Monday, April 22, 2024

ክፍል 4 ጌታቸው ረዳ Ethiopian Semay 4/27/24 የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያየሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚል ከክፍል 3 የቀጠለ.... ከፍል 4

 

ክፍል 4

ታቸው ረዳ

Ethiopian Semay

4/27/24

የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያየሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚል ከክፍል 3 የቀጠለ.... ከፍል 4

ትችቴን ከመቀጠሌ በፊት ለጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ የማስተላልፈው መልዕክት የሚከተለው ነው፦ << ክታች በቪዲዮ ላይ የሚደመጡት የሴት ወታደሮች እመባ ይፋረድህ!  እያልኩ ወደ ከፈል 4 ተችቴ እገባልሁ፡፡

በዚህ ክፍል 4 የምተቸው የዜጠኛ የያየሰው ሽመልስ የሚከተለውን ክሕደት ነው፡፡

<< (ወታደሩ) ሲኖትራክና ታንክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡ ደግሞም ተሳክቷል፡፡ ይህ ሁሉ እንዳልተፈጸመ የትግራይ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ ዐብይም ፤ ብርሃኑ ጁላም ሆነ አዳምነህ መንግሥቴ (የሰሜን ዕዝ ሲማረክ ምክትል አዛዠ የነበረው ያውቃል፡፡>> የሚለው “የራ እርካብ የደም መንበር (ገጽ 54)” ፈጣጣ የታሪክና የወንጀል ማዛባት መጽሐፉ ውሰጥ የዘገበበትን  እንመለከታለን፡፡

የሩዋንዳው የሑቱ ‘ዱርየ ቡድን’ ያስናቀ 33 አመት ሙሉ በጸረ አማራነታቸውና ፀረ ኢትዮጵያነታቸው የታወቁት የባሕር ወደቦቻችን ያስነጠቁን በናዚ መርሐግብር የሚመራው የትግሬ ኢንተርሃሙዌ መሪዎች ትዕዛዝ ምክያት ምንም ባልተተናኮላቸው የሰሜን ዕዝ ሠራዊት የሕዝቡን እህል እያጨደና አምበጣ እያባረረ ውሎ ደክሞት በተኛበት በውድቅት ሌሊት ያደረሱበትን ግፍ  በክፍል 2  ከተጠቀሱት ዘግናኝ ግፎችን ታሰታወሱ እንደሆን ሠራዊቱ ወደ ኤርትራ ድምበር ለማፈግፈግ ሲሞክር የገጠመው በክፍል 2 እና 3 እንዲህ ቀርቦ ነበር፡፡

 <<...በህይወት የቀሩትንም መሳርያ፤ጩና ገጀራ የታጠቁት ልዩ ሃይሎች ለናንተ ጥይት አናባክንም በማለት እጃቸው የሰጡትን ማረድ ጀመሩ፡፡

አምስት ጋዶችን አንገታቸውን እየቆረጡ፤ሆዳቸውን እየዘከዘኩ ፤ ዓይናቸውን እያውጡ ፤ የወንዶችን ብልት እየቆረጡ ፤የሰውን ገላ እንደጨርቅ እየተረተሩ በታተኑት፡፡

ከገደሏቸው ውሰጥ የአስር/አለቃ ስንታየሁ መጀመሪያ ጡቶን ቆረጡ፡፡ቀጥሎ አንገትዋን ቆረጡ አንገንና ጡቶን ዛፍ ላይ አንጠለጠሉ፡ የህን ሲያደርጉ ሠራዊቱ ያያል፡፡ ይህ አልበቃ ሲላቸው እዛው ገርሁ ስርናይ ከተማ  እጅ በሰጡ ሴት ወታደሮች ላይ የተሰራው ግፍ ሕሊና ያቆስላል፡፡ እጅ ከሰጡት ውስጥ ሴት ወታደሮችን ልብሳቸውን አስወለቁ፡፡ ወደ ብልታቸው እንጨት እየከተቱ አሰቃዩዋቸው፡፡ ስቃዩን መቋቋም ሲያቅታቸው ለመንፈራገጥ ሲሞክሩ ፅጉራቸውን ይዘው መንገድ ላይ ጎተትዋቸው፡ ይህ አልበቃቸው ሲል ራቁታቸውን እንደሆኑ የከተማው ሕዝብ እያያቸው እንዲሮጡ አደረጉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከበሮ ይዘው እይጨፈሩና ራቁታቸው የሆኑትን ሴቶች ፎቶ እያነሱ ቪዲዮ እየቀርፁ ነው፡>> የሚለ አይተናል፡፡

በክፈል 3 ደግሞ ብሔር እየለዩ በተለይ በአማራ ወታደሮችና መኮንኖች እንዲሁም ከአማራ ወታደሮች የወለዱ የሠራዊቱ ሚስቶችና ህጻናት ልጆች  ላይ ምን ግፍ እንደፈፀሙ አይተናል (“አማራን እባክህን በእናትህ አይደገመኘም እያለ ‘ዋይ’ ‘ዋይ’ በቃኝ! እስኪል አሰኘነው” እያሉ በወያ የጥላቻ ጡጦ እየጠቡ ያደጉ የትግራይ ኢንተርሃሙው የኪንት ቡድን ሕዝብ ሰብስበው ሲያሰጨፍሩ የሚያሳይ ‘ቪዲዮ’ አባሪ አደር የለጠፍኩትን በከፍል 3 እንዳያችሁት ተስፋ አደርጋለሁ)፡፡  በዚህ ሁሉ ድርጊት ብዙውን የትግራይ ሕዝብ የወያ ባንራ እያወለበለበ እንደዘወትሩ የወያ ደጋፊ በመሆን በጥላቻ ዘመቻና አስፀያፊ የወንጀል ድርጊት ሲካፈል፤ ጨዋ የሆነው የኢሮብ ማሕበረሰብ ግን ሰብአዊ ባሕሪው እንደተላበሰ ያስመሰከረበት “ሠራዊቱ ድንገት በትግ ናዚዎች እንደተጠቃ” እየተታኮሰ ወደ ርትራ ሲያፈገፈግ የነበረውን ሠራዊት እየተንከባከበ ውሃ እየሰጠ መንገድ እየመራ በሠላም እንዲሻገር የረዳ መሆኑን በዚሀ አጋጣሚ ካነበብቸው ሰነዶችና ከተከዳው የሰዝ መፅሐፍ  ላይ የተጠቀሰ መሆኑን ሳልገልጽ አላልፈም፡፡

ያንን መዝግበን ዛሬ ደግሞ ጋዜጠኛ ያየስው ሽመልስ  ለወያኔ ያለው ፍቅር  ያሰምሰከረበትን መጽሐፉ <<የሴራ እርካብ የደም መንበር>> ወሰጥ፦

<< (ወታደሩ) ሲኖትራክና ታንክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡  የሚለው ውሸቱን አጋልጣለሁ፡፡

ከታች ያለው ማስረጃ ታፍነው በድል የተረፉ የሰሜን እዝ አባላት <<በህይወት እያሉ ታንክ ተነድቶባቸዋል፤ አስክሬናቸውም አስፋልት ላይ ሲጎተት ተመልክተናል>> በማለት ለ ኢ.ዜ.አ የሰጡት የሴት ወታደሮች  ቃለ መጠይቅ ነው፡፡

በአዲግራት የ11ኛ ክፍለጦር የስታፍ አባል ምክትል አስር አለቃ ደስታ ጌታ፤ መሳሪያ በዙሪያዋ ተደቅኖ በድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን ቀርባ ጁንታውን የሚደግፍ ንግግር እንድታደርግ መገደዷን ገልፃለች።

የጁንታው ቡድን ከሰሜን እዝ አባላት እየመረጠ በአይናቸው ላይ በርበሬ በመበተን እያቃጠለ በማሰቃየትና በመግደል ግፍና ጭቃኔ መፈፀሙንም ትናገራለች።

በህይወት እያሉ ታንክ እየተነዳ ግድያ የተፈፀመባቸው የሰሜን እዝ አባላት እንደነበሩም ታስታውሳለች።

የሞቱ የሰራዊቱን አባላት አስከሬናቸው አስፋልት ላይ እንዲጎተትና ከዚያም በአራዊት እንዲበሉ በማድረግ ጭካኔውን አሳይቶናል>> ብላለች።

"አራስ ልጄን ይዤ የታጣቂዎችን አስከሬን ተሸከሙ አሉን"

 "....ቁስለኞችን ሳይቀር ገደሏቸው"

ከዚህም ባለፈ ጡታችንን እየቆረጡ ሊረሽኑን ቀጠሮ ይዘው ባልተጠበቀ ሰዓት የመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶ ደርሶ ህይወታችንን ታድጎታል>>  ብለዋል።

ይህ በተጥቂዎቹ ‘ድምፅ’ ከታች የምትሰሙት ቪዲዮ እያለቀሱ የገለጹት የስቃይ ድምጽ በጋጠኛ ያየሰው ብር <<ውሸትና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የተነገረ ነው፤አለተፈመም>> ይለናል፡፡

ሎች ማስረጃዎችን ላቅርብ፡

እንትጮ (ዓደዋ) ትግራይ ውስጥ የተደረገ ደግሞ እንዲህ ነበር፦

<<….በቅርብ ርቀት የምትገኘው እንትጮ የምትባለዋ ከተማ ከ3 ሺ በላይ የሚሆን ሕዝብ ከጠላት ታጣቂ ጀርባ ተሰብስቦ ነበር፡፡ብርጌድዋ ዘጠኝ ቀን ሙሉ ትጥቅ አለመፍታትዋ ሕዝቡ አብግኖታል፡፡

....ይህ እንደ አው የሚያደርገው ድምፅ አልባ መሣሪያ ይዞ የመጣው ሕዝብ ባዶ እጁን ሆኖ በጠላት የተከበበውን ሠራዊት ሊውጠው ሊሰለቅጠው ደረሰ፡፡ ሠራዊቱን በድንጋይ ወገሩት፡ በዱላ ቀጠቀጡት፤በጩ ካራና ገጀራ አረዱት፡፡በውጊያ ቆስሎ ወድቆ ለመነሳት የሚፈጨረጨረውን መ//አለቃ ጨባ ጫንቆ የተባለ ድ የእኛው የግራዥ አባል የነበረ ሻለ/መ/ባሻ መላኩ የተባለ የትግራይ ተወላጅ በመኪና ጨፍልቆ ከአፈሩ ጋር አመሳሰለው፡፡

 ላው በዓይናቸው እያዩ ጓዳቸው በታንክ ጨፍልቀው ሲገድሉት ያዩ አማራ ተብለው ተለይተው ሊገደሉ ተራቸው ሲጠብቁ ከነበሩት አ/አለቃ ያድን በላይነህ እና ሀ/አለቃ አድማሱ እንዲህ ሲሉ ለ “የተከዳው የሰዝ” ደራሲ ለጋሻየ ናው እንዲህ ሲሉ ነግረውታል፡፡  

<< እየተጠሩ ከሚገደሉት መካከል አንደኛው የመሞቻ ተራው ደርሶ ተጠራ፡ ሲጠጋቸው ተኮሱበት፡፡ የተተኮሰበት ጥይት ሙሉ በሙሉ ሰላላገኘው ቆስሎ ለማምለጥ ሮጠ፡፡ በክላሹ ሊጨርሰው ሊተኩስ ሲል ታንክ ውስጥ የነበረው “ተወው” አለውና ታንኩን ነብሱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል ወደ ሚያደርገው ድ አምዘገዘገው፡፡ ከሀዲው የትግራይ ተወላጅ ያለምንም ርህራሄ አብሮት ተራራውን ይወጣ፤ቁልቁለቱን ይወርድ... የነበረውን ቆስሎ ህይወቱን ላማትረፍ የሚንፏቀቀውን ድ <<በታንክ ጨፍልቆ ሳው እንኴ እስከማይታይ ከአቧራው ጋር አመሳሰለው፡፡>> ሲሉ መስክረዋል፡፡

የመሳሰሉት በታንክና በሲኖትራክ እየተደፈጠጡ የተገደሉ የኢትዮጵያ የሠራዊት አባላትን በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች ገልጸውታል፡፡ ይህ ወንጀል ተፈጽሞ እያለ ሆን ብሎ ለወያኔዎች ሥስ ልብ ያለው “ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ” በመጽሐፉ ውስጥ የፋሺዝም “አይዲኦሎጂ” የታጠቁት  የትግራይ ታጣቂዎች ወንጀል በመደበቅ << (ወታደሩ) ሲኖትራክና ታንክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ ያመጣው የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል ነበር፡፡ ደግሞም ተሳክቷል፡፡ ይህ ሁሉ እንዳልተፈጸመ የትግራይ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ ዐብይም ፤ ብርሃኑ ጁላም ሆነ አዳምነህ መንግሥቴ (የሰሜን ዕዝ ሲማረክ ምክትል አዛዠ የነበረው ያውቃል፡፡>> የሚለው “የራ እርካብ የደም መንበር (ገጽ 54)” ሲል አስተባብሏል፡፡ እስኪ አንዳንዱን ማስረጃየን ከታች የለጥፍኩትን ቪዲዮ አድምጡና ፍርዳችሁን አስቀምጡ፡፡

እስካሁን ለተከታተላችሁኝ ምስጋናየ የላቀ ነው፡፡

ጌታቸው ረዳ (Ethiopian Semay አዘጋጅ)



Wednesday, April 17, 2024

ክፍል 3 ጌታቸው ረዳ የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚል ከክፍል 2 የቀጠለ.... 4/17/24 (በፈረንጅ ዘመን)


ክፍል 3

ታቸው ረዳ

የወያነ ፍቅር ሰግጦ የያዘው የአማዞንን ገበያ ያጨናነቀው……የያሰው ሽመልስ መጽሐፍ.... ከሚል ከክፍል 2 የቀጠለ....4/17/24  (በፈረንጅ ዘመን)

ከፍል 1 እና 2 ከጠበቅኩት በላይ ከፍተኛ አንባቢ ተመልክቶታል፡፡ ስልን ማን እንደሰጣቸው ባላውቅም (ምናልባትም ከድሮ ጽሑፎ?) ሁለት የማላውቃቸው ሰዎች ከአገር ት ደውለው የተሰማቸው ምስጋና ሲቸሩኝ አንደኛው፤ በውድቅት ሊት  <<እነዚህ እርጉማን ያደረሱብን በደል ፈጣሪም ሊገልጸው ይከብደዋል፡፡ አንተ ከጠቀስካቸው ባንደኛው አሳዛኙ ያገዳደል ድርጊት በ ሲፈጸምባቸው ዓይነ እያየ ስለነበር አሁንም ሊት ቀርቶ በቀን ሰላም ያሳጣኛል...መጽሐፍ ጻፈ የምትለው ጸሓፊ ባላውቀውም “እርሱም እንደነሱ እርጉም ይሁን”፡፡ ብቻ ተባረክ!።” የሚል በውድቅት ሊት ተኝ ይህ ወታደር  ከውስጥ ሐዘኑ ጋር እየታገለ ደውልኝ፡ ከዚያም ንቅልፌን ማሸነፍ  ኣልቻልኩም፡፡

ታስታውሱ እንደሆነ፤ በክፍል 1 ትችጠኛ ያየሰው ሽመልስ በጻፈው የመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጾች አካባቢ ሳነብ እጅግ የሚመስጥ የወጎቹ ፍሰትና የቃላቶቹ ውበት በማንበ የኦነጉና የሻዐቢያ ‘የፖለቲካ ኩሊ’ የነበረው ማቹ ተሰፋየ ገብረአብ በድንቅ አጻጻፉ ይተካዋል ብየ ማድነቄን ታሰታወሳላችሁ፡፡ በሚያሳዝን መልኩ አሁን፤ አሁን ምጽሐፉን እያነበብኩ ወደ ውስጥ ጠል በገባሁ ቁጥር ያንን አድናቆ በሚጻረር መልኩ፤ የጽሑፍ ፍሰቱና ወጉ ደብዝዞ ፤ የሚያደንቃቸው የሚገጥምላቸው የወያ መሪዎቸና አዋጊዎች  ከሚመግቡት ወግ ተሞርኩዞ “በሚያሰለች የኩት፤ ኩት ባይ ብ” የወይን ጋጣ ጋዝጠኞችን የሚያስንቅ ዘጋቢ ሆኖ ሳገኘው ለማንበብ የነበረኝ ጥማት ቆረጠውና መጽሐፉን በይደር አኖርኩት፡፡

ምን ታመጡ! በሚል አጻጻፉ  ባንድ ወራጅ ጅረት (ወንዝ) ተዝናንተው እግራቸው ሲታጠቡ በጠላት ታይተው ስለተገደሉ በጸረ አማራነታቸው የምናውቃቸው ‘ዘላፊዎች’ የወያ  ራልና አንድ ኮሎ “ተጠቦ ተጨንቆ ስለ ጀግንነታቸው አንድ ግጥም ገጥሞላቸዋል፡፡” ከዚያ ውዲያ  በቻ ጸሓፊው እንደጠበቅሁት አላገኝሁትምና የማንበብ ጉጉን አላረካ ሲለኝ  መጽሐፍን አጥ ወደ መደርደርያ ከተትኩት፡፡

ለዛ ቃል እንደገባሁላቺሁ ደራሲው ያየሰው ሽመልስ ባሳተመው “የራ እርካብ የደም መንበር” መጽሐፉ ውስጥ የሩዋንዳ ኢንተርሃሙን የሚያስንቁ ገጀራና <<USA>> የሚል የተጻፈቡቸው አዳዲስ የመግደያ ካራዎች በብዛት ታድለው የታጠቁ ጸረ አማራ ወጣት የትግራይ ‘ተዋጊ ሃይላትን’ ወንጀል ለመከላከል ሲል በተጨፈጨፈውና በተከዳው  የሰሜን ዕዝ ሕይወት ላይ  <<ሠራዊቱ በማንነቱ ተመርጦ ታረደ፡፡ በዳንሻ በኩል አማራ ተጠቃ፡<< ሲኖትራክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል አብይ የተጠቀመበት ፕሮፓጋንዳ እንጂ አልተፍጸመም....’፡ >> የተለመደ ቀጥፈቱና ጦርነቱንም ሕዝባዊ ለማድረግና አማራና የትግራይ ሕዝብንም ደም ለማቃባት የያዘው የኢሳያሰ ተልኮ እንዲሰምር ነው..............።ወዘተ........። ስለሚለው እንመለከታለን፡፡

ደራሲው እዚያም እዚህም ‘’የትግራይ ኢንተርሃሙዎቹን ቀዳዳ ለመሸፈን እየሮጠ ያለው ጥድፍያ ፤ ‘’ጠ/ሚኒስትሩ’’ እንዲሀ አለ፤ መረጃ ሳያገኝ (መገናኛ ዝግ በሆነበት ወቀት ሊያውቅ አይቻለውም)  የሚለው የዳርዳር ወጉ የሚያመለክተን ፤ “ወያ በአማራ ጥላቻ አይታማም” ለማለት ነው”፡፡

እስኪ ንግግሩን እንፈትሸ፡፡

ወያ  አማራን ከትግራይ ሕዝብ ጋር ደም ለማቃባት የኢሳያስ ተንኮል አላሰፈለገውም፡፡ የ1967 ትግሉ የጀመረው አማራን ዓይነተኛ ጠላቱ አድርጎ በኪነቶቹ በኩል እስከዛ ድረስ እያስዘፈነ ሲነግረን የኖረ ነው፡፡ በጫካ ዘመኑ ሙርከኞች አማራ ወታደሮችን በመርዘና በጥይት ሲጨፈጭፍ የነበረ  አማራና ትግራይን  ወልቃይት ላይ ደም ሲያቃባ 17 አመት የጫካ ታሪኩን አይታውቅም ነው? በነገሠበት 27 አመት ወስጥ የአማራ መሁራንና አገር ወዳዶችን  እየለቀመ ምን ግፍ ይፈጽምባቸው እንደነበረ እንደማናውቅ ለምን ጋዜጠኛ ያየሰው ሊያሞኘን ፈለገ?

 “አማራና ኦርቶዶክስ አከርካሪውን ሠብረነዋል” እያለ በይፋ ያወጀው  ገና ገና ኢሳያሳያስ ገና ወደ ትግራይ ጦርነት እግሩ ሳይረግጥ ነው፡፡ በጦርነቱን አሳብቦ አማራ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የኢሳያስ ተል  አላስፍለገውም ፡፡

ያየሰው ‘’አብይ ያደገበት ትምሕርት አማራን በመጥላት ወያነ የተካነ እንደሆነና እራሱም ያንን መቅሰሙን ያወቃል፡፡ አማራን ‘’በከፋ ሁታ’’ እየለዩ እንደሚያጠቁ ፍላጎት እንዳላቸው  “ገምቶ” ነበር፡፡ ግምትም ከነበረ ግምቱ ልክ ሆኖ ሲገኝ ጋጠኛ የያሰው ግን ራሱን ትብት ላይ ከመጣል የፈየደው የለም፡፡

እሰኪ ታሪኩ ክአማራዎቹ ከራሳቸው አንደበት የነገሩንን እናድምጥ፡፡

ታሪኩ የሚጀምረው ወያ ያፈናቸው ወታደሮችን ሰብስቦ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ዘግቶባቸዋል፡፡ “ጁንታው” የይኒቨርሲቲው ዲን ቀለብ አውጥቶ ለሠራዊቱ እንዲያቀርብ ቢያዘውም፤ ‘’ምግብ እንዳቀርብ ከተፈለገ አቅርብላቸው ብሎ የሚያዘኝ ክልሉ ሳይሆን የደራል ትምሕርት ሚኒስር ስለሆነ ትዛዙ ከዚያ ይመጣልኝ’’ ብሎ በማሾፍ በረሃብ ተዘግተው እንዲሰቃዩ አደረገ፡፡

የአክሱም ሕዝብና አካባቢው ተሰባስቦ የመጣ ሕዝብ “የኛን ሰው ጨርሰውብናል፡ እነሱንም እንጨርሳልን” አለ ሕዝቡ፡ ዩኒቨርሲቲው በር ላይ ተሰብስቦ፡፡ የታፈነው ሠራዊት መሸሸጊያው መደበቅያው ጠፋው፡፡ያ እንደ አራስ ነብር የሚያናዝረው በደም የሰከረ ሕዝብ ወደ ግቢው ገብቶ ቢሆን ከፍተኛ ልቂት ይከሰት ነበር፡፡ ነገር ግን ደጋግ ስዎች ሕዝቡን ለምነው መለሱት፡፡

አንድ ጓድ ከዩኒቨርሲቲው በአጥር ሾልኮ ወጣ፡፡ገጠራማው አክባቢም በእግሩ ብዙ ተጓዘ፡፡ ሃሳቡ ከሰው በላው ጁንታ መወጣት ነው፡፡ ሃገሩን የሞሉት ደግሞ እነሱ ናቸው፡፡ አዝመራ የሚያጭዱ ገበሬዎችን አገኘ፡፡ መንገድ ያመላክቱኛል በማለት ቀረብ ብሎ ጠየቀ፡፡ ለጥያቄው ምላሽ ሳይሰጡት በጥያቄ አጣደፉት፡፡ ወታደር መሆኑን ሲሰሙ ያን ያህል የተለየ ነገር አላሳዩም፡፡ “ብሔርህ ምንድነው?” አማራ መሆኑን ሲነግራቸው ሰዎቹ በአንድ ጊዜ አውሬ ሆኑበት፡፡በያዙት ማጭድ ገላውን እየሸነታተሩ ተናጠቁት፡፡ እንደ ቅርጫ ሥጋ ተቦጫጨቁት፡፡ በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ ሁነቱን ያዩ ልዩ ኃይሎች አስጣሉት፡፡>> ይላል ደራሲው “ቻቻው”፡፡

 በማስከተልም “እንዴት ሲሆን ገበሬዎች በቀጥታ ከሚዋጉት ልዩ ኃይሎች በላይ ሊጨክኑ ቻሉ? እንዴትስ ልዩ ኃይሎች ከገበሬዎች በላይ ሊራሩ ቻሉ? “ነገሩ ቅ ነው?” በማለት ስለ ሁኔቱ አግራሞቱን በጥያቄ ያስቀምጣል፡፡

 ግን ይልና ቀናዎቹ ልዩ ኃይሎች ዘግይተዋል፡፡ ጓዱ በሕይወት ሊተርፍ አልቻለም፡፡ ዘግናኝ አሟሟቱን ልዩ ኃይሎች ለታፋኙ ሠራዊት ተናገሩና የሠራዊቱን ፍርሐትና ሐዘን አናሩት፡፡>> በማለት ቻቻው በመቀጠል  ብሔርን ለይተው ምን እንደፈጸሙ እንመልከት፡፡

<ባፈናቸው የሠራዊት አባላት ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ሠራ፡፡ ከሀዲ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት፤ ለአመታት ከሠራዊቱ ጋር ሰለኖሩ በየጋንታቸው በየሻምበላቸው፤ ሻለቃቸው ብሎም በብርጌድ ማን የየትኛው ብሔር ተወላጅ እንደሆነ ልቅም አድርገው ያውቃሉ፡፡ የብሔር ተወላጆችም ተለቅመው ተለይተዋል፡፡ አፍነው ባንድ ቦታ ከሰበሰቧቸው ውሰጥ የአማራ ተወላጆች ሥም መጥራት ተጀመረ፡፡

“አስናቀ” ይባልና የጠራል፡፡ የዋሁ ጓድ አስናቀ ‘ማን ነው የጠራኝ?’ ይልና “አቤት” ብሎ ወደ ተጠራበት ይሄዳል፡፡

ግንባሩን በጥይጥ...!

“ደሳለኝ” ተረኛው ይጠራል፡፡ በነብስ ግቢ ነብስ ውጪ ጭንቀት!

ወደ ተጠራበት ቦታ ይዳል፡ “እንካ ቅመስ በጥይት!

ተረኛው የጠራል

”በልእስቲ!”...

በርካታ ጓዶች (አማራዎች) አብረው ሲኖሩበት በነበረው ካምፕ ውስጥ በራሳቸው መሣሪያ ሬሳ አደረጓቸው፡፡

የህንን ያዩ የሞት ፅዋቸውን ለመቀበል ተርታቸው ሲጠብቁ ከነበሩት ‘አ/አለቃ ያዲን በላይነህ’ እና ሃ/አለቃ አድማሱ’ “አብይ ዓዲ” ማጎርያ እስር በተገናኘንበት ወቅት “የኛ ሥም እስኪጠራ እንጠብቅ ነበር፡፡ በፍፁም በሕይወት እንውጣለን ብለን አላሰብንም ነበር” አሉኝ፡፡>> የላል የተከዳው የሰሜን ዕዘ ደራሲ የ፶ /አለቃ ጋሻዬ ጤናው፤ ከየቦታው አየተለቀሙ ተምቤን አብይ ዓ፟ዲ “ማጎርያ _ ኮንሰንትረሺን ካምፕ ከተገናኙ በላ፡፡

በመጨረሻም ኮሎኔል አብየ መኩሪያ አማራነታቸውና ሰንደቃላማቸው ሲዋረድ በማየታቸው የሆነውን ሁነት “ደፋሩ ታፋኝ” ከሚለው ዘገባ እንመልከትና ልደምድም፡፡

7ኛ ም/ክ/ጦር ስታፍን ትጥቅ ያስፈታቸው “ሸራሮ” የሚገኘው ካምፓቸው ላይ እንዳማርያም (ማርያም) ቤተክርስትያን ወሰጥ ዲሸቃና ሌሎች መሣሪያ ጠምደው ነው፡፡ታፋኞቹ ከሸራሮ አስወጥተው ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ያስገቧቸው፡፡ ታፋኞቹን ሰብስበው..... አብይ ከመጣ ጀመሮ አገሪቱ ሰላም አጥታለች;.... የሰው ሞት በዝቷል ወዘተረፈ... እያሉ ፕሮፓጋንዳ ይለፍፋሉ፡፡ ሰው በተሞላ ጢቅ ባለው አዳራሽ ወስጥ፤ ማንም ሊናገረው የማይችል የጁንታው መልዕከተኞችን ያሰደንገጠ ነገር፤ ከፍ ባለ አስገምጋሚ ድምጽ ተሰማ፡፡ ኮ/ል አብየ መኩሪያ ናቸው፡፡

<<በኢትዮጵያ ሰላም የምታደፈርሱ እናንተ ናችሁ፡፡አገራችን ሰላም የምታገኘው እናንተ ሰትጠፉ ነው፡፡ ምናልባትም እኛን ገድላችሁን ላናይ እንችላለን፡፡ ያ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ትጠፋላችሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ እናንተ ትጠፋላችሁ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸንፋል፡፡ ያኔ ኢትዮጵያ ሰላም ትሆናለች!”

አዳራሹ ከዳር እስከዳር ፀጥ ... ረጭ....ዝም.......ያስባለ ንግግር፡፡የሚያስፈራ ፀጥታ የሚያስደነግጥ ዝምታ፡፡

መድረክ መሪው ጁንታ በአንዴ ፊቱ ተቀያየረ፡፡ጆሮውን ሊያምነው አልቻለም፡፡” የተናገርከው ድገመው እስኪ?” አለ፡፡

 ኮ/ል አብየ የተናገሩትን ሳይቀንሱ ሳይጨምሩ ደግመው ሲናገሩ ምላሳቸው ጎልደፍ አላለም፡፡ድምፃቸው አልተለወጠም፡፡ አንደበታቸው አልተሞሰሞሰም፤ ፊታቸው አልተቀያየረም፡፡ ደገሙላቸው፡፡አዳራሽ የሞላው ሠራዊት በኮሎኔሉ ተገረመ፡፡

ኮሎኔሉን ጠየቅኴቸው፡

የህንን ሲናገሩ ይገድሉኛል ብለው አልሰጉም? አልኴቸው፡፡ "በግሌ ሁሉንም ሠራዊት ይረሽኑታል በየ ነበር የማስበው፡፡ እኔ እንደምሞት እርግጠኛ ነበርኩ፡ መሞቴ ካልቀረ ደግሞ ተለማምጨ መሞት አልፈለግኩም፡፡ መሣሪያ የለኝ፤አልዋጋ ነገር፡፡ በወቅቱ የነበረኝ ኃይል አፌ ብቻ ነው፡፡ የልቤን እውነቱን ተናግሬ መሞት መረጥኩ፡፡ ደሞ እሱ በሙሉ አምኜበት ነው የተናገርኩት፡፡ እንደምናሸንፉ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡” አሉኝ፡፡

ኮሎኔል አበየ ዩኒቨርሲቲ ማጎርያ ግቢ ከገቡ ጀመሮ የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ ስንደቅዓላማ ለብሰው ነው፡፡ በተደጋጋሚ ‘’እኔ አማራ ነኝ በኢትዮጵያ ግን መደራደር አላውቅም’’ ፤ አያሉ ግቢውን እየዞሩ ለታፋኙ ሠራዊት ድመፃቸውን ከፍ አድርገው ይናገራሉ፡፡ የትግራይ ልዩ ኃይል ወይም ሚሊሺያ ሲያገኙ ደግሞ “እመኑኝ ትሸነፍላችሁ፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ ያሸነፋል” እያሉ ይናገራሉ፡፡ በዚህም ታፋኙ ሠራዊት ኮሎኔሉን እንደ ዕብድ ሰው ማየት ጀመረ፡፡

ሰንደቅዓላማ ለምን ለበሱ? በተደጋጋሚ ደግሞ እኔ አማራ ነኝ እያሉ ይናገሩ ነበርና ለምን አማራ ነኝ ማለት ፈለጉ? በየ ጠየቅኴቸው፡፡

ከጥቅምት 24 ጀመሮ በምንንቀሳቀስበት ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ የለም፡ በሙሉ አወረደውታል፡፡በየቦታው የትግራይ ባንዴራ ብቻ ይታያል፡፡መኪኖችና ባጃጆች የትግራይ ባንዴራ አደረገዋል፡፡የታፈነው ሠራዊትን እያንጨበጨቡና ከበሮ እየመቱ የሚቀበሉ ወጣቶቸና  እናቶች እንኴ የትግራይ ባንዴራ ብቻ ነው የያዙት፡፡ ሰንት መስዋእትነት የተከፈለባትና የታገልንላት የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ ግን መሬት ላይ ተጣለች፡፡በጣም ተናድጄ ነበር፡፡አጋጣሚ እንደ ከፈተኛ መኮንን ሰንደቅዓላማ ይዞ አገኘሁትና ሰጠኝ፡፡ ያቺን ሰንደቅዓላማ ለበስኴት፤ ያቺን ሰንደቅዓላማየን ለብሼ ተኩሰው ቢገደሉኝም ክብሬ ነው፡፡ በዚህ ጥቃት የታዩ ቢነገሩ ለትወልድም የማይበጅ ነገሮች የተፈጸመው ዘርን እየለዩ ማጥቃቱን ነው፡፡ ሃገሬ ብሎ ምሽግ ውስጥ የኖረን ሠራዊት አማራን እየለዩ ገድለዋል፤ አሰቃይተዋል፡፡ በብሔር ታርጋ እየለጠፉ መሳድበና ማሸማቀቅ ሕሊና የሚያደማ ነው፡፡ ባልናገረው ይሻላል.....ለዚያ ነው አማራ ንኝ የምለው፡፡’’

ኮሎኔሉ ያንን ንግግር ከተናገሩ በኋላ ልዩ ኃይሎች ወሰደዋቸው፡፡ እጅና እግራቸውን አሰሯቸው፡፡

በመቀጠል ኮሎኔሉ እንዲህ ይላሉ፡፡ ‘’ዕድሜየን ሙሉ ከነሱ ጋር ታግያለሁ፡፡ በሰው ልጅ ሊደረግ ይማይቻል ነገር አድርገውብኛል፡፡ አስረው ደብድበውኛል፡፡ ሽንቴን መሽናት እሰከማልችል ድረስ ነው ያሰቃዩኝ፡፡ ይላሉ ኮ/ል አብየ መኩሪያ፡፡

የኸን ሁሉ ስቃይ ድብደባና ስድብ ሲያደርሱብኝ አካሌ ቀርቶ አፅሜ ሁሉ ተነከቶ ነበር፡፡ በትክክል ማሰብ ተሳነኝ፤ ራሴን ሁሉ ስቼ ነበር፡፡ በእርግጠኛነት ራሴን እስክስት ድረስ ደብድበውኛል፡፡ ከዱላው በላይ አዕአምሮየን የነካው ስድባቸው ነው፡፡ <<አንተ አህያ” እያሉ ነበር የሚሰድቡኝ፡ ይህ በጣም፣ ያማል፡፡እ ግን አልፈራቸውም ነበር፡፡ አዎ “አማራ ነኝ” እንደ እናንተ ግን ኢትዮጵያን የምከዳ አማራ አይደለሁም፡፡ በአማራነቴ እሞታለሁ!” አያልኴቸው ነበር፡፡” የላሉ ኮሎኔሉ፡፡

ኮ/ል በመቀጠል

<የሚገርምህ...” አሉና ከገቡበት የሐዘን  ስሜት ለመውጣት እየሞከሩ፤ “...ከዱላው በላይ የሚያመው ስድባቸው ነው፡፡ሳይሳደቡ ዝም ብለው ቢደበድቡኝ አጥንቴ ቢሰበር እንኴ ምንም አይመሰለኝም ነበር፤፡ ስድባቸው ግን ያማል፡፡ ቀደም ብሎ የሚገርፉኝ ወንዶች ነበሩ፡፡ አንድ ቀን አንዲት ሴት ስትደበድበኝ ‘እ እኮ ብዙ አመት ለሃገሬ የታገልኩ ኮሎኔል ነኝ፡፡ በማርያም አትደብድቢኝ፡ ባይሆን ወንዶች ይደብድቡኝ በየ ለመንኴት” አሉኘ ፡፡ የኸኔ ሲናገሩ ከወሰጣቸው ሕመም ጋር እየታገሉ በሚያሳዝን ደመፅ ነው፡፡

ሰድበው ደብድበው ሲጨርሱ “ይገደል ብለው ወሰኑ” ሞቴን እየተጠባበቅኩ እያለሁ የሚያሰቃዩኝ ልዩ ኃይሎች በማረሚያ ቤት ፖሊሶች ተቀየሩ፡፡ ወዲያው ደግሞ ሠራዊቱ ወደ አክሱም ሲጠጋ ወደ ተምቤን ወሰዱኝ”፡፡ ይላሉ  ኮሎኔሉ ከሞት ያመለጡበትን ሁኔታ ሲናገሩ፡፡

ሌሎች ሁለት የሚሳይል ኮድ የደበቁ ናቸው የተባሉ የአየር ሃይል አባላት ከመቀሌ ወደ አክሱም ተወስደው አብሯቸው ሲገረፉና ሲሰቃዩ የነበሩ ጋዶችን ኮ/ል አበየ መኩሪያ  የራሳቸው ሕመምና ስቃይ ተቋቁመው አይዟችሁ እያሉ ያበረታትዋቸው ነበር፡፡ 'ሁለቱ ጋዶች ጥፍራቸው እየተነቀለና አይተደበደቡ ተሰቃይተዋል'፡ በግርፋትና በድብደባ ብሔር ተኮር ሰድብም አዕምሮአቸው የተሰቃዩ ብዙ ናቸው፡፡ ኮሎሉ ያሉት አልቀረም አቋማቸው ሳይቀይሩ በፅናት እንደቆዩ ከበዙ ሰቃይ በላ የተናገሩት ደረሰና ጁንታው በሳምንታት ተሸነፎ ተምቤን በረሃ ገባ፡፡ ኢትዮጵያ አሸነፈች፡፡የተናገሩት እውን ሆነና ምን ተሰማዎት ? ብየ ስጠይቃቸው፤ ባጭሩ ነበር የመለሱለኝ፡

“እነሱ ቆፍረው መቅበር ብቻ ነው የሚያወቁት ፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን ቆፍረን መዝራትም ቆፍሮ መቅበርም ይችላሉ በማለት የሩዋንዳው ሰው አራጁ የሑቱ ‘ዱርየ ጋንጎችን’ ያስናቀ 33 አመት በጸረ አማራነታቸው የታወቁት የትግሬ ኢንተርሐሙዌ መሪዎች ትዕዛዝ ምክያት ምንም ባልተተናኮላቸው ሠራዊት 'ደክሞት በተኛበት' በውድቅት ሌልት ያደረሱበትን ግፍ አየታወቀ አያለ፡

ጋዜጠኛ ያየሰው ግን ለትግሬ ኢንተርሃሙው ቡድን በመወገን <<ሠራዊቱ በማንነቱ ተመርጦ ታረደ፡፡ በዳንሻ በኩል አማራ ተጠቃ፡<< ሲኖትራክ ተነዳበት ወዘተ፣ የሚል ፕሮፓጋንዳ የሕዝብ ልብ ለመግዛት በሚል አብይ የተጠቀመበት ፕሮፓጋንዳ እንጂ አልተፈጸመም....’፡ >> የተለመደ ቀጥፈቱና ጦርነቱንም ሕዝባዊ ለማድረግና አማራና የትግራይ ሕዝብንም ደም ለማቃባት የያዘው የኢሳያሰ ተልኮ እንዲሰምር ነው..............።ወዘተ........። እያለ ‘’ከነብ ቀጥሎ ጋዜጠኛነቴን እወደዋለሁ’’ እያለ እየተበጠረቀ ሚዛናዊ ጋዜጠኛነቱን በሚጥስ መልኩ “በደበረጽዮን የሚታዘዘው የወያ ሚዲያ የመናገርና የመጻፍ መበን ወደ ትግራይ በመሄድ ነፃነን ጠበቅውለኛል እያለ በሚያስቀን መልኩ እያሞጋገሳቸው”  ወንጀሎቻቸውን በኮሽታ እያለፈ ምንም ያልተተናኮላቸው በተኛበት የተጨፈጨፈውን ሠራዊት ሳይመሰከርለት ታሪክ ላንደኛው ወገን  በሚያዳላ መልኩ እንዲዘግበው አዛብ ዘግቧል፡፡

 ክፍል 4 ወታደሩን በታንክና በሲኖትራክ  እየደፈጠጡ ጨፍልቀው ይገድሉትም እደነበር የካደበትን ‘ደርጊቱ እንደተፈፀመ’፤ በሚቀጥለው ቀናት እንመለከትና የትችቴ ፍፃሜ የሆናል (መናልባት)፡፡

በድጋሚ መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ፡፡

ከታች የተለጠፈውን

 ቪዲዮ እዩና ፍረዱ፡፡

 ጌታቸው ረዳ  4/17/24  (በፈረንጅ ዘመን)