነ ነጋሶ ጊዳዳ “የኢትዮጵያን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ከጠየቁ በሗላ” መሆኑንም ይበለጥኑ ይገርማል። እነ ገብሩ ከዚያ ካንገት በላይ ፀፀት በሗላ “አሰከ መገንጠል” የሚለዉ ፖሊሲያቸዉ ፤ያዉም “ዛሬ የአማራ ገዢ ትግራይንና ሌለዉን ባልጨቆነበት”፤ “እኩል ሆነናል ባሉበት አፋቸዉ ባለንበት ዘመን” ፤ “ሸዋዊያን ተጋሩ በስደትና በመቃብር በሉበት” ዘመን” ተመልስዉ ዛሬ ለመገንጠልና ለማስገንጠል በጽናት እንታገላለን እያሉን ያሉትን ዲሞክራሲያዊ አብዮታቸዉ፦ ከ1971-1981 ተብሎ ፤ ተብሎ “እመቢ” ያላቸዉ የመገንጠሉ ሴራቸዉ ዛሬ በዓረና ትግራይ ስም ትግራይን ገንጥሎ መሸሸግያ ምሽግ ለማበጀት ይመስላል። አይደረግም እንዳትሉ።ማስገንጠል መብታቸዉ ከሆነ መጠራጠርም መብታችን ነዉና አስኪ እንጠራጠር። ያልተመነጠረ ተጠረጠጠ! ስንትስ ጊዜ እንመንጠር? ብንጠራጠርስ ይፈረድብናል?ተጎድተናል፤ተከድተናል እኮ! ምጽዋ ላይ አፍአበት ላይ ለኢርትራኖች ወግነዉ እኛኑንና እኛነታችንን ገድለዉ፤ ወደብ አልባ እኮ ነዉ ያስቀሩን። ሆ! አሁንም ያለማፈራቸዉ፤ ድፈረቱ! ድፍረቱ!። ሁለት ምርጫ ይዘዋል።- ማተራመስ ወይንም መገንጠል፦ ”የስብሓት ነጋ ያስር ዓመት (1971-1981) የህወሓት ሊቀመንበርነት ዘመን እንኳ የመገንጠሉን ፍላጎት በትግራይ ሕዝብና በታጋይ አእምሮ ዉስጥ ማስረጽ ስላልቻለ በኢህአደግ ስም ሚኒሊክ ቤተመንግስት ዉስጥ ሆኖ አገሪቱን ማተራመስ መርጧል” (ሃይሉ መንገሻ የተሓህት መስራች አባል።ኢትኦፕ ነሐሴ 1993 ዓ/ም ከተደረገዉ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)። ወያኔ- “በኢህአዴግ” ስም አገሪቱን ማተራመስ ከቻለ አንጃዉ በ“ዓረና” ስም በፈረቃ ሊገዙን በሚችሉበት ዘዴ እያመቻቹን ይሆን የሚል ጥያቄ ይታየኛል። ከጥዱ ወደማጡ እንዳይከቱን ያስገነዘቡንን አቶ ሓይሉ መንገሻ ሲቀጥሉ፦<በዘመነ ሕንፍሽፍሽ (ትርምስ) ብዙ ንጹሃን ታጋዮች በወገንተኝነትና ጎጠኝነት ሳቢያ ያለቁት ንጹሃን የትግራይ ታጋዮችና ታገልንልህ እየተባለ የሚመጻደቁበት የትግራይ ሕዝብ ስፍር ቁጥር የለዉም።……….አሁንም የመለስን መንግሥት ሊቋቋሙት የሚችሉት እነዚህ አሁን የተወገዱት መሆናቸዉ አይካድም። ሆኖም ትግላቸዉ ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን ከሌሎች የህብረ-ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ዘለቄታ ሰላም እነዲሰሩ መታገል ይጠበቅባቸዋል>> (ሃይሉ መንገሻ - ከላይ ከተገለጸዉ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ) በጎጠኝነት በዘመነ ሕንፍስፍሽ (ትርመስ) ያለቁት የትግራይ ተወላጆች ተሪክ፤- ዛሬ ዓረናዎች ለመጠቀም ያልፈጉትን አጋጣሚ ያገኙትን የሕዝቡ ቸርነት፤ይቅር ባይነት ተጠቅመዉ ታሪክና ታሪካቸዉን በይቅርታ የታጀበ ኑዛዜ ሊነግሩን በተገባቸዉ ነበር። አልታደሉም! ኑዛዜዉ ቀርቶብን ጭራሽኑ አገር የመበተናቸዉን ፤የፋሽስቶችና የኮሚኒስቶች ርዕዮት አጀንዳቸዉን አንቀጽ 39ኝን እንደ ዋናዉ የመታገያ አጀነዳቸዉ ይዘዉ ተመልሰዉ ብቅ ማለታቸዉ የባሰዉ የንቀታቸዉ ብዘት ያሳዝናል። በነዚህ ጎጠኞች ያለቁት የንጹሃን ደም ማን ይናገር? ለጠፉት፤ ለተሰወሩት፤ ማን ይቁምላቸው? እዉነታዉ እነዳይገለጽ ሲሸፋፍኑ ከርመዉ አሁን ለፍትሕ እንታገላለን ሲሉ ትንሽ ሐፍረት እነኳ አልተሰማቸዉም! ያኔ ባለፈዉ ሰሞን <“ስየ” በኔ ታሪክ ሳይሁን እኔ በምናገራቸዉ ብቻ እንወያይ> ሲለን አድናቆታቸዉን ለግሰዉ ”የኢትዮጵያ ቅርስ” (ሶቨኒር) ነዉ ብለዉ ሸኙት።የሰራነዉ ጉድ አትነጋገሩ፤ እኛ በምንሰጣችሁ አጀንዳ ብቻ ተነጋገሩ ብሎ አነጃዉ ክፍል ሲለን፤ “እኛ ወያኔዎች አይደለንም አንተ በፈለግከዉ አጀንዳ መነጋገር የምትችለዉ ከወያኔዎች ጋር እንጂ ከኛ ከተጎጂዎች ጋር ሊሆን አይችልም፦…. አዳምጡኝ እያልከ እንዳለኸዉ የኛኑንም ስሞታ አዳምጥ፡….. ብለዉ ለተካራከሩ ዜጎች “ኤክስትሪሞች” ብለዉ የሰደቡን በተቃዋሚነት የቆሙ ታዋቂ ግለሰዎች ሰዎች አሉ። ንቀት?! ተማርኩ የሚለዉ የትግራይ ዜጋም ብሔራዊ ክህደትለፈጸሙ አምባገነኖች ሽንጡን ገትሮ በሙታኖች ስም ወደ ህግ ማቅረብ አልቻለም። ይህ ቸልተኝነታቸዉን ፤የምን አገባኝነትን ወላዋይ ባህርአቸዉን ስናጋልጥ የማይወዱን አሉ። ይህ ቸልተኝነትና የምን ቸገረኝ ራቅ ብሎ ተመለካችነት ባህሪያችንን በመታዘብ ዛሬም እየናቁን መንደርተኞቹ አንቀጽ 39ን “ያለገደብ” ለመተግበር ይሄዉና ተዘጋጅተዋል። አንድ በሉ! ሁለተኛዉ ታላቁ ሴራ ደግሞ ይመጣል - ጠብቁ! ታድያ አገሪቱን ማን ያድናት? አቶ ሃይሉ መንገሻ እነደላዩት “ኢህአዴግን መታገል የሚችለዉ የተነጠለዉ ቡድን ከሆነ” የተቀረዉ ተስፋ ቢስ ሙሁር ወደባረያ ተገዢነቱ ለሁለተኛ ዙር መዘጋጀት ይኖርበታል። አልያም ሙሁሩ አገሪቷ መታገድ ካልቻለ፡- አቶ ሃይሉ መንገሻ እንዳሉት <<ሠራዊቱ የምትታመሰዉን አገር ያድናት”>> (ሃይሉ መንገሻ ኢትኦጵ ነሓሴ 1993 ዓ/ም) ሙሁሩ ምንተሕፍረቱን አጋለጦ ወታደሩ ሕዝቡን እንዲያድን ሲማጸን፤ እኛ ያልተማርን ዜጎች እግዜር ከመአቱ ራሱ ያድነን ከማለት ሌላ ምን እንበል? <<ይህ አዲስ ቡድን፡ መለስንና አንዳንድ ደጋፊዎቻቸዉን የተወሰነ ፖሊሲዎችን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንቅናቄዎች ስለነቀፈ ብቻ ኢትዮጵያዊ አጀነዳ ማንሳቱን ለማረጋገጥ እንችል ኢሆን? “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት” ዓላማ እንዳለዉ ለማየት እፈልጋለሁ>> ጸጋየ ገ/መድህን አራአያ ቅጽ 9 ቁትር 6 1994 ጦቢያ -በፈረቃ ሊገዙን ባይመኙ!) “ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን። ለኢትዮጵያ አንድነትና ቤተሰባዊነት ትናንት ቆመናል፤ ዘሬም ነገም በጽናት እንቆማለን።ቁጥር ስፍር የሌላቸዉ በወያኔ ጎጠኝነትና ማን አለብኝነት የተረሸኑ ታጋዬችና የትግራይ ገበሬዎች ደም አሁንም ይጮሃል።”ኢትዮጵያ” ለዘላም ትኑር! ጌታቸዉ ረዳ ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ አሜሪካ መጋቢት 2000 ዓ/ም-/-

“Arena” Should Stop Hatching TPLF’s Decadent Egg!

Please read the article with Ge’ez Unicode fonts at Geez Unicode.com (it is free and works with MS words) ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን። አሁንም አሁንም መንደርተኝነቱ አልለቅ ብሎናል። በጣም ክፉ በሽታ! ከተመሰረተ ስድስት ወር ያስቆጠረው ከአፍቃሬው የኤርትራዉ ቡድን ከነመለስ ዜናዊ ይልቅ የተሻለ መርሃ ግብር ይዞ ይመጣ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀዉ የእነ ገብሩ አስራት ፤ “ዓረና ትግራይ” ጋሽቦ የወጣዉ የ30 ዓመት አረማቸውን ይዞ እንደና ብቅ ብሏል። ። ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት ግብ እንታገላለን በማለት በግንቦት 21 አና 22 / 2000 ዓ/ም ትግራይ ዉስጥ በመቀሌ ከተማ “ሚላኖ” (ባልታጣ ሥም) ተብሎ በሚጠራዉ ሆቴል ባካሄደዉ ጉባኤ፡ አስቀድሞ በወየኔ የተነደፉትን አንቀጾችና በተለይም አንቀጽ 39ኙ የኮሚኒሰቶች አገር የማፈራረስ መርሐ ግበሩን “በአልተገደበዉ” መብት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ጉባኤዉ በተነጋገረባቸዉ በለ6 ዋና ዋና ነጥቦች በትግርኛ ቋንቋ የተጻፈዉ መግለጫዉ በኢትዮ- ሚድያ ፤ በደቂ አሉላ እና በአይጋ ድረ-ገጾች ለጥፎታል። “ኢትዮ ሚድያ” በተባለዉ ድረገጽም < ቅንጅት ናችሁ፤ ጠላት ናችሁ…… እያለን ነዉ> ሲሉ ዓረናዎች እሮሮአቸዉ እያሰሙ ነዉ ሲል ዘግቧል። አዲስ ሆነብን’ሳ እንዴት ነዉ ነገሩ?! ተቧድኖ መሰዳደብ የጀመሩት ገና አሁን አይደለም እኮ። በመሰዳደቡ ሁሉም አልተሰናነፉም። የቸገረን ነገር “ለመሰዳደቡ” መሰረት የሆናቸዉ ልዩነታቸው ግን በኢትዮጵአዊነት ዙርያ ያጠነጠነ ትኩረት ያለመሆኑን ሳያሳስበን አልቀረም። አሁን እተሰደብን ነዉ እያሉት ያለዉን መሰረታዊ ቅራኔያቸዉን አስኪ ወደሗላ መለስ ብለን ጸሐፍት የዘገቡዋቸዉንን ለዉይይታችን መነሻ ያመቸን ዘንድ እንቃኝ። “በፓለቲካዊና በማህበራዊው ዘርፍ ተንሰራፍተዉ የሚገኙት የኢትዮጵያ አስከፊ ችግሮች ከወያኔ የዘር ፍልስፍና ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ” (አታልቅስ ነዉ ሚያስለቅሰኝ - አሸኔ ጌጡ ዜጋ ጥር - የካቲት 1994)። ሁለቱም ይሄንን አይጋሩትም። ረዢም ገለጻ የሚፈልጉ አስከፊ የሚባሉት የአገሪቷ ችግሮች መሀንዲሶቹም፤ወያኔዎች ሲሆኑ፤ ወያኔዎች የምንላቸዉ ደግሞ ሁለቱንም ቡድን የሚያጠቃልል ሁለቱም የሚኩራሩበት ድርጅት ነዉ። የዓረና ኮሚኒስቶች አሁንም እንምራችሁ እያሉን ያለዉን መንገዳቸዉ ከነ መለስ ዜናዊ አቋም አይለይም። አሁንም ድሮም በበሰበሰዉ አንጃዉ (በመለስ አንደበት) እና በተምበርካኪዉ የቤተመንግሰቱ ቡድን (በአንጃዉ አነጋገር መሰረት) ያኔ ካሰራጩዋቸዉ ጽሁፎች መረዳት እንደተቻለዉ የፖሊሲ ልዩነት አልነበረም። ልጥቀስ < እነ አቶ ተወልደ የኢትዮጵያ ችግር በዘር ላይ ከተመሰረተ አድሎአዊ ሥርዓት የመነጩ ናቸዉ የሚል አመለካከት የላቸዉም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በይዘቱ ከደቡብ አፍሪካዉ ዘረኛ ሥርዓት ያልተለየ ዘረኝነት መሰረት ያደረገ አስከፊ ሥርዓት መመስረቱን አየቀበሉም። ዛሬም ዘርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት፤የወዳጅና የጠላት ትንተና አለ። ትመክህተኛና ጠባብ በሚሉት ሃሳቦች ዙርያ ምንም አይነት አስተሳሰብ ለዉጥ የላቸዉም። በዚህም አቋማቸዉ ከነመለስ ጋር ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸዉ ፀባቸዉም መሰረታዊ ቅራኔ አለመሆኑን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። (አሸኔ ገጤ - አታለቅስ ነዉ የሚአስለቅሰኝ) አቶ ያሬድ ጥበቡም በዜጋ መጸሔት ቁጥር 11/1993 ባስነበቡት መጣጥፍ እነ ተወለደ (ያሁኑ ዓረናዉንም ጨምሮ) እንዲህ ብለዉ ነበር ፦ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” (ተወልደ ወልደማርያም)። በእወነቱ እነ ተወለደ እና እነ ገብሩ ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ አንድነት አዛኞችና ተቆረቋሪዎች ናቸዉ? የሚከተለዉን ከ አቶ አሽኔ ገጤ (አታልቅስ ነዉ ሚአስለቅሰኝ መጣጥፍ) ስለ አንጃዉ ዘረኝነት አና እንካስላንትያ ስድብ የተለዋወቱባቸዉን ባሕርያቶቻቸዉን የተዘገቡትን እንመልከት፦ <በረከት ወደ ተጠናወተዉ አፍራሽ ሚና ስንመለስ የሚያናፍሰዉ ነገር….የራሱን ዘር ማጥራት ቅሬታ መነሻ በማድረግ የመለስን መልክት ይዞ ብብእዴን ፖሊት ቢሮ በኩል ሰፊ እነቅስቃሴ ማድረጉን ነዉ>።< …….. ህወሓትን እንደ ድርጅት ከትምክህተኞችና ከሻዕቢያ ፕሮፓጋንዲስቶች ባልተናነሰ ማጥላላት ነበር የተያያዘዉ። ህወሐት ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ ፤ካድሬዎቹ እንደፈለጉ ሲሆኑ ምንም ዓይነት እርምጃ እንደማይወስድ አድርጎ ለማቅረብ በስፋት ተንቀሳቅሷል።>> (ሪፖርተር መጽሔት ቅጽ 5 ቁጥር 39) አንጃዎቹ - ስለ ድርጅታቸዉ ምንነት አንዴ አምባገነንት ለብዙ አመታት ነፍሶ በሆደ ሰፊ አቻችለን አዚህ ድረስ ደርሰናል ሲሉን፤ አንዴ ደግሞ ህወሓት ፈላጭ ቆራጭ አይደለም ገና አሁን ነዉ ዱብ ዕዳዉ የመጣዉ ሲሉ እያደመጥናቸዉ ነዉ። <<ወያኔ ግለሰብም ሆነ የድርጅትን ፖለቲካን የሚመዝነዉና ሚለካዉ በዘር ነዉ። ኦሮሞዉን ጠባብ ብሔረተኛ፤ አማራዉን ትምክህተኛ በማለት ። ለምሳሌ << ከትምክህተኞቹ ድርጅቶች ባልተናነሰ ሁኔታ>> ያሉት፤የአማራዉን ህዝብ ከዘር ማፅዳት መአት ለማዳን (አቅሙ ባይኖሮዉም እንኳ) ሲባል የተቋቋመዉን “መ አ ህ ድ” ን ለመጥቀስ ተፈልጎ ነዉ>። (አሸኔ ጌጤ)። በኢትዮጵያ ዙርያ ያጠነጠነ ፀብ አይደለም የልኩት ለዚህ ነዉ። ከዛ አኳያ አንጃዉን የመሩት አቶ ተወልደ “የትግራይ ሁኔታስ መልክ ይዟል የሚያሳዝነዉ ያኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ነዉ” ሲሉ <፤ለማይወዷት ለማያከብሯት ለማይቀበሏት ለማይፈልጓት ኢትዮጵያ ህወሓቶች (እነ አቶ ተወልደ ጭምር) ተቆርቋሪ ናቸዉ ማለት ተጨፈኑ እናሞኛችሁ አይነት ቀልድ ነዉ> (- አቶ አሸኔ ጌጤ- አታልቅስ ነዉ የሚያስለቅሰኝ ፡ዜጋ መጽሔት)። የ “ዓረና ትግራይ” መስራቾች እነ ገብሩ አስራት፤ አዉዓሎምና እና አረጋሽ አዳነ ትናንት በረከትን- ዘረኛ፤ አዲሱና ተፈራን- ተጎታች፤ መለስና ሌላዉን የህወሃት መአከላዊ ኮሚቴ አባላቱን -ተምበርካኪና ጥገኛ . ሲሉት የነበረዉን ቡድን ፤ዛሬ “ጠላቶች ናቸሁ ፤ቅንጅቶች ናቸዉ…..አለን” ቢሉን ፤እኛኑን ምሰኪኖች ሲሰዳደቡ ግራ ለማጋበት ካልሆነ ፤እየተጓዙበት ያሉበትን ጎዳና፤መዝሙራቸዉና ሰንደቃላማቸዉ ያዉ የተሓህት ነዉ።በዚህ ከቀጠሉ የሚያስቡት የመጨረሻ ግባቸዉ በምናቸዉ እንወቅ ? <ኢህአዴግ ምን እንደሚያስብ ሳይንስም እግዚአብሔርም አያዉቀዉም> ብለዉታል እኮ ደ/ር መረራ ጉዲና። ከፕሮግራሙና ከታሪክ ጀርባዉ ከ’ዚያ ሁሉ ትርምስና ትምህርት በመቅሰም ከወያኔ ወጥዉተዉ በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገዉ የኢደፓ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ “ያደረግነዉ ጥፋት ከልምድ ማነስ ነዉ..” አያሉ የቅርታ መሳይ እንዳልጠቃቀሱ ሁሉ አሁን ተመልሰዉ አገርን ለመገንጠል የኮሚኒስቶች ሕግ ስራ ላይ ያለገደብ ለማዋል በጽናት እታገላለሁ ብሎ አንቀጽ 39ን በአዋጅ የሚደነግግ የትግራይ ተወላጅና ድርጅት በትግራይ ስም “ዓረና ትግራይ” ሲሉ ከተደራጀዉ “ኤርትራዊዉ ወየነ ትግራይ” ለይይተን የምንቀበለዉ መንገድ ከቶዉኑ በምኑ?። በአጽንኦት ዛሬም የምለዉ፡ የነስብሐት ነጋ ፕሮግራም በዓረና ፓርቲ ስም ተግበራዊ እንዳይሆን ሀቀኛ የትግራይ ተወለጆች የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ መቀጠል ይጠበቅባቸዋል። ዛሬም ማንም ይሁን ማንም ከመንደርተኞች፤ ጋር ያለዉ ቅራኔ ዛሬም ነገም ለወደፊቱም ትግሉ በአነድነት ሃይሎች በኩል በሰፊዉ ይቀጥላል። ሞት የማይቀር ጽዋ ነዉ፤ ግን ታሪክ የእያንነዳንዳችን ስራ እየዘገበ ነዉ! የትግራይ ሕዝብና በተለይም ምሁሩ ክፍል ይህንን የታሪክ ሴራ ሰብሮ መዉጣት ይጠበቅበታል። ከ 7 ዓመት በፊት ያስተጋባናቸዉ ድምጾቻችን ስንመረምር፡ እነ ገብሩ ከተሓህት ሲነጠሉ ያኔ በአገር ዉስጥ በሚታተሙ መጸሄቶች ላይ የኔ ጽሁፎችን ተከታተላችሁ ከነበረ፤ቡዱኑ ቢነጠልም ያዉ ወየነ የሚሸተዉ ባህሪዉ እንደማይለቀዉ “ሃሎ! ሃሎ! መቐለ ድዩ? ሃሎ ማዞርያ! ሃሎ!ሃሎ መቀሌ ነዉ? ….” በሚል በዜጋ መጽሄት ላይ ስተነበይ። አብሮም፤ ወያኔዎች ለሁለት ሲነጠሉ በዉጭ አገር የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በጋራ እና በተናጠል ካዉሮፓ ፤ከካናዳ እና ከሰሜን አሜሪካ ያስተላለፉዋቸዉን በታሪክ የተመዘገበ አሳፋሪ ያቋም መግለጫዎቻቸዉ ከትችት ጋር አቅርቤ ነበር። አብዛኛዉ የትግራይ ተወላጆች ለአንጃዉ ለእነ ገብሩ ቡድን ድጋፋቸዉን ና የነበራቸዉን ከበሬታ በየመግለጫቸዉ ገልጿዋል።ዉጭ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ወያኔዎች ለሁለት በመነጠላቸዉ ምክንያት ለምሳሌ ከስያትል የትግራይ ተወላጆች በሚል የተላለፈዉ የእንግሊዝኛዉ መግለጫ ብንመለከት፦ “አንቀጥቅጥ ብርድ ይዞ ከወደሰማይ እየቀዘፈ የመጣ ነፋስ ቆፈን መና አስቀርቶናል፡ብርድ ብርድ ብሎናል፤ቀፍፎናል። በዚህም አልተደሰትንም ፤ከፍቶናል። የተለየዉ የማአከላዊዉ አባሎችና አመራሮች ወደስልጣናቸዉ ባስቸኳይ ይመለሱ>>፤ ብሎ ሲደመድም ፦ ከሚድዌሰት ዩ፤ኤስ ኤ የትግራይ ተወላጆችም የተላለፈዉ በተመሳሳይ እንዲህ ብሎ ነበር፡- << ስለመሪዎቻችን መከፋፈል ምንኛ እነደተሰማን ቃላት ኖሮን ለመግለጽ ብንታደል ጥሩ ነበር፤ግን ቃላትም ተፈልጎ ሊገልጸዉ አልተቻለም። አጠቃላይ ግን የመሬት መደርመስ ያህል ተሰማን። ስሜቱ መንፈሳችንን ገነጣጥሎታል፤ደንግጠናል፤ወና ነገር ፤አነዳች ነገር ሆነናል ፤ ተከድተናል ፤ተዋርደናል፤አፍረናል እጅግ ተቆጥተናል። የፈለገዉ ዓይነት ምክንየት ቢኖርም እነደዚህ ዓይነት መዓት ለማየት በቂ ምክንየት ነዉ የሚባል ነገር ሊያሳምነን አይቻለዉም።ይህ ዕብደት ነዉ። የናንተ የመሪዎቻችን መተክያ አይገኝለትም።>> ይህ ሁሉ ድንጋጤ እና ከበሬታ የሰጥዋቸዉ ምክንያት በግላችን የተቆጠበ አስተያየት ቢኖረንም፡የህወሐት መስራች አንዱ ከነበሩ. በሎስ አንጀለስ አሜሪካ ዉስጥ ሚኖሩት አቶ ሃይሉ መንገሻ ግን በዉጭ ያሉት የትግራይ ተወላጆች ፤ያኔ ለአንጃዉ ያሳዩት ያልተቆጠበ አክብሮትና ለድጋፋችዉ ዋና ምክንያት የሚከተለዉ እነደነበር ይገልጻሉ። <” አሁንም በነመለስ የተወገዱት የህወሐት ማአከላዊ ኮሚቴ አባላት እዚህ ሁኔታ ላይ ያደረሳቸዉ መለስ ብቻ ሳይሆን አብረዉ የፈጠሩት ኢ-ዲሞክራሲያዊ ብቸኛ ድርጅት መሆኑን አምነዉ ከዚህ በመማር ሰፊዉን ኢትያጵያ ህዝብ ሊያሳትፍ የሚቻልበትን ከልብ ከተነሱ’ና ከሌሎች ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ለመስራትም ከቻሉ ያሁኑ ፍርክስከስ አዎንታዊ ገጽታ ይኖረዋል። በነገራችን ላይ በዉጭ አገር ያሉት የትግራይ ተወላጆችም እርዳታዉንና ድጋፉን የሚለግሱላቸዉ በዚህ መንገድ ይጓዛሉ ከሚል ጽኑ እመነት ነዉ።”>> (ሃይሉ መንገሻ አትኦጵ መጽሄት ነሓሴ 1993 ዓ/ም) ታድያ በአቶ ሃይሉ እላይ እንደተመለከተዉ፡ አንጃዉ አሁን ይዞት ብቅ ያለዉ የወየኔዉ ማኒፌስቶ አንቀጽ 39ኝን ያክል አበጣባጭ የጠላት ፕሮግራም ተይዞ ለአንድነት ከሚታገሉ ህብረ ቢሄር የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪል ማሀበሮች ጋር እንደ ወያኔዎች በጥርጣሬ ዓይን እንዲታዩ ሊዳርጋዉ ካልሆነ በቀር አብሮ ሊያራምዳቸዉ ይችላል? የትግራይ ተወለጆች ላንጃዉ መቆርቆርና ለድጋፋቸዉ ምክንያት ያ ከነበረ ይህንን በጽናት እንታገልለታለን እያሉለት ያሉትን የጣልያኖቹን አንቀጽ 39 የፕሮግራም (ቅጂ) ይዞ የተነሳዉን “ዓረና”ሊቀበሉት ይችላሉ? አብረን የምናዉ ይሆናል። “ዓረና” ከስሙ አንጻር “አንድ የመሆንን” ነጋሪነትን ያሳያል። አንድነት ለማን? ከእነ ማን ጋር? በየትኛዉስ አገራዊ ፖሊሲ? በ ወያኔዉ አንቀጽ 39? ወያኔንና መለስን በብዙሃን ኢትዮጵያ ያስጠላዉ እና በታሪክ ትቢያ ዉስጥ እንዲመዘገብ ያደረገዉ “ዋነኛዉ ሴራዉ” እኮ ይህንኑ ዓረናዎች ተግባራዊ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን የሚልለትን አንቀጽ 39ኙን ነዉ! ታድያ ወየኔ የምንታገል ክፍሎች ዓረናን እንዴት እንደወዳጅ ድርጅት ቆጥረን ስለሱ በጎነት ማስተማርና የጋርዮሽ ህብረት ማቀናጀት የታሰባል? መገንጠል እንዴት የዲሞክራሲ መፍትሄ እና አማረጭ ምንጭ ሊሆን ይታሰባል? የኢሳያስ ኤርትራ ተገንጥላ አሁን የት ነዉ ያለችዉ? አረናዎች ሊነግሩን ይቻላቸዋል? መለስ ዜናዊ የኮሚኒሰቶች “እስከ መገንጠል “ያለገደብ” መርሖ ለማተራመሻ መገልገያ (means) በመጠቀሙ ኦኖጎች እና ሌሎች ጠላቶች እየጠየቁት ያሉትን የመገንጠል ዓላማ፤ያንኑ አንቀጽ “ያለ ገደብ” እንሰጣለን ብለኸናል ነዉ ፀቡ።ኦኖጎች የሚሉት ፤አገር የማፍረስ መብት “ያለ ገደብ” የሚለዉን ”ተፈራርመናልና ያለገደብ ለግሰን”፤ ነዉ -እያጋጫቸዉ ያለዉ ነገር። ግጭቱ ስለ ዲሞክራሲ ሳይሆን “ያለ ምንም ገደብ የመገንጠል መብት ጥያቄ ነዉ” ።በዚህ የደረሰዉ ኪሳራ ይታያችሁ።ክፍለ ሀገሮቹን ካስራ አራት በላይ ገነጣጥሎ በአዳዲስ አምባገነን ኤሊቶች ሕዝብን ማሰቃየት የዓረና ትግራይ “አዲሱ የዲሞግራሲ አብዮት” ሌላዉ ገጽታዉ ነዉ። በዘህ አኳያ፤ አሁን እየተገባዉ ያለዉ ጉዞ፡”ትብስን ሰድጄ ትገድድን አመጣሁ!” የሚሉትን ዓይነት ወደ ሦስተኛዉ ዙር ጉዞ እየመሩን ይመስለኛል። ይህ ሁሉ እየሆነዉ ያለዉ እነ ገብሩ አስራት ፤እነ ነጋሶ ጊዳዳ “የኢትዮጵያን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ከጠየቁ በሗላ” መሆኑንም ይበለጥኑ ይገርማል። እነ ገብሩ ከዚያ ካንገት በላይ ፀፀት በሗላ “አሰከ መገንጠል” የሚለዉ ፖሊሲያቸዉ ፤ያዉም “ዛሬ የአማራ ገዢ ትግራይንና ሌለዉን ባልጨቆነበት”፤ “እኩል ሆነናል ባሉበት አፋቸዉ ባለንበት ዘመን” ፤ “ሸዋዊያን ተጋሩ በስደትና በመቃብር በሉበት” ዘመን” ተመልስዉ ዛሬ ለመገንጠልና ለማስገንጠል በጽናት እንታገላለን እያሉን ያሉትን ዲሞክራሲያዊ አብዮታቸዉ፦ ከ1971-1981 ተብሎ ፤ ተብሎ “እመቢ” ያላቸዉ የመገንጠሉ ሴራቸዉ ዛሬ በዓረና ትግራይ ስም ትግራይን ገንጥሎ መሸሸግያ ምሽግ ለማበጀት ይመስላል። አይደረግም እንዳትሉ።ማስገንጠል መብታቸዉ ከሆነ መጠራጠርም መብታችን ነዉና አስኪ እንጠራጠር። ያልተመነጠረ ተጠረጠጠ! ስንትስ ጊዜ እንመንጠር? ብንጠራጠርስ ይፈረድብናል?ተጎድተናል፤ተከድተናል እኮ! ምጽዋ ላይ አፍአበት ላይ ለኢርትራኖች ወግነዉ እኛኑንና እኛነታችንን ገድለዉ፤ ወደብ አልባ እኮ ነዉ ያስቀሩን። ሆ! አሁንም ያለማፈራቸዉ፤ ድፈረቱ! ድፍረቱ!። ሁለት ምርጫ ይዘዋል።- ማተራመስ ወይንም መገንጠል፦ ”የስብሓት ነጋ ያስር ዓመት (1971-1981) የህወሓት ሊቀመንበርነት ዘመን እንኳ የመገንጠሉን ፍላጎት በትግራይ ሕዝብና በታጋይ አእምሮ ዉስጥ ማስረጽ ስላልቻለ በኢህአደግ ስም ሚኒሊክ ቤተመንግስት ዉስጥ ሆኖ አገሪቱን ማተራመስ መርጧል” (ሃይሉ መንገሻ የተሓህት መስራች አባል።ኢትኦፕ ነሐሴ 1993 ዓ/ም ከተደረገዉ ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)። ወያኔ- “በኢህአዴግ” ስም አገሪቱን ማተራመስ ከቻለ አንጃዉ በ“ዓረና” ስም በፈረቃ ሊገዙን በሚችሉበት ዘዴ እያመቻቹን ይሆን የሚል ጥያቄ ይታየኛል። ከጥዱ ወደማጡ እንዳይከቱን ያስገነዘቡንን አቶ ሓይሉ መንገሻ ሲቀጥሉ፦<በዘመነ ሕንፍሽፍሽ (ትርምስ) ብዙ ንጹሃን ታጋዮች በወገንተኝነትና ጎጠኝነት ሳቢያ ያለቁት ንጹሃን የትግራይ ታጋዮችና ታገልንልህ እየተባለ የሚመጻደቁበት የትግራይ ሕዝብ ስፍር ቁጥር የለዉም።……….አሁንም የመለስን መንግሥት ሊቋቋሙት የሚችሉት እነዚህ አሁን የተወገዱት መሆናቸዉ አይካድም። ሆኖም ትግላቸዉ ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን ከሌሎች የህብረ-ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ዘለቄታ ሰላም እነዲሰሩ መታገል ይጠበቅባቸዋል>> (ሃይሉ መንገሻ - ከላይ ከተገለጸዉ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ) በጎጠኝነት በዘመነ ሕንፍስፍሽ (ትርመስ) ያለቁት የትግራይ ተወላጆች ተሪክ፤- ዛሬ ዓረናዎች ለመጠቀም ያልፈጉትን አጋጣሚ ያገኙትን የሕዝቡ ቸርነት፤ይቅር ባይነት ተጠቅመዉ ታሪክና ታሪካቸዉን በይቅርታ የታጀበ ኑዛዜ ሊነግሩን በተገባቸዉ ነበር። አልታደሉም! ኑዛዜዉ ቀርቶብን ጭራሽኑ አገር የመበተናቸዉን ፤የፋሽስቶችና የኮሚኒስቶች ርዕዮት አጀንዳቸዉን አንቀጽ 39ኝን እንደ ዋናዉ የመታገያ አጀነዳቸዉ ይዘዉ ተመልሰዉ ብቅ ማለታቸዉ የባሰዉ የንቀታቸዉ ብዘት ያሳዝናል። በነዚህ ጎጠኞች ያለቁት የንጹሃን ደም ማን ይናገር? ለጠፉት፤ ለተሰወሩት፤ ማን ይቁምላቸው? እዉነታዉ እነዳይገለጽ ሲሸፋፍኑ ከርመዉ አሁን ለፍትሕ እንታገላለን ሲሉ ትንሽ ሐፍረት እነኳ አልተሰማቸዉም! ያኔ ባለፈዉ ሰሞን <“ስየ” በኔ ታሪክ ሳይሁን እኔ በምናገራቸዉ ብቻ እንወያይ> ሲለን አድናቆታቸዉን ለግሰዉ ”የኢትዮጵያ ቅርስ” (ሶቨኒር) ነዉ ብለዉ ሸኙት።የሰራነዉ ጉድ አትነጋገሩ፤ እኛ በምንሰጣችሁ አጀንዳ ብቻ ተነጋገሩ ብሎ አነጃዉ ክፍል ሲለን፤ “እኛ ወያኔዎች አይደለንም አንተ በፈለግከዉ አጀንዳ መነጋገር የምትችለዉ ከወያኔዎች ጋር እንጂ ከኛ ከተጎጂዎች ጋር ሊሆን አይችልም፦…. አዳምጡኝ እያልከ እንዳለኸዉ የኛኑንም ስሞታ አዳምጥ፡….. ብለዉ ለተካራከሩ ዜጎች “ኤክስትሪሞች” ብለዉ የሰደቡን በተቃዋሚነት የቆሙ ታዋቂ ግለሰዎች ሰዎች አሉ። ንቀት?! ተማርኩ የሚለዉ የትግራይ ዜጋም ብሔራዊ ክህደትለፈጸሙ አምባገነኖች ሽንጡን ገትሮ በሙታኖች ስም ወደ ህግ ማቅረብ አልቻለም። ይህ ቸልተኝነታቸዉን ፤የምን አገባኝነትን ወላዋይ ባህርአቸዉን ስናጋልጥ የማይወዱን አሉ። ይህ ቸልተኝነትና የምን ቸገረኝ ራቅ ብሎ ተመለካችነት ባህሪያችንን በመታዘብ ዛሬም እየናቁን መንደርተኞቹ አንቀጽ 39ን “ያለገደብ” ለመተግበር ይሄዉና ተዘጋጅተዋል። አንድ በሉ! ሁለተኛዉ ታላቁ ሴራ ደግሞ ይመጣል - ጠብቁ! ታድያ አገሪቱን ማን ያድናት? አቶ ሃይሉ መንገሻ እነደላዩት “ኢህአዴግን መታገል የሚችለዉ የተነጠለዉ ቡድን ከሆነ” የተቀረዉ ተስፋ ቢስ ሙሁር ወደባረያ ተገዢነቱ ለሁለተኛ ዙር መዘጋጀት ይኖርበታል። አልያም ሙሁሩ አገሪቷ መታገድ ካልቻለ፡- አቶ ሃይሉ መንገሻ እንዳሉት <<ሠራዊቱ የምትታመሰዉን አገር ያድናት”>> (ሃይሉ መንገሻ ኢትኦጵ ነሓሴ 1993 ዓ/ም) ሙሁሩ ምንተሕፍረቱን አጋለጦ ወታደሩ ሕዝቡን እንዲያድን ሲማጸን፤ እኛ ያልተማርን ዜጎች እግዜር ከመአቱ ራሱ ያድነን ከማለት ሌላ ምን እንበል? <<ይህ አዲስ ቡድን፡ መለስንና አንዳንድ ደጋፊዎቻቸዉን የተወሰነ ፖሊሲዎችን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንቅናቄዎች ስለነቀፈ ብቻ ኢትዮጵያዊ አጀነዳ ማንሳቱን ለማረጋገጥ እንችል ኢሆን? “ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሸት” ዓላማ እንዳለዉ ለማየት እፈልጋለሁ>> ጸጋየ ገ/መድህን አራአያ ቅጽ 9 ቁትር 6 1994 ጦቢያ -በፈረቃ ሊገዙን ባይመኙ!) “ዓረና ትግራይ” አሁንም ወያኔ ወያኔ የሚሸተዉ እንቁላሉን መታቀፉን የቁም እንላለን። ለኢትዮጵያ አንድነትና ቤተሰባዊነት ትናንት ቆመናል፤ ዘሬም ነገም በጽናት እንቆማለን።ቁጥር ስፍር የሌላቸዉ በወያኔ ጎጠኝነትና ማን አለብኝነት የተረሸኑ ታጋዬችና የትግራይ ገበሬዎች ደም አሁንም ይጮሃል።”ኢትዮጵያ” ለዘላም ትኑር! ጌታቸዉ ረዳ ሳን ሆዘ ካሊፎርኒያ አሜሪካ መጋቢት 2000 ዓ/ም-/-